Wednesday, October 9, 2013



አቶ ሐ/ደሳለኝ በሟች መለስ ዜናዊ አማካይነት በኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ ሲሉ ቀለዱ ....

የተቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ መብታቸው ነው ሕገ መንግስታዊ መብታቸው ነው::ያው የሚጠይቁት ጥያቄም የሚታወቅ ነው አዲስ ጥያቄ አይደለም::ቤት ቁጭ ብሎ መጠየቅና አደባባይ ወቶ መጠየቅ ነው ልዩነቱ ሰለዚህ ሕዝቡም ሰንቷቸዋል ዋናው ጉዳይ ሰልፍ የሚወጣው ሕዝቡን ለማሰማት ይመሰለኛል.... ሕዝቡን አሰምተውታል...ሰለዚህ ዲሞክራሲ ተሳክቷል ማለት ነው .... የዲሞክራሲ ሰርዓት ሂደት ተሳክቷል ማለት ነው ....ድምፃቸውን ማሰማት ሕዝቡን እንዲያውቅ ማድረግ ችለዋል ....ሕገ መንግስቱም የሰጣቸው መብት ሰለሆነ ማንም በችሎታ የሰጣቸው አይደለም...ሰለዚህ ያንን ፈጽመዋል ይሄ ሕገ መንግስታዊ ሕግ ነው::ነገር ግን ምን ምላሽ እንደሚሰጥ አናውቅም ::ይሄ እንግዲህ ከ100 ግዜ በላይ መልስ ሰተናል:: እንግዲህ ጫና ፈጥረን መንግስት ሃሳቡን እንዲቀይር ለማድረግ የሚያስቡ ይመሰለኛል....በሂደት ውስጥ መንግስት ትክክለኛና እውነተኛ ምላሽ መሆን ያለበትን ምላሽ አሰቀድሞ የሰጠ ሰለሆነ አሁን ጫና ፈጥረው የሚቀየር ነገር ብለው የሚያስቡት ነገር ካለ የሚፈጠርም የሚቀየርም ነገር የለም::ሰለዚህ አሰቀድመን የሰጠ መልስ ተከታታይ ነው ......ነገር ግን የሚያሳዝነው ሌት ከቀን ተመሳሳይ ጥያቄ እየያዙ ጥበቃ ሰናካሄድ ተመሳሳይ ጥያቄ እየያዙ ጥበቃ ሰናካሄድ በየ እሁዱ ጥበቃ ስናካሄድ በየ እሁዱ ጥበቃ ሰናካሄድ መሰልቸት ነው የሚሆነው እንጂ ጥያቄው ያው ነው:: አንዱ ሲተው ሌላኛው እኛ አገር 99 ፓርቲ ነው ያለው እንግዲህ 99 እሁድ መጠበቅ አለብን ማለት ነው:: ነገር ግን ዲሞክራሲ ሰለሆነ እንታገሳለን ....የሆነው ሆኖ በጣም ብዙ ሰራ ያሰፈታል......መታወቅ ያለበት አንድ ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚጠየቅ ከሆነ እኛም አንድ ቦታ ሰንደርስ ለዚህ ጥያቄ እኮ ብዙ ግዜ መልስ ሰተናል ጥያቄው ይሄ ከሆነ ሰልፍ ምንድነው ትርጉሙ ብለን የምናቆምበት ግዜ እንደርሳለን ማለት ነው ሰልፍ ለዘላለም ዝም ብሎ የሚካድ ያለበት ሃገር ያለ አይመሰለኝም::ሰለዚህ ይሄ መታየት አለበት ::

ሁለተኛው ይሄ ሰልፍ የሚያካሄዱበት ዕቅድ የራሳቸው ዕቅድ አይደለም.... አቅደው የሰጧቸው ከኋላ ባለቤቶቹ አሏቸው:: ባለቤቶቹ ሰልጠና ሰተዋቸው አሜሪካን ወይም ሌላ ሃገር ቁጭ አርገዋቸው አሰልጥነው በዚህ በዚህ ብትሄዱ መንግስተን አጣብቂኝ ውሰጥ ትከታላቹ ሰለዚህ ተከታታይ የሆነ ሰልፍ ለማካሄድ ዕቅድ አውጡ ብለው እራሳቸው አቅደው አሰልጥነው ኦሬንቴሽን ሰተው በዕቅዱ ላይ አሰማርተዋቸዋል......ሰለዚህ የባለቤታቸውን ሰራ እየሰሩ ሰለሆነ ....የራሳቸው ሰራ ስላይደለ በሂደት ያው ባለቤቱም ይሰለቻል እነሱም ሰልችቷቸው የሚያቆሙ ይመሰለኛል:: እኛ ግን እንደመንግሰት ሃላፊነታችን ሕገ መንግስታዊ መብታቸው ሰለሆነ ያንን እንዲያሰተናግዱ ማድረግ ነው :: ከዛ ባሻገር አሁን ምን እናድር ? መንግስት እኛን አልሰማም እናንተ ንገሩልን እያሉ ነው ያቀዱትን አካላት ማለት ነው :: እነዛ ደግሞ አይ እናንተ በቀጥታ የምትሳተፉበት ጉዳይ እንደመሆኑ መጤን እኛ ደግሞ ለመንግስት ሄደን መናገር አንችልም ይልውቸዋል .....ሰለዚህ ሂደቱ እንደዚህ አይነት ደካማ ሂደት ነው ያለው so በኛ በኩል በተደጋጋሚ ምላሽ ሰተናል በተደጋጋሚ ምላሽ የሰጠነው ጉዳይ ሰለሆነ ተጨማሪ የምንሰጠው ምላሽ በዚህ ጉዳይ ላይ የለንም::ብለው ቀልዳቸውን ዘግተዋል ::

ባጭሩ አቶ ሐ/ማርያም ደሳለኝ ያሉት ኢትዮጵያ ውሰጥ እኛን ለመቃወምም ሆነ ያንን የመሰለ ሰልፍ ለማቀናጀት ብቃት ያላቸው ፓርቲዋች የሉም ጭንቅላት የላቸውም አይነት በንቀት የተሞላ ቀልድ ነው የተናዘዙት (እሳቸው እራሳቸው በሙት እየተመሩ እንደሆነ ማን በነገራቸው ያሉሽን ባልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ አለ ሽምሱ) በዚህ አጋጣሚ እሳቸውና መንግስታቸው ለዘላለም እንደሚገዙም ሊነግሩን ሞክረዋል :: 99 ፓርቲ ነው ያለው ላሉት ይሄ ወያኔ ሌ ንቅፍት እውቅና የሰጣቸውም አብረው እንደተቆጠሩ እናውቃለን እኛ አሉ የምንላቸው ወያኔ 5 ለአንድ አድርጎ ፓርቲ ያላቸውን ሳይሆን በተግባር እየሰሩ ያሉትን ብቻ ነው:: የኢትዮጵያ ሕዝብ የተነሳለት ምን ይሉ ይሆን ?


ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!!

No comments:

Post a Comment