Tuesday, December 9, 2014

የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኢትዮጵያ
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
ማለዳ ፌስቡክ እንዴት አደረ? ብዬ ስከፍት የተዋናይት ሜሮን ጌትነትን ለወሊድ አሜሪካ ልትሄድ መሆኑን አንብቤ ቴዲ አፍሮ ትዝ አለኝ ። የሜሮን አይገርምም ። አሁን ልጆቻቸው ኢትዮጵያ እንዲወለዱ የሚፈቅዱ ወላጆች ጥቂት ወይም እዚያ የመውለድ እድሉ የሌላቸው ናቸው ። የባለሀብት ፣ የባለስልጣን ፣ የፓይለት ፣ የሆስቴስ ፣ ወዘተ ልጆች አሜሪካ ነው በብዛት የሚወለዱት ። ለብዙዎች ኢትዮጵያ አንደ ቀን አሜሪካ ጠቅለው እስኪሄዱ መሸጋገሪያቸው ናት ። እነዚህ ኢትዮጵያ የልጃቸው መኖሪያ እንድትሆን ያልፈቀዱ ዜጎች "ኢትዮጵያ ሀገሬ እወድሻለሁ " ሊሉ እንዴት ይችላሉ? ሰው እንዴት በእንግድነት ካለበት ቤት ፍቅር ሊወድቅ ይችላል? ምንድነው ሀገር መውደድ? አጋጣሚ ሆኖ ደግሞ እነዚህ ሀገሪቱን ጊዜያዊ መኖሪያ ያደረጉና በቀጣይ ሀገሪቱ የተሻለች መኖሪያነቷ ላይ ጥያቄ ያላቸው ዜጎች የሚበዙቱ የስርዓቱ ተጠቃሚዎች መሆናቸው ነው ።
በዚህ ስርዓት ቅጠቀጣ የበዛበት ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከሀገር ለመውጣትና እዚያው ለመኖር በቂ ምክንያት አለው ። ድምፃዊው ግን ብልጥ ብቻ ሳይሆን ብልህ ነው ። ከሀገሩ ቢወጣ ከባህር የወጣ አሳ እንደሚሆን ያምናል ። ከነችግሩም ሀገርና ህዝብ እንደሚበልጡ ይረዳል ። ከሀገር ወጥተው ከባህር የወጡትን ያያል ። ከዚህ ሁሉ በላይ ሀገሩን ይወዳል ። ይህች የሚወዳት ሀገሩ ለእሱ ባትመቸው እንኳ ለልጆቹ የመኖሪያ ሀገር መሆኗ ላይ ጥያቄ አላነሳም ። ልጆቹን ለሀገሩ ነው የሰጣቸው ። ስለዚህም ባለቤቱ አምለሰት እርግዝናዋ ገፍቶም እዚያች ለብዙዎች " የተስፋዪቱ ምድር " የሆነች ሀገር ስትቆይ እዚያው እንደምትወልድ ነበር የገመቱት ። አምለሰት ግን ብዙዎች ወደዚያ በሚሄዱበት ወቅት ወደዚህ መጣች ። የቴዲ ልጅ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ተወለደ ። ይህ ብዙ ማለት ነው ። ትልቅ ውሳኔ ነው ። በሀገር ለመማረርና ሀገርን " ለመጥላት" ፣ ቢያንስ በሀገርና በስርዓቱ (ብዙዎች ዘላቂዋን ሀገርና ነገ የሚወድቀውን ስርዓት ለይተው አያዪም) እምነት ለማጣት ቴዲ ይቀርባል ። ይህ ሁሉ ግን ልጁን አሜሪካዊ ለማድረግ ውሀ የሚቋጥር ምክንያት አልሆነለትም ። ስለዚህ የቴዲን ሀገሬ እሰማታለሁ ። ሀገሬ ሲል እውነትም ሀገሩን እያሰበ ነው ። ቴዲ " ሀገሬ ለእኔ የሙዚቃ ግጥም ማድመቂያዬ አይደለችም ፤ ሀገሬ ናት " ቢለኝ አምነዋለሁ ። ብዙዎች ግን አፋቸው እንጂ ተግባራቸው ይህን አይልም ። የቴዲ አፍሮ ኢትየጵያ በስሟ ግጥም የሚሰራላት ፣ ዜማ የሚንቆረቆርላት ፣ ብር የሚታፈስባት ብቻ አይደለችም ። እንደ ትናንቱ ሁሉ ዜግነቷ የሚወደድ በጭንቅ ውስጥ ያለች የተስፋ ሀገር ናት ። ቴዲ ልጆቹን በጉዲፈቻ ማሳደግ የፈቀደ ክፉ አባት አይደለም ። የሚዘፍንላትና በዘፈኑም ሀብት ያፈራባትን ሀገሩን የንግድ መደብር አላደረጋትም ። መኖሪያውና የልጆቹ ማደጊያ እንድትሆን መርጧታል ። ብዙዊች ግን ፣ የቴዲ ከሳሾችም ጭምር ይህ የሀገርን ሀገሬ የማለትና ባለሀገር የመሆን ሞራላዊ ድፍረት በውስጣቸው የለም ።

Tuesday, December 2, 2014

ዘጠኙ ፓርቲዎች ለቀጣይና ለቀሩ ስራዎቻቸው ያወጡትን እቅድ በተመለከተ መግለጫ ሰጡ።እንዲሁም የህዳር 27 እና 28 የተቃውሞ ሰልፉን እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው።


ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል ህዳር 22 ቀን  ድብዳቤ መጻፉን አስታውቀዋል፡፡
“በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ መሆኑንና ሠልፉም በታቀደው ጊዜና ቦታ እንደሚደረግ ወስኖ የመልስ ደብዳቤ ” ማስገባቱንም ገልጸዋል።
የፓርቲዎቹ መግለጫ አያይዞም “ትግላችን ነጻነታችንና ክብራችን የማስመለስ በመሆኑ መንገዱም ፍጹም ሠላማዊ፣ ህጋዊና  ህገ- መንግሥታዊ ስለሆነ የህዳር 27/28  ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርና የማይቀርበት መሆኑን ለመግለጽና ነጻነትና ክብርን ወዳድ ኢትዮጵዊያንና የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ለዚህ ታሪካዊ ዕለትና ሠላማዊ ትግል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪያችንን እናቀርባለን።” ብሎአል። 

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ኑ- ለነጻነታችንና ክብራችን ድምጻችንን በጋራ እናሰማ!

ከባርነትና ውርደት ለመላቀቅ ነውና በፍጹም አይቀርም፣ አይቀርም!

የ9ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ ››በሚል መርህ የመጀመሪያ ዙር ዕቅዱን ለህዳር ወር አዘጋጅቶ ወደ እንቅስቃሴ ከገባ ሦስት ሣምንታትን አሳልፏል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራትና የተጓዝንበትን መንገድ ለጉዳዩ ቀዳሚ ባለቤትና ለባለ ድርሻ አካላት ስናሳውቅ የነበረ በመሆኑ ያጋጠሙንን ችግሮች በመደጋገም ማሰልቸት አንሻም፡፡

ስለሆነም የዛሬው መግለጫችን በቀጣይ ለቀሩን ተግባራት የደረስንበትን ድምዳሜና ያወጣነው ዕቅድ በሚመለከት ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ በእስከዛሬው እንቅስቃሴያችን ይዘን የተነሳነው ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› የሚለው መርህ ትክክልና ወቅታዊ፣ ያነሳናቸው ጥያቄዎችም አግባብ መሆናቸውን ያረጋገጥንበትና ገዢው ፓርቲ መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማለት ፍጻሜዬ ነው በሚል ከገባበት ከፍተኛ የፍርኃት ስሜትና ሥጋት ለተቃውሞ ጎራው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በሩን ለመዝጋት የተዘጋጀ መሆኑን አገር ለ23 ዓመታት በላይ ካስተዳደረ መንግስታዊ ሥርዓት የማይጠበቅ መረን የለቀቀ የውንብድና ተግባራት ያረጋገጥንበት ነው፡፡ በመሆኑም ጥያቄዎቻችንን በህገ መንግስቱና በአገሪቱ ህጎች መሠረት ለመመለስ ቀርቶ ለመስማትና ለማንበብ ፍቃደኝነቱና የኃላፊነት ስሜቱ እየተሟጠጠ በመሆኑ የአፈናና ማስፈራራት መንገድን ብቸኛ አማራጭ አድርጎታል፡፡ ይህ በመሆኑም የራሱን መንግሥታዊ መዋቅር አሰራር ሥርዓት እንኳ በአደባባይ ለመቀበል እምቢተኛ መሆኑን በአደባባይ አረጋግጧል፡፡ ባለሥልጣናቱ በግንባር ያቀረብነውን ደብዳቤ ካለመቀበል አልፈው በመንግሥታዊው ፖስታ ቤት የተላከ ደብዳቤ ያለመቀበላቸው የሚያመለክተው ይህንና የደረስንበትን የመልካም አስተዳደር አዘቅት ነው፡፡

በተቃራኒው አበረታችና መልካም ዜናም አለ፡፡ ይህም ይህን የአፈናና ማስፈራትት አካሄድ አንቀበልም ያሉ ለነጻነታቸውና ክብራቸው፣የራሳቸው ብቻ ሣይሆን የመንግሥት መዋቅሮችና ባለሥልጣናትም ነጻነት መረጋገጥ አለበት ብለው የቱንም መስዋዕትነት ለመክፈል በቁርጠኝነት የተዘጋጁ በትብብሩ የታቀፉ ፓርቲዎች፣ አመራርና አባላት መኖራቸውና በትግሉ ለመቀጠል መወሰናቸው ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ትብብሩ ለመጀመሪያ ዙር ዕቅዱ ማጠቃለያ የህዳር 27/28 የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ አመራሩ በግንባር ቢያቀርቡም አሻፈረኝ አንቀበልም ያሉት አሰራርና ባለሥልጣናት ከፖስታ ቤት እንዲቀበሉ ተደርጓል፡፡ለዚሁ ደብዳቤ መስተዳድሩ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ (ቁጥር 3/1983) ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል በዛሬው ቀን (22/03/07) መልስ አድርሶናል፡፡ በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ መሆኑንና ሠልፉም በታቀደው ጊዜና ቦታ እንደሚደረግ ወስኖ የመልስ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡ በመሆኑም ለተግባራዊነቱ ዝግጅቱን በሙሉ አቅም ጀምሯል፤ ለዚህም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከአገር ውስጥና ከውጪ አጋርነታቸውን ገልጸዋል፤ አበረታተውናል፡፡ ይህም የያዝነው የትብብር የጋራ ዓላማችን ተቀባይነት፤ የኅብረትና አንድነትን ዋጋ አመላካች፣ ለማይቀረው ሠላማዊ ትግላችን ሥንቅ ነውና በታላቅ አክብሮት ተቀብለነዋል፡፡

ስለሆነም ይህ መግለጫ ትግላችን ነጻነታችንና ክብራችን የማስመለስ መንገዱም ፍጹም ሠላማዊ፣ ህጋዊና ህገ- መንግሥታዊ ስለሆነ የህዳር 27/28 ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርና የማይቀርበት መሆኑን ለመግለጽና ነጻነትና ክብርን ወዳድ ኢትዮጵዊያንና የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ለዚህ ታሪካዊ ዕለትና ሠላማዊ ትግል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ነጻነታችንና ክብራችን ለማስመለስ ዋጋ ለመክፈል እንዘጋጅ፣ ያለመስዋዕትነት ድል የለምና!

Thursday, November 27, 2014


የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ የወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት ታላቅ ሰላማዊሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ ተካሄደ!!!

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ የወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት በዛሬው እለት ሀሙስ (November 27,2014)  በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሩቅም ከቅርብም በአንድነት በመሰባሰብ ከቀኑ 13፡30 እስከ 15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
DSC_0233DSC_0220DSC_0268
የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ  በአንምባ ገነኑ የወያኔ ቡድን በህገ ወጥ መንገድ ታፍነውና ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም ሲሆን በሰልፉ ስፍራ የተገኙ ሰዎች ሁሉ አቶ አንዳርጋቸው ለዲሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት መከበር ከወጣትነት ጀምሮ የታገለ ታላቅ የሰላም ምሳሌ፣ የፍትህ ተምሳሌት፣ የነጻነት በር ከፋች እንዲሁም አገራዊ ስሜት የተላበሰ አርበኛ እንጂ እስር፣ ድብደባና መሰቃየት የሚገባው ሰው አልነበረም በማለት ለእንግሊዝ መንግስት በኢንባሲው አማካኝነት ዜጋዋን ከአረመኔና ጨካኝ መዳፍ እንድትታደግና ፍትህ እንዲያገኝ  በከፍተኛ ድምጽ አሳስበዋል።
ወጣቶች እጃቸውን በሰንሰለት በማሰር እኛም እንደ አርበኛው አንዳርጋቸው ጽጌና በእስር ቤት የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውን የቁም እስረኞች ነን የሚል ጥልቅ መልእክት አስተላልፈዋል። ብዙ መስራትና መጻፍ የሚችሉ እጆች፣ መናገር የሚችል አንደበት፣ የእውቀት ባለቤት የሆነ አእምሮ ታስረዋልና እኛም ወጣቶች እስረኞች ነን በሚል ውስጣዊ ስሜት ለስዓታት የኖርዌ ብርድና ቁር ሳይበግራቸው እጃቸውን በሰንሰለት በማሰር ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል።
DSC_0185DSC_0193DSC_0208DSC_0323

እንዲሁም ሰልፈኞቹ  የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ድምጽና ስሜት ለኢንባሲው  አሰምተዋል።  ከአሰሟቸው  መፈክሮች መካከል ለአብነት “ UK, were is your citizen, Free Andrgachew Tsige, Andargachew is our icon of democracy, where is your action , stop discrimination among citizens, Yes, we are all Andrgachew Tsige, Brtain dont support terrirost regim in Ethiopia” የሚሉት ይገኙበታል::
ሰልፎኞችም የኢንግሊዝ  መንግሥት የነጻነት ታጋዩን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ከወያኔ እጅ እስካላወጡ  ድረስ ተቃውሞው በቀጣይ እስከ መጨረሻው ድረስ ከዚህ በበለጠ ቁጣና እልህ በተሞላበት ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ ተናግረዋል።  በተመሳሳይም ለአንዳርጋቸው ያላችውን ፍቅርና ክብር በአደባባይ አስመሰክረዋል።
በመጨረሻም በድርጅቱ የተዘጋጀውን  ደብዳቤ በድርጅቱ ሊቀመንበር በአቶ ዮሃንስ ዓለሙ  አማካኝነት ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ ጉዳዩ ትኩረት የሚሻና ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን ለማሳሰብ ቢፈለጉም ተወካይ ሊመጣ ባለመቻሉ ደብዳቤው በበር ጠባቂው አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጓል። በተጨማሪም ደብዳቤውን በኢሜይል በድጋሚ እንደሚላክ ለሰልፈኞች አሳውቀዋል። ወደፊት በሚደረገው ተቃዉሞ ላይ ተወካይ መጥቶ እስካልተቀበለንና አቶ አንዳርጋቸው የደረሱበትን እስካላወቅን ድረስ ከኢንባሲው በር የማንቀሳቀስ መሆኑን ሁሉም በከፍተኛ ድምጽ አሰምተው ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ ከቀኑ 15፡00 ተጠናቋል።

ዛሬም ነገም ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ታልቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ ተካሄደ!!!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ የወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት በዛሬው እለት ሀሙስ (November 27,2014) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሩቅም ከቅርብም በአንድነት በመሰባሰብ ከቀኑ 13፡30 እስከ 15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአንምባ ገነኑ የወያኔ ቡድን በህገ ወጥ መንገድ ታፍነውና ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም ሲሆን በሰልፉ ስፍራ የተገኙ ሰዎች ሁሉ አቶ አንዳርጋቸው ለዲሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት መከበር ከወጣትነት ጀምሮ የታገለ ታላቅ የሰላም ምሳሌ፣ የፍትህ ተምሳሌት፣ የነጻነት በር ከፋች እንዲሁም አገራዊ ስሜት የተላበሰ አርበኛ እንጂ እስር፣ ድብደባና መሰቃየት የሚገባው ሰው አልነበረም በማለት ለእንግሊዝ መንግስት በኢንባሲው አማካኝነት ዜጋዋን ከአረመኔና ጨካኝ መዳፍ እንድትታደግና ፍትህ እንዲያገኝ በከፍተኛ ድምጽ አሳስበዋል።
ወጣቶች እጃቸውን በሰንሰለት በማሰር እኛም እንደ አርበኛው አንዳርጋቸው ጽጌና በእስር ቤት የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውን የቁም እስረኞች ነን የሚል ጥልቅ መልእክት አስተላልፈዋል። ብዙ መስራትና መጻፍ የሚችሉ እጆች፣ መናገር የሚችል አንደበት፣ የእውቀት ባለቤት የሆነ አእምሮ ታስረዋልና እኛም ወጣቶች እስረኞች ነን በሚል ውስጣዊ ስሜት ለስዓታት የኖርዌ ብርድና ቁር ሳይበግራቸው እጃቸውን በሰንሰለት በማሰር ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል።
Like· 

Monday, November 17, 2014

ለሃገር መከላከያና ለፖሊስ ሰራዊቱ ፤ እንዲሁም ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አባላት በሙሉ የቀረበ ሃገራዊ ማሳሰቢያ፤
በጥቂት ፈላጭ ቆራጮች የሚመራው የህወሓት/ኢህአዴግ ሥርዓት ሃገርን የማጥፋትና ህዝብን የመነጣጠል እኩይ ዘመቻ፤ ኤርትራን በማስገንጠል ተጀምሮ፤ ዛሬ ውድ ዜጎቻችን ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬአቸው በግፍ ተገፍተውና በየሜዳው ተወርውረው በረሃብ እየማቀቁ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ መሬትና ሃብት ፍፁም ግዴለሽ በሆነ መልኩ፤ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ብቻ በዉለታ ለባዕዳን ሃገራት አየተሰጠና ይህ ነው የማይባል ፋይዳ በሌለው ቤሳበስቲን አየተቸበቸበ ይገኛል። ለዘመናት በደም ተጠብቆና ተከብሮ የኖረው የማንነታችን መገለጫ አርማችን፤ ሰንደቅ አላማችን፤ ክብር ተነፍጎ በየስርቻው ጨርቅ ነው ተብሎ አየተጣለ ይገኛል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚገነዘበው እነኝህ ጥቂት አምባገነኖች ላለፉት 23 አመታት በሃገርና በህዝብ ላይ በማናለብኝነት ያደረሱትን ግፍና መከራ፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስታስፈጽሙና በቸልተኝነት እንደ ባዳ ስትመለከቱት እንደነበራችሁ ይታወቃል። ይሁንና ይህ ሁሉ በደል ሲደርስ አንጀታችሁ እያረረ ልባችሁ በሃዘን እየተሰበረ ምንም ማድረግ ሳትችሉ የቆያችሁበት ምክንያት ሥርዓቱ ያደርስባችሁ በነበረው ከፍተኛ ተፅዕኖና አፈና መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ይረዳል። ነገር ግን ይህን ጠንካራ የህዝብ እምነት የምታረጋግጡት እናንተና እናንተ ብቻ መሆናችሁ የሁሉም ህብረተሰብ እምነት ነው።
ዛሬ ሁላችሁም በጥልቀት መርምራችሁ በማስተዋል መፍትሄዎችን ልታበጁባቸው ግድ የሚሉ ዘርፈብዙ ችግሮች ከፊት ለፊታችሁ ተደቅነዋል። እስከመቼ የጥቂቶች የበላይነት በሃገራችን ነግሶ ይኖራል!? እስከመቼስ በዚህች ታላቅ ሃገርና በክቡር ህዝባችን ላይ የሚደርሰው በደል እንዲቀጥል እንፈቅዳለን!? እስከመቼስ ጥቂቶች በእናንተ ትከሻና ጉልበት ተጠቅመው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብን ሲጨቁኑ ይኖራሉ!? እስከመቼስ ጥቂት የህዝብ ጠላቶችን ስልጣንና ጥቅም ለማስከበር አገልጋይ ሆናችሁ በዝምታ መኖር ይቻላችሁ ይሆን!? እስከመቼስ በጥቂቶች ቀጭን ትዛዝ የምትወዱትን ንፁህ ወገናችሁን ስታሳድዱና ስትገሉ ትኖራላችሁ!? እስከመቼስ በጥቂት ግለሰቦች ጭፍን ትዕዛዝና በናንተ ፈፃሚነት ብዙዎች ሲሰቃዩና ሲጎዱ ይኖራሉ!? የዚህ ሁሉ ችግር ምንጮች ጥቂት አምባገነን ገዚዎቻችን ቢሆኑም፤ መፍትሄው ግን በጃችሁና በጃችሁ ይገኛል።
ውድ የኢትዮጵያ ልጆች! ዛሬ ይህ ለሃገራችሁ የሚጠበቅባችሁን ሃላፊነት በአግባቡ እንዳትወጡ በተለያዩ አፈናዎች ጠፍንጎ መፈናፈኛ በማሳጣት፤ አዋርዶ የምትወዱትን ህዝብና ሃገር ጎድታችሁ የጥቂት አምባገነኖችን ስልጣንና ጥቅም ለማስጠበቅ አገልጋይና ሎሌ ሆናችሁ እንድትቀሩ እያስገደዳችሁ የሚገኘው ጨቋኝ አገዛዝ፤ በህዝብ ትግል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚወገድበት ወቅት መድረሱ እሙን ሆኗል። ይህ ታላቅ ህዝባዊ ድል የተገኘው እንደው ዝም ብሎ በመመኘት ሳይሆን፤ በመላው ኢትዮጵያውያን በዋነኝነት ደግሞ በወጣት ወገኖቻችሁና ልጆቻችሁ የተገነባው ህዝባዊ ንቅናቄ ባካሄደው በሳል ስትራቴጂ፣ ትግልና፣ መስዕዋትነት መሆኑን እንደምትረዱ እናምናለን። ይሁንና ይህ የተቀደሰ የትግል ጅማሮ ፍፃሜው እናንተን ጨምሮ፤ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብን ነፃነት ሊያረጋግጥ የሚችለውና በውጥኑ መሰረት ለሁሉም እኩል የሆነችና ከቂም በቀል የፀዳች ሠላማዊት ሃገርን መገንባት የምንችለው፤ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ቆራጥ ትግልና ርብርብ መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል። ይህ ህዝባዊ ትግል፤ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ፤ እናንተም የህዝባችሁን ህልውናና የሃገራችሁን ዘለቄታዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ከህዝብ ጎን በቁርጠኝነት ተሰልፋችሁ በፅናት በመታገል፤ ነፃነታችሁን የምታረጋግጡበት ወሳኝና መልካም አጋጣሚ ነው። በመሆኑም በቀጣይ በሚደረገው ህዝባዊ የትግል ሂደት ለብዙሃኑ ህዝብ ከለላ በመሆንና ወገንተኝነታችሁን በተግባር በማሳየት፤ ብሎም ህዝብ የጣለባችሁን ከፍተኛ ሃገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት፤ ታሪካችሁን አድሳችሁ በክብር መዝገብ ላይ ታሰፍሩ ዘንድ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚጠብቅ ተገንዝባችሁ፤ የሚጠበቅባችሁን ታሪካዊ ሃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ እንድትሆኑ ስንል ከታላቅ ሃገራዊ አደራ ጋር እናሳስባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Sunday, October 26, 2014

የኖርዌይ ኦስሎ ወጣቶች ስለአገራቸው ውይይት አካሄዱ

የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የወጣቶች ክፍል ቅዳሜ ጥቅምት 10/2007 ዓም(ኦክቶበር 25/2014) “ለአገር እድገትና ለድሞክራሲ ግንባታ የወጣቶች አስትዋጾ” በሚል ሰፊ ውይይት ከ15:00 እስከ 18:00 ስዓት ተካሄደ።
የመግቢያ ንግግሩ በድርጅቱ ህዝብ ግንኙነት በአቶ አቢ አማረ የውይይቱን ዓላማና አስፈላጊነት ለተሳታፊው በመግለጽ ወጣቶች ውይይቱ ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ እንዲካሄድ አጽንኦት ሰጠው ውይይቱ ቀጥሏል።
OLYMPUS DIGITAL CAMERAOLYMPUS DIGITAL CAMERA
በመቀጠልም የአንድ አገር ቀጣይነት ያለው እድገት የሚለካው በአላት ሃብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን ያንን ተረክቦ በአደራ ለትውልድ ማስተላለፍ የሚችል ትውልዳዊ ትስስር መኖርና ይህንንም እንደ ድልድይ ሆኖ ከአንዱ ትውልድ ወደቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንደሆነ፤ በማንኛውም አገር፣ ጊዜና ዘመን እያንዳንዱ ተተኪ ትውልድ የአገሩ ወራሽ፣ ተተኪና ተረካቢ፣ ጠባቂና ለሚቀጥለውም ትውልድ የማውረስ፣ የማስተላልፍና የማስረከብ ኃላፊነትና ግደታ እንዳለበት፤ ወጣት ለአንድ አገር በሦስቱም ዘርፍ ማለትም በማህበራዊ፣ በምጣኔ ሃብታዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማድረግ እንደሚችል ተረድቶ ወጣቱ ትውልድ በዓላማ፣ በቁርጠኝነት፣ በዕቅድና በመደራጀት ለአገር እድገት፣ ነጻነት፣ፍትህና ዲሞክራሲ መታገልና ለውጥ ማምጣት እንዳለበት በክፍሉ ተወካይ በወጣት ይበልጣል ጋሹ ለውይይት እንደ መነሻ ባቀረበው ሃሳብ ላይ ገልጿል። እንዲሁም የወያኔን አስከፊ፣ ዘረኛና አምባገነናዊ ሥርዓት ለማስገወገድ ወጣቱ ትውልድ የበኩሉን ሃላፊነት ወስዶ ይህን ለአገርና ለህዝብ መቆም እንዳለበት በመግለጽ የውይይት ሃሳቦችን አስቀምጦ ስዓቱን ለውይይት ክፍት አድርጓል።
OLYMPUS DIGITAL CAMERAOLYMPUS DIGITAL CAMERA
በውይይቱም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወጣቱ ለክፉም ለመልካምም የራሱ የሆነ ትልቅ አገራዊ ታሪክ እንዳለው በመግለፅ ወጣቱ እንዴት መታገልና ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ገንቢ አስትያየቶች፣ ምክሮችና አቅጣጫ ተሰጠዋል። ከተነሱትት ሃሳቦች መካከልም በበቂ ሁኔታ መደራጀት፣ በእውቀት እራስን ማብቃት፣ አገራዊ ስሜት መላበስ፣ታሪክን ጠንቅቆ ማዎቅ፣ አንድነት መፍጠር፣ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ስልታዊ እቅድ መከተል፣ አቀራረባችንን እና ትኩረታችን መለየት፣ ቀጣይነት ያላቸው የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት እና ክፍሉን ማደራጀት ከተነሱት አበይት ሃሳቦች መካከል ነበሩ። በተጨማሪም ክፍሉ ከሌሎች የወጣት ህብረት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ ወጣቱን ይበልጥ ማንቃትና ፖለቲካዊ አድማሱን ማስፋትና የወያኔን ጨቋን መንግሥት ሊታገል የሚችልበትን አቅጣጫ ማሳየትና መንደፍ ተገቢ መሆኑን አጽንኦት ተሰጦበታል።
በአጠቃላይ ወጣቶች ለአገር እድገት፣ ለነጻነት፣ ለሰባዊ መብት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ ግንባታ የወጣቱ አስትዋጾ ከፍተኛ መሆኑን ተረድቶ በሁለገብ ትግል ወያኔን/ ሕወሓትን ለማስወገድ የበኩሉን ኃላፊነትና ግዴታ መወጣት እንዳለበት በሥፋት ተገልጿል።
በመጨረሻም በአቶ ልዑል ታደሰ ድርጅቱ የድርጅቱ ጉዳይ ሀላፊ የውይይቱ ሂደት ጥሩና የተሳካ መሆኑን ገልጸው ለክፍሉ በማነኛውም መልኩ ድጋፍ ማድረግና ማጠናከር ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅ መሆኑን መልእክት አስተላልፈዋል። ውይይቱም ቀጣይነት እንዲኖረው በተሳታፊዎች አስትያየት ተሰጦ ውይይቱ ተጠናቋል።
ኢትዮጵያለዘላለም ትኑር !!
የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የወጣቶች ክፍል!!

Wednesday, October 22, 2014

አልበርት አነስታይን ኢኒስቲቲውት በኖርዌይ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖችን ለሁለት ስአታት የቆየ የትግል ስልት ስልጠና ስጠ

  • 891
     
    Share
በቅርብ አመታት በነውጥ አልባ የትግል ስልት ጥቃት ሳቢያ ስልጣናችውን ያጡትን በርካታ የስሜን አፍሪካ ጨቋኝ መንግስታትን እጣ ለወያኔ ለማቋደስ ቆርጠው የተነሱት በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጲያውያንን መስረታዊ ትግል ስልቶችን ለማስተማር በማስብ ዴሴሶን ራዲዮ ኦክቶበር18 2014 ያዘጋጀው ስብስባ ውጤታማ ሆኖ ተጠናቋል
የአልበርት አነስታይን ማህከል ዋና ዳይሬክተር የሆነችው ጀሚላ ራኪብን በመጋበዝ የተካሄደው ስብስባ ሰላሳ የሚጠጉ ኢትዮጲያውያን የተገኙበት ሲሆን ፣ የማእከሉ ዋና ዳይሬክተርም ስፊውን ግዜ በመውስድ ሰለ ማእከሉ መስራች ዶር ጂን ሻርፐ ምርምሮችና ስራዎች አብራርታለች።
ላለፉት ሰላሳ አመታትም በጂን ሻርፐ ጥናቶች እገዛ ውጤት ያስመዘገቡ አገሮችን ነባራዊ ሁኔታ በከፊል አብራርታ ህዝባዊ ነውጥ አልባ ትግል እጅግ መታቀድ ያለበት እንደሆነ በመጠቁም ሲሳካም ለምን እንደተሳካ ሲከሽፍም ለምን እንደከሽፈ ማጥናት እንደሚገባ አስረድታለች በተጓዳኝም በርካታ መስረታዊ ጽንስ ሃሳቦችን የተነተነች ሲሆን ከተስብሳቢው በርካታ ጥያቄዋችም ተነስተዋል በነውጥ አልባ ትግልንና ወታደራዊ ትግልን በማጣመር ሁለገብ የሚባለው የትግል ስልት ጥናት እየተደረገበት እንደሆና አመርቂ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችልም ጠቁማለች ።
ውይይቱም 15: 30 ላይ ቢጠናቀቅም በቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ ተመልሳ በመምጣት ስፋ ያለ ስልጠና እንደምትስጥ ለራዲዬ ክፉላችን አስታውቃለች።
rte

Thursday, October 16, 2014

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ወገንተኝነቱን የሚያሳይበት ወቅት አሁን ነው!

ዘረኛውና ፋሽስታዊው የህወሓት አገዛዝ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝነት በመከፋፈል ሹመቱና ጥቅማ ጥቅሙን ለራሱ ወገን፣ ችግሩንና መከራዉን ግን ለሌላው ኢትዮጵያዊ ያደለ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ሳይማሩና ሳይሰለጥኑ የጄኔራልነት ማዕረጎችን በሙሉ ሰብስበው የወሰዱት የህወሓት አባላት መሆናቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው።
በወያኔ መዳፍ ውስጥ እየተሰቃየች ባለችው ኢትዮጵያችን ውስጥ በዘርም ይሁን በፓለቲካ አመለካከት ከህወሓት የተለዩ ኢትዮጵያዊያን ቢማሩም ቢሰለጥኑም ለከፍተኛ አመራርነት እንደማይበቁ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያየነው ነው። አገዛዙ ቅራኔ ውስጥ በገባባቸው ቦታ ሁሉ እየዘመቱ ሕይወታቸውን እየገበሩ ያሉት ግን በመካከለኛና ዝቅተኛ ማዕረጎች ያሉ ኢትዮጵያዊያን መኮንኖችና ብዙሃኑ የሠራዊቱ አባላት የሆኑ ወታደሮችናቸው። ብዙሃኑ የሠራዊት ክፍል አለቆቹን ከመጠበቅ ባለፈ ድምጹን ከፍ አድርጎ ለመናገር እንኳን የማይፈቀድለት ሎሌ ተደርጓል።
ለኢትዮጵያዊ ወታደር ለህወሓት ሎሌ ከመሆን በላይ የሞት ሞት የለም። ብዙሃኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊቱ አባላት በጥቂት የወያኔ ሹማምንት የሚረገጥ መሆኑ የሠራዊቱን አባላት የግል ስብዕና ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሠራዊቱን ክብር ይነካል። የሠራዊታችን የህወሓት አገልጋይ መሆን የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያን ያዋርዳል። ይህ ዉርደት በዚህ ሁኔታ መቀጠል የለበትም።
ከእንግዲህ ጄኔራሎችና ሌሎችም የበላይ አዛዦች ሁሉ የአንድ አካባቢ ተወላጆች በሆኑበት ሠራዊት ውስጥ ተስማምቶ መኖር መቀጠል እያንዳንዱን የመከላከያ ሠራዊት አባል ሊያሰፍር ይገባል። የህወሓት ጄኔራሎች ጮማ በውስኪ ሲያወራርዱ፤ በህንፃዎች ግንባታ፣ በባንኮች ንግድ፣ በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተሰማርተው ቢዝነሳቸውን ሲያጧጥፉ፣ ምስኪኖቹ የሠራዊቱ አባላት በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአማራና በሌሎች የአገሪቱ ግዛቶች እየተወረወሩ ወገኖቻቸውን የሚፈጁበት ሥርዓት ማብቃት አለበት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ብዙሃኑ አባላት ቤተሰቦቻቸው በችጋር እየተቆሉ የአዛዦቻቸው ሀብት ጠባቂ መሆናቸው ማክተም አለበት።
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የጭለማ ዘመን ታሪክ እያበቃ መሆኑን የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ነው። መሣሪያዎቻቸውን እንደያዙ የነፃነት ኃይሎችን የሚቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨረመ መጥቷል። ሠራዊቱ ከሕዝብ ጎን እንደሚቆም ውስጥ ውስጡን የሚላኩ መልዕክቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። ይህ አበረታች ዜና ነው፤ ግን በቂ አይደለም። ወያኔን ከውስጥም ከውጭም የምናጣድፍበት ጊዜው አሁን ነው። የነፃነት ኃይሎችን መቀላቀያ ጊዜ አሁን ነው፤ በሠራዊቱ ውስጥም በህቡዕ መደራጃ ጊዜ አሁን ነው። ይህን ጊዜ መጠቀም ብልህነት ነው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ጥቂት የህወሓት ጥጋበኞች በብዙሃኑ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ላይ የሚያደርሱት በደል ማብቃት አለበት ይላል። ግንቦት 7፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሙስና የደለቡት፣ ትዕቢተኛና ጨካኝ መሪዎቻቸው ፍጹም ኢትዮጵያዊ ባህርይ የሌላቸው ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች እንደሆኑ በመረዳት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ክንዱን እንዲያነሳባቸው ጥሪ ያደርጋል። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሕዝብም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አንድ ወጥ እንዳልሆነ እና በመካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ ያሉ መኮንኖችና አብዛኞዎቹ ወታደሮች የሕዝብ ወገን መሆናቸውን እንዲገነዘብ ያሳስባል። “አብረን ነው ዘረኛውና ፋሽስቱን ወያኔን ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ አውርደን የምንጥለው” ስንል አብዛኛው የመከላከያ ሠራዊታችን ኢትዮጵያዊ ወገናችን እንደሆነ እና በወደፊቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ውስጥም ጉልህ ሚና እንዲጫወት የምንፈልግ መሆኑን ግልጽ ማድረግ እንሻለን። የመከላከያ ሠራዊቱም የሕዝብ ወገንተኝነቱ በተግባር እንዲያሳይ ጥሪ እናደርጋለን። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ አካል ነው፤ የሕዝብ ወገናዊነቱ በተግባር የሚያሳይበት ትክክለኛ ጊዜ ደግሞ አሁን ነው እንላለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
የወያኔ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም ለጥቂ ተሳቱ
ሀፍረትና ይሉኝታ የሚባሉ ነገሮች በአጠገባቸው ያለ የማይመስላቸው ብልግና ጭካኔ ወገንን ካለ ህግ መግደል ማዋረድ የህዝብ ሀብት በጠራራ ፀሐይ መዝረፍ ለሰው የተስጠ ፀጋ አድርገው የሚቆጥሩትን የወያኔ መንግስት በሔደበት ቦታ ሁሉ መዋረድ ማየትና መስማት የተለመደ ሆኖአል።

በዛሬው አለት በኖርዌ Invest in Ethiopia ተብሎ በ Norwegian-African Business Association አዘጋጅነት በተጠራው ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ወደ ኖርዌ የመጣውን የወያኔ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም ላይ Human right before investment አና የተለያዩ መፈክሮች በማሠማትና የእንቁላል ናዳ በማውረድ የሚንስትሩን አንገት በማስደፋት የኖርጂያንን ፖሊስ አጨናንቀውት ውልዋል

የዚህ የወረበላ የወያኔ መንግስት መውደቂያ አሁን ነው በዘር በሐይማኖት መከፋፈል ያክትማል እጅ ለ እጅ ተያይዘን የነፃነት ዜማ አናዜማለን ኢትዮጵያ የብሔር ቢሔረስቦች አገር እንጂ ያአንድ ብሔር አይደለችም በማለት የተቃውሞ ስልፉን በተሳካ ሁሄታ አጠናቋል http://www.nrk.no/nyheter/1.11989821

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኖርዌይ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በተጠራ ጉባኤ ላይ የተገኙትን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በመቃወም የተጠራው ሰልፍ የአገሪቱን ዋነኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢነርኬን ሽፋን አግኝቷል።
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በተጠራው ተቃውሞ፣ ኢትዮጵያውያን የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ ኖርዌይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከሚፈጽመው መንግስት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት እንድታቆም ጠይቀዋል።በኢትዮጵያ ለሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት ኖርዌይ ተጠያቂ መሆኗንም ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደ/ር ቴዎድሮስ ወደ ሆቴላቸው ሲያመሩ መኪናቸው በእንቁላል መደብደቡ የአገሪቱን የሚዲያ ትኩረት ስቧል።
Ethiopians in Norway demonstrated against Ethiopia’s Foreign Minister Dr. Tedros Adhanom today.
He was expected to participate in ‘Invest in Ethiopia’ seminar. The seminar wa organized by the Norwegian-African Business Association (NABA).
"በኢትዮጵያ ኢንቨስት ኣድርጉ" ሰሚናር ተከታታይ ዘገባ
ተከታታይ ዘገባ
ኖርወይ ንግድ ምክርቤት ኮንፈደርሽን ጽ/ቤት ኦስሎ
የኖርወይ የንግድ ምክርቤቶች ኮንፈደረሽንና(NHO)የኖርወጂያን ኣፍሪካን የንግድ ቻምበር እንዲሁም የኖርወይ የግል ንግድ ሰክተር ልማት ኣማካሪ ጽ/ቤት(Veiledningskontoret)በጋራ ያዘጋጁት "በኢትዮጵያ ኢንቨስት ኣድርጉ" የተስኘው የዛሬው ኦክቶበር 16 2014 ሰሚናር በኦስሎ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡ ፡ በኢትዮጵያ የኖርወይ ኣምባሳደር ኣንድሪያስ ጎርደር ጨምሮ ኣዘጋጆች የእንኳን ደህና መጣችሁና የመግቢያ ንግግር ኣድርገዋል፡ ፡በፕሮግራሙ መሰረት በ 10:35 የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ተዎድሮስ ኣድሓኖም ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡ ፡ በኖርወይና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሚና ያላቸውና የኖርወይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመወከል የተገኙ 8 ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ብቻ በስብሰባው የመሳተፍ ዕድል ኣግኝተዋል፡ ፡ ሌሎች ተሳታፈዎች ከኖርወይ መንግስትና የንግድ ምክርቤቶች የመጡ ናቸው፡ ፡
እንደተለመደው የኣገሪቷ ልማት የማይዋጥላቸው ጥቂት የ ግንቦት 7 ጀሌዎች ስብሰባዉ ከሚካሄድበት ርቀዉ የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ነው፡ ፡
Publisert: 16.10.2014 10:16
Av Girmay Assemahegn
 በኖርወይ የኢትዮጵያ ኤክስፐርት ሸቲል ትሮንቮል መድረኩን ይዘዋል፡ ፡ የኢትዮጵያ መንግስት ያስገኛቸውን የኤኮኖሚያዊ ድሎችን የማይክዱትና በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሂደት ሂስ በማቅረብ የሚታወቁት እኝህ ምሁር በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግስት  ላይ ያላቸውን ሂስ በማለዘባቸው በ ኣክራሪዎቹ በኖርወይ የግንቦት 7 ጀሌዎች ሲወረፉ ሰንብተዋል፡ ፡ ሸቲል በዛሬው ንግግራቸው የኢትዮጵያ ልማታዊ እድገት የሚደነቅ መሆኑን ኣልሸሸጉም፡ የንግግራቸውን ኣንኳር ነጥቦች በሚቀጥለው ዘገባቸን ይዘን እንቀርባለን፡ ፡ ሸቲል የዛሬው ንግግራችው  የኢትዮጵያ ፖሊቲካ ኣደጋዎች ግምገማ  የሚመለከት " Risk assessement perspectives on Ethiopian politics " በሚል የተዘጋጀ ነው፡ ፡

ዶክተር ተዎድሮስ ኣድሓኖም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መድረኩን ይዘዋል፡ ፡ ዶክቶር ተዎድሮስ ንግግር መስህብ እንዲኖረው ዘና ባለመንፈስ ታዳሚዎቹን ፈገግ እያሰኙ የኣገሪቷን ተጨባች ሁኔታ ኣንኳኳር ነጥቦቹን ጠቅሰዋል፡ ፡  በ ስብሰባው መጨረሻ ታዳሚዎች ጥያቄና ኣስተያየት ለማቅረብ ዕድል ይሰጣቸዋል፡ ፡

 የኖርወይ የንግድ ምክርቤቶች ኮንፊደረሽንና የኖርወድያን ኣፍሪካን የንግድ ችምበር የኢትዮጵያና የኖርወይ የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኝኑት በኣሁኑ ጊዜ ካለበት ተስፋ ሰጭ ሁኔታ ይበልጥ እንዲጎለብት በማለም ያዘጋጁት ሰሚናር የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክቶር ተድሮስ ኣድሃኖም ጠቃሚ መልእክት ኣስተላልፈውበታል፡ ፡
ስብሰባው ተጠናቋል፡ ፡  
 እራሱን " Democratic Change in Ethiopia Support Commitee " ብሎ የሰየመው የ ግንቦት 7 ጀሌዎች ስብስብ ፎረም ለ ኣንድ ወር ያህል ጥገኝነት ጠያቂዎችን ስሜት በመበዝበዝ ስብሰባውን ለማሰናከል ያደረገው ቅስቀሳ የኖርወጂያውያንና የትዉልድ ኣገራቸውን ጥቅም ለመጻረር በማይፈልጉ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ድጋፍ ስላላገኝ ከሽፏል፡ ፡

ይህ በእንዲህ እያለ ስብሰባው ከተካሄደበት እጅግ ርቆ በሚገኘዉ የ ኖርወይ ፓርላማ(ስቱርቲንገ) ኣከባቢ በዉጭ ጒዳይ ሚኒስትሩ ላይ እንቁላል ለመጣል ይሞከራሉ ተብለው የተጠረጠሩ  ሁከተኞች በፖሊስ ሃይል ከቦታው መወገዳቸው ኤን.ኣር. ኮ. ዘግቧል፡ ፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስብሰባው በኋላ እቅዳቸው መሰረት ከኖርወይ ባለስልጣናት ጋር የሚያደርጉትን ዉይይትና ጉብኝት ቀጥለዋል፡ ፡ 
ዶክቶር ተዎድሮስ ኣድሃኖም በኖርወይ
ዶክቶር ተድሮስ ኣድሓኖም "ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ" በሚል መርህ በኖርወይ መንግስት ትብብር የኖርወይ ንግድ ምክርቤቶችና ኖርወጂያን ኣፍሪካን ቻምበር ባዘጋጁት ሰሚናር ላይ ከምሳ በፈት ከተሳተፉ በኋላ ከሰዓት በኋላ የስራ ጉብኝቱ  በስከታማነት ኣጠናቀዋል፡ ፡ ማምሻዉን ደግሞ በ ግራንድ ሆቴል ኢትዮጵያ በኣሁኑ ጊዜ እያጠደፈች ባለችው የንግድ የኤሌትሪክና የምድር ባቡር ግንባታ ከፍተኛ እዉቀት ያካበቱትና እዉቀታቸውን ለኣገራቸው ጥቅም ለማዋል የሚፈልግ ኢትዮጵያውያንን ጋር ተገናኝተዋል፡ ፡ 


Publisert: 16.10.2014 20:41
Av Girmay Assemahegn
የኢትዮጵያ ደመኛ ጠላቶች ተላላኪዎች የሆኑ 15 ግለሰቦች  ከስብሰባው በኋል በ ፓርላማዉና በግራንድ ሆቴል ኣከባቢ እንቁላል ለመወረወር ሲሞክሩ በስፍራው ለጥበቃ የተሰማራ የፖሊስ ቡድን ለጊዜው በቁጥጥር ስር በማዋል ማንነታቸውን በመመዝገብ ከስፍራው ኣስወግዷል፡ ፡ ማምሻውን የኖርወይ ተለቪሽን  15 መለቀቃቸውን ዘግቧል፡ ፡ የፖሊስ ጥበቃ ቡድን ተወካይ መኮንን በሃገሪቱ ተለቪሽን በመቅረብ " በዚህ ዓይነት መልኩ ራስን ማጋለጡ ኣጸያፊ እንደሆነ ገልጸዋል" ጨዋ ሰላምዊ ትዉልደ ኢትዮጵያዊን የኖርወይ ኗሪዎችን የማይወክሉት እኒዚህ  ግለሰቦች ማምሻዉን ኣሳፋሪ ድርጊታቸው ነውር መሆኑን በይፋ ሌላ ጥቁር ነጥብ ኣስመዝገዋል፡  በተለይ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ሂስ የነበራቸው የኖርወይ የኢትይጵያ ጉዳይ ኤክስፐርት ሸቲል ትሮንቮል ለ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ድጋፍ ያቀረቡት ንግግር በእጅጉ ያናደዳቸው መሪዎቻቸው ሙሉ ለወር ያህል ያሰለጠኗቸውን ጥገኝነት ጠያቂዎች ዕለቱን  በማሰማረት ለኢሳት ተለቪዥን የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሊያነሱ የፈለጉት የዋሺንግተን ኤምባሲ መሰል የ"ጀብዱ" ክሊፕ ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡ ፡  
ቪድዮውን ይመልከቱ

16-10-2014 Gunbot 7 kilet be Oslo.htm
ከ 7፡30 ደቂቃ ጀምሮ ያለውን ይመልከቱ›
" የፖሊስ መኮንኑ በዚህ ዓይነት መልኩ እራስን ማጋለጥ ኣስነዋሪ መሆኑን በመግለጽ ትዝብታቸውን ገልጸዋል፡ ፡ ይህንን  ቅሌትና  ዉርደት  የህግደፍ ሎሊዎች ሜድያ እንደ ጀብዱ ያላደረገውን በመጨመር ያለሃፍረት ዘግቦታል፡ ፡

På Amharisk
16.10.2014 10:16
ተከታታይ ዘገባ
ኖርወይ ንግድ ምክርቤት ኮንፈደርሽን ጽ/ቤት ኦስሎ
የኖርወይ የንግድ ምክርቤቶች ኮንፈደረሽንና(NHO)የኖርወጂያን ኣፍሪካን የንግድ ቻምበር እንዲሁም የኖርወይ የግል ንግድ ሰክተር ልማት ኣማካሪ ጽ/ቤት(Veiledningskontoret)በጋራ ያዘጋጁት "በኢትዮጵያ ኢንቨስት ኣድርጉ" የተስኘው የዛሬው ኦክቶበር 16 2014 ሰሚናር በኦስሎ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡ ፡ በኢትዮጵያ የኖርወይ ኣምባሳደር ኣንድሪያስ ጎርደር ጨምሮ ኣዘጋጆች የእንኳን ደህና መጣችሁና የመግቢያ ንግግር ኣድርገዋል፡ ፡በፕሮግራሙ መሰረት በ 10:35 የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ተዎድሮስ ኣድሓኖም ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡ ፡ በኖርወይና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሚና ያላቸውና የኖርወይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመወከል የተገኙ 8 ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ብቻ በስብሰባው የመሳተፍ ዕድል ኣግኝተዋል፡ ፡ ሌሎች ተሳታፈዎች ከኖርወይ መንግስትና የንግድ ምክርቤቶች የመጡ ናቸው፡ ፡
እንደተለመደው የኣገሪቷ ልማት የማይዋጥላቸው ጥቂት የ ግንቦት 7 ጀሌዎች ስብሰባዉ ከሚካሄድበት ርቀዉ የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ነው፡ ፡
Les mer
12.10.2014 12:42
 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተጣለውን ማዕቀብ ኣፈጻጸም የሚከታተለው የኤርትራና የሶማሊያ ተቆጣጣሪ ቡድን(Monitoring Group)ለሶማሊያ መንግስት የተሰጠው የጦር መሳርያ ወደ ኣሸባሪው ቡድን ኣልሸባብ እንደሚደርስ ባቀረበው ሰፊ ሪፖርት ጠቀሰ፡ ፡
ማርች 2013 የጸጥታው ምክርቤት በሶማሊያ ከ 1992 በኋላ ተጥሎ የነበረውን የጦር መሳርያ ሽያጭ ማዕቀብ በከፊል እንዲነሳ ማድረጉ ይታወሳል፡ ፡ በወቅቱ ብዙ ኣገሮች ለ ሶማሊያ ኣዲሱ መንግስት የጦር መሳርያ መሸጥን በተመለከተ ስጋታቸውን ገልጸው የነበሩ ቢሆንም ኣሜሪካ የኢስልምና ኣክራሪ ሽብርተኛ ድርጅቱን ኣልሸባብ ለመታገል የጦር መሳርያ እንደሚያስፈልጋቸው በመከራከር ማዕከቡ በከፊል እንዲነሳ ተደርጓል፡ ፡
በቅርቡ የቁጥጥር ቡድኑ ባወጣው ሪፖርት ከሶማሊያ መንግስት ኣዲስ የጦር ሃይል መሳርያዎች ወደ ሽብርተኛው ቡድን እንደተላለፉ በማስረገጥ በምን ዓይነት መንገድ እንደሚተላለፍ ጭምር ሰንዷል፡ ፡ 
Les mer
11.10.2014 17:50
  በኣምባገነንኑ የሻዕብያ መንግስት ፋይናንሳዊ ድጋፍ የሚንቀሳቀስው የግንቦት 7 ኣሸባሪ ቡድን ኣባላት በኖርወይ ጸረ ኢትዮጵያ ያሰለፍዋቸውን ጥቂት ጋጠወጥ  ጀሌዎቻቸዉን በማስከተል ሁከት ሲፈጥሩ እንደቆዩ ይታወሳል፡ ፡  በኦክቶበር 16/2014 Invest in Ethiopia በሚል ርእስ በሚደረገው ሴሚናር የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክቶር ተዎድሮስ ኣድሓኖምን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደሚገኙ በመግለጽ ዕለቱን በድረገጾቻቸውና በ ማህበራዊ ገጾቻቸው "ታላቅ የዉርደት " ቀን በሚል ስይመው የሽብር ተግብራቸውን በዕለቱ እንደሚፈጽሙ ሲዝቱና ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል፡ ፡
 
የሃገራቸውን ሰላምና ልማት የሚመኘውን በኖርወይ የሚገኘው ሰላማዊ ኣብዝሃ ኢትይይጵያውያን ተእግስት  እንደ ፍርሃት በመቁጠር የኖርወይ ሕግ ጥሰው ከሻዕብያ በሚደረግላቸው ድጋፍ በኦስሎ ክተማ "የዉርደት ቀን" ብለው የጠሩትን ድራማ ለማሳየት ተዘጋጅተው ነበር፡ ፡ 

ይህን የሽብር ድርጊትና ሁከት ለመፈጸም ሊጠቀሙበት ያሰቡት የመጀመርያው መንገድ ኣገሪቱ ኢንቨስትመንት የሚያንገበግባቸው ኣገርወዳዶች መስለው በስብሰባው በመገኝት በኢትዮጵያውያን ባለስልጣናት ላይ ጥቃት ለማድረስ ነበር፡ ፡ምሽቱን እራሳቸው በድረገጻቸውና በፈይስ ቡክ ገጻቸው ላይ እንዳወጡት ማስታወቅያ የመጀመርያው ስልታቸው የተነቃበት ስለሆነ ሌላ ዘዴ ተጠቅመዉ በስብሰባው እንዲመዘገቡ ኣዲስ የ ኢ.ሜል ኣድራሻ ሰጥተዋል፡ ፡

Friday, October 10, 2014

‘አሸባሪ ብዕሮች’ ክንፉ አሰፋ

ይህች አጭር ጽሁፍ የተወሰደችው በአውስትራሊያ ከምትታተም “አሻራ” ከተሰኘች መጽሄት ልዩ እትም ላይ ነው።
የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር “ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።” ነበር ያለው።
አንባገነኖች ፕሬስን ይፈራሉ። ይጠላሉም። የህዝብ መሰረት የሌላቸው፤ በራሳቸው የማይተማመኑ ሁሉ ነጻ ሃሳብን ይጠላሉ። ነፍጥን ብቻ ተማምነው በሕዝብ ጫንቃ ላይ የሚቀመጡ፤ እንደምን ነጻ አመለካከትን ሊቀበሉ ይችላሉ? ፍጹም አንባገነናዊነት በሰፈነባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች፤ ህግ አውጭው ህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ የለም። ይህንን ቁጥጥር በጥቂቱም ቢሆን ተክቶ ይሰራ የነበረው ነጻው ፕሬስ ነው። ከዚህም አልፎ ሕዝቡ መብቱን እንዲያውቅና መብቱንም እንዲያስከብር ብዙ ሰርቷል-ፕሬሱ። ሙስናን አጋልጧል፣ እንደ እንባ ጠባቂም እየሆነ የህዝብን በደልም ይፋ አድርጓል። ይህን የተቀደሰ ተግባር ማከናወን እንደወንጀል፤ ጠንከር ሲል ደግሞ እንደ ሽብርተኝነት የሚቆጠርበት ሃገር ሆናለች የዛሬይቱ ኢትዮጵያ።
መብትን ማወቅ እና ማሳወቅ፤ ‘ህዝብ ለጦርነት እንዲነሳ ማድረግ፤ ወይንም በስራዓቱ ላይ ጥርጣሬ መፍጠር ነው’ ተብሎ ከተተረጎመ ደግሞ ጋዜጠኛን በአሸባሪነት መፈረጁ ብዙ ሊደንቀን አይገባም።
ኢትዮጵያ ላለፉት አስርት-አመታት ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ በቁጥር አንደኛ ደረጃ ላይ የነበረች ሃገር ናት። አሁን ይህንን ደረጃዋን ለቃለች። እድገትና ትራንስፎርሜሽኑን ተከትሎ ከመጡት ለውጦች አንደኛው መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ የአንደኝነት ደረጃዋን ያጣችው ታዲያ ትራንስፎርሜሽኑ ይዞት በመጣው መሻሻል አይደለም። ነጻ ፕሬሱ ከሃገሪቱ እንዲጠፋ በተደረገ ሁለገብ ጦርነት እንጂ። አብዛኛው ጋዜጠኛ ተሰድዷል፣ ጥቂቶቹ ታስረዋል፣ አንዳንዶቹም አቅማቸው ተሟጦ አልቆ፤ ዝም ብለው እንዲቀመጡ ተደርገዋል። ለነጋሪ የተረፉትንም እስከዛሬዋ እለት ድረስ እያሳደዷቸው ይገኛሉ።
ከጅምሩ በፕሬሱ ላይ የተከፈተው የገዥው ፓርቲ ውግያ ቀላል አልነበረም። ፕሬሱ ግን እለት ተዕለት የሚያርፍበትን የአንባገነኖች ጡጫ ሁሉ ችሎ ብዙ ተጉዟል። እየተንገዳገደ፤ እየወደቀና እየተነሳ የህዝቡን የህሊና ንቃት እንዲሰፋ ከማድረጉም ባሻገር በኢትዮጵያ የማንበብ ባህል እንዲዳብር ነጻው ፕሬስ ተግቶ ሰርቷል። የህትመት ዋጋ እስከ 500% እንዲጨምር ቢደረግም ፕሬሱ አልቆመም ነበር። ጋዜጠኞች እንደጥጃ እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣ እየተሰቃዩም ስራቸውን ላለማቋረጥ መትጋታቸውን አላቆሙም። በካድሬ ዳኞች ፍርደ-ገምድል ፍትህ ሲሰጣቸው፤ ያለ አግባብ በእስርና በገንዘብ ሲቀጡም ሰራቸውን አላቋረጡም…
የአሜሪካው ፍሪደም ሃውስ በተከታታይ ባወጣቸው ዘገባዎች ኢትዮጵያን ፕሬስ (Status: NOT FREE) “ነጻ ያልሆነች” ሃገር ሲል ፈርጇል። የፕሬስ አዋጁንም ፍጹም አፋኝ ሲል ይከሳል። የፈረንሳዩ ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ፣ የኒውዮርኩ ሲ.ፒ.ጄ. እና የብራስልሱ አይ.ኤፍ.ጄ. በሽብር ክስ የተያዙ የጋዜጠኖችን ሰነድ እያከታተሉ አሳፋሪነቱን ቢገልጹም አፍ እንጂ ጆሮ ከሌለው ስርዓት ያገኙት የስድብ ምላሽ ብቻ ነው። አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዋችም አፈናውን ይፋ ማድረጉን ተያይዘውታል። ከገዥው ፓርቲ የሚያገኙት ምላሽ “የኒዮ ሊበራል” አቀንቃኞች የሚል ስድብ እና ዛቻ ብቻ ነው።
ከምርጫ 97 ነኋላ ግን የህወሃት እድገት እና ትራንስፎርሜሽን፤ ጫን ያለ ነገር ይዞ ብቅ አለ።
ሽብርተኝነት!
ከዚህ በኋላ ጋዜጠኛ በህገ-መንግስት ሳይሆን፤ ህጉን በሚጻረረው አዋጅ መዳኘት እንዳለበት ተነገረ። ስርዓቱም በባሩድ ሳይሆን ይልቁንም በብእር ጫፍ እንደሚሸበር አረጋገጠ።
ይህ የሽብርተኝነት አዋጅ ቃል በቃል የተቀዳው ከአሜሪካ እና ከእንግሊዝ መንግስታት ሰነድ መሆኑን ሃይለማርያም ደሳለኝ ለቢቢሲ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ድንቅ ነው። ሰውየው ግን ምን እየተናገሩ እንደሆን የሚያውቁት አይመስልም። በዚህች በሙት መንፈስ የምትመራ ሃገር ሌላም ብዙ እንግዳ ነገር እንሰማለን። የቡሽ አስተዳደር ከቶኒ ብሌየር ጋር አልቃይዳ የተባለውን አደገኛ ሽብርተኛ ለማጥፋት የነደፉት ይህ ሰነድ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞችን ለማጥፋት እየተጠቀሙበት እንደሆነ ነው የሚነግሩን። የፈረንጆቹ ሽብርተኝነት (terrorism) ሲተረጎም፤ “በሃይማኖት ወይንም በርዕዮተአለም ጥላ ስር ተደራጅቶ አመጽን የማድረግ ተግባር” እንደሆነ ይነግረገናል።
በሽብርተኝነት ተወንጅለው በየእስር ቤቱ የተጣሉት የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ የትኛውን ርዕዮተ-አለም ወይንም ሃይማኖት ተንተርሰው አመጽ እንደፈጠሩ፣ የትኛውን አውሮፕላን እንዳስጠለፉ፣ የትኛውን ህንጻ እንዳፈረሱ፣ የትኛውን ንጹህ ዜጋ እንደገደሉ አልተነገረንም።
እርግጥ ነው። የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እየተቹ ይጽፋሉ። ትችቱ ታድያ ለውጡ ላይ አይደለም። የለውጡ አቅጣጫ ላይ እንጂ። አቅጣጫው ትክክለኛ መስመር መያዝ እና አለመያዙን መተቸት “ወንጀል ነው” ሲባል ለቀረው አለም አዲስ ነገር ሊሆን ይችላል። ከዚያ የባሰም አለ። ገዢውን ፓርቲ መተቸት እና ስለ ለውጥ አስፈላጊነት መጻፍ በሽብርተኛነት ያስከሰሰ ወንጀል ሆኖ ሰማን። አስቂኙ ነገር፤ አዋጁ ለኦሳማ ቢን ላደን ሽብር በምእራባውያን ሀገሮች የረቀቀ የጸረ-ሽብር ህግ መሆኑ ነው።
ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ሲፈረጁ ነው ነጻው ፕሬስ በኢትዮጵያ አፈር የለበሰው። ይህ የመጨረሻ ጥይታቸው መሆኑ ነው። አለማቀፍ የጋዜጠኞች ተሟጋች ተቋማት ሳይቀሩ ተስፋ የቆረጡ እስኪመስል ድረድ በዘንድሮ አመታዊ ዘገባቸው የኢትዮጵያን ጉዳይ ችላ ብለውታል። እነዚህ ተቋማት በየአመቱ ስለኢትዮጵያ ፕሬስ ሁኔታ የሚያወጧቸው ዘገባዎች የሚዘገንኑ ነበሩ። ወያኔን የማይማር፣ የደነዘዘ እና የማይለወጥ ስርዓት አድረገው ስላዩት ችላ ያሉት ይመስላል። ሃያ አመት የማይሰማ፣ ያሃ አመት የማይሻሻል፣ ሃያ አመት የማይማር ስርዓት… ውሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ሆነባቸው።
በምርጫ 97 ሰሞን በርካታ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች ቃሊቲ ተወርውረው ነበር። በጉዳዩ ላይ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዲያሬክተር ከነበሩት ዶ/ር ማርቲን ሂል ጋር ስናወራ አንድ ጥያቄ አነሱልኝ።
“ለመሆኑ ሰርካለም ፋሲል ላይ ለምን እንዲህ ጨከኑባት? ” የሚል ነበር የማርቲን ጥያቄ። እኝህ ታላቅ ሰው ይህን ጥያቄ ለምን እንዳነሱልኝ አሁን ነው የተገለጠልኝ።
የሰርካለም ፋሲልን ጉዳይ ማንሳቱ የኢትዮጵያን ፕሬስ የሰቆቃ ጉዞ በከፊልም ቢሆን ይገልጸዋል።
ሰርካለምን ከባለቤትዋ እስክንድር ነጋ ጋር አፍነው ወደ ቃሊቲ ሲወስዷት ነብሰ-ጡር ነበረች። የመውለጃዋ ቀን ሲደርስም ከእስር አልለቀቅዋትም። በምጥ ስቃይ፣ ነብስ ውጭ፤ነብስ ግቢ ሁኔታ ውስጥ ሆና እንኳን አሳሪዎችዋ ርህራሄ አላሳዩዋትም ነበር። በመጨረሻ እዚያው ቃሊቲ እስር ቤጥ ናፍቆትን ተገላገለች። በዚያ የጭንቅ ወቅት የሚይዘውን እና የሚጨብጠውን ያጣ ስርዓት ምን እያደረገ እንደነበር እንኳን በውል አየውቀውም። “የመንግስት ጠላት” የሚል ታፔላ ተለጥፎለት የሚንቀሳቀስ ጋዜጠኛ፤ ሊወድቅ ከሚንገዳገድ ስርዓት ከዚህም በላይ ሊደረግበት እንደሚችል ለማስረዳት ሞከርኩ።
ነብሰ-ጡርዋ ሰርካለም የተከሰሰችው ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ እና ለማፍረስ፣ ጥላቻን የምታስፋፋ፣ ጥርጣሬን የምትነዛ… ተብላ ነበር። በ “ምህረት” ከእስር እንደተፈታች ወደ ኬንያ ተሰደደች። በኋላም ሀገር ሰላም የሆነ ሲመስላት ከስደት ተመለሰች። ይህች ወጣት እትብትዋ ወደተቀበረባት ሃገርዋ ብትመለስም እንደዜጋ የመኖር ዋስትናዋ ግን በአንባገነኖች መዳፍ ስር ሆነ። በኑሮዋ እና በትዳርዋ ዙርያ ካለፈው የባሰ ችግር መጣባት። ባለቤትዋ እስክንድር ነጋ በሽብርተኝነት ተከሶ በፍርደ-ገምድል ዳኛ ለአመታት ተፈረደበት። ቤት ንብረታቸውም በግፍ ተቀማ። ከዚህ በኋላ በመኖር እና ባለመኖር የሚደረግ ምርጫ ውስጥ መግባት ግድ ሆነባት። እናም ባለቤትዋን ወህኒ ቤት ጥላ ዳግም ተሰደደች። እስዋም ሆነች በሰቆቃ የተወለደ ልጅዋ በመንገድ ከመወርወራቸው በፊት ያላቸው አማራጭ ይህ ብቻ ነበር። የሚወዷት ሃገራቸውን ጥለው ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ስደተኛ ጋዜጠኞችን ተቀላቀሉ። እንደቀልድ የሚነገር ሌላም እውነታ አለ። ከ”ሽብርተኛ” ጋር በስልክም ሆነ በአካል ያወራ፣ አብሮ የታየ፣ አብሮ ሻይ የጠጣ፣ የተነካካ ሰው ሁሉ ሽብርተኛ እንደሆነ አዋጁ ይደነግጋል። ሰርካለም እና ናፍቆት በእስር ያለው እስክንድር ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት ሽብርተኛ ተብለው ሊወነጀሉም ይችሉ ነበር።
በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ፍርሃት ውስጥ እንዳሉ ግልጽ ነው። በጋዜጠኛ የሚናድ ሀገ-መንግስት ይዘው ስንት አመት ሊዘልቁ እንደሚችሉ ባናውቅም፤ አሁንም ጋዜጠኞችን ሲያስሩ ይህንንኑ ዘፈን ይደጋግሙታል። 99.7 በመቶ በህዝብ የተመረጠ መንግስት መራጩን ሕዝብ ከቶውንም መፍራት አልነበረበትም። ነገሩ ስላቅ ነው። ይህ ቀልዳቸው ግን የህዝቡን ንቃተ-ህሊና ዝቅ አድርጎ ከመመልከት የሚመጣ ይሁን እንጂ ጉዳዪ ሌላ ነው። አንባገነኑ ናፖሊዮን ቦናፓርት ብሎታል። ከሺ ሳንጃ አንድ ጋዜጠኛ ያስፈራል። የጭቆና እና የአፈና ስርዓት ገንብቶ ለረጅም አመት የቆየ አንባገነን በታሪክ አልታየም።
የፈቀደውን መምረጥ የሚችልን ህዝብ አዲስ ዘመንን ብቻ እንዲያነብ መምከራቸው ብቻ አይደለም በሕዝብ ላይ ያላቸው ንቀት፤ የፍትህ ስርዓቱን ለበቀል የሚዘረጋ እጃቸው አድርገው ነጻውን ፕሬስ ለማጥፋት ሲጠቀሙበትም እጅግ ያንገበግባል። የህግ የበላይነትን እንዲህ እያደረጉ ናዱት።
ኢሕአዴግ የፕሬስ ነጻነትን ለህዝቡ እንዳጎናጸፈ ይመጻደቃል። ይህ ስህተት ነው። መናገር፣ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ፣ መጻፍ፣ … ወዘተ መብት የሰው ልጅ የተፈጥሮ ጸጋ እንጂ አንድ ስርዓት የሚያጎናጽፈን ጉዳይ አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ይሀው ስርዓት እነዚሁኑ መብቶች እየጨፈለቀ እነሆ ሃያ ሶስት አመታትን ዘልቋል።
ነጻ ፕሬሱን ለምእራባውያን የዲሞክራሲ ማሳያ አድርጎ እንደተጠቀመበት እርግጥ ነው። የአለም ባንክ እና ለጋሽ ሃገሮች በኢትዮጵያ የሳንሱር አዋጅ እንደጠፋ ነው የሚነገራቸው። የእርዳታና ብድር እጃቸውን የሚዘረጉልንም ከቀድሞው የተሻለ የመጻፍና የመናገር ነጻነት አለ ብለው ስለሚያምኑ ይመስላል። ግና ይህ የሳንሱር አዋጅ በአእምሮ ሳንሱር መተካቱን የምናውቀው እኛ ብቻ ነን። ሳንሱር ቢኖር ይህ ሁሉ ጋዜጠኛ ባልታሰረ፣ ባልተንከራተተ እና ባልተሰደደ ነበር።
ምርጫ መጣ! ጋዜጠኛ ይውጣ! እንዲሉ… በቅርቡ በስድስት ነጻ ፕሬስ ህትመቶች ላይ ከተመሰረተው ክስ ጋር በተያያዘ አስራ ሁለት ጋዜጠኞች ለስደት መብቃታቸው ተዘግቧል። በጭላንጭል የነጻነት ድባብ ይንቀሳቀሱ የነበሩት፤ አዲስ ጉዳይ፣ ሎሚ፣ ጃኖ፣ አፍሮ ታይምስ እና እንቁ ጋዜጦች እንዲቋረጡ ተደርጓል። ጋዜጠኞቹም በአሸባሪነት ሽፋን ተከስሰው እስከ አስራ ስድስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተበይኖባቸው የነእስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርእዮት አለሙ እጣ ይደርሳቸዋል። እነዚህ ጋዜጠኞች የነበራቸው አማራጭ የሽብር አዋጁ ሰለባ መሆን አልያም አገር ለቀው መሰደድ ነው። ተሰደዱ። የስደተኛ ጋዜጠኛውን ቁጥር ወደ 210 አሳደጉት።
ውንጀላው ግን በተያዘለት መርሃ-ግብር ቀጥሏል። ሰሞኑን “ያልተገሩ ብዕሮች” በሚል ርእስ በኢቲቪ የቀረበውን “ዘጋቢ ፊልም” ያስተውሏል? በአንድ በኩል የጋዜጠኖቹ ጉዳይ በህግ የተያዘ እንደሆነ ይነግሩናል። በሌላ በኩል ደግሞ “ልማታዊ” ተዋንያን እና የስርዓቱ አጎብዳጆችን በመገናኛ ብዙሃን አቅርበው ፍርድ እንዲሰጡ ያደርጓቸዋል። በእርግጥ በመገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ አንድ ተጠርጣሪን በወንጀለኝነት መፈረጅ አዲስ ነገር አይደለም። የፍትህ አካሉ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ተጠርጣሪው በኢቲቪ የፖለቲካ ፍርድ ይበየንበታል። ከዚያም እንደ “ዳኛ” ልዑል አይነት የሲቪል ሰርቪስ ምርቶች ውሳኔውን ያጸኑታል።
በዚያ የኢቲቪ ቅንብር ሃይሌ ገብረስላሴም ተዋንያን ነበር። የሚናገረውም የትዬለሌ። “ትልቁ የጦር መሳርያቸው ፕሬስ ነው።… ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይባላል… ” ይለናል ሃይሌ ገብረስላሴ። “ዘጋቢ” ፊልሙም የእነ እስክንድር ነጋን ፎቶ፣ የእነ ተመስገን ጽሁፎች ያሳየናል። የዚህ ድራማ ሌሎቹ ተዋንያን ከሙያው ጋር የተያያዝን ነን የሚሉ አድርባዮች ናቸው። ሃይሌ ግን ምን ቤት እንደሆነ ግልጽ አይደለም። በየትኛውስ እውቀቱ ነው ፍርድ ሊሰጥ የደፈረው? “አንድ ጋዜጣ የውሃ አምራች ድርጅትን እንዲዘጋ አድርጓል።” ሲል ሃይሌ በዚያ “ዘጋቢ ፊልም” ይወነጅላል። አንድ ጋዜጠኛ እውነትን ጽፎ የንግድ ድርጅትን ወይንም የመንግስት ተቋምን ማፍረስ ወይንም በተቋማቱ ላይ ጥርጣሬ መፍጠር ከቻለ እንዲያውም ጀግና ነው የሚባለው። ጋዜጠናው የሚጽፈው ውሸት ከሆነ ደግሞ ፍርዱን ለህዝቡ ለምን አይተውለትም?
አብራሃ ደስታ ሌላው በአሸባሪነት ሽፋን የተከሰሰ ጋዜጠኛ ነው። አብርሃ አሸባሪ መሆኑ የተረጋገጠው ፍርድ ቤት ሲገባ እና ሲወጣ ነው። ሲገባ በጭብጨባ ሲወጣ በጭብጨባ ተሸኝቷል። ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ኣብርሃ ጀግና! የነፃነት ታጋይ! እንወዳሃለን፤እናከብርሃለን ሲለው እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ የት ነበሩ?
ያልተገራ አንደበታቸውን በመገናኛ ብዙሃን ሲከፍቱ የነበሩት እነዚህ ተዋንያን የሚነግሩን እጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። አጠቃላይ ይዘቱ በመንግስት ላይ ምንም አይነት ትችት መቅረብ የለበትም የሚል እንድምታ አለው። የህወሃትን አንባገነናዊነት መተቸት፣ የስርዓቱ ፖሊሲዎች መንካትና በባለስልጣናቱ ላይ ጥርጣሪ እንዲኖር ማድረግ… ስርዓቱን ያፈርሰዋል ነው እያሉን ያለው። ህግ አውጭው ከህግ አስፈጻሚውን፣ ህግ አስፈጻሚው ደግሞ ህግ ተርጓሚውን እርስ-በርስ የሚቆጣጠሩበት እና የሚያስተከክሉበት አካሄድ በሌለበት ሃገር ነጻው ፕሬስ ከዚህ ውጭ ምን ይስራ ነው የሚሉት? ፕሮፓጋንዳ?
ለፕሮፓጋንዳውማ በርካታ አማራጮሽ አሉ። አዲስ ዘመን ጋዜጣም አለልን። ለ90 ሚሊዮን ህዝብ የቀረው ጋዜጣ። አዲስ ዘመን በቁጥር ስንት ሺ እንደሚታተም ባናናውቅም በኪሎ እየተሸጠ የሸቀጥ እቃ መጠቅለያ ሆነ እንጂ። ‘የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተመረቁ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሱዳን ሄዱ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከሱዳን ተመለሱ። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ 11 እጅ እንደሚያድግ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።’ …. የሚሉ ዘገባዎችን እየያዘ ከሸቀጥ እቃ መጠቅለያነት ውጭ ለሚመጻደቁለት እድገት ምንም እንዳልፈየደ እንኳ አያውቁትም።
የመገናኛ ብዙሃን አፈናው በነጻ ፕሬሱ ላይ ብቻ አልተገደበም። በኢትዮጵያ የመረጃ መረቦችም ታፍነዋል። ከሰብ ሰሃራ አፍሪካ በኢንተርኔት ይዞታ እና አገልግሎት የመጨረሻዋ ሃገር ናት። ኢንተርኔቱን የሚቆጣጠረው መንግስታዊው ቴሌኮም ስርዓቱን የሚተቹ ድረ-ገጾችን በቻይና ቴክኖሎጂ እንዲዘጉ አድርጓል። የዜጎችን ስልክ በህገወጥ ማንገድ መጥለፍ የተለመደ ተግባር ነው። እንዲሁም ስካይፕ እና ቫይበር ያሉ የቮይስ ኦቨር ስልኮች ደግሞ ፊን ፊሸር በተባለ የኮምፒዩተር ቫይረስ አማካኝነት ይጠለፋሉ። እንዲህ እያሉ በዜጎች የግል ህይወት ሳይቀር እየገቡ ቴሌን ሙሉ በሙሉ የስለላ ተቋም እንዳደረጉት የአሜሪካው ሂዩማን ራይትስ ዋች ይፋ አድርጓል።
ኢትዮጵያን ወደ ጨለማ ዘመን እየወሰዳት ያለው ይህ የህወሃት ስርዓት የኢንተርኔት ተጠቃሚው እንዲያሽቆለቁል እየጣረ እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት። በተለይ የፌስቡክ አብዮትን ለመግታት ስለሚሻ የኢንተርኔት አገልግሎትን ማዳከሙ ላይ ጥብቅ አቋም ይዟል። መንግስት አልባዋ ሶማልያ እንኳን፣ ስድስት የቴሌፎንና ስልክ አቅራቢ ኩባንያዎች አሏት። በዚህ ቀላል ቴክኖሎጂ እንኳን ከሶማልያ በታች ሆኖ ስለ እድገት መመጻደቃቸው ሊያፍሩበት ይገባል።
እጅግ የሚያሳዝነው ይህ ስርዓት ለፈጸመው ለዚህ ሁሉ በደል ለሽልማት መብቃቱ ነው። ልማታዊው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ በአርቲስቶች ስም ለሟቹ ጠቅላይ ሚ/ር የወርቅ ብዕር ነበር ያበረከተላቸው። ብዕር ትልቅ ትርጉም አለው። ብእር የሚሸለም ሰው ለፕሬስ ክብር ያለው፤ ፕሬስን የሚያከብር ሰው ነው። ሰራዊት የወርቅ ብዕር እንዲሸልም አርቲስቶች አልወከሉትም ነበር። ይህንን ሲያደርግ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እስር ቤት ውስጥ ይንገላቱ ነበር። ሰራዊት ይህንን ሲያደርግ የአለም አቀፍ ህብረተሰብ ጠ/ሚኒስትሩን የፕሬስ አፈና በእጅጉ ያወግዝ ነበር። እንደ ሰራዊት ያሉ ሃላፊነት የጎደላቸው ሰዎች ብዙ አይደሉም። ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ሲሉ እንዲህ አይነት ስራ እየሰሩ በሰው በቁስል ላይ እንጨት ይሰድዳሉ። ታዲያ እንደነዚህ አይነቶቹ አድርባዮችም ለፕሬሱ መጥፋት ሚናቸው ቀላል አይደለም። የማያልፍ የለም። ሁሉም ያልፋል። መንግስትም እንደ አንሶላ ተጠቅልሎ ይሄዳል። ይህ ቀን አልፎም ለትዝብት ያበቃናል።
ማን ነበር “ፕሬስ የሌለው መንግስት ከሚኖረን መንግስት የሌለው ፕሬስ ቢኖረን እንመርጣለን።” ያለው? እርግጥ ነው። ያለ ፕሬስ የሚኖር ህዝብ በጨለማ ነው የሚጓዘው። ያለ ነጻ አስተሳሰብ እና ያለ ነጻ ፕሬስ፣ እድገት ይመጣል ማለት አይታሰብም። እንዲያው የህዝብን ንቃተ-ህሊና ዝቅ አድርጎ መመልከት ይሆናል እንጂ።
ምንጭ የኢትዮጵያ ሜዲያ መድረክ
ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ /“INVEST IN ETHIOPIA”/ በሚል ርእስ በኦክቶበር 16/2014 ኦስሎ ላይ ሴሚናር ይካሀዳል፥፥ ዝግጅቱቱን ያዘጋጀው Norwegian-African Business Association /NABA/ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የአምባገነኑ የወያኔው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረየስ፥ እንዲሁም የኖርዌይ አምባሳደር በኢትዮጵያ ሚ/ር አንድሪያስ ጋርደር እና አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ የተለያዩ የኖርዌጂያን የንግድ ድርጅቶች ጋር ተገናኝተው ለመወያየትና ፓሮግራም ተይዟል፥፥
ዝግጅቱ የሚደረገው በሃሙስ ኦክቶበር 16/2014 ከ 09:00-11:30 ሲሆን ከ11፥30—12፥30 የምሳ ፕሮግራም ይኖራቸዋል፥ በመሆኑም ውድ ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ በሙሉ እንድታውቁትና በንቃትእንድትከታተሉ እናሳስባለን፥፥
አድራሻው Confederation of Norwegian Enterprise (NHO) ማለትም Næringslivets Hus
Middelthuns gate 27
Majorstuen, Oslo ሲሆን ተጨማሪ መረጃ በቅርብ ቀን
ለበለጠ መረጃ፥ http://norwegianafrican.no/news/16th-of-october-invest-in-ethiopia-seminar-in-oslo
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
come and tell to Teedros adhanom as he can not represent ethiopians......
16th of October: “Invest in Ethiopia” seminar in Oslo
Norwegian companies are welcome to meet Ethiopia’s Foreign Minister Dr. Tedros Adhanom Gebreyesus when NABA welcome you to an “Invest in Ethiopia” seminar at the Confederation of Norwegian Enterprise (NHO) on Thursday 16th of October from 09:00 – 11:30. (with lunch from 11:30 – 12:30)
In this seminar you can also meet Norwegian companies already present in
16th of October: “Invest in Ethiopia” seminar in Oslo
Ethiopia. Norwegian Ambassador to Ethiopia H.E. Andreas Gaarder and Ethiopia’s Ambassador accredited to Norway, H.E. Woinshet Tadesse will also be present and available to meet companies during the seminar