Saturday, September 27, 2014

የወያኔ/ኢህአዴግ ጨቋኝ ሥርዓት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ቁጥር ስፍር የሌላቸው አፋኝ ህጎችን በመጫን፤ እንዳሻው ንጹሃን ዜጎችን መጥፎ ስም በመስጠት፤ ባልሰሩት ሃጥያትና በተፈበረከ የሃሰት ወያኔያዊ ውንጀላ በየእስር ቤቱ እንዲማቅቁ እያደረገ መሆኑ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ግልጽ ነው። ይህ አፋኝ ሥርዓት የምንወዳት ሃገራችን ኢትዮጵያንና ህዝቧን የማጥፋት እኩይ አላማ ሰንቆ፤ ምሁራን ዜጎች ለሚወዷት ሃገራቸውና ለሚሳሱለት ህዝባቸው የበኩላቸውን ማበርከት እንዳይችሉ እያደረገ ይገኛል። ይህ አስከፊ ሥርዓት በአመት ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ህፃናት በማደጎነት፤ ከ45 ሺህ በላይ ሴቶቻችን ለሳውዲ አረቢያ፤ እንዲሁም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዜጎቻችን ለሌሎች አረብ ሃገራት በሃራጭ በመሸጥ ላይ ይገኛል። ከዚህም በከፋ መልኩና በሚያሳፍር ሁኔታ፤ ሴቶች እህቶቻችን በየአረብ ሃገሩ ለመስማት እጅግ በሚያዳግት ሁኔታ አሰቃቂ በደሎች ባደባባይ ሲፈፀምባቸው በተደጋጋሚ እየታዩ፤ ቢያንስ ተቃውሞውን ሊያሰማ ፈፅሞ ፍላጎት እንደሌለውና፤ ይባስ ብሎ በደሉን በተቃወሙ ዜጎች ላይ ከበዳዮቹ ሃገራት ጋር በማበር ንፁሃን ዜጎችን የሚደበድብ፣ የሚያስርና፣ ከፍተኛ እንግልትን የሚያደርስ አስነዋሪና ጭካኝ ስርዓት መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቶናል።

ሁላችንም እንደምናቀው የኬኒያ፣ የሱዳን፣ የጅቡቲና፣ ሌሎች የጎረቤት ሃገራት በወያኔ በደል ምክንያት ሳይወዱ ተገደው ህይወታቸውን ለማዳን ከሃገራቸው በተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ላይ በተደጋጋሚ አፈና እየፈፀሙ ይገኛሉ። በቅርቡ በኬኒያ መንግስት ታፍኖ ለወያኔ ከተሰጠ በኋላ ህይወቱ እስክታልፍ ድረስ ለአመታት በወያኔ እስር ቤት በተሰቃየው በወንድማችን ወጣት ተስፋሁን ጨመዳ ላይ የተፈፀመውን አሳዛኝ በደልና በኦብነግ አመራር አባላት ላይ የተደረገው አፈና፤ በደቡብ ሱዳን በአቶ ኦኬሎ አኩአይና ሌሎች የጋምቤላ ንቅናቄ አባላት ላይ በተመሳሳይ መልኩ የተደረገው አፈና ያለምንም ተጨባጭ እርምጃ በዝምታ ታልፈዋል። ዛሬ ደግሞ የየመን መንግስት በአሳዛኝ ሁኔታ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በማገት ለወያኔ/ኢህአዴግ ሰውበላ ሥርዓት አሳልፎ ሰጥቶታል። በዜጎቻችን ላይ እየደረሱ ለሚገኙት አሰቃቂ በደሎች በዋነኝነት ተጠያቂው የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ቢሆንም፤ በስደት የሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ ከወያኔ መንግስት ጋር በመተባበር በተደጋጋሚ አፈና እየፈፀሙና አጋልጠው እየሰጡ የሚገኙ የጎረቤት ሃገራት ወደፊት በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ተጠያቂ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለንም። ነገር ግን ይህ አፈና እስከመቼ ይቀጥላል!? ዜጎች ጭቆናን በመቃወማቸው ብቻ በስደት ከሚደርስባቸው ስቃይ በላይ ለምን በየጎረቤት ሃገሩ ይታፈናሉ!? እኛ ኢትዮጵያውያን እስከመቼ እየተናቅን እንኖራለን!?

Friday, September 26, 2014

ስልጠና የሚያስፈልገው ላልሰለጠነው የወያኔ ጉጅሌና ሎሌዎቹ ነው!


አምባገነኖች በውድም በግድም ህዝብ ስብሰባ ጠርተው ህዝቡ ፊት በቆሙ ቁጥር ሌት ከቀን የሚያባንናቸውን የተመረረ ህዝብ የነጻነት አመጽ የሚያስቀሩ ይመስላቸዋል። የህዝብ ሃብትና ጊዜ በከንቱ እንዳሻቸው እያባከኑ፣ ነጋ ጠባ ስብሰባ፣ ግምገማ፣ “ስልጠና” ወዘተ የሚጠሩት ህዝብ የነሱን ፍላጎትና ውሳኔ የኔ ነው ብሎ የሚቀበላቸው፣ የሚሰማቸው እና ፍርሃታቸውን ያቀለላቸው እየመሰላቸው ነው።
የወያኔ ጉጅሌና ሎሌዎቹ ሰሞኑን ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ ሰራተኞችንና መላውን ለፍቶ አዳሪ ተሰብሰብና እናሰልጥንህ የሚሉት በአገዛዛቸው የተንገፈገፈው ህዝብ ምሬቱ ወደ አመጽ እንዳይገነፍል ያደረጉ እየመሰላቸው ነው። ዲሞክራሲንና የህዝብ ወሳኝነትና ልእልናን በተቀበሉ ሀገሮች እንደወያኔና ቀደም ብሎ እንደነበረው የደርግ ስርአት የመንግስት ስብሰባ የማይዘወተረው ለዚህ ነው። የህዝቡን ፍርድ በስብሰባ እና በስልጠና እንደማያቆሙት ስለሚያውቁ ህዝብን ስለሚያከብሩ ነው።
ሰሞኑን በመላ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ወያኔዎች ‘ስልጠና’ ብለው የሚጠሩት፣ በይዘቱ አያቶቻችንን ድሮ ላውጫጪኝ ይጠቀሙበት የነበረውን አፈርሳታ የመሰለ የመደናቆሪያ ስብሰባ አላማው ግልጽ ነው።
አላማው ህዝብ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ ቢቻል ለማደንዘዝ ካልተቻለም ለማስፈራራት ነው። ግፍን፣ ፍትህ ጥፋትን ልማት፣ ጭካኔን፣ ርህራሄ ለማስመሰል አፈጮሌ ነኝ ያለ ካድሬ ሁሉ የምላስ ጂምናስቲክ የሚሰራበት ጉባኤ ነው። ከተሰብሳቢው ህዝብ ከረር ያለ ጥያቄ በመጣ ቁጥር መላ ቅጡ የሚጠፋቸውም ለዚህ ነው። እነሱ የተዘጋጁት የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ አይደለማ! የህዝቡን ጥያቄ እንደማይመልሱማ ያውቁታል።
ነገሩ መልከ ጥፉን በስም ይደገፉ ሆነና ይህንን ቧልት ‘ስልጠና’ ብለው ይጠሩታል። እነዚህ ራሳቸው መሰረታዊ ስልጣኔ የሌላቸው አሰልጣኞች መምህራኑን ስለትምህርት ጉዳይ ሊያሰለጥኗቸው ሲንጠራሩ አይፍሩም። ባለሙያውን ሁሉ በሙያው ካላ ሰለጠንህ ብለው ግዳጅ ስብሰባ ያጉሩታል። ይህ የወያኔ ተግባር እውቀትና ስልጣን ከተምታታባቸው የወያኔ ጉጅሌዎች ስለመጣ ብዙ ላያስገርም ይችል ይሆናል። እንደ ህዝብና እንደ ዜግነታችን ግን በያንዳንዳችን ላይ እየደረሰ ያለ ውርደት ነው። ወያኔ ካላዋረደንና ሰበአዊ ክብራችን ካላሳነሰ የሚገዛን አልመሰለውም።
ግንቦት 7 ውስጥ ያለን የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆች ይህ ዘርፈ ብዙ ውርደት እንዲቆም ነው የምንታገለው። የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ ዘመን ይህን በመሰለ ውርደት ውስጥ ሊኖር የሚገባው ህዝብ አይደለም ብለን እናምናለን። የማያቋርጠው ጥሪያችን ዛሬም ተመሳሳይ ነው። ፈልገናቸው ሳይሆን በሃይል ራሳቸውን የጫኑብንን የወያኔ ጉጅሌዎች ከጫንቃችን ላይ እናራግፋቸው።
በአንድነት እንነሳ! በያለንበት ለዚህ ውርደት እምቢ እንበል። ውርደታችን እምቢ ያልን ቀን ይቆማል። ያን እለት ጨለማው ይገፈፋል። የነጻነታችንና የክብራችን ጎህ ይቀዳል።
በያለንበት እምቢ እንበል! ስለተገፋንና ስለተዋረድን ማመፅ መብታችን ነው። የቻልክ ተቀላቀለን። ያልተመቸህ በያለህበት በራስህ አነሳሽነት ራስህን አደራጅ። የነጻነታችን ቀን ቅርብ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Wednesday, September 24, 2014

ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ

ሰነዱ አሜሪካንን ጨምሮ ለኃያላን አገሮች ቀርቧል
puntland somaliland
ራሳቸውን ራስ ገዝ አገር አድርገው በማስተዳደር ላይ ያሉት ሶማሌላንድና ፑንትላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ውህደት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ማቅረባቸው ተሰማ። ሰነዱ ለእንግሊዝና ለሌሎች የአውሮፓ ሃያል አገራት መቅረቡም ታውቋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች “እንሰጋለን” ሲሉ የውህደት ጥያቄው ሊተገበር የሚገባው እንዳልሆነ አመልክተዋል
ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ጥያቄ ያቀረቡት ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች የተጠቀሰውን ሰነድ ማቅረባቸውን የተናገሩት የጎልጉልምንጮች፣ የሰነዱን ዝርዝርና ውህደቱ በምን መልኩ ሊከናወን እንደሚችል ዝርዝር መረጃ ለጊዜው ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ራሳቸውን ከተበጠበጠችው እናት አገራቸው ነጥለው አገር ማስተዳደር ከጀመሩ ዓመታት ቢያስቆጥሩም እስካሁን ድረስ በአገርነት እውቅና አላገኙም። በዚህ መነሻ ይሁን በሌላ፣ ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች ኢትዮጵያን እናት አገራቸው ሆና እንድታስተዳድራቸው ሰነድ አዘጋጅተው ከማቅረባቸው በፊት ከኢህአዴግ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ሲመክሩ ቆይተዋል።
“ባለራዕዩና ወደር የሌለው የኢትዮጵያ ልጅ” እየተባሉ የሚጠሩት ሟቹ ጠ/ሚ/ር በህይወት እያሉ የተጀመረው ይህ የውህደት ጥያቄ ተግባራዊ ሊሆን ስለሚችልበት፣ ስለሚያስገኘው ጥቅምና ጉዳት አስተያየት እንዲሰጡ የተጠየቁ ዲፕሎማት “እኔም ሆንኩ ሌሎች ስጋት አለን” ይላሉ። ሲያስረዱም “ወደብ እናገኛለን። ቆዳችን ይሰፋል። ነገር ግን ችግሩ ደግሞ ከዚህ ሁሉ የከፋ ነው” ብለዋል።
mapችግሮቹን መዘርዘር ምን አልባትም በአገር ቤት የተለያዩ የእምነት ተቋማትና ምዕመናን ዘንድ ቅሬታ ሊያስነሳ እንደሚችል ያመለከቱት ዲፕሎማት ኢህአዴግ እጁን ሰብስቦ ሊቀመጥ እንደሚገባ መክረዋል። በሶማሊያ አካባቢ ካለው የአክራሪ ሃይላት መስፋፋት ጋር በተያያዘ ለደህንነት ሲባል ሃያላን አገሮች ጥያቄውን ሊደግፉት እንደሚችሉ ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ “ውህደቱ በግፊትና በድጎማ ስም ተግባራዊ ይሁን እንኳን ቢባል ቅድሚያ የኢትዮጵያ ህዝብ በይፋ ደምጽ ሊሰጥበት ይገባል፣ ከፍተኛ የእምነት ቁጥር አለመመጣጠን ያስከትላል” የሚል ጥቅል ሃሳብ ሰንዝረዋል።
ኢህአዴግ በቀድሞ መሪው አማካይነት የሶማሌ ወደቦችን አማራጭ አድርጎ የመጠቀም ስትራቴጂ እንዳለው በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር። ለዚሁ ተግባራዊነት መጨረሻው በይፋ ባይታወቅም በኢትዮጵያ ወጪ ወደቡ ድረስ ዘልቆ የሚገባ የመኪና መንገድ ግንባታ ተጀምሮ አንደነበር የሚታወስ ነው። በተለይ የፑንትላንድ ፓርላማ ሰዎች በተደጋጋሚ አዲስ አበባ ይመላለሱ አንደነበርም አይዘነጋም።
የህወሃት ሰዎች የወደብ ጉዳይ ካሳሰባቸው የኢትዮጵያ ንብረት የሆነውን የአሰብን የባህር በር ወደ ቀድሞው መንበሩ የመመለስ ስራ አጠንክረው መስራት የሚያስችላቸው ሰፊ የህግና የመብት አግባብ ስለመኖሩ የተናገሩት ዲፕሎማት “ሶማሌ አሁን ችግር ውስጥ ብትሆንም ህጋዊ ክልሎቿን ለመጠቅለል መስማማት የአንድን አገር ሉአላዊነት የመዳፈር ያህል በመሆኑ ጊዜ ጠብቆ ዋጋ ያስከፍላል። የህግ ድጋፍም የለውም፤ በፌዴሬሽን ለመቀላቀልም ቢሆን የሚያስችል አግባብ የለም” ብለዋል
በቅርቡ ለመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት “ፓርላማው” ሳያውቅ ከኢትዮጵያ ተቆርጦ የተሰጠውን መሬት አስመልክቶ ለተፈጠረው ቅሬታ መልስ የሰጡት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ “ከጅቡቲ ጋር የሚፈጸመው ውህደት አንዱ አካል ነው” በማለት የመሬቱን አላግባብ መሰጠት ማስተባበላቸው የሚታወስ ነው። ሪፖርተር ቃል አቀባዩን ጠቅሶ በወቅቱ እንደጠቆመው ኢህአዴግ ለጅቡቲ ያቀረበው የመሬት ግብር /ስጦታ/ በሂደት “ለመጠቃለል” የሚያስችል ውለታ ተደርጎ የሚቆጠር መሆኑን ነው። ኢትዮጵያ በራሷ ወጪ በጅቡቲ ወደብ ላይ የወደብ ኮሪዶር ለመስራት ከስምምነት መድረሷንም አስቀድሞ በቃል አቀባዩ አማካይነት መገለጹ አይዘነጋም። ይህንን የሚያስታውሱ የቀደመው ወደብ የመገንባት ውል እያለ ባቋራጭ “የውህደት ሃሳብ እንዴት ተሰነቀረ?” ሲሉ ይጠይቃሉ።
በተመሳሳይ ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ፍላጎት ቢኖራቸውም በተግባር ሊውል የማይችል ቅዠት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች አመልክተዋል። ሁለቱ ክፍለ ሃገሮች የኢትዮጵያ አካል ከሆኑ በኋላ በአንቀጽ 39 ንዑስ ቁጥር 1 መሠረት “የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን እስከ መገንጠል ድረስ ያለው ያልተገደበ መብት” መሰረት በማድረግ ዳግም የመገንጠል ጥያቄ በማቅረብ ኢህአዴግ አስቀድሞ እውቅና እንዲሰጣቸውና አንደ ኤርትራ ውለታ እንዲሰራላቸው ተመኝተው ሊሆን አንደሚችል የሸረደዱም አሉ።

በጎደሬ ወረዳ የዘር ግጭት ተነሳ፤ መከላከያ ገብቷል

የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች ከነቤተሰቦቻቸው ተገደሉ
gode-rie
በጋምቤላ ዞን በጎደሬ ወረዳ ነጋዴዎችና ሰፋሪዎች ከአካባቢው ተወላጅ የመዠንገር ጎሳ አባላት ጋር ተጋጩ። በግጭቱ ከ17 ሰባት በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በግጭቱ የመዠንገር ዞን አስተዳዳሪና የጎደሬ ወረዳ ዳኛ ከነቤተሰቦቻቸው የግጭቱ ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። ግጭቱን ለማብረድ የመከላከያ ሠራዊት የገባ ሲሆን፣ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል ግጭቱን ለማብረድ በጉዞ ላይ እንዳለ በተሰጠ መመሪያ እንዲመለስ ተደርጓል
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለጎልጉል እንደገለጹት በወረዳው በመሬት ባለቤትነትና በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ከመሀል አገር በመጡ ሰፋሪዎችና ነጋዴዎች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ዓመታትን አስቆጥሯል። የፌዴራል አገዛዙም ሆነ የክልሉ አመራሮች ችግሩ ሳይሰፋ ሰላማዊ መፍትሄ ባለማፈላለጋቸው ችግሩ ሊካረር ችሏል። ኢህአዴግ የሚከተለው በዘር ከፋፍሎ የመግዛት ፖሊሲ ለችግሩ መባባስ በዋንኛነት ተጠቃሽ ነው።
ባለፈው ሃሙስ በአንድ የመሃል አገር ሰፋሪና የአካባቢው ተወላጅ በሆነ አርሶ አደር መካከል ድንገተኛ ጸብ ተነስቶ ነበር። በጸቡ የመዠንግር ጎሳ አባል የሆነው አርሶ አደር ህይወት አለፈ። በጎሳ አባላቸው መገደል የተበሳጩ ዘመዶች ውሎ ሳያድር በወሰዱት የበቀል ርምጃ አንድ ሰፋሪ የመሃል አገር ሰው ህይወት አለፈ። እንደ ዜናው አቀባዮች ከሆነ በዚሁ በመሬት ጉዳይ በተከሰተው የሁለት ግለሰቦች ህልፈት ተከትሎ ችግሩ ተካረረ።
በተመሳሳይ ቀን ማምሻው ላይ ከመሃል አገር የመጡት ሰፋሪዎች የዞኑን አስተዳዳሪ፣ ባለቤታቸውንና ሁለት ልጆቻቸውን መኖሪያ ቤታቸው በመሄድ በስለት ገደሉ። በተመሳሳይ አንድ የጎደሬ ወረዳ አስተዳዳሪ ከባለቤታቸውና ከልጃቸው ጋር ተገደሉ። በደቦ የተጀመረው የስለት ግድያ እየሰፋ የሟቾችን ቁጥር 17 እንዳደረሰውና በስለት የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ከ40 በላይ መሆኑን በስልክ የገለጹት ያካባቢው ነዋሪዎች “አሁን ፍርሃቻ አለ። ቤት ለቤት የተካሄደው ግድያ የት ጋር ያቆማል? የመከላከያ ሠራዊት ሚናም ግልጽ አይደለም” ብለዋል።
goderieየጋምቤላ ዞን ልዩ ኃይል ግጭቱን ለማብረድ እየገሰገሰ ባለበት ወቅት ከአዲስ አበባ በተሰጠ ትዕዛዝ ወደ ጋምቤላ እንዲመለሱ መደረጉን ያመለከቱት እኚሁ ክፍሎች፣ “የጋምቤላ ልዩ ኃይል ግጭቱ ያለበት ቦታ ሲደርስ በራሱ ክልል ሰዎች ላይ መጤዎች ጉዳት ማድረሳቸውን ሲመለከት ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ግጭት ሊፈጠር ይችላል” በሚል ስጋት የልዩ ኃይሉ ወደ ጋምቤላ የተመለሰበትን ምክንያት ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በገጀራና በተለያዩ የስለት መሳሪያዎች የተካሄደው ግድያ የሚዘገንን እንደነበር፣ ቀን ጠብቆ ተጎጂው አካል ከመበቀል ወደኋላ እንደማይል፣ በስለታማ ቁሶች የሚከናወነው ግድያ ሊሰፋ እንደሚችል ስጋታቸውን አክለው የገለጹት ነዋሪዎች ኢህአዴግ ሰላማዊ መፍትሄ ሊፈልግ እንደሚገባ ከወዲሁ ጠይቀዋል። በጋምቤላ ክልል በሳንቲም የሚቸበቸበውና የተፈጥሮ ደን እያወደመ ያለው ኢንቨስትመንት የተወሳሰበ ችግር ማስከተሉ አይዘነጋም። በዚሁ ሳቢያ በርካታ ንጹሃን ህይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው። ክልሉን ከላይ ሆነው የሚመሩት አቶ አዲሱ ለገሰ መሆናቸው ይታወቃል።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ጉዳዩን አስመልክቶ ከኦስሎ ለጎልጉል አስተያየት ሲሰጡ “ባሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው ላለፈ ወገኖች የሰላም ረፍት ይሁን፣ ፍትህ በልጅ ልጆቻችሁ ትፈርድላችኋለች፣ ፍትህ ሩቅ አይሆንም” በማለት ነበር የጀመሩት። አያይዘውም “ምንም እንኳ ባል ፖለቲከኛ ቢሆን ሚስትና ልጆች ምን አደረጉ? ህጻናትና ሴቶች በማያውቁት ጉዳይ ለምን ሰላባ ይሆናሉ? ቀደም ሲል አብረው የሚኖሩ ሰዎች ዛሬ ለምን ይጋጫሉ?” ሲሉ ችግሩ ሁሉ የሚመነጨው ኢህአዴግ ከሚከተለው ጎሳን መሰረት ያደረገ የከፋፍለህ ግዛው መርህ አንደሆነ ገልጸዋል።
“መመሪያ ሰጪው፣ ገዳዩ፣ አስገዳዩ፣ ቆሞ ተመልካቹ፣ … ሁሉም ከፍትህ አደባባይ አያመልጡም” ያሉት አቶ ኦባንግ “ዘርን እየለየ የሚከናወን ግድያ “ጄኖሳይድ” ነው። አኙዋኮች ላይ በጅምላ ከተከናወነው ጭፍጨፋ ለይተን አናየውም” ሲሉ በጉዳዩ ክፉኛ ማዘናቸውን አመልክተዋል።
የሚመሩት ድርጅት ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለና አስፈላጊ ነው የሚለውን ስራ እያከናወነ እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ ሁሉም ያካባቢው ነዋሪዎች ሰፋሪም ሆነ የቀዬው ተወላጆች እንደቀድሞ በፍቅር ሊኖሩ የሚያስችላቸውን እሴቶች እንዲጠብቁ መክረዋል። በተለያዩ ያገሪቱ ክፍሎች ጎሳን እየለየ የሚካሄደው ግድያና ማፈናቀል እየሰፋ እንጂ እየቀነሰ ባለመሆኑ ስጋቱ ከፍተኛ እንደሆነም ገልጸዋል። በዚህ ከቀጠለና ህወሃት የቀበራቸው የጎሳ ፈንጂዎች ሲነዱ እሳቱ ሁሉንም ስለማይምር ሁሉም ዜጎች ጥንቃቄ እንዲወስዱ አሳስበዋል። ኢህአዴግም ችግሮችን ከማስፋት ይልቅ የሚቃለሉበትን አግባብ ለራሱ ሲል ሊከተል እንደሚገባ ጠቁመዋል። ጎልጉል የዞኑንና የወረዳውን አስተዳደር ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ይሁን እንጂ የክልሉ ፖሊስ ዝርዝር መግለጫ ባይሰጥም የተባለው ቀውስ ስለመፈጠሩ አልካደም።

“ኣብራሃ ደስታን ኣላሰርኩም” የመቐለ ህወሓት (አምዶም ገብረስላሴ – ከትግራይ)

September 24,2014

የትግራይዋ ህወሓት ማለቴ በሰማእታት ሓወልት ፅሕፈት ቤትዋ ያደረገችው ህወሓት( ኣዲስ ኣበባ የህወሓት ኣንጃ ሰላለች ነው) “ኣብራሃ ደስታ የታሰረበት ምክንያት ኣላውቅም” ኣለች።

ይህ ኑዛዜ የተሰማው በኣገር ደረጃ ለመንግስት ሰራተኞች እየተሰጠ ያለው ስልጠና የሚሉት(ተቃዋሚና ያለፉት ስርዓቶች የሚሰድቡበት መድረክ ስለመሰለ ነው) በትግራይ ክልል ፅህፈት ቤት(ደጀን ቢሮ) የሚሰሩ ሰራቶኞች በፕላኔት ሆቴል እየተካሄደ ባለው መድረክ ነው።

በዚህ መድረክ እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎችና ሃሳቦች እጅጉን ጠንካሮችና የህወሓት ተራ ኣባላትና ጥቂት ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ፍፁም ታላቅ ልዩነት መነሩ የሚያሳዩ ናቸው።

በዚህ መድረክ “…ኣብራሃ ደስታ ህገ መንግስት የስጠው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቱን በኣግባቡ በመጠቀሙ ለምን በሽብር ኣምካኝታቹ ኣሰራቹት?…” ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ ነው የመቐለዋ ህወሓት ኣብራሃን እንዳላሰረችና” የማሳሰርያው ምክንያትም ኣላውቅም” ብላ የካደችው።

ስብሰባው እየመሩት የነበሩት የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ “..ስለ ኣብራሃ ደስታ መታፈንና መታሰር በፌስቡክ ስሰማ በቀጥታ ወደ ህወሓት ቢሮ ሂጀ ኣነጋጋርኳቸው። ከህወሓት ፅህፈት ቤት ያገኘሁት መልስ ምንም የሚያውቁት እንደሌለና ህወሓት እንዳላሳሰረው ረግረውኛል..” ሲሉ በስብሰባው ገልፀዋል።

ኣብራሃ ደስታን የመቐለዋ ህወሓት ካላሳሰርችው ሌላዋ ተጠያቂ የኣዲስ ኣበባዋ የህወሓት ኣንጃ ናት ማለት ነው።

ከፍተኛ ቁጣ የተላበሰው የፕላኔት ሆቴል ተስብሳቢ ህዝብ ለህወሓት መሪዎች ኣስፈሪ ነበር።

ኣገሪትዋ እየበጠበጥዋት ያሉት መላ የህወሓት ኣባላት ሳይሆኑ የተወሰኑና ጥቂት ሰዎች መሆናቸው በግልፅ በመላ ትግራይ ያሉ ስብሰባዎች የተነሱ ሃሳቦች ቁልጭ ኣድረገው እያሳዩ ናቸው።

ሌላው ከፍተኛ የመወያያ ኣጀንዳ በዓረና ኣባላት እየደረሰ ያለው ዓፈና፣ እንግልት፣ ድብደባ፣ ኣማራጭ ሃሳብ ወደ ህዝቡ እንዳይቀርብ ማደናቀፍ የኣዲስ ኣበባዋ ኣንጃ ሳትሆን የመቐለዋ ኣንጃ ስራ መሆኑ በግልፅ ተነግራቸዋል።

እጅጉን ያስደስታል ህዝቡ ነፃነት ፈልጓል፣ ዲሞክራሲን ናፍቆታል፣ መልካም ኣስተዳደርን ቋምጣል። ለዚህ ማሳያ በዓረና የሚደረገው የማፍረስ፣ እንዳይንቀሳቀስ የመከልከል ተግባር ውጉዝ ከመኣርዮስ እያለው ይገኛል።

ስዊድን የኤርትራ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

September 24,2014
ኢሳያስ አፈወርቂ ጉዳዩ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሴራ ነው አሉ
ስዊድንና ኤርትራ በዲፕሎማቲክ የእሰጣ እገባ ውስጥ ከገቡ በርከት ያሉ ጊዜያት የተቆጠሩ ሲሆን በስዊድን የኤርትራ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ባልተገባ ተግባር ተገኝተዋል በሚል የሀገሪቱ ዲፕሎማቶች ስዊድንን በ48 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ የስዊድን መንግስት ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድርጊቱ የኢትዮጵያና የአሜሪካ እጅ አለበት ብለዋል። በስዊድን የወጣውን አዲስ ሕግ ተከትሎ የስዊድን መንግስት በኤርትራ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል ባላቸው ከፍተኛ የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ላይ በዚያው በስዊድን ክስ መመስረቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሻክሯል።
isayas afewerki
የኤርትራ መንግስት ዋነኛ የውጪ ምንዛሪ ገቢ በተለያዩ ሀገራት በሚኖሩ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች ላይ የጣለው ሁለት በመቶ የገቢ ታክስ ሲሆን በድርጊት በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኤርትራውያን በኢምባሲያቸው ላይ ቅሬታ ሲያሰሙ ቆይተዋል። በስዊድን የሚገኙ ኤርትራውያንም ኢምባሲያቸው የሚጠበቅባቸውን የታክስ መጠን ካልከፈሉ የተለያዩ የዜግነትና የጉዞ ዶክመንቶችን ከመከልከል ባለፈ በኤርትራ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው በማያዣነት ተጠቅሞ እስከማስፈራራት ደርሷል በሚል ለስዊድን መንግስት ክስ ሲያሰሙ መቆየታቸው ታውቋል። የኤርትራ መንግስት በስዊድን በሚገኙ ኤርትራውያን እና የስዊድን ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኤርትራውያን የተደራጀ ተቃውሞ እየገጠመው ሲሆን የተቃውሞ አደራጅ ግለሰቦችን ለይቶ ለመከታተል በስዊድን የሚገኘውን ኤምባሲውን እና ዲፕሎማቶችን ይጠቀማል በሚልም ጭምር ነው የስዊድን ባለስልጣት የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ለማባረር በምክንያትነት ያስቀመጡት።
የኤርትራ መንግስት በየሀገሩ በሚገኙ ኤምባሲዎቹ አማካኝነት ከኤርትራ ዲያስፖራዎች በታክስ መልኩ በሚሰበሰበው ሁለት በመቶ ገቢ ሽብርተኞችና በፋይናንስ እያገዘ ነው በሚል በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አማካኝነት ማዕቀብ ከተጣለበት ዓመታት ተቆጥረዋል። ሆኖም ከማዕቀቡ በኋላ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ መንግስት በተለያየ ሀገራት ኤምባሲዎች በኩል ታክሱን ለመሰብሰብ የሚያደርገው ሙከራ በየሀገራቱ መንግስታት ተቃውሞ እያስነሳበት ነው። ከዚህ ቀድም በተመሳሳይ መልኩ ካናዳና ኤርትራ ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የካናዳ መንግስት በቶሮንቶ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን በ48 ሰዓታት ውስጥ እስከማባረር ደርሷል።
የስዊድን እርምጃ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሰጡት ማብራሪያ ድርጊቱ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ሴራ ነው ብለውታል፡፡ ሁለቱ ሀገራት የኤርትራ መንግስት ሁለት በመቶ ታክሱን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በሽብርተኝነት ለማተራመስ ይጠቀምበታል በሚል ማዕቀቡ እንዲጣልበት ሰፊ የዲፕሎማሲ ሚናን መጫወታቸውን በምስራቅ አፍሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሠራው ጂስካ አፍሪካ ኦንላይን ዘግቧል። (ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው)

በመላ ሃገሪቱ የተነደፈው የተቀናጀ የጐልማሶች ትምህርት ስኬታማ አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ተናገሩ፡፡

በመላ አገሪቱ ከ40 ሚሊዮን በላይ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ወጣት እና ጎልማሶች አሉ ያሉት አቶ ሺፈራው ፤  ይህንን የትምህርት እድል ያለገኙ ወጣቶች እና ጎልማሶች አማራጭ
ትምህርት እንዲያገኙ የተደረገው ሙከራ አፈፃጸሙ ከዜሮ በታች ነው ብለዋል። በኢህአዴግ የእቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ እንደቀረበው በጎልማሶች የትምህርት አቀራረብ  አማራ 0.9፣ ኦሮምያ ፣ 0.71 ፣ደቡብ 0.63 ፣ትግራይ 2.9
በመቶ ፈጽመዋል።
ኢህአዴግ ደርግን ባመሰገነበት የምክር ቤት ውይይት ፤ “ለምን ህዝቡን በዘመቻ አናስተምርም?” ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ ፤ “ኢህአዴግ የተፈጠረው ከዘመቻ ነው፡፡ ወጣቱ ሌላ የትጥቅ ትግል እንዲያደራጅ  መሳሪያ አንሳ ብለን አንልክም”
የሚል መልስ ተሰጥቷል። “በገጠር መሬት አልባ የሆነው ወጣት ፤ በከተማ ስራ አጥ የሆነው የተማረው ሃይል በአንድነት ተገናኝቶ ሊፈጥረው የሚችለው አደጋ ሰፊ ነው፤ ይህ ስጋት ሳይሆን ሃቅ ነው” ሲሉ አቶ በረከት እና አቶ አበይ ፅሃየ
በመደጋገፍ እየተናገሩ ጎልማሶችን በዘመቻ ለማስተማር የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል፡፡ አቶ በረከት እንዲህ አይነቱን አስተያየት የሚያቀርቡት በትጥቅ ትግሉ ወቅት ያልነበሩ አመራሮች ናቸው በሚል አዳዲስ የኢህአዴግን አመራሮች
መወረፋቸው ከኢህአዴግ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

Tuesday, September 2, 2014

ዴግ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ለሰራተኞች የሚሰጠውን ስልጠና ለማስቀጠል አቅዷል
ነሃሴ ፳፯(ሃያሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሁለት ሣምንታት ለዩኒቨርሲቲ አዲስና ነባር ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የመጀመሪያ ዙር
አስገዳጅ ሥልጠና የፊታችን ቅዳሜ የሚጠናቀቅ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ሥልጠና ወዲያውኑ ለመቀጠል ትምህርት ሚኒስቴር መዘጋጀቱን መረጃዎች ጠቁመዋል።
ተማሪዎችተገድደውበገቡበትበዚሁየሥልጠናቆይታቸውደስተኛያለመሆናቸውንበመናገርላይናቸው፡፡
በዋነኛነት የመንግሥት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ለተማሪዎች ለማስተዋወቅ በሚል በመንግሥት ከፍተኛ በጀት ከ33
በላይ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው በዚሁ ሥልጠና ላይ የኢህአዴግ ዋና ዋና ካድሬዎች በአሰልጣኝነት የግንባሩን ርዕዮተ ዓለም ለማስተዋወቅና ለማስረጽ
ሲጠቀሙበት ከርመዋል። ተማሪዎቹ በሥልጠና ቆይታቸው ከምግብና የታሸገ ውሃ መጠጥ በተጨማሪ በቀን 35 ብር ውሎ አበል የታሰበላቸው ሲሆን በአንድ
ለአምስት ተጠርንፈው የቀን የውይይት አጀንዳዎችን እንደገና እርስ በእርስ ተወያይተው እንዲመጡ አስገዳጅ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑና በዚህም በሒደቱ በከፍተኛደረጃመሰላቸትናየእርስበእርስአለመተማመንእንዲፈጠርመሆኑእንዳሳዘናቸውበመናገርላይይገኛሉ፡፡
ትምህርትና ሥልጠና በፍላጎትና በምርጫ የሚወሰድ መሆኑንና ላለመገደድ ያላቸውንሕገመንግስታዊመብትበገዥውፓርቲከመነጠቃቸውምበተጨማሪ
በአስገዳጅሁኔታየገዥውፓርቲርዕዮተዓለም ለማስረጽየሚደረገውጥረትአብዛኛውንተማሪይበልጥለግንባሩያለውንጥላቻያሳደገነውሲሉተችተውታል፡፡
በዚሁ ሥልጠና ላይ ስለሙስናና ብልሹ አሠራር መስፋፋት፣ስለፍትህ መጓደል፣ስለሰዎች አለአግባብ መታሰር፣ስለኑሮ
ውድነት ፣ስለኤሌክትሪክ፣ውሃእናየቴሌኮምአገልግሎቶችጥራትማሽቆልቆልእና የመሳሰሉሀገራዊየሆኑ
ፖለቲካዊናኢኮኖሚያዊጉዳዮችተማሪዎቹበአስተያየትናበጥያቄመልክያቀረቡቢሆንምካድሬዎቹለእነዚህጥያቄዎች
ቀጥተኛምላሽከመስጠትይልቅ «ይህየጸረሰላምሃይሎች፣የኪራይሰብሳቢዎችአስተሳሰብነው…» የሚሉምላሾች
ሲሰጡበመደመጣቸውተማሪዎቹበእንደነዚህዓይነትሰዎችሀገሪትዋእየተመራችመሆንዋይበልጥሀዘኔታናግራመጋባትእንደፈጠረባቸውአስረድተዋል፡፡
ኢሳት ከተማሪዎች ጋር ያደረገውን ውይይት በተከታታይ ቀናት እንደሚለቅ ለመግለጽ ይወዳል።
በሌላ ዜና ደግሞ የአዲስአበባከተማአስተዳደርኢህአዴግጽ/ቤትባዘጋጀውየድርጅትአባሎችስልጠናመርሃግብርመሰረትለከተማውበየደረጃውለሚገኙ
ሁሉምየመንግስትሰራተኛየኢህአዴግአባሎችዛሬበይፋስልጠናጀምሯል፡፡
ስድስትኪሎበሚገኘውሚኒልክት/ቤት የሚካሄደው ስልጠና ከዛሬ ነሃሴ 27 ጀምሮጀምሮለተከታታይ 10 ቀናትይካሄዳል።
ለእያንዳንዱ ሰልጣኝ ከ50-100 ብርአበልእንደሚከፈል ታውቋል። በስልጠናውርዕሰጉዳይላይ ተጨማሪ ዘገባዎችን ለወደፊቱ ይዘን እንቀርባለን።
ኢህአዴግ ለመስተዳድሩ የፖሊስ አባላትም ተመሳሳይ ስልጠና እያሰጠ ይገኛል።

የግንቦት 7 ለነፃነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በኦስሎ ከተማ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አደረገ!!

ሚሊየን / ሊማ ከኖርዌይ
ኦገስት 31, 2014

ኦገስት 31, 2014 በኖርዌ ዋና ከተማ ኦስሎ የግንቦት 7 ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱን በተሳካ ሁኔታ አደረገ። የግንቦት 7 ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በተለያዩ ከተሞች እያደረጋቸው ካሉት ህዝባዊ ስብሰባዎች አንዱ የሆነውና በኦስሎ ከተማ የተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ በተጋባዥ እንግድነት በስፍራው የተገኙ ሲሆን ይህንን ስብሰባ ያዘጋጀው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ነው።

ዝግጅቱ በኖርዌጂያን የሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 1500 ላይ የተጀመረ ሲሆን የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የመክፈቻ ንግግ አድርገው ባለፉት 23 አመታት በወያኔ የግፍ አገዛዝ ህይወታቸው ላጡ ንፁሀን ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማስደረግ ዝግጅቱን በይፋ አስጀምረዋል።  በመቀጠል የግብረኃይሉ ዋና አስተባባሪ የሆኑት ጠንካራ ሶስት መልክቶችን አስተላልፈው የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እራእይና አላማን እንዲሁም የትግሉን ደረጃ በቪዲዮ የተደገፈ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ከዚህ በመቀጠል የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ዋና ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዮሐንስ አለሙ ይህን ዝግጅት ድርጅታቸው በማዘጋጀቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው እስከዛሬ ከሄድንባቸው የትግል ስልቶች ትግሉን አንድ ደረጃ በማሳደግ የተግባር ስራ መስራት እንደሚገባና ወያኔን ከስልጣን ለማውረድ ሁለገብ ትግላችንን ያለማቋረጥ በተከታታይ ማድረግ እንዳለብን እንዲሁም ያለንበት ሰአት የተግባር ስራን የሚጠይቅ በመሆኑ  ለተግባራዊነቱ የሁላችንንም ቆራጥነት የሚጠይቅ መሆኑን በማሳሰብ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበሩም በተያዘላቸው ሰአት የትግሉን ደረጃና የግንቦት 7ትን ራእይና አላማ ለህዝቡ በዝርዝር በማስተላለፍ በተለይ ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ በመሆናቸው ወደ ትግሉ እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል። በቀረበው ጥሪ መሰረት በርካታ ሰዎች የድርጅቱን ፎርም በመሙላት ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ግንቦት 7 ትን ተቀላቅለዋል። በስብሰባው መሃልም የአርበኞች ግንባር፣ የትግራይ ህዝብ ንቅናቄ እንዲሁም የግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል ኃላፊዎች በስልክ ለታዳሚው መልክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በቀጣይ አንዳርጋቸው ፅጌ ማን ነው የሚል የአንዳርጋቸውን ስራዎችና የህይወት ታሪኩን የሚዘክር ቪዲዮም ቀርቧል።

በመጨረሻም የአንዳርጋቸውን ፅጌን ምስል የያዘ ፎቶ ግራፍ ለጨረታ ቀርቦ ህዝቡ በከፍተኛ የገንዘብ መጠን ፉክክሩል አሳይቷል። ከፍተኛውን ገንዘብ በመክፈል የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ጨረታውን በማሸነፉ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ምስል ከአቶ አበበ ቦጋለ እጅ ተረክብዋል። ለዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ሎተሪዎች፣ መፅሀፎት፣ ትኬቶች ምግብና መጠጥ እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች ለሽያጭ የቀረቡ ሲሆን ከሽያጩም ከፍተኛ ገቢ ተገኝትዋል። በመቀጠል የግንቦት 7 ምክትል ሊቀመንበሩ ከተሰብሳቢው ጋር የጥያቄና መልስ ውይይት አድርገዋል። በማጠቃለያም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ም/ሊቀመንበር የመዝጊያ ንግግር አድርገው በህዝባዊ ኃይሉ መዝሙር ስብሰባው በተያዘለት ሰአት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል።

Monday, September 1, 2014

Andargachew Trafalgar Square 1

Ginbot 7 movement for justice freedom and democracy public meeting and fundraising in Norway/Oslo

https://www.youtube.com/watch?v=puBSohE1Enk&app=desktop
http://www.ethiotube.net/video/31844/New-Campaign--I-am-Andargachew-Tsige
http://ethsat.com/video/sat-andargachew-trafalgar-square-aug-30-2014/#.VARSYCX4U6A.facebook