Monday, January 26, 2015

 ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና ዲሞክራሲያዊ የመብት ጥሰት ተመልክቶ ከእስር ሊወጣበት የሚችልበትን አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ ለማሳሰብ ነው።
በተጨማሪም አንዳርጋቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በወያኔ የተፈጸመውን የውንብድና ድርጊት በመቃዎም ለእንግሊዝ መንግሥት በተለያየ መልኩ የአገሩን ዜጋ ህይወት ይታደግ ዘንድ በተደጋጋሚ ለማሳሰብ ቢሞከርም አፋጣኝ እርምጃ አለመወሰዱ ብዙዎችን አስቆጥቷል።
አንዳርጋቸው አገር ወዳድ፣ ሰላም ፈላጊ፣ ነጻነትና ፍትህ ናፋቂ፣ ለህዝብና ለአገር ክብር ተቆርቋሪ፣ ከእራሱ እና ከሚወዳቸው ቤተሰቦቹ ይልቅ ለእናት አገሩ ኢትዮጵያ ጊዜውን፣ እውቀቱንና ህይወቱን የሰዋ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ጀግና መሆኑን በኩራት መስክረዋል። የውጭ ዜጎችም ሳይቀሩ ኢትዮጵያዊ ማንዴላ ብለው ሰይመውታል። ለዲሞክራሲ መከበር ለሚታገል አርበኛ እስርና እንግልት ኮቶ እንደማይገባ በተለይ የእንግሊዝ መንግሥት በትኩረት ሊመክርበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እና በወያኔ ላይ ግፊትና ጫና መፍጠር እንዳለበት ሁሉም ተሰላፊዎች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
እንዲሁም ሰልፈኞቹ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ድምጽና ስሜት የኖርዌይ ቅዝቃዜና በረዶ ሳይበግራቸው ለኢንባሲው አሰምተዋል። ከአሰሟቸው መፈክሮች መካከል ለአብነት ፣ “Andargachew is a freedom fithter, UK, were is your citizen, Free Andrgachew Tsige, Andargachew is our icon of democracy, where is your action , stop discrimination among citizens, Yes, we are all Andrgachew Tsige, Yes, Andargachew is an Ethiopian Mandela, Brtain don't support terrirost regim in Ethiopia, ” የሚሉት ይገኙበታል::
እንደተለመደው በድርጅቱ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በድርጅቱ ተወካዮች በአቶ ይበልጣል ጋሹ እና በአቶ ዮናስ ዮሴፍ አማካኝነት ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳዩ ትኩረት የሚሻና ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን በመግለጽ ህይወቱም በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለ በጥብቅ በማሳሰብ ደብዳቤውን በኢምባሲው ተወካይ አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
በመጨረሻም ግፈኛው የወያኔ ቡድን በለመደው ተራ የሀሰት ወሬ በሚያወራበት ቴሌቪዥኑ ላይ ለትርጉም በሚያስቸግር መልኩ ቆራርጦና በጣጥሶ አንዳርጋቸውን ለማስወራት መሞከሩ የወያኔን ከንቱነት እና እውቀት ዓልባነቱ እንዲሁም ለህዝብና ለአገር የሚሰጠው ንቀት ይበልጥ ለዓለም መጋለጡ ለእኛ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ህብርትና አንድነት ፈጥረን በእልህ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት ከበፊቱ በበለጠ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ትልቅ በር ከፍቶልናል፤ ለትግልና ለተቃውሞም ይበልጥ አነሳስቶናል። እንደ አርበኞችና ግንቦት ሰባት የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ውህደት ፈጥረው በሁለገብ ትግል ዘረኛው ወያኔን ለማስወገድ ቆርጠው እንዲነሱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ዓለሙ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በተመሳሳይም የወጣቶች ክፍል ተወካይ አቶ ይበልጣል ጋሹ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለነጻነትና ዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል አስትዋጾ ማድረግ እንዳለባቸው በአጽንኦት አሳስበዋል።
ወጣት ሁሉን ነገር የመለወጥ ኃይልና አቅም አለው!አምባገነን መንግሥትን ማስወገድ እንችላለን! ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ማስወገድ እንችላለን!
ዛሬም ነገም ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
የወጣቶች ክፍል
Unlike ·  · 

Tuesday, January 20, 2015


ስልጣኔን አትንኩ ብሎ ቢንፈራገጥ
አሁን ቀኑ ቀርቧል ጉዱ ሚታይበት
በአገር ወዳድ ህዝብ የሚከበብበት
ገመድ በአንገቱ የሚጠልለቅለት
ረጃጅም ቀንዶቹ የሚስበሩበት
እግሩ ተጎትቶ የሚዘረርበት
ህዝቤ በርታ ባክህ ይሄው መጣንልህ
ድምጸህን ላስማ ሩቅ ላሉት ወገነህ
ኢሳት ነኝ ፋሲል ነኝ መሳይ ነኝ እኔማ
የታፈነውን ድምጸ ሁሌም የማስማ
ዴሴሶን ራዲዮ በሳሊ አብረሃም
Like ·  · 

Monday, January 19, 2015

In Picture: ESAT Journalists with Freedom Fighters

JANUARY 19, 2015
The two top notch ESAT (Ethiopian SATELLITE Television) journalists Mesay Mekonnen and Fasil Yenealem are in Eritrea to gather news and reports about the Ethiopian patriots (freedom fighters), the following pictures are taken from Mesay Mekonnen’s Facebook page.
ESAT Journalists with Freedom Fighters
ESAT Journalists with Freedom Fighters
ESAT Journalists with Freedom Fighters
ESAT Journalists with Freedom Fighters
ESAT Journalists with Freedom Fighters
ESAT Journalists with Freedom Fighters

Please LIKE our Facebook page - it makes us stronger

Sunday, January 18, 2015

ማስታወቂያ
የዲሞክራሲ ለውጥ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የ3ኛና 4ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ክንውን የሚቀርብበትና ለወደፊት ሊሰሩ የሚገባቸውን ተግባራት ለመወሰንበህገ ደንባችን መሰረት ምልዓተ ጉባኤ ማዘጋጀት አስፈልጓል። ስለዚህ የድርጅቱ አባላት በሙሉ በፌብሯሪ 14/2015 ከቀኑ 13፡00 እስከ 16፡00 ስዓትእንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን!ከዚህበመቀጠልም
የአርበኛው አቶ አንዳርጋቸው ፷ኛ ዓመት የልደት በዓል!
ለኢትዮጵያ አገራችን ነጻነትና ፍትህ ለማስፈን የህይወት መስዋትነትን እስከ መክፈል ድረስ እየታገለ የሚገኘውን የነጻነት ተምሳሌት የጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌ ፷ኛ ዓመት የልደት በዓልን በዓለም አቀፍ ደረጃ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። ስለዚህ በኖርዌይ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ፌብሯሪ 14/2015 ከ16፡00እስከ 22፡00 ስዓት በልደት በዓሉ ላይ ተገኝተታችሁ የአላችሁን አክብሮት ትገልጹ ዘንድ ተጋብዛችኋል።
የዝግጅት ቦታ፡ በቅርብ ቀን እናሳውቃለን

Thursday, January 15, 2015

ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!

      ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን! 
የነጻነትና የፍትህ ታጋዩ አርበኛው አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ፋሽስታዊ መዳፍ እጅ ከወደቀበት ቀን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በእልህ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት ከበፊቱ በበለጠ ትግላችንን አጠናክረን መቀጠላችን ያሳሰበው ወያኔ ተራ የውሸት ወሬ በሚያወራበት ቴሌቪዥኑ ላይ ለትርጉም በሚያስቸግር መልኩ ቆራርጠውና በጣጥሰው አንዳርጋቸውን ለማስወራት ሞክረዋል። 
ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያስቡት በላይ እውነቱን ያውቀዋልና የወያኔ አላማ ከንቱ ሁኖ ግቡን ሳይመታ ቀርቷል፤ በተቃራኒው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ለትግልና ለተቃውሞ ይበልጥ አነሳስቷል።  
ስለዚህም ለዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የወጣቶች ክፍል የእንግሊዝ መንግሥት የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ አጽንኦት በመስጠት እና ከወያኔ አረመኔ ቡድን መዳፍ እንዲለቀቅ አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ግፊት ለማድረግ ሰኞ ጥር /ጃንዋሪ 25/2015 ከ14:00_15:00 kl በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ  ሰልፍ ይደረጋል። እናንተም በስዓቱና በቦታው እንድትገኙ በአክብሮት አገራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! 
በዲሴሶን የወጣቶች ክፍል

Tuesday, January 13, 2015

የኢህአዴግ ካድሬዎች የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ
• ‹‹በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ዘመቻ ተከፍቷል››
ብአዴን/ኢህአዴግ በምስራቅ ጎጃም ዞን ‹‹የምርጫ ግብረ ኃይል›› በሚል አደረጃጀት የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ አቶ ሳሙኤል አወቀ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የብአዴን ካድሬዎች በምስራቅ ጎጃም በተለይም ደብረማርቆስ ከተማ ላይ ቤት ለቤት እየዞሩ ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ በሚቀሰቅሱበት ወቅት የምርጫ ካርድ አልወስድም የሚሉ ዜጎችን ‹‹አልወስድም ስትል ፈርም›› እያሉ እያወከቡ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ‹‹የምርጫ ግብረ ኃይል›› በተሰኘው መዋቅር የምርጫ ካርድ እንደማይወስዱና እንደማይፈርሙ ስለሚገልጹት ዜጎች ከሌሎች መረጃ በመጠየቅ ለማስፈራራት እየሞከሩ መሆንን ገልጸውልናል፡፡
ከዚህም ባሻገር ካድሬዎቹ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ለምርጫ ጽ/ቤት አቅጣጫ እንደሚሰጡ፣ የምዝገባ ሰነዶችም በእነሱ እጅ እንደሆኑና የምዝገባ ሂደቱን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተግልጾአል፡፡ ካርድ የማቅረብና የመመዝገብ ኃላፊነት የምርጫ ቦርድ ስራ ሆኖ እያለ ሞጣ አካባቢ የምርጫ ካርድ አለቀ ሲባል በብአዴን ካድሬዎች ትዕዛዝ ከጎዛመን ወረዳ የምርጫ ካርድ ወደ ሞጣ መላኩን በመጥቀስ ብአዴን/ኢህአዴግ ምርጫ ቦርድን ተክቶ እየሰራ መሆኑን ኃላፊ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የብአዴን ካድሬዎች ሰማያዊ፣ አንድነትና መኢአድ ከፓርቲነት ተሰርዘዋል እያሉ እያስወሩ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን በተለይ በየገጠሩ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ እውቅና የለውም፡፡ እውቅና ከሌላቸው ሌሎች ፓርቲዎች ጋርም ህገ-ወጥ ትብብር ፈጥሮ እየሰራ ነው፡፡ በመሆኑም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ከመስራታችሁ በፊት ህገ-ወጥ መሆኑን ልታውቁት ይገባል፡፡ ራሳችሁን ችግር ላይ እንዳትጥሉ›› እያሉ እየቀሰቀሱ መሆኑን አቶ ሳሙኤል አወቀ ገልጸዋል፡፡ በተለይ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ዘመቻ ተከፍቷል ያሉት ፀኃፊው ብአዴኖች በከተማና በገጠር በሚኖረው ህዝብ ውዥንብር ለመንዛት እየጣሩ እንደሆነ ታዝበናል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ፣ ግንቦት7 እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ የውህደት ስምምነት ተፈራረሙ
Jan 11th, 2015 · 0 Comment
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ፣ ግንቦት7 እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ በጋራ ባወጡት መግለጫ ”ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ካሉበት አዘቅት በማውጣት ሕዝቡ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት የግድ የሚለን ደረጃ ላይ ደርሰናል” ብለዋል። ድርጅቶቹ አያይዘውም ”አገራችንና ሕዝባችንን ከአዘቅት ለማውጣት በመጣመር ብቻ ሳይሆን በውህደት አንድ ሆነን አገራችንንና ሕዝባችንን አንድ በማድረጉ ረገድ አስፈላጊው መስዋዕትነት በመክፈል የትግል እድሜ እናሳጥር በሚል ለውህደት የሚያደርሰንን ውይይት ለመጀመር የሚያስችል ሂደቶችን አጠናቀን ወሳኝ ወደሆነው ሂደት ውስጥ መግባታችንን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ወዳጆች ማብሰር እንፈልጋለን።” ብለዋል።

የኢህአዴግ ካድሬዎች የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ

የኢህአዴግ ካድሬዎች የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ
• ‹‹በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ዘመቻ ተከፍቷል››
ብአዴን/ኢህአዴግ በምስራቅ ጎጃም ዞን ‹‹የምርጫ ግብረ ኃይል›› በሚል አደረጃጀት የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ አቶ ሳሙኤል አወቀ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የብአዴን ካድሬዎች በምስራቅ ጎጃም በተለይም ደብረማርቆስ ከተማ ላይ ቤት ለቤት እየዞሩ ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ በሚቀሰቅሱበት ወቅት የምርጫ ካርድ አልወስድም የሚሉ ዜጎችን ‹‹አልወስድም ስትል ፈርም›› እያሉ እያወከቡ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ‹‹የምርጫ ግብረ ኃይል›› በተሰኘው መዋቅር የምርጫ ካርድ እንደማይወስዱና እንደማይፈርሙ ስለሚገልጹት ዜጎች ከሌሎች መረጃ በመጠየቅ ለማስፈራራት እየሞከሩ መሆንን ገልጸውልናል፡፡
ከዚህም ባሻገር ካድሬዎቹ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ለምርጫ ጽ/ቤት አቅጣጫ እንደሚሰጡ፣ የምዝገባ ሰነዶችም በእነሱ እጅ እንደሆኑና የምዝገባ ሂደቱን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተግልጾአል፡፡ ካርድ የማቅረብና የመመዝገብ ኃላፊነት የምርጫ ቦርድ ስራ ሆኖ እያለ ሞጣ አካባቢ የምርጫ ካርድ አለቀ ሲባል በብአዴን ካድሬዎች ትዕዛዝ ከጎዛመን ወረዳ የምርጫ ካርድ ወደ ሞጣ መላኩን በመጥቀስ ብአዴን/ኢህአዴግ ምርጫ ቦርድን ተክቶ እየሰራ መሆኑን ኃላፊ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የብአዴን ካድሬዎች ሰማያዊ፣ አንድነትና መኢአድ ከፓርቲነት ተሰርዘዋል እያሉ እያስወሩ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን በተለይ በየገጠሩ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ እውቅና የለውም፡፡ እውቅና ከሌላቸው ሌሎች ፓርቲዎች ጋርም ህገ-ወጥ ትብብር ፈጥሮ እየሰራ ነው፡፡ በመሆኑም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ከመስራታችሁ በፊት ህገ-ወጥ መሆኑን ልታውቁት ይገባል፡፡ ራሳችሁን ችግር ላይ እንዳትጥሉ›› እያሉ እየቀሰቀሱ መሆኑን አቶ ሳሙኤል አወቀ ገልጸዋል፡፡ በተለይ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ዘመቻ ተከፍቷል ያሉት ፀኃፊው ብአዴኖች በከተማና በገጠር በሚኖረው ህዝብ ውዥንብር ለመንዛት እየጣሩ እንደሆነ ታዝበናል ብለዋል፡፡

Wednesday, January 7, 2015

የገና ዛፍ ለምን

የገና ዛፍ ለምን ?
በአገራችን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል በምናከብርበት ወቅት ለበዓሉ ድምቀት ሲባል የሚደረጉ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው የገናን ዛፍ መትከል ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በየቤቱ ይህንን ዛፍ ለመትከል ሲል በየከተማው ያለው ዛፍ ይጨፈጨፋል፣ አሁን አሁንማ በከፍተኛ ዋጋ እየተሸጠ ነው፡፡ በአገራችንም ብቻ ሳይሆን በሰለጠኑ አገሮችም የዚህ ዛፍ ጉዳይ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ሆኗል፡፡ እንዲያው ያ ዛፍ በመብራት ተሸቆጥቁጦ በየቤቱና በየቤተክርስቲያን መድረኮች ላይ ካልቆመ በዓሉ በትክክል እንዳልተከበረ ሁሉ ሊታሰብ ይችላል፡፡ ለበዓሉ አከባበር ሲባል የሚቆረጠው ማንኛውም ዛፍ ሳይሆን የሚመረጠው ጥድ ነው፡፡ የገና ዛፍ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ጋር የሚያይዘው ምንድነው፣ ምንስ ትርጉም አለው እንዴትስ በዚህ ታሪካዊ ሁኔታ ውስጥ ሊገባ ቻለ ማለትና መልስ ማግኘት የሚገባ ይመስለኛል፡፡
የገና ዛፍ አጠቃቀም ታሪካዊ አመጣጥ በምንመለከትበት ወቅት ይህ ድርጊት የተጀመረው በጥንታዊቷ ጀርመን በ15ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ ጀርመኖች አሬንጓዴ ዛፎች ወዳሉባቸው ቦታዎች በመሄድ በተለያዩ መብራቶችና የፍራፍሬ ዓይነቶች የስጌጡአቸው ነበር፡፡ የማይደርቁና የማይጠወልጉ አሬንጓዴ ዛፎች ርኩስ መናፍስትን፣ ምትሐትን፣ በሽታንና ድህነትን ያርቃሉ የሚል እምነት ስለነበራቸው ይህንን አጠንክረው ያድርጉታል፡፡ አብዛኛዎቹ የጥንት ሰዎች ፀሐይን አምላክ ብለው ስለሚያመልኩ ክረምት የሚመጣው ያ አምላክ የሆነው ፀሐይ ሲታመም ወይም ሲደክም ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ ከዓመት እስከ ዓመት ሳይጠወልጉና ቅጠላቸው ሳይረግፍ የሚቆዩ እንደ ጥድ ያሉ ለምለም ዛፎች የታመመው ወይም የደከመው ፀሐይ አምላክ እንደገና ኃይል አግኝቶ እንደሚበረታና ክረምቱም አልፎ ፀሐይ እንደሚመጣ የሚያሳስቡ ስለሆነ በጣም ይንካከቡአቸዋል፣በመብራትና በልዩ ልዩ ጌጣጌጦች እያስዋቡአቸው ያመልኩአቸዋል፡፡ አምልኮቱ ግን ለዛፎች ብቻ ሳይሆን ከዛፎች በስተጀርባ ላለው አሬመኔአዊ አምላክ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የጥንት ጀርመናውያን ለምለም ዛፎችን በያሉበት ያስገጡቸው እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ዛፎቹን የተለያዩ ሻማዎችን በማብራት ፣ እንደ ፖም፣ ብርቱካንና፣ ለውዝ ያሉ የአትክልት አይነቶችንና ሌሎች ምግቦችን በቅርንጫፎቻቸው ላይ በማጠልጠልና ልዩ ልዩ ደማቅ ቀለም ያሉአቸውን የጨርቅ ሪባኖችን በላያቸው ላይ ከላይ እስከ ታች ድረስ በመዘርጋት ወዘተ በማስገጥ ያመልኩአቸው ነበር፡፡ በዛፎቹ ላይ ሻማ መብራት የተጀመረው ግን በ18ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡
አሁን ያለን አማኞችም ሆነን ሌሎች የጥድ ቅጠል በየቤታችን ወይም በየበራችን እንደምናደርገው በ15ኛውና በ16ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከዓመት እስከ ዓመት ድረስ ሳይረግፉና ሳይጠወለወጉ አሬንጓዴ እንደሆኑ የሚከርሙትን ዛፎች( Evergreen Trees) ባሉበት ማስገጡ ብቻ ሳይሆን ውሎ እያደረ እያንዳንዱ አምላኪ የዛፎቹን ቅርንጫፍ ቆርጦ ወደቤቱ አምጥቶ በበሩና በመስኮቱ እንዲሁም በቤቱ ጣሪያ ላይ ማንጠልጠል ጀመረ፡፡ ይህንን በማድረጋቸው በሽታ ፣ ድህነትና ርኩስ መንፈስ ሁሉ ከበር ይመልስልናል ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡ ከዚያም የተነሳ የአሬንጓዴ ዛፎች ዋጋና ለእነርሱ የሚሰጠው ግምት ምን ጊዜም ከፍተኛ እየሆነ መጣ፡፡ በተለይም ደግሞ ዛፎቹ ከፍተኛ በረዶ በሚወርድቸው የክረምት ወራት ልዩ ትርጉም አላቸው፡፡ በምዕራቡ ዓለም በጋው አልፎ ክረምቱ ማለትም የበረዶ ወቅት በሚመጣበት ጊዜ ዛፎች ሁሉ ቅጠላቸው ይረግፍና የደረቁ እስክመስሉ ድረስ እንጨት ብቻ ይቀራሉ፡፡ ይህ ሲሆን እነዚያ ለምለም (evergreen) የሚባሉ ዓመቱን ሙሉ አሬንጓዴ የሚሆኑ ዛፎች ብቻ ይቀራሉ፡፡ ያኔ ከሰማይ የወረደው በረዶ በየዛፎች ቅርንጫፍ ላይ ቦግ ብሎ መታየት ይጀምራል፡፡ስለዚህም ነው የምዕራባውያን አገሮች የገና በዓል በሚያክሩበት ወቅት በረዶ ወርዶ መሬቱ፣ዛፍ ቅጠሉና የቤት ጣሪያው ሁሉ ነጭ ካልሆነ ደስ የማይላቸው፡፡ ለምሳሌ የዘንድሮ የ2014 ክርስትማስ በሚከበርበት ጊዜ ከምን ጊዜም ይልቅ በአሜሪካን አገር በረዶ በሚያጠቃቸው እንደነ ሚቺጋንና ዊስኮንሲን መሳለሱ ግዛቶች እንኳ በረዶ ስላልወረደ በዓሉ ደማቅ ቢሆንም የብዙዎች ደስታ ቀንሷል፡፡
ጀርመን 15ኛውና 16ኛ ምዕተ ዓመታት የገናን ዛፍ በውጭ ባሉባቸው ቦታዎች ሄደው ማምለክም ሆነ ዛፉን ወደ ቤት በማምጣት የተለየ ትኩረት ሰጥተው በማምለክ ቀዳሚ ትሁን እንጂ በዓለም ዙሪያ ብዙ አገሮች የገናን ዛፍ የማሳመር ሥርዓት ወጋቸው ካደረጉ ቆይተዋል፡፡ በአንዳዶች ዘንድ እንደ ልማድ የሚደረግ ሲሆን አብዛኛዎቹ ግን ቀጥታ የሆነ አምልኮ ያደርጉበታል፡፡ የጥንት ግጻውያንም ኤራ(Ra) የሚባለውን አምላክ ያመለኩት ሲሆን ይህ አምላክ በጭንቅላቱ ላይ ባደረገው ዘውድ ፀሐይን እንደሚያንጸባርቅ ነበልባል የሚለብስ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በጀርመኖች አምላክ እንደነበረው ኤራም ስለሚታመም ከበሽታው እንዲያገግም ግብጻውያኑ ለምለም ዛፎችን ወደ ቤታቸው አምጥተው የሚያስገጡአቸው ሲሆን ይህ ለእነርሱም በሽታንና ሞትን ድል ያደርግልናል ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡ የጥንት ሮማውያንም ሳቱርን ( Saturin) የሚባል የእርሻ አምላክ ነበሩቸው፡፡ ለዚህ አምላክ የሚሰጡት አምልኮ ሳቱሪናሊያ(Saturinalia) መባል የሚታወቅ ሲሆን የአምልኮ ሥርዓቱ የሚከናወነው መኖሪያ ቤቶችንና ቤተ መቅደስን በለምለም ዘፎች ቅርንጫፍ በማጌጥ ነበር፡፡
ጀርመኖች ፀሐይን አምላክ አድርገው በሚያመልኩበት ወቅት የሰማይና የምድር ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ክርስቲያኖች ደግሞ ነበሩ፡፡ የተሃዲሶ እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ሲሄድ የፕሮቴስታንት መሪዎች በዓለም ያሉትን ለመማረክ ሲሉ መንፈሳዊ ነገርን በዓለማዊ ልማድ ውስጥ እያስገቡ ሰዎችን በወንጌል የመድረስ ሥራ መሥራት ጀመሩ፡፡ ከእነዚህ ተግባራት አንዱ አሬማውያን የሚያከብሩትን የዛፍ አምልኮ ከኢየሱስ ልደት ጋር ማያያዝ ነበር፡፡ የተሃዲሶ አንጋፈው አቀንቃኝ የነበረው ማርቲን ሉተር የቀድሞዋ ጀርመን ሂዳሴ ወቅት በዛፎች ላይ የሻማ መብራት አስቀምጠዋል ተብሎ በመነገሩ ምክንያት ፕሮቴስታንቶች በክርስቶስ ልደት ጊዜ በአሬንጓዴ ዛፎች ላይ ልዩ ልዩ ጌጦችንና የሻማ ብርሃን በማስቀመጥ ማክበር ጀመሩ፡፡ አሬማውያን አዲስ ዘመን የሚቀበሉት ዛፎች ሁሉ ቅጠላቸው በሚረግፍበት፣ እንደነጥድ ያሉት ደግሞ አሬንጓዴ ሆነው በሚቆዩበትና በረዶ በሚወርድበት የክረምት ወራት በመሆኑ በዓላቸውን የሚያከብሩት የፀሐይ አምላክ ታሞና ደክሞ ከተኛበት እስክነቃ ድረስ እነዚህ ዛፎች ችግርን መከራንና መጥፎ መንፈስን ከበራችን ያርቁልናል ብለው ስለሚያምኑ የዛፎችን ቅርንጫፍ ወደ ቤታቸውም አምጥተው በበራቸውና በመስኮታቸው ሲያኖሩ አማኞች ደግሞ በአንጸሩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ የተወለደበትን በዓል በዚያው ጊዜ ያከብሩ ነበረ፡፡ ስለዚህ እነርሱ በበኩላቸው የክርስቶስ የመወለዱ ዜና የሚያውጁበት አደረጉት፡፡ ይህ ሁኔታ በዚሁ እየቀጠለ መጣና ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች ሁሉ ይዛመት ጀመረ፡፡
በመካከለኛው ዘመን የነበሩ ሰዎች የገና ዛፍን በኤደን ገነት አዳምና ሔዋን የበሉት ዛፍ መታሰቢያ አድርገው ወስደውታል፡፡ እንዲያውም በገና ዛፍ ላይ የምንጠለጠለው የፖም( የአፕል ፍሬ) ሔዋን የበላችው የዛፍ ፍሬን ሲወክል በሥሩ የሚበተነው ብሰኩትና ሳሳ ያሉ ወረቀቶች ለኢየሱስ ሞት መታሰቢያ የሚወሰደውን ቅዱስ ቁርባንን ይወክል ነበር፡፡ ይህም የሚደረገው ዛፎች ባሉበት ቦታ ሲሆን የኋላ ኋላ ግን እነርሱም ሌሎች እንደሚያደርጉት ሁሉ ዛፎችን ቆርጠው ወደ ቤት በማምጣት የማክበሩ ሥርዓት ተለማመዱት፡፡ በአብዛኛው ግን የገና ዛፍ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ወቅት ማክበሩ በተለያዩ አገሮች ሁሉ ልምድ እየሆነ መጣ፡፡ የጀርመኗ ንግሥት ቪክቶሪያ ባለቤት የሆነው ፕርንስ አልቤርት በ1848 በዊንዲሰር ካስተል የገናን ዛፍ ካቆመ በኃላ በክርስቶስ ልደት በዓል ወቅት ዛፍ የማጌጥ ሥርዓት ከጀርመን ጀምሮ፣ በእንግሊዝ፣ በካናዳ፣ በአሜሪካና እንዲሁም በሌሎች አገሮች ሁሉ ተስፋፋ፡፡ ጀርመኖች የገና ዛፍ ለካናዳዎች ያስተዋወቁት በ1700 ላይ ነው፡፡ ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ደግሞ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አማካይነት የገና ዛፍ የክርስቲያኖች ልማድ እየሆነ መጣ፡፡ በተለይም ኤድዋርድ ኤች ጆሐንሶን በ1882 በኒው ዮርክ የመጀመሪያውን ገና ዛፍ ላይ የሚንጠለጠሉ መብራቶችን ከተፈላሰፈና በሥራ ላይ ካዋለ በኋላ የገና ዛፍ ድምቀት እየጨመረ ስለ መጣ ጆሐንሰን the Father of electric Christmas tree light የሚል ግጽል ስም ተሰጠው፡፡ በየዓመቱ በአሜሪካን አገር የገና ዛፍ የሚተከል ሲሆን የሚሸጠውም በውድ ዋጋ ሆነ፡፡ አሜሪካኖች በየዓመቱ ከ33 እስከ 36 ሚሊዮን የተፈጥሮ ገና ዛፎች የሚተክሉ ሲሆን በየቤቱና በአደባባይም የሚቆመውን ሁሉ ጭምሮ ከ1.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገና ዛፍን ለማሳመር ሲባል እንደሚባክን ይገመታል፡፡
ይሁን እንጂ የገና ዛፍ የአሬማውያንን ልማድ ወደ ክርስትና ልማድ ለመቀየር በሚደረገው ጥረትና ተሳትፎ እንዲሁም በኤዴን ገነት የነበረው ዛፍ መታሰቢያ ለማድረግ ሲባል ከተፈጠረው ሰውኛ ልማድ በቀር ሌላ ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም፡፡ አሬማውያን የሚያደርጉትን የጣዖት አምልኮ፣ ዘፈን ፣ እንዲሁም ሌሎች ምልክቶች ተጠቅመን የጌታን ማዳን እናውጅ የሚለው ከመንፈስ ቅዱስ ልዩ አመራር ካላገኙ ሰዎችን ወደ ጌታ ከማምጣት ይልቅ ሊያርቃቸው ሁላ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ መዘምራን ሽብሽባ ለእግዚአብሔር ክብር ሀይማኖታዊ የአምልኮ ሥርዓት ቀይረው በዓለም ያሉትን ለመማረክ ሲባል ከመንፈሳዊ መዝሙር ጋር እስክስታ ምንጃርኛ ፣ ጎጃምኛ፣ ወላይትኛ ፣ ጉራግኛ፣ እንዲሁም ሮምኛ ጭፈራዎችን አክለውበታል፡፡ ይህ ለምን ሆነ ለሚል መልሱ ዓለምን ለመዋጀት ወይም ለእግዚአብሔር ክብር ሲባል ነው ይባላል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ጌታ የሰጠን ዜማና ውዝዋዜ ነው ይሉ ጀምረዋል፡፡ ጌታ ከዘፈን ወስዶ ዜማ፣ ከዓለማዊያን ዳንስ ወስዶ ሽብሸባ የሚሰጠው ምን አልቆበት እንደሆነ ምላሹን ከእነርሱ! ከ2 አሥርት ዓመታት በፊት አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጊቢ ባንደራ ሲተከል ከታየ ያቺ ቤ/ክ በፕሮቴስታንቶች ዘንድ ከፓለቲካው ጋር የተቆራኘት ተደርጋ ትነቀፍ እንደነበር ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ባንዳራ የማይተከልበት የፕሮቴስታንት መድረክ በጣም ጥቂት ነው፡፡ አንዳንዶች ምክንያት ኖሮአቸው ሲያደርጉ ሌሎች ደግሞ ሲደረግ ሲላዩና የመድረኩን ድምቀት ለመጨመር ሲባል ያደርጉታል፡፡ ልምምድ ከአንዱ ትውልድ ወደ ሌላው ሲሸጋገር እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሙጥኝ የሚሉት ዓይነት ስለሆነ ነው፡፡ የገና ዛፍም ጉዳይ ልክ እንደዚህ ነው፡፡ ምንም የቅዱስ ቃሉ መሠረት ባይኖረውም የቀደሙት ስላደረጉት ብቻ የሚደረግና ከጎደለም የጌታን ልደት በአግባቡ ያላከበርከው ተደርጎ ስለሚወሰድ ነው፡፡
ምዕራባውያን በክርስቶስ ልደት በዓል ወቅት የገናን ዛፍ የሚያስጌጡት አንዴም ከአሬማውያን አምልኮ ጋር ስለሚያያይዙትና ሌላም ደግሞ ባህላቸው ስላደረጉት ነው፡፡ በአገራችን ግን ዛፍን በጨርቅ በማስጌጥ፣ በሥሩ ጭስ በማጨስ፣ ቅቤም በመቀባት የሚያመልኩበት መጥፎ ነገር እንጂ ጤናማ ልማድ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል የተወገዘ ሰይጣናዊ አሠራር ነው( ዘጸ፡20፡1-3)፡፡ ሰው እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክና ለእርሱ ብቻ እንዲሰግድ እንጂ ሌላ አምላክ እንዲኖረው አይገባውም፡፡
ምዕራባውያን በተለይም አንደ አሜሪካን ያሉ የሰለጠኑ አገሮች ለገና በዓል ጊዜ የሚሸጡ ዛፎች የሚመረቱበት እርሻና በዚህ የተሰማሩ ገበሬዎች ስላላሉ የእርሻ ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ ሲሆን በአገራችን ግን ማንም በየከተማው የቆመውን ዛፍ በመጨፍጨፍ ወደ ቤቱ መውሰድ ነው፡፡ ድርጊቱን ለሚያይ ሰው የዛሬው በዓል ይድመቅልኝ እንጂ ነገ የሚመጣው ጥፋት አይመለከኝም የሚል ትውልድ እየተፈጠረ ያለ ይመስላል፡፡ የክርስቶስን ልደት ስናከብር እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረ በኋላ ይጠብቃትና ያበጃትም ዘንድ በምድር ላይ ካስቀመጠበት ዓላማ ጋር የሚቃረን የዛፍ ጭፍጨፋ ማካሄድ እግዚአብሔርን ያስከብራል ፣ ለሰውም ጥቅምና ደስታ ይሆናል የሚል የቤተ ክርስቲያንም ትምህርት ሆነ የእግዚአብሔር ህግ የለም(ዘፍ 2፡15)፡፡
ሰለዚህ የጌታችንን የኢየሱሰ ክርስቶስን የልደት በዓል በምናከበርበት ወቅት የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሠራሽ ዛፎችን እቤታችንና በቤክርስቲያንችን መድረኮች ብንተክል አናተርፍም ባንተካላቸውም አይጎድልብንም፡፡ ይልቁንስ ሐዋሪያው ጳውሎስ እንዳለ ጌታችን ኢየሱስ በልባችን ይሳል ዘንድ ይገባዋል፡፡ ክርስቶስ በልባችን መሳሉና መተከሉ የእውነተኞች የእግዚአብሔር ሰዎች ምጥና ጭንቀት ስለሆነ እኛም ስለዚያ ልንጨነቅ ይገባናል(ገላ.4፡19)፡፡ ስለ ዛፍም ከተነሳ መልካምን ፍሬ እንደሚሰጥ በወንዝ ዳር እንደተተከለች ፍሬዋም እንደማይረግፍና ቅጠሉዋም እንደማይጠወልግ ዛፍ ፣ ከክፉዎች ምክርና ከኃጢአተኞች ዱለታ የራቅንና በእግዚአብሔር ሕግ ጥዋትና ማታ የምንደሰት ልንሆን ይገባናል(መዝ 1፡1-6)፡፡ ጌታችን በሰው ሠራሽ መብራት የሚሽቆጠቆጥ ዛፍ ሳይሆን እንደ መልካም የወይን ቅርንጫፍ አብዝቶ የሚያፈራ እውነተኛ የክርስትና ሕይወታችንን ይፈልጋል( ኢሳ 5፡1-5፣ ዮሐ.15፡1-7)፡፡ በመጨረሻው ጊዜ የዚህ ምድር ኑሮ ሁሉ አልፎ እግዚአብሔር ላመኑት ያዘጋጀላቸውን መንግሥት፣ ሞት የሌለበት፣ እምባ የማይታይበት ፣ መርገምም ከቶ የማይሆንበት፣ የእግዚአብሔርና የበጉ ዙፋን ያለባት፣ እኛ ባሪያዎችም በግምባራችን ላይ ስሙ ተጽፎ ፊቱን እያየን የምናመልክባት፣ የፀሐይ ብርሃን በማያስፈልግባትና በጉ ኢየሱስ ብርሃን ሰለሆነ ሌሊትና ጨለማ የሌለባት አገር ልንወርስ ተጠርተናል፡፡ በዚህች አገር ቅጠሏ ለሕዝብ ሁሉ መፈወሻ የሚሆን በየወሩ 12 ፍሬ የምትሰጥ የሕይወት ዛፍ አለች( ራዕይ 22፡1-5)፡፡ ይህቺ ዛፍ ያለችበትን ውብ አገር ሊያስወርሰንና መንገድ ሊሆነን ጌታችን ኢየሱስ በመጨረሻው ዘመን ከሕግ በታች ከሴት የተወለደበትን እያሰብን በእውነትና በመንፈስ እናምልከው እንጂ በልማድና በወግ ብቻ አይሁን(ገላትያ 4፡4፣ዮሐ 4፡24)፡፡ የኢየሱስ መወለድም የመጨረሻውን ዘመን የሚያሳይ ስለሆነ የክርስቶስ ዳግም ምጽዓት በደጅ እንደሆነ እናስተውል፡፡ የዘንድሮው የልደት በዓል ብዙዎች የክርስቶስን አዳኝነት አውቀው ሕይወታቸውን ለጌታ እንዲሰጡ አንደበታችን የሚመሰክርበት የተባረከ በዓል ይሁን፡፡ አሜን፡፡