ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!
የነጻነትና የፍትህ ታጋዩ አርበኛው አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ፋሽስታዊ መዳፍ እጅ ከወደቀበት ቀን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በእልህ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት ከበፊቱ በበለጠ ትግላችንን አጠናክረን መቀጠላችን ያሳሰበው ወያኔ ተራ የውሸት ወሬ በሚያወራበት ቴሌቪዥኑ ላይ ለትርጉም በሚያስቸግር መልኩ ቆራርጠውና በጣጥሰው አንዳርጋቸውን ለማስወራት ሞክረዋል።
ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያስቡት በላይ እውነቱን ያውቀዋልና የወያኔ አላማ ከንቱ ሁኖ ግቡን ሳይመታ ቀርቷል፤ በተቃራኒው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ለትግልና ለተቃውሞ ይበልጥ አነሳስቷል።
ስለዚህም ለዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የወጣቶች ክፍል የእንግሊዝ መንግሥት የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ አጽንኦት በመስጠት እና ከወያኔ አረመኔ ቡድን መዳፍ እንዲለቀቅ አፋጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ግፊት ለማድረግ ሰኞ ጥር /ጃንዋሪ 25/2015 ከ14:00_15:00 kl በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል። እናንተም በስዓቱና በቦታው እንድትገኙ በአክብሮት አገራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
በዲሴሶን የወጣቶች ክፍል
No comments:
Post a Comment