Monday, July 22, 2013

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት እና የአንድነት መሪዎች እንደ ጋንዲ!

July 22, 2013
ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
ሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነጻነት የሚለው ስትራተጂካዊ ዘመቻ ግቡ ምን እንደሆነ እና እድሜው ሶስት ወሮች እንደሚሆን አንድነት ፓርቲ ግልጽ አድርጓል። ከመግለጫው እንደተረዳሁት አንድነት ፓርቲ ጊዜ ወስዶ ብዙ አውጥቶ እና አውርዶ ያሰላው ለነፃነት እና ለዴሞክራሲ የሚደረግ ዘመቻ ነው። አንድ ነገር ግልጽ መሆን የጀመረ ይመስለኛል። ከንዋዮች መንግስት ፍንቀላ ጀምሮ ኢትዮጵያችን ለ50 አመቶች ያህል ብዙ ህይወት እየከፈለች በፖለቲካ ስርዓት ለውጥ ትግል ጎዳና ስትወድቅ እና ስትነሳ ከርማ ዛሬ ትክክለኛውን ወደ ዴሞክራሲMillions of voices for freedom - UDJየሚያደርሳትን ጎዳና ያገኘችው መሰለኝ። ወደፊትም መውደቅ መነሳት ሊኖር ይችላል። መንገዱም አልጋ ባልጋ አይሆንም። ይሁን እንጂ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ኢትዮጵያ ትክክለኛውን ጎዳና ማግኘቷን አብስሯል። የዚህ ዘመቻ ስሌት የፖለቲካ ትግል ባህላችንን እድገት ያመለክታል። የስልጣኔም ምልክት ነው። የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ በርቀት ብርሃን አሳይቷል። በዚህ ጉዳይ ላይ ሶስት ተከታታይ ክፍሎች ያሉት ጽሑፍ በማቅረብ የተሰማኝን ለአንባቢ አጋራለሁ። ክፍል ሁለት በሽብር ህግ እና በሽብርተኛነት በታሰሩት የሰላማዊ ትግል ሐዋርያት ዙሪያ ያተኩራል። ክፍል ሶስት ደግሞ ዛሬ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ እና ወደፊት የሚካሄዱ ተመሳሳይ ዘመቻዎችን ከብክለት እና ከውድቀት ለመጠበቅ ይረዳሉ የምላቸውን ምክሮች አንድ ሁለት እያልኩ ለአንባቢ አቀርባለሁ። ክፍል አንድ ግን የፖለቲካ ትግል ባህል ሽግግር በማድረግ ላይ መሆናችንን እንደሚከተለው ያቀርባል።
የትናንቱ እንደሚከተለው ነበር። የገደልን እኛ (The People)። የሞትን እኛ (The People)። የትግሉ እና የድሉ ባለቤት ግን እርስ በርስ ካጫራሱን ቡድኖች ውስጥ በጦርነቱ የቀናው ቡድን ሲሆን የመሰረተው መንግስት ደግሞ የጋራ አገራችንን የግል የጓሮ እርሻው ያደረገ እና ከቀድሞው የከፋ ሽብርተኛ አምባገነን ነው የሚል ነበር የትናንት የፖለቲካ ትግላችን ታሪክ። የትናንቱ የፖለቲካ ለውጥ ትግል ጎዳና በጦርነት የተሞላ ነበር። ብዙ ትምህርት ቤቶች ፈርሰዋል። መንገዶች ወድመዋል። የጦር ካምፖች እና የጦር መኪናዎች ጋይተዋል። ያ ሁሉ የኛ ንብረት ነበር። በህዝባችንም መካከል መቃቃር እና ክፍፍል እያደገ እንዲሄድ በማድረጉ የተወሰኑት ጥለውን እንዲሄዱ እና ከቀረነው ውስጥም ወደ ውጭ የሚመለከቱ እንዲፈጠሩ አድርጎ አንድነታችንን ክፉኛ አዳክሟል የትናንቱ የፖለቲካ መንገዳችን። አዲሱን አምባገነን መንግስት አብዣኛው የአገሪቱ ዜጎች ህጋዊ አድርገው ስለማይቆጥሩት እሱ ስልጣን የጨበጠበትን የመጨራረስ አዙሪት ጉዞ እንድንደግም የሚሰብኩን አዳዲስ ቡድኖች ተፈጥረዋል። የፖለቲካ ትግል ባህላችንም ቢሆን በመገዳደል ደም የተጨማለቀ በመሆኑ የመንግስት ስልጣን የጨበጡት ግለሰቦች ስብዕናቸው የተሟጠጠ ነው። ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ደግሞ በስልጣን ላይ የሚገኙት መሪዎች ፖለቲካ ባህል ከደም መጽዳት እና ስብዕናቸው የተሟላ መሆን ወሳኝ ነው። ባጭሩ ከሶስት ሺ አመቶች በላይ አብሮን የቆየው የፖለቲካ ትግል ባህላችን ከዴሞክራሲ ጋር ጸበኛ ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲኽ ግን ህዝባችን የትናንቱን ደም አፋሳሽ የፖለቲካ ትግል ባህል አዙሪት ሰብሮ በመውጣት አዲስ የፖለቲካ ትግል ባህል ጀምሯል። ይኽ አዲስ ክስተት በትልቁ እውቅና እና ድጋፍ ሊለገሰው የሚገባ የፖለቲካ ትግል ባህል እድገት ምልክት ነው። ስልጣኔም ነው። የሙስሊሙ ማህበረሰብ ከአንድ አመት በላይ በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች ያካሄዳቸው እና ዛሬም የሚያካሂዳቸው በድስፕሊን የታነጹ እንከን የለሽ ሰላማዊ የመብት ትግሎች የፖለቲካ ትግል ባህላችን ማደጉን ያመለክታሉ። መንግስት ለህዝብ ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጥ ጫና ለማድረግ ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን በአዲስ አበባ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ አጀማመር እና አፈጻጸም የፖለቲካ ትግል ባህላችን ሰላማዊነትን እንደመረጠ ይጠቁማል። በተለይ ‘የሚሊዮኖች ድምጽች ለነፃነት‘ በሚል ቀዳሚ መርህ አንድነት ፓርቲ የኢትዮጵያን ሽብር ህግ እዲሰረዝ እና የህጉ ሰለባ የሆኑት የሰላማዊ ትግል ባህል ሐዋሪያት እንዲፈቱ በመንግስት ላይ ጫና ለማድረግ ሐምሌ 7 ቀን በጎንደር እና በደሴ ከተሞች ያካሄዳቸው ሰላማዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች የፖለቲካ ትግል ባህላችን መብሰሉን እና መሰልጠኑን ያመለክታል።
በተጨማሪ ሐሙስ ሐምሌ 12 ደግሞ አንድነት ፓርቲ ከሐምሌ 21 እስከ መስከረም 5 ቀን 2006 ዓመተ ምህረት የሚዘልቁ አዲስ የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ ስምሪቶች ይፋ አድርጓል። እነሱም፥ በወላይታ ሶዶ፣ በመቀሌ፣ በድሬ ደዋ፣ በአዋሳ፣ በአምቦ፣ በደብረ ማርቆስ እና በአዲስ አበባ ያቀዳቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች እና በባህር ዳር፣ በጅንካ፣ በአርባ ምንጭ፣ በአዳማ፣ በባሌ፣ በወሊሶ፣ በፍቼ፣ በአምቦ፣ በጋምቤላ፣ በአሶሳ እና በአዲስ አበባ ያቀዳቸው ሰላማዊ ሰልፎች ናቸው። እያንዳንዱ ዘመቻ ስኬታማ እንዲሆን እራሳችንን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሰራዊት አባል አድርገን የምንቆጥር በሙሉ የተቻለንን ያህል ተሳትፎ ማድረግ አለብን።
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአደባባይ ተቃውሞ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በተካሄዱት ሰላማዊ ትግሎች እርስ በርስ አልተላለቅንም እኛ (The People)። ትምህርት ቤት፣ መንገድ፣ ፋብሪካ አልፈረሰም። ስራ አልተቋረጠም። የአንድነት ፓርቲ መሪዎች ሳይቀሩ በአደባባይ ከህዝብ ጎን ቆመው ሲታገሉ፣ ከህዝብ ጋር ሲታሰሩ እና ሲፈቱ አስተውለናል። አንድነት ፓርቲ አንድ የፓርላማ አባል (ግርማ ሰይፉ) ብቻ ቢኖረውም ካለምንም ስስት እሱንም በደሴው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አሰማርቶት ነበር። እንግዲህ በአለማችን ታዋቂዎቹ የሰላም ትግል መሪዎች እነ ጋንዲ፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ እና ሌሎችም ሌላ ምን አደረጉ? ያደረጉት ይኽንኑ ነበር። ከህዝባቸው ጋር እየታሰሩ እና እየተፍቱ መታገል። የሰላማዊ ትግል መሪዎች ከትግሉ ሂደት ውጭ አይሆኑም። ግባቸው እራሳቸውን መረማመጃ አድርገው ህዝቡን የአገሩ እና የስልጣን ባለቤት ማድረግ ነው። ይኽ የሰላማዊ ትግል ባህል ህዝብን ከማቀራረብ አልፎ የትግል እና የድል ፍሬ ባለቤት ያደርገዋል። ህዝብ መሪዎቹን በቀርብ እንዲያውቃቸው ያደርጋል። እንደ ትጥቅ ትግል የእውቀታቸው እና የአዕምሮዋቸው ጤንነት ደረጃ የማይታወቁ ካለ ህዝብ ተሳትፎ ብድግ ብለው አገር የሚያፈርሱ እንደ መለስ ዜናዊ አይነት መሃይም እና ንክ (እብድ) የትጥቅ ትግል መሪዎች ገዢዎቹ አይሆኑም። አዎ! መሐይም። አዎ! ጥራዝ ነጠቅ ነበር። የአልቤንያ እና የሲቪየት ህብረት አምባገነኖች የጻፉትን የፖለቲካ መመሪያ ቃል በቃል ገልብጦ ኢትዮጵያ ላይ በመድፋት የኢትዮጵያ ህዝብ በሽብር አስፈራርቶ አመራሩን እንዲቀበል ማድረግ አዋቂ መሪ አያደርግም። በአውሮፓ ከተሞች ስለ አየር ጸባይ በእንግሊዘኛ ቋንቋ መናገርም ብቻውን አዋቂ መሪ አያደርግህም። ተሳዳቢነት እና አጭበርባሪነትም አዋቂ አያደርግህም። የአዋቂ መሪ መስፈርቱ ሌላ ነው። የራስን አገር ህዝብ ታሪክ ሳትንቅ በጥልቀት አጥንተህ እና አውቀህ፣ ኢትዮጵያዊ የሆነ የአመራር አሳብ አመንጭተህ፣ ከተቃዋሚዎችህ ጋር አብረህ መስራት ችለህ፣ ቀደም ባለው ታሪካችን የተፈጸሙ ስህተቶችን አርመህ፣ ህዝብን አግባብተህ እና አቀራርበህ ፊቱን ወደ ዴሞክራሲ እና እድገት እንዲመልስ ማድረግ ከቻልክ ብቻ ነው ምናልባት አዋቂ መሪ የምትባለው። መለስ ዜናዊ ግን ችግራችንን አባብሶ ሄደ። የሆነው ሆኖ በጎንደር እና በደሴ እንዳስተዋልነው የአንድነት ፓርቲ መሪዎች እንደ ጋንዲ በህዝባቸው መካከል ሆነው መብት እንዲከበር ታግለዋል። ይኽ ሁኔታ ህዝባዊ ስብዕናቸው እንዲያድግ እንጂ እንዲሟጠጥ አያደርግም። የፖለቲካ ባህላቸውም ከገዳይነት ደም የጸዳ እንዲሆን ያደርጋል። በዚህ አይነት የትግልም ሆነ የድል ባለቤት የሚሆነው እራሱ ህዝቡ ነው። ማለትም በምርጫ የመንግስት ስልጣን ባለቤት የሚሆነው እራሱ ህዝቡ ነው። ስለዚህ ሰላማዊ ትግል እና ዲሞክራሲ የማይነጣጠል ዝምድና አላቸው።
ወሳኙ የውስጥ ትግላችን ነው። ዜናዎች እንደሚያመለክቱት የአውሮፓ ህብረት፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂውማን ራይትስ ዋች፣ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ሳይቀሩ በኢትዮጵያ ውስጥ መብት ለማስከበር እየተካሄደ ባለው በሳል እና እንከን አልባ ሰላማዊ ትግል ተደንቀዋል። ድጋፋቸውን ለግሰዋል። እየተጠናከረ በሄደ ቁጥር ትግሉ የሚያገኘው ድጋፍ እንደሚጨምር አትጠራጠሩ። እንግሊዝ እና አሜሪካም ለምነውን የሚደጉን ቀን ቅርብ ነው። ወሳኙ የውስጥ ትግላችን መጠናከር እንደሆነ ለአንዲት ደቂቃ እንኳን እንዳንዘነጋ።
ስለዚኽ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ የምንኖር የሰላም ትግል ሰራዊት እና የዴሞክራሲ አርበኞች ኢትዮጵያውያን በመካሄድ ላይ ያለውን አገር አቀፍ የሚሊዮኖች-ድምጽ-ለነፃነት ዘመቻ በሙሉ ልብ መደገፍ እና መሳተፍ አለብን። እያንዳንዱን ዘመቻ ለማደራጀት (ለማዘጋጀት እና ለማኪያሄድ) ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ግልጽ ነው። የገንዘብ እርዳታ በማድረግ የዚህ ታላቅ የፖለቲካ ባህል ለውጥ ታሪክ አካል እንሁን! ነፃነት ገፋፊው የሽብር ህግ እንዲሰረዝ እና የህጉ ሰለባ የሆኑት የሰላማዊ ትግል ሐዋሪያት እንዲፈቱ በመንግስት ላይ ጫና ለማድረግ በተጀመረው ዘመቻ ካለ ምንም ስስት እንሳተፍ። በአሳብ ወይንም በገንዘብ! በተለይ በውጭ ያለን ዜጎች ዘመቻውን በገንዘብ በመርዳት ኢትዮጵያ በመስራት ላይ ባለቸው ታሪክ ላይ ማህተማችንን እናስቀምጥ!
በክፍል ሁለት እንገናኝ

ይድረስ ለክቡር ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

July 22, 2013
በዘውገ ፋንታ
Seattle, U.S.A
በዚህ ሐምሌ ወር (2005 ዓ/ም) የጻፉትን እንደተለመደው በጉጉት ማንበብ ጀምሬ በመንሰፍሰፍ ጨርሻለሁ። መልዕክቶችዎ ብዙ ዘመን የሸፈናቸውን ትዝታዎች እንዳስታውስና ብዙ ትውስቶችን እንዳሰላስል አድርጎኛል። ብዙ ሆድ የሚያባቡ ሃሳቦች ነበሩ። የአብዘኽኘው ሰው ስሜት እንዴት እንደሆነ ባላውቅም፣ ሁላችንም ያለንበት ጀልባ አንድ፣ ያለንበት ባሕር አንድ፣ ጉዞአችንና አቅጣቻችን እንዲሁ አንድ ነው ብየ ስለማምን ያንዱ ስሜት የጋራ ነው ብዬ ገምቻለሁ። ሆኖም በዚያ የተነሳ ይህን ጽሑፍ ስጽፍ የግል ስሜቴ እንዳይለውጠው ጥንቃቄ አድርጌአለሁ። የቀረ እንክርዳድ ሃሳብ ምንጊዜም ስለማይጠፋ፣ ስለሱ አስቀድሜ አንባቢን ይቅርታ እጠይቃለሁ። በ”መንሰፍሰፍ” ያልኩት ቃል ለየት ያለ ይመስል ይሆናል። ክቡርነትዎ ያስተላለፏቸው መልዕክቶች የሚያስፈሩ፣ የሚያባቡና የሚያርበተብቱ ይሁኑ አይሁኑ ለይቸ ለማወቅ ተስኖኛል። ፍራቻና መባባቱም ቅጥ አጥቷል። ሆኖም ግን፣ አሜርካ ውስጥ ስለምኖር በዕርግጥ ፍራቻ አላውቅም። ስለ ሀገራችን መውደቅና መጥፋት ሳስብ የምለውና የማስበው ዝብርቅርቅ ያለ ይሆናል። ለሞት ስንቅ ቢኖረው የኔንና የሌላውን ከምሬ ነበር።
የክቡርነትዎ ጽሑፍ ብዙ አሮጌ ዐመቶች የሽፈኗቸውን የጥንት አጋጣሚዎች አስታውሶኛል። ከታወሱኝ መካከል  አንዱ ጎልቶ የታወሰኝ ይህ ነበር። በእንግሊዝ ሀገር ስኖር፣ በለንደን ከተማ ወጣ ባለች ቤተመንግሥት የልዑል መሥፍን አለማየሁ ቴዎድሮስ አፅም የተቀመጠበትን ቦታ እንድጎበኝ አንድ እንግሊዛዊ ሰው ወሰደኝ። በዚያን ጊዜ የተሰማኝን ደስታ በትክክል ለመግለጽ ቃል ያጥረኛል። ከዚያ በፊት አባቱ አፄ ቴዎድሮስ የቆሙባትን ቦታ መቅደላን አይቸ ነበር። ንጉሡ በተንጓለሉበት ቦታ ላይ ቁሜ በታሪክ ያነበብኩትን እያስታወስኩ ሳስብ የተሰማኝ ስሜትና የልጃቸው አፅም ባረፈበት ቦታ ላይ ቆሜ  ሳሰላስል የተሰማኝ ስሜት እጅግ የተለያየ ነበር። የልዑል መሥፍን አለማየሁ ፎትግራፍ በእንግሊዝ ነገሥታት ፎቶግራፎች መካከል ተቀምጦ ሳይ የተሰማኝ ኩራት ወደር የሌለው ነበር። ፎቶግራፉን አይቸ የማልጠግበው እንደሆነብኝ ትዝ ይለኛል። ደስታየን እንድካፈል እንደኔ የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ባጠገቤ ባለመኖሩ አወራጭቶኝ ነበር። ልዑል መሥፍን አለማየሁ አድጎ ምን እንደሚመስል ማወቄ እራሱ ጉድ ታሪክ ሆነብኝ። ግን ብዙ ሳልቆይ እበሳጭ ጀመርኩ። ስለ እሱ የተጻፉትን ታሪኮች እየተጠያየኩ መሰብሰብ ጀመርኩ። የታላቁ ንጉሥ ልጅ አፅም በባዕድ ሀገር መኖሩ ጥያቄ አሳደረብኝ። እስከመቸስ በባዕድ ሀገር ተቀብሮ ይኖራል እያልኩ ለረጅም ጊዜ ሳሰላስል ቆይቻለሁ። የልዑል መሥፍን አለማየሁን ብዙ ውጣ ውረድ፣ መንገላታት፣ ብቸኝነትና በመጨረሻም አሟሟቱን አንብቦ የማያለቅስ፣ የማይጸጸትና የማይበሳጭ ኢትዮጵያ ይኖራል ብዬ አላምንም። እንዲህ ማለቴ ከአርባ ዓመት በፊት በነበረው የኢትዮጵያ ሰው ልቦና አንጻር ነው።  ልዑል መሥፍን አለማየሁ ብዙ ነገሮችን ናፍቆና አምሮት እንደሞተ ግልጽ ነበር። ስለ እሱ የተጻፉት ታሪኮች አንድንዶቹ የዕውነቱ-ደበና ቢሆኑም አለመታደሉን ያስረዳሉ። የሀገሩ እሸት፣ ቋንጣ፣ ቆሎ፣ ዳቦ፣ ፍትፍቱ፣ ቅራሪና ብርዙ፣ የለመደው ምግብና መጠጥ ሁሉ ናፍቆት መሞቱ አያጠራጥርም። ከዚያም በላይ መጫወቻ ግቢው፣ ሜዳው፣ አየሩ፣ እንስሳው፣ መንደሩን እና ያገሩን ሰው እየናፈቀ እንደሞተ ወይም ናፍቆት እንደገደለው ለመረዳት አይከብድም። በልዑል መሥፍን አለማየሁ ቴዎድሮስ ከደረሰው ግፍ፣ በኢትዮጵያኖች ላይ አሁን ባለንበት ወቅት ባገራቸውና በባዕድ አገሮችም እየተካሄደ እንደሆነ እያንዳንዳችን ምስክር ነን።
ሌላው ትዝታ ብዙ ነገሮችን ያፈራርቃል። ክቡርነትዎ ደሴ መጥተው የሁለተኛ ደረጃ ማለፊያ ፈተና ሲያካሂዱ አንዱ ተፈታኝ ነበርኩ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እርስዎን አውቄአለሁ። ከዚያም ካርታ ድርጅት ሰሰራ፣ ወዳጆችዎ፣ ክቡር አምባሳደር ኃይሉ ወልደማርያምና ክቡር አቶ ታየ ረታ፣ “መስፍን ካርታዎች ይፈልጋልና ሂድህ የሚፈልገውን ጠይቅና ሰርተህ ስጠው” እየተባልኩ፣ ከእርስዎ ቢሮ እየመጣሁ ብዙ የተለያዩ ካርታዎች በተለያዩ ጊዜ እያዘጋጀሁ ሰጥቸዎታለሁ። ቢሮዎንም አስታውሳለሁ። እንደተባለው በር ይኑርና አይኑረው የማይታወቅና ዝው ተብሎ የሚገባበት ነበር። እርስዎን በውስጧ ላላየ ሰው፣ የዕርስዎን ቢሮ (አዕምሮ እንደሚገምተው አይነት) ሲፈልግ ውሎ ይመሻል እንጂ አያገኛትም ነበር። የት ነው ብሎ ለሚጠይቅ ሰው ግን መልሱ “ምን ሁነሀል? ወደዚያ ሂድ፣ ታገኘዋለህ!” የሚል ነበር። መጽሐፉና የተጠቀለለው ወረቀት መደርደሪያውዎቹን ሞልቶ በዕግርዎ ስር ተከምሮ ነበር። ይኽ በጥንት ጊዜ ከአርባ ዓመት በፊት የነበረውን የሚገልጽ እንጂ ከዚያ በኋላ ትንሽ ቤተመንግሥት የሆነውን የሚያመለክት አይደለም።  የኢትዮጵያና የአዲስ አበባ ከተማ በብዙ ቀለም የተሰራ ካርታ አሳትሜ ስለነበር ለእርስዎና ከእርስዎ ቢሮ ብዙ ጊዜ ቆመው ለማያቸው ፕሮፌሰር (ስማቸውን ዘነጋሁ) ስሰጣችሁ፣ ሁለታችሁም አድንቃችሁ በጣም ጥሩ በርታ ብላችሁኝ ነበር። ከዚያ በኋል አላየሆትም፤ ተቻኩየ አገር ጥየ ወጣሁ።
ቀጥየ፣ እርስዎ የሚጽፉትን፣ የሚናገሩትንና ስለእርስዎ የሚነገረውን የኢትዮጵያ ታሪክ አካል የሆነውን በታላቅ ስሜት እከታተል እንደነበር ለማመልከት እፈልጋለሁ። በዚያን ወቅት በተማሪዎችና በሰራተኞች ደምቀውና ጎልተው ከሚዘወተሩት ቡና ቤቶች አካባቢ የሚነፍሱ ብዙ ፌዞች ነበሩ። አንድ ድርጊት ሲፈጠር፣ በሚቀጥሉት ቀኖችና ወሮች ጉዳዩ መሰረቱን ስቶና ተለውጦ በአስቂኝ ፌዝ ተደለባብሶ ይነገራል። አሁን ሳስበው፣ አዲስ አበባ የዓለም ፌዝ  መናገሻ መባል ይገባት ነበር እላለሁ። ለፌዘኞች የሹም-ሽረት ወቅት ትልቅ ዓመትበዐላቸው ነበር። በአንድ ሹም-ሽረት ወቅት፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ለምን ፕ/ር መስፍንን የአንዱ ምንስትሪ ምንስትር አልሆኑም እያለ ይጠይቅና ያወሳ ነበር። በ’ሹም-ሽረት” ዋዜማ ሕዝብ የሚሾመውንና የሚሻረውን አስቀድሞ(የራሱን ምርጫ ይሆናል)ማናፈስ ይጀምራል። ብዙው ትችት የፖለቲካ ‘አሳስኔሽን’(ግድያ) ቢባል ተገቢ ነበር። በማግስቱ ደግሞ“ተሻረ” ወይም “ተሾመ” የተባለው ሳይሆን “ተረሳ” ወይም “ተረሱ” የተባሉት ሰዎች ስም ነበር የሚወሳው። በዚያ ጉዳይ ቆሽታቸው የተነካ ወይም የቆሰለውን የሚያውቁ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሁም በዲ.ሲ ከተማ በህይዎት እንዳሉ እገምታለሁ። ኢትዮጵያኖች ንጉሡ ለምን ፕ/ር መስፍንን የትምሕርት ምንስትር ወይም ሌላ ከፍተኛ ስልጣን አልሰጧቸውም እያሉ የሚጠይቁ ብዙ ቅን ሰዎች ነበሩ። ለዚያ ጥያቄ መልስ የሚነገረው ብዙ ነበር። አንድ መጥቀስ የምሻው አለኝ። እሱም ስለ አማርኛ ቋንቋ ጥልቀትና የአዲስ አበባን ሰው እንደ አቅሙ አቻችሎ ያኖረ የምንግሥቱ ሕጎች ሳይሆኑ የአማርኛ ቋንቋ ነብር ብዬ አምናለሁ። አሁኑ ተበልዞ ጣዕሙን ያጣውን ደረቅ ዐይነት አይደለም። ስገምተው አሁን ሕዝብ መግባቢያ ቃሎቹ “እምቢ! አላውቅም!እንጃ! እንደፈለግህ!” ይመስሉኛል። በዚያን ጊዜ የሚነገረው አማርኛ፣ ሕዝብ እንዲሳሳቅ፣ አንዱ ሌላውን እንዲያስገርም፣ ሰለልተኛው እንዲነቃና እንዲያሰላስል የሚያደርግ ነበር ብየ ብናገር፣ በዚያን ጊዜ የነበረው ትውልድ ምስክሬ ይሆናል ብዬ  እተማመናለሁ። ክቡርነትዎ ለምን እንዳልተሾሙ ይወራ የነበረው ምክንያት ከጥሩ አፍ እንደሰማሁት፣ እርስዎን ለማሾም ንጉሡ ፈቃዳቸው እንዲሆን ሲጠየቁ፣ ንጉሡ “እኛ እሱን አንሾምም!” በማለት እምቢ ስላሉ ነው ተብሏል። “ባይሆን የትምህርት ምንስትር  እንዲሆኑ ግርማዊነትዎ ይፍቀዱ” ብለው ሲማለዱ፣ ንጉሡ “ለሱ ሹመት ወይስ ሽረት? የቱን አስባችሁ ነው?” የሚል መልስ ሰጧቸው ይባላል። በምንሊክ ቤ/መ  አካባቢ በይበልጥ በአንዳንድ ቦታዎች የሚነገር እንደነበር አስታውሳለሁ። ይህን የሚያውቁ ወይም የሰሙ “አዎ፣ ተብሏል” የሚሉ ከዚህ በዲ.ሲ በአዲስ አበባም እንደ አሉ አምናለሁ፤ እግዜአብሔር ያቆያቸውና ይመሰክራሉ። የንጉሡ ንግግር አስተርጓሚ ወይም ማብራሪያ በተለይ ለቀ.ኃ.ሥ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደሚያስፈልጋቸው ይነገር ነበር። ንጉሡ “እኛ እሱን አንሾምም!” ያሉበትን ምክንያት አዋቂዎች ሲያብራሩት፣ የርስዎ ቢሮ ያልተደነገገችና መስፈርት ያልተደረገላት ስልጣን ናት ማለታቸው ነበር ተብሏል። ቀጥለውም ነጉሡ “ሹመት ወይስ ሽረት?” በማለት የጠየቁት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ የነበርዎትን ሰፊ ስልጣን አሰመልክቶ ነው ተብሏል። የተባለውን ቃል በቃል ለማንጸባረቅ ጥሬአለሁ። በሌላ መስካሪዎች ቃሎቹ ተሻሽለው ቢቀርቡ አሚን ብየ እቀበላለሁ።
መጀመሪያ አዲስ አበባ ስመጣ የዘጠኝ ዓመት ልጅ ነበርኩ፣ ብዙ ያስደንቁኝን ሁሉ ከዚህ ባላሰፍርም፣ ትቂት አስገራሚ ሆነው የታዩኝን ለመግለጽ፣ የአቡነ ጴጥሮስና የምንሊክ ኃውልቶች ዋናዎቹ ነበሩ። ቀኑን ሙሉ ከሀውልቱ ግርጌ ቁጭ ብየ እያንጋጠጥኩ እያየሁ ብውል የምጠግበው አልነበረም። የአዲስ አበባ የሰፈር ስም ብዛት እያስገረመኝ እንደ ኢትዮጵያ ‘ጂዖግራፊ’ ማጥናት ጀምሬ ነበር። የአዲስ አበባን ካርታ ስሰራ ያጠናኋቸው ስሞች ረድተውኛል ብል ትክክል ነው። ኋውልቶቹ፣ የመንገዶቹ፣ የአደባባዩና የሰፈሮቹ ስሞች በኢትዮጵያ ታላላቅ ጀግኖችና ንጉሦች ስመ የተሰየሙ ስለሆኑ፣ አዲስ አበባ የታሪክ ገጾች ሆኖ ትታየኝ ነበር። ወደር የማይገኝላቸው የነዚያ ታላላቅ ጀግኖችና ሰማዕታት ስምና ታሪክ አብሮን የሚኖር በየቀኑ የሚታወሱ አድርጓቸዋል ቢባል ከዕውነት የራቀ አይሆንም። የሁሉም ጀግኖች ኃውልቶች በየሰፈሩና አደባባዮች ቁመው ቢታዩ የአዲስ አበባ ገጽ እንዴት በይበልጥ ባማረ! የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነቱን መልሶ ሲቀዳጅና መንበረ መንግሥቱን በእጁ ሲይዝ ለጀግኖቹ ውለታ ብቻ ሳይሆን፣ ለራሱ ክብር ሲል ማስታወሻ ኃውልታቸውን እንደሚያዎም አልጠራጠርም።
በኢትዮጵያኖች ላይ የደረሰው ግፍ፣ በማናቸውም ሕዝብ በቀላሉ ሊፈጸም የማይችል ነው። የዓለም ሕዝብ ሊቀበለው የምይችል፣ ለዚያም በላይ ለሰብዐዊ መብት ሲል ተገዶ የሚወስደው ዕርምጃ ነበር። አለመሆኑ፣ “ልጁ ቀማኛ አባቱ ዳኛ” የሚባለውን እስስር ሁኔታ በግልጽ አሳይቶናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያውቀው ረቂቅ ሴራ ወራሪን የሚቋቋምለትንና ከተገዥነት የሚያድነውን አካል እንዲያጣ ተደረገ። የሀገርና የሕዝብ ሰንሰለቶች በረቀቀ የሴራ ስልት ተበጣጠሱ። ከታች እስክላይ የነበረው የአስተዳደር ድርብርብ በዘዴ ተናደ። የተረፈው ዳግም እንዳይነሳ በተቀደደለት በር ወደ ውጭ ጎርፎ እንዲወጣ ተደረገ። ለማዳን ከተባለ ይሁን። እስራኤልም የተፎከረበትን የአማራ ሰው ለማዳን ጎትታ አውጥታለች። ኢትዮጵያ ወገኗን በህይዎት ልትጠበቅ ስላልቻለች፣ የቀረው ለመኖር ሲል በዓለም ዙሪያ ተሰደደ። ያረገጠው ምድር የለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የዘመኑ እስራኤሎች (አይሁዶች) ሆነዋል። ምክንያቱና መነሻው አንድና ተመሳሳይ ነው። የተሰደዱት ኢትዮጵያኖች ባረፉበት ምድር ሁሉ ሌላ ፈተና እንደሚገጥማቸው ግልጽ ነበር። ገዳይን ቢሸሹ ከሌላ መከራ አራቁም። ብዙዎቹ ለአስከፊ ግፍ ተዳርገዋል። በውጭ የሚኖርቱ ከናት ሀገራቸው ጋር ያለውን  የባህል፣ የቋንቋና የኃይማኖት እስስር እንዳይቋረጥ በያሉበት በአላቸው አቅም እየሞክሩ ነው። ግን፣ በሄዱበት ተከትሎ የሚሄድ ጣጣ አለ፣ ከዚያም በላይ ኢትዮጵያን የሚገዛው ጨቋኝ ኃይል፣ ስደተኞችን እየተከታተለ ባሉበት ሀገር ኑሮአቸው እንዲናጋ ለማድረግ የሚፈጽመው ሴራ ሊላ እጅግ አስጊ ሁኔታ ፈጥሯል። ብዙ የተንገላታ ሰው በቆየ ህመም በድንገተኛ ሞት እየተቀጨ የሚያልቀው ቁጥር ብዙ ነው። አንድ ሰው የዕድሜውን መጨረሻ ሲረዳ፣ አገሩ እንዲቀበር ምኞቱን ይገልጻል። ወይም ወዳጆችና ጎደኞች አስበው ሬሳው በውድ ሀገሩ እንዲያርፍ ያደርጋሉ። ሆኖም በአረፈበት ሀገር መቅበር እየተለመደ ነው። ኢትዮጵያኖች ሲሰደዱ በወንዝና በባህር ውስጥ ሰምጠው፣ በበርሃ ሲጓዙ ተርበው፣ ተጠምተው፣ ታመውና በአውሬ ተበልተው ያለቁ መቃብር ቀርቶ ያልተለቀሰላቸው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ናቸው። የጠፉት ሰወች አባቶች/እናቶችና አያቶች በቆረቆሯቸው ከተሞች ውስጥ እንዳይኖሩ ሲባረሩ፣  የአረመኔዎቹ መሪ ይህ በማይባል ልቅሶና ዳንኪራ ተቀብሯል። የት? ከአያቶቻቸው ጎን! እንደውም በዚችው መናገሻ ከተማ ኃውልቱ እንዲቆም ታስቧል!
ክቡር ፕ/ር መስፍን፣ ሸሽተናል፣ ሀገር ጥለን ሄደናል። ሆኖም በህይዎት ወደ ሀገሩ ተመልሶ ለመኖር የማይመኝ ሰው ካለ ጣት ይቁጠረው። በውጭ የሚኖር ሰው ሬሳው በሀግሩ እንዲያርፍ መጠየቁ ይህን ምኞቱን ያመለክታል። ሕዝብ ታሪክ የሆነውን ምግባርና ድርጊት አመዛዝኖ ያውቃል። አንድ ሰው የራሱን ኑሮና ህይወት ሰውቶ ለወገኑና ለሀገሩ ጥቅም ታላቅ ምግባር ሲፈጽም፣ ሕዝብ በበኩሉ ለታሪክና ለትውልድ ጥቅም ሲል የጀግኖችን ስምና ታሪክ ወርሶ የሀገሪቱ ቅርስ ያደርጋል።

Thursday, July 18, 2013

orway will maintain its international obligations and have a humane refugee and asylum policy!!!

Posted: July 18, 2013 in Human Rights
0
11
Amnesty International is concerned that Norway will maintain its international obligations and have a humane refugee and asylum policy.
CHALLENGES IN NORWAY
The government and political parties in Parliament have used expressions as a ‘fugitive power’ and thus given a false impression that Norway virtually flooded with refugees.
Amnesty is very critical of how many politicians choose to communicate attitudes and views on refugee and asylum policy in Norway. Politicians helps to discredit asylum seekers for example by using the term ‘fortune hunters’.
This undermines respect for the individual applicant and the UN Refugee Convention .
Government and opposition parties claim constantly that the vast majority of the refugees who come to Norway not bring identification documents or provide their identity. This is true in most cases.
According to the Directorate of Immigration (UDI) has very many of those seeking asylum identification papers and 93 percent of those who received asylum in 2011 had confirmed or probable his identity during the processing of asylum applications.
REFUGEES IN NORWAY
The actual number of people who have fled their homes in the world today is in great contrast to the number of refugees seeking asylum in Norway.
More than 16 million people are displaced outside their own country. Of these, in 2011 9100 who sought asylum in Norway. That means it is 0.06 per cent of the world’s refugees find their way to Norway and seeking protection here.
WHERE SEARCHING FLUKT?
Stricter rules has led to the term ‘European fortress’ is often used to describe how difficult it has been for a refugee seeking asylum in a European country.
The majority of the world’s refugees come from Asia and Africa, and the vast majority of refugees seeking refuge in neighboring countries. These are often countries with great poverty, yet still receives millions of people in need of protection.
Amnesty POSITION Accepting refugees and asylum seekers is about rights and obligations, not volunteerism and charity.According to the UN Refugee Convention and the Universal Declaration of Human Rights of people who are persecuted or life is in danger due to war and conflict the right to apply for asylum in another country.Amnesty believes that Norway as a minimum should follow the recommendations of the UN High Commissioner for Refugees (UNHCR). When the government chooses to act contrary to UNHCR’s recommendations by showing that you follow Norwegian law, it creates an artificial and dangerous contradiction between international obligations and so-called Norwegian law. It is unprincipled and opportunistic political voice picking. WHAT DO AMNESTY? we are consultative body on proposed amendments to the Immigration Act, the meetings with the authorities, and petitions against the Norwegian practice or on behalf of individual asylum seekers. We also participate actively in the public debate. Amnesty working closely with several asylum lawyers and help with documentation on the land situation in a number of asylum cases. In particular asylum requests Amnesty expert witness when the matter is taken to court. Exceptionally, we follow individual cases through the application process if we see that it is of fundamental importance

ግልጽ ደብዳቤ ለሃይሌ ገብረሥላሴ (ከአበበ ገላው)

July 18, 2013
ከአበበ ገላው
ውድ አትሌት ሃይሌ፣ ከነመላው ቤተሰብህ እንደምን ከርመሃል? ልጆቹ እንዴት ናቸው፣ አለምስ እንዴት ሰንብታለች?
ሰሞኑን የወዳጅ የዘመድ ምክር አላዳምጥ ብለህ እንደነ ጋሼ ግርማና ጋሼ ሃይለማርያም ደሳለኝ የህወሃቶች አሻንጉሊት መሆን እንዳማረህ ስሰማ በጣም ተገረምኩ። በመላው አለም ዝና ያተረፍክበትን እሩጫ ትተህ “ቤተመንግስት” ወይንም “ፓርላማ” ቁጭ ብለህ ዝንብ ማባረር ምን ይጠቅመኛል ብለህ ነው? አንተም እንደነጋሼ ግርማና ሀይለማሪያም በቁምህ ከመሞትህ በፊት ምክሬን ባትሰማ እንኳን ለማንኛውም ይቺን አጠር ያለች ጦማር ልጽፍልህ ወሰንኩ።
Open letter to Haile Gebreselassieእኔ ያቺን “ሪከርድ” የሰበርክባትን ቲሸርት ነፍሳቸውን ይማርና ለዛ ህዝብ ላፈኑ፣ ላሰቃዩ፣ ለረገጡና ለጨረሱ፣ እንኳን በቁማቸው ሞተውም ላስመረሩን የሂትለርና የሞሶሊኒ ግልባጭ በአደባባይ ስትሸልም መካሪ ማጣትህን ገምቻለሁ። ግለሰቡ መሸለም ሳይሆን ተይዘው እንደ ናዚዎቹ ኑረንበርግ ለፍርድ መቅረብ ይገባቸው እንደነበር ጠፍቶህ ነበር ማለት አይቻለኝም። ግን ሃያሉ ፈጣሪ ፍርዱን እንደማያዘገይ አሳየን።
ከሁሉ የገረመኝ ደግሞ ልክ እንደ ህወሃት ካድሬዎች በኢቲቪ ቀርበህ “ታላቅ መሪ” አጣን እንባ አዋጡ እያልክ ካሜራ ፊት እንባ ስትጨምቅ ማየቴ ነበር። ያቺን የዋህ ደራርቱ “ለኛ ብሎ ታገለ፣ መስዋት ሆነ፣” ምናም እያለች ስታነባ በኢቲቪ ሳይ አንተ ሳታሳስታት እንዳልቀረህ በልቤ ገምትኩ። ከተሳሳትኩ ይቅርታ!
ውድ ሀይሌ፣ በህዝብ ዘንድ መከበርና መወደድ በቢሊዮን ዶላር እንኳን እንደማይገዛ ከቱጃሩ አላሙዲን መማር ይቻላል። ቱጃሩ አላሙዲን ሰሞኑን ወደ ዋሽንግተን ከአስር አመት በሁዋላ ሲመጡ የተከራዮት ታላቅ እስታዲየም በህዝብ ይጨናነቃል ብለው ጠብቀው ነበር። ይሁንና ነበር ባይሰበር ሆነና ነገሩ ያን ያሚያህል ስታዲየም እንኳን ሰው ወፍ ዝር ሳይልበት እንደሰማነው ከሆነ አራት ሚሊዮን ዶላር የፈሰሰበት ድግስ ከንቱ ቀርቶ የሚበላው ጠፍቶ ተደፋ:: ቱጃሩም በሃፍረት ተሸማቀው መሰወራቸውን ስነግርህ በታላቅ ሃዘን ነው። ይህ ቱጃር በህዝብ ዘንድ ምን ያህል የተከበሩና የተወደዱ እንደነበር፣ የዛሬን አያድርገውና፣ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ሁሉ አልሳካ ቢላቸው ምስኪኑ ቱጃር ከሩቅ ሆነው አፋችንን ለማዘጋት እየዛቱ ነው። ዝርዝሩን ሰሞኑን አጫውትሃለሁ::Sheikh Mohammed Hussen Alamudi
ቱጃሩ ድንገት በምርጫ 97 (ዝ)ንባቸውን በኩራት ደረታቸው ላይ ለጥፈው “ለህወሃት እሞታለሁ እያሉ ያዙኝ ልቀቁኝ” አበዙ። አስተዋዩ ህዝባችን ፊቱን አዞረባቸው። በቃ፣ ያሁሉ ቢሊዮን ከንቱ መሆኑ ታየ። ገንዘባቸውም አድናቂ አጣ፣ እርሳችውም ክብር እና ፍቅር በገንዘብ እንደማይሸመት ተረዱት። ዛሬ የሚያጅቧቸውም ጥቂት ግለሰቦች እርሳቸውን ሳይሆን ገንዘባቸውን ያፈቀሩ መሆኑ ያደባባይ ሚስጥር ነው። በዚህ በክፉ ቀን ህዝብን ከከዳህ ቀባሪህ ጅብ እንጂ ሰው አይሆንም።
ወደ ተነሳሁበት ቁም ነገር ልመለስና ስለምኞትህ ትንሽ አስተያየት ልሰንዝር። ከሚድያ መረዳት እንደቻልነው ሁለት ምኞቶች አሉህ። አንደኛው የመቶ አለቃ ግርማን መቀመጫ መረከብ ሲሆን ሌላው ደግሞ የፓርላማ አባል ለመሆን ነው። እኔንም የገረመኝ የምኞቶችህ ከንቱነት ነው።
እንደምታውቀው “ፕሬዚዳንት” ተብሎ የሚሰየመው ሰው የህወሃቶች አሻንጉሊት ሆኖ ዋና ስራው እንግዶች መቀበልና መሸኘት ነው። ዶሮን ሲያታልሏት ሆነና ነገሩ አቶ መለስ ይህ “ስልጣን” የሚገባው ኦሮሞ ለሆነ ሰው ነው ብለው ባደባባይ ወስነው ስለነበር ቦታውን ሁለት የኦህዴድ አባላት ይዘውት ቆይተዋል። ኦህዴድ እንደሚታወቀው የፈጣሪው የህወሃት ሎሌ እንጂ ታላቁን የኦሮሞን ህዝብ ፈጽሞ አይወክልም። ኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን የጠየቁት እውነተኛ እኩልነት እንጂ አሻንጉሊት እንዳልሆነ እንኳን አዋቂ አፍ ያልፈታ ህጻን የሚያውቀው ጉዳይ ነው።
የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ነጋሶ የነበሩ ሲሆን እርሳቸውም አሻንጉሊትነት በቃኝ ብለው ጥያቄ መጠየቅ ሲጀምሩ እንዲነሱ ተደረገ። አንተ ጎበዙ እሯጭ በምን መስፈርት ነው ታዲያ ፕሬዚዳንት መሆን ያማረህ? የዘር መሰፈርትን ካላሟላህ፣ እጅና እግር እያለህ፣ ሕሊና ካለህ እንደ ኳስ መንከባለል እንዴት ይቻልሃል?
ነጋሶ ቢያንስ ከመሰናበታቸው በፊት መለስን “መንግስቱ መንግስቱን ሸተትከኝ” ማለታቸው የሰሩትን ስህተት ማረሚያ ሲሆናቸው ገነት ዘውዴን ግን ማስለቀሱን ተጽፎ አነበብን። እንደ ሰማነው ገነትን ያንሰቀሰቃቸው ላቶ መለስ ያላቸውን ፍቅር ለመግለጥ ብቻ ሳይሆን የነጋሶን ወንበር ይመኙ ስለነበር ነው። “ፕሬዚዳንት ገነት ዘውዴ” ምናምን እያሉ እራስ ለማታለል ማለት ነው።
ነጋሶ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ስልጣን በሰላማዊ መንገድ በህዝብ ለተመረጠ ሰው ሲሰጥ በአይኔ በብረቷ አየሁ ብለው የድንቢጥ ማስክርነት ሰጥተው የነበሩት ገነት ዘውዴ፣ ለመለስ ምን አስለቀሳቸው ብለን መመራመር አያስፈልገንም። ነገሩ “ሆድ ሲውቅ…” እንደሚባለው መሆኑ ነው። ግን ያዞ እንባቸውም ከንቱ ቀረ። የወይዘሮ ገነት ዘውዴም ጌታ በዚያው አሸለቡ፣ እኛም ታዝበናቸው ቀረን። ምስኪን!
ነጋሶ ሲሰናበቱ ያተንኮለኛ አንባገነን ጥያቄ የማይጠይቅና አሻንጉሊትነቱን ሙሉ በሙሉ የሚቀበል ሰው አፈላልገው መቶ አለቃ ግርማን ፕሬዝዳንት ብለው ሰየሙ። ጋሽ ግርማ መቼም ድሮም ወስላታ እንደነብሩ አብረዋቸው የሰሩ ሁሉ የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው። ህሊናቸው አይወቅሳቸውም። ይኸው እስካሁን አልጋ ላይ ሆነው፣ በዊል ቼይር እየተገፉ የህወሃቶች ላንቲካ እንደሆኑ መሞቻቸው ተቃርቧል። መቶ አለቃ ግርማ ወደ መቃብራቸው በህወሃቶች ሰረገላ ታጅበው ሲጋዙ ዶ/ር ነጋሶ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው ለህዝባችን አንድነትና ነጻነት እየታገሉ ይገኛሉ። ከጥፋቱ የሚማር ሁሉ ታላቅ ሰው ነው።
ሃይሌ ሆይ፣ ያንተ ዋናው ጉብዝና እሩጫ ነው። እንኳን አጸያፊውንና የሚከረፋውን የህወሃቶች የዘር ፖለቲካ መፈትፈት ይቅርና ሽምግልናም አልሆነልህ። ታስታውስ እንደሁ አቶ መለስ በግፍ ያሰሯቸውን አገር ወዳዶች ለማስፈታት ከነፕሮፌሰር ኤፍሬም ጋር
ሆነህ ያደረከው ጥረት መልካም ቢሆንም ምንም ያልበደሉ ንጽሃን ዜጎች ስንት ግፍና ጭፍጨፋ የፈጸሙትን መለስ ዜናዊን ይቅርታ እንዲጠይቁ ተደርጓል። ይሄ ደግሞ በታሪክ ያስወቅሳል።
በርግጥ ህወሃቶች ምን ቃል እንደገቡልህ አላውቅም። ይሁንና እንኳን ፕሬዚዳንትነት ጠቅላይ ሚኒስትነት ፈጽሞ አይመጥንህም። ጠቅላይ ሚኒስቴር ስል ጋሼ ሃይለማሪያም ትዝ አሉኝ። እኚህ ግለሰብ ገና አርባ ምንጭ ሲሰሩ ጀምሮ የሚታወቁበት አንድ መለያቸው ለህወሃቶ ጭራ መቁላት ነበር። ቀስ በቀስ ወደ ባለራዩ መሪ ቢሮ ጠጋ ሲሉም ስራቸው ከጭራ መቁላት ወደ ምንጣፍ አንጣፊነት ከፍ እንዳለ የሚውቋቸው ሁሉ የሚናገሩት ጉዳይ ነው።
ዛሬ በህወህት ጄኔራሎችና አማካሪዎች ታጅበው የመሪነት ስልጣን ሳይሆን የአሻንጉሊትነት ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ። እኚህ ሰው የሌለና ያልነበረ ራእይ እጠብቃለሁ ብለው ደፋ ቀና ሲሉ በቁሙ የሞተው “መሪ” የሚል ቅጽል ወጥቶላቸው ተከብረው ሳይሆን የህወሃቶች ላንቲካና መጫውቻ ሆነው ሲሽከረከሩ ይውላሉ። ሰው ለህሊናው ማደርን ትቶ ሆድ ለመሙላት ብቻ ከኖረ የሚያዳምጠው ህሊናው የሚናገርውን እውነት ሳይሆን የሆዱን ፍላጎት ብቻ ነው። ጋሽ ሃይለማሪያም ህሊናቸውን አፍነው ሆዳቸውን እያዳመጡ መኖራቸው የሚያስከብራቸው ሳይሆን ለዘላለም የሚያስንቃቸው የታሪክ እውነታ ነው።
ውድ ሃይሌ፣ ሌላው ምኞትህ ደግሞ ፓርላማ ገብቶ ህግ ማውጣት ነው። ለመሆኑ ይሄ የህወሃቶች አዳራሽ ከመቼ ወዲህ ነው ለሃገርና ለወገን የሚጠቅም ስራ ሰርቶ የሚያውቀው። ወያኔዎች ዴሞክራሲ አመጣን ብለው ሁሉን ነገር ሙሉ በሙሉ እንደፈለጋቸው ተቆጣጥረው፣ ህዝብ እያስለቀሱ ፣ እያፈኑ፣ እየገደሉ፣ እያሰቃዩና እየዘረፉ ሲኖሩ ለመሆኑ መቼ ነው ፓርላማ ተብዬው የህዝብ ብሶት ተወያይቶ የሚያውቀው? የትኛውን መብት ነው ያስጠበቀው?የትኛውን ህግ ነው ያስከበረው? እኛ እስከምናውቀው ፓርላማ ማለት የህወሃቶች የቧልት አዳራሽ ነው። ቧልት ካማረህ፣ ለህወሃቶች ጭራ እየቆላህ፣ እያጨበጨብክ መኖር ካማረህ ወደ አዳርሹ ግባና የሚሉህን ሁሉ አድርግ። እኔ ግን ኪሳራ እንጂ ትርፍ እንደማታገኝ ከወዲሁ ልነግርህ እወዳለሁ።
እንደሰማሁት ከሆነ የሙስና እናት በመባል የሚታወቁት አዜብ መስፍን ከፓርላማ አባልነታቸው፣ ከኤፈርት ቁንጮነታቸው በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከንቲባና የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት መሆን ይፈልጋሉ። አዜብ ከባላቸው ሞት በሁዋላ ፍላጎታቸውም በጣም እንደጨመረ እንደውም የመለስን እራእይ አስጠባቂ እኔ ነኝ ማለታቸው ትክክል ነው። በዘር ላይ ተመስርቶ የኢትዮጵያን ህዝብ ደም እየመጠጠ ያለው ኤፈርት ባለቤቶ ጋር መወዳደር በፖለቲካው ብቻ ሳይሆን በንግዱም ዘርፍ ብዙ ኪሳራ ስለሚያስከትልብህ ጠንቀቅ ብትል ይሻልሃል። ፕሬዚዳንትነቱንም ሆነ ፓርላማውን ለነአዜብ ተውላቸው። የነሱ የፍርድ ቀን እሩቅ አይደለም…
አንተም የኢትዮጵያን ህዝብ ማገልገል ከፈለክ ህዝባችን ከህወሃቶች የአፓርታይድ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት የሚያደርገውን ትግል በሙሉ ልብህ ደግፍ። ትንሽም ብትሆን መሰዋእትነትና ዋጋ ክፈል። ፓርላማም ሆነ ቤተምንግስት ገብተህ የህወሃቶች ጉልቻ አትሁን።
ለማንኛውም የኔን ምክር ተውና የባለቤትህን የአለምዬን ምክር ስማ። ሴት መቼም ሁል ጊዜም ብልህ ነችና፣ አለም አያዋጣህም ብልሃለች። “ጨው ለራስህ ብትል…” ነው ነገሩ።
እኔ በበኩሌ የምመኘው በአገሬ እንደማንም ተራ ዜጋ ተከብሬ የነጻነት አየር እየተነፈስኩ መኖር ብቻ ነው። ከቤተ መንግስት ይልቅ የእናቴ ደሳሳ ጎጆ ትናፍቀኛለች።
ነጻነታችን ሲታወጅ ቤተመንግስት ሳይሆን አዲስ አበባ መንገድ ላይ እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ።የሰው ምክር ብትሰማ መልካም፣ ካልሰማህ ግን አንተንም እንደ አቶ መለስ በአደባባይ ካገኘሁህ ቀልብህን ገፍፌ….በማለት በፈገግታና በደስታ አጭሯን ጦማሬን አጠቃልላለሁ። …ለአለምዬ ልባዊ ሰላምታዬን አድርስልኝ። ያንን ቱጃር ግን ካገኘኸው እንደማለቀው ንገርልኝ!
ለማንኛውም መልካም እድል ለሁላችን

ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ

July 18, 2013

የማነቂያው ገመድ ከርሯል፤ “ትግሉ ይቀጥላል” ኦባንግ ሜቶ

ኢህአዴግ ለሚገዛት ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ዕርዳታ የሚሠጠው የዓለም ባንክ፤ ለዕርዳታና ልማት የሚልከው ገንዘብ ኢህአዴግ የሕዝቡን ሰብዓዊ መብት ለመጣስ ተጠቅሞበታል በሚል ሙሉ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዘ፡፡ የባንኩ ውሳኔ ኢህአዴግን የማነቂያው ገመድ እንደሚያከረው ተገለጸ፡፡ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል በሰጡት መግለጫ “ይህ በጥናት ከምናካሂደው ትግል አንዱ ውጤት ነው፤ ገና ጅማሬ ነው፤ ጠንክረን እንሠራለን” አሉ፡፡
Ethiopia land grab
ለምንጣሮ የተዘጋጀ መሬት
የዓለም ባንክ ለልማት ሥራዎች የሚሰጠው የእርዳታ ገንዘብ በኢትዮጵያ በተለይም በጋምቤላ ክልል የሚኖሩትን ዜጎች ሰብዓዊ መብት በመጣስ ላይ ውሏል በሚል ከዚህ በፊት ክስ ቀርቦበት እንደነበር ይታወሳል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጉዳዩን ከ9 ወራት በፊት በዘገበበት ወቅት ተጠቂዎቹ ዜጎች ያቀረቡትን ማስረጃና የኢንስፔክተር ቡድኑ የሚያደርገውን ምርመራ በዝርዝር ሰፍሮ ነበር፡፡ በወቅቱ ምርመራውን ያደረገው የመርማሪ ቡድን (ኢንስፔክሽን ፓናል) በአካባቢው የሚገኙትን ተጠቂዎች ካነጋገረ በኋላ ለባንኩ የሥራ አመራር ቦርድ በሰጠው ሪፖርት በዕርግጥ የዕርዳታው ገንዘብ በሰብዓዊ መብት ረገጣ ላይ መዋሉን ይፋ አድርጓል፡፡
ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ ለአገራት የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡
ቡድኑ መረጃውን ይፋ ባደረገበት ወቅት ቢያንስ የ600 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ከዚህ ካለፈም በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የማጣት ጭንቀት ውስጥ የገባው ኢህአዴግ አንገቱ መታነቁን ሲያስተውል የኢንስፔክሽን ቡድኑን ውሳኔ አጣጥሎት ነበር፡፡ በወቅቱ መግለጫ የሰጡት በጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ቢሮ አፈቀላጤ የነበሩት ጌታቸው ረዳ “ከኢንስፔክተር ቡድኑ ጋር አንተባበርም፤ ትብብር ማድረግ ካስፈለገንም ከዓለም ባንክ ጋር ይሆናል፤ … ይህ በኢህአዴግ ላይ የተነጣጠረ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ነው፤ … ኢንስፔክሽን ፓናል የራሱ የዓለም ባንክ ኢንስፔክተር (መርማሪ) ቡድን አይደለም፤ … ቡድኑ የራሱን ልብወለድ ዘገባ በዓለም ባንክ አሠራር ላይ ለመጫን ያደረገው ሙከራ ነው” በማለት ነበር ያጥላሉት፡፡
ከዚህ በኋላ የዓለም ባንክ በኢንስፔክተር ቡድኑ የውሳኔ ሃሳብ መሠረት ሙሉ ምርመራ እንዳያደርግ ኢህአዴግ እንደለመደው ውሉ ያልለየለት አካሄድ በመከተል ሲከላከል አምስት ወራት አስቆጥሯል፡፡ በመጨረሻም ለዛሬ ሐምሌ 11 (ጁላይ 18) ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከአዲስ አበባ፤ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በመሆን የዓለም ባንክን አመራሮች ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው እያለ ባንኩ ከአንድ ቀን በፊት ሙሉ ምርመራ እንዲካሄድ ማዘዙ “ኢህአዴግን የማነቂያው ገመድ” እየከረረ መምጣቱን የሚጠቁም ነው፡፡ ከዚህም በላይ ባንኩ በራሱ ገንዘብ ማንም ሊያዝበት እንደማይችል ያሳየበትና ለኢህአዴግም እጅግ አሳፋሪ ውሳኔ መሆኑ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) እና ሌሎች ክፍሎች ይናገራሉ፡፡ በውሳኔው መሠረት አሁን የሚካሄደው ሙሉ የምርመራ ዘገባ ኢህአዴግ በእርግጥ የሚሠጠውን ገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ረገጣ ማዋሉን ካረጋገጠ፤ ኢህአዴግ በትንሹ600ሚሊዮን ዶላር ያጣል፤ ጉዳቱም እስከ ቢሊዮኖች እንደሚደርስም ይገመታል፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ከሚያካሂደው ሁሉን ዓቀፍ ትግል ይህ አንዱ ክፍል አንደሆነ የተናገሩት የንቅናቄው ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ “እኛ በመሠረቱ ልማትን አንቃወምም፤ ሆኖም ግን በልማት ስም የሚሠጠው ዕርዳታ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለመርገጥ የሚውል ከሆነ ህወሃት/ኢህአዴግ ተጠያቂ መሆን ይገባዋል” ብለዋል፡፡ የግልጽነትና ተጠያቂነት ዕጥረት እንዲሁም የሙስና በሽታ እንዳጠቃው በራሱ መሪዎች የሚነገርለት ኢህአዴግ፤ የፈለገውን ነገር እንደፈለገው የማድረግ አምባገነናዊ አሠራሩ ራሱን አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚከተው አቶ ኦባንግ በተለይ ለጎልጉል በስካይፕ በሠጡት አጭር ቃለምልልስ አስታውቀዋል፡፡ እልህ አስጨራሽ ቢሆንም የጋራ ንቅናቄው በጥናትና በዕቅድ ከሚያካሂደው ሁሉን ዓቀፍ ትግል አንዱ እንደሆነ የጠቆሙት የንቅናቄው ዳይሬክተር፤ “ይህ ገና ጅማሬ ነው፤ በተጠናከረ መልኩ በመንቀሳቀስ ጉዳዩን ዳር በማድረስ የተጎዱ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን መከራ” እንደሚታደጉ ጨምረው አመልክተዋል፡፡
ባንኩ የሚልከው የመርማሪ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በቅርቡ እንደሚንቀሳቀስና ኢህአዴግም ቡድኑ ለሚያደርገው ሙሉ ምርመራ በሩን ክፍት ማድረግ እንዳለበት ተመልክቷል፡፡ የምርመራው ውጤት ከዚህ በፊት የተደረገውን ምርመራ የሚያጸና ከሆነ ኢህአዴግ ለልማት ሥራ እንዲያውለው በዕርዳታና ድጎማ ስም የሚያገኘው ገንዘብ እንዲሁም ሌሎች የእርዳታ ምንጮች እጅግ ከፍተኛ አደጋ ላይ ይወድቃሉ፡፡ ባንኩ ከዚህ በፊት በደቡብ እስያ አገር ላይ የወሰደው ዓይነት አስከፊም እርምጃ ሊወሰድ ይችላል፡፡
ጉዳዩ እንዴት እዚህ ደረጃ ደረሰ? ለሚሉት ጥያቄዎችና ኢህአዴግ ስለተከሰሰባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (“ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”፤ ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል) በሚል ርዕስ February 16, 2013 እንዲሁም (ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!) October 12, 2012 አስቀድሞ የዘገበውን ማጣቀስ አግባብ ሆኖ በመገኘቱ ከዚህ በታች እንዳለ አቅርበነዋል።

ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!

ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!
ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም።
ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል።
የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል።
አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡
የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡
በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡
ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)
ጎልጉል የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።
በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።

“ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”

ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል
/ዜና ጎልጉል/ ኢህአዴግ ላይ ቀደም ሲል ሲቀርቡበት ከነበሩት ሪፖርቶች በተለየ ጥቅሞቹ ላይ ያነጣጠሩ አስደንጋጭ መረጃዎች እንደወጡበት ተሰማ። መረጃው የኢህአዴግን አንገት የማነቅ ያህል እንደሚቆጠርና ለተግባራዊነቱ የተንቀሳቀሱትን አካላት “የአስተዋይነት” ትግል ውጤት እንደሆነ ተጠቁሟል።
ኢህአዴግ በህዝብ ስም በብድርና በርዳታ የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ እንደሚያውለውና ለአፈና ተቋማቱ ማጠናከሪያ እንደሚጠቀምበት የተከሰሰበት ሪፖርት መጠናቀቁን የገለጹት የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ናቸው። ምንጮቹ እንዳሉት ሪፖርቱ የቀረበለት የዓለም ባንክ በቅርቡ መረጃውን ተቀብሎ ርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል። ኢህአዴግ ርምጃው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ለማክሸፍ የተለመደውን ሩጫ መጀመሩ ተሰምቷል።
በኢህአዴግ ላይ የቀረበው ሪፖርት የመፍትሄ ሃሳብም ያካተተ እንደሆነ የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የዓለም ባንክ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሪፖርቱን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበለውና ይፋ እንደሚያደርገው አስረድተዋል። የምርመራ ዘገባውን ስላጠናውና ስላቀረበው የኢንስፔክሽን ተቋምና የስራ ተሞክሮ በቂ ግንዛቤ ያላቸው እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት የዓለም ባንክ ቦርድ ይህ ተቋም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ያቀረባቸውን ሪፖርቶች ላለመቀበል አንገራግሮ እንደማያውቅ ያስረዳሉ።
በሚመሩት ህዝብ ላይ ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትና በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያካሂዱ አገራት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በስፍራው በመገኘትና መረጃዎችን ከመሠረታቸው ዘልቆ በመመርመር  አጥንቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) የሚባለው ተቋም ከኢትዮጵያውያኑ ሰለባዎች ውክልና በመውሰድ ስራውን ለማከናወን እንቅስቃሴ መጀመሩን ጎልጉል ምንጮቹን በመጥቀስ መዘገቡ ይታወሳል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝርየሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቆ ነበር።
ኢህአዴግ በርዳታና በብድር የሚያገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለፖለቲካ ስራ፣ ለአፈና፣ ለወታደራዊ አቅም ግንባታ፣ ለተለያዩ የአፈና ተቋም ሰራተኞቹ ደሞዝና ህዝብን በመርገጥ ስርዓቱን ለሚንከባከቡ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን በመክፈል ገንዘቡን ለመጠቀም ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንደሚያውለው በበርካታ መረጃዎች ያረጋገጠው የኢንስፔክሽን ቡድን ለዚሁ ስራው ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ በቅርቡ አቅንቶ ነበር።
ምርመራው ያስደነገጠው ኢህአዴግ በተለያየ መልኩ ሰለባዎች በደላቸውን እንዳይናገሩ፣ በጥቅም የተደለሉ ሰዎችን በየቦታዎቹ በማዘጋጀትና በማስፈራራት አፈና ማካሄዱን የጎልጉል የመረጃ ምንጮች በወቅቱ ቢያስታውቁም ጎልጉል መረጃውን ለስራው መሳካት ሲባል ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።
ከቀናት በፊት ሪፖርቱን አጠናቆ ለዓለም ባንክ ቦርድ ያቀረበው የኢንስፔክሽን ቡድን (ፓናል) በማያወላዳ መንገድ ተጽኖ ፈጣሪ ተቋም መሆኑንን ያስረዱት ለስራውና ለተቋሙ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች፣ ሪፖርቱን ከቦርዱ አባላት አንዱ እንኳ አልቀበልም ቢሉ ምን ሊከሰት እንደሚችልም አብራርተዋል።
“አንድ ወይም ከአንድ በላይ የቦርድ አባላት የፓናሉን ሪፖርት ውይይት እንዲደረግበት እስካልጠየቁ ድረስ ፓናሉ ባቀረበው መሠረት እንዳለ ይጸድቃል። ከጸደቀም በኋላ ሪፖርቱ በዓለም ባንክ ስም ይፋ ይሆናል። ሪፖርቱ ታምኖበት ይፋ ከሆነ በሪፖርቱ የቀረቡት የመፍትሄ ጭብጦች ተግባራዊ ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። እስካሁን ባለው አሰራር የፓናሉ ሪፖርት ተቃውሞ አጋጥሞት አያውቅም” ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።
“ይህ ታላቅ ውጤት የተገኘው በእቅድና አስተውሎ በመራመድ ነው። ወደፊትም በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራቶች አሉ። የአገዛዙን ትምክህትና ማን አለብኝነት የሚያረግቡ፣ ብሎም የሚያተኑ ስራዎች ለመስራት ለተጀመረው ስራ ይህ ውጤት ከፍተኛ መነቃቃት ይሆናል” ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል እዚህ ያበቁት ክፍሎች አስረድተዋል።

Please Leave the Ethiopian Muslims’ Movement alone!

July 18, 2013
by Maru Zeleke
The Ethiopian Muslim population, generally reflective of the wider Ethiopian context, comprise of diverse cultures, histories and political affiliations. What ties them together is their allegiance to a common religion. This fact has been starkly reflected in the now two years but few months old peaceful struggle of Ethiopian Muslims. The movement has managed to regulate, but not eliminate, the diverse manifestations of difference within the Muslim population and channel their grievances into a unified call for freedom. This unity in diversity has been an exemplary success of the struggle, but it has by no means escaped some challenges.
The recent political reflections by Jawar have raised much dust, almost “rocky” one. Ethiopian nationalists and some Muslim activists alike have felt obliged to air their sharply critical views on it. Due to the person’s relatively high profile in Ethiopian political discourse, some aspect of the fuss is expected. But at least one aspect of it is not at all commendable.
Hinging on Jawar’s apparent association with the Ethiopian Muslim movement, some writers have tried to question his intentions behind his support for it. While some have attributed to him an ethno- Islamist agenda, others have simply made of him a political entrepreneur trying to make use of religion for political purposes. Both positions, however, have tried to accuse him not only of parochialism but also hypocrisy.
What is worse, some have gone to the extent of calling Ethiopian Muslims to distance themselves from him. The Ethiopian Muslims’ struggle, they claim, is self-evidently an Ethiopian rights’ struggle that should not be taken hostage by a few “extremists” and “ethnic nationalists”. Hence, the need for the call to “liberate” the struggle from “unwanted elements”.
In connection with this last point,–which is my concern in this short piece—it should be known by all and sundry that the Ethiopian Muslim movement is a broad-based struggle for religious freedom. It has, first, brought together Muslims from diverse backgrounds and, most importantly, political outlooks. Any conscious and concerned Muslim has immediately become part of this struggle, regardless of his/her political attitudes and associations. In fact, the strength of the movement has emanated from its openly embracing a plurality of views and background.  Second, the moral and political appeal of this historic movement has drawn the attention of a wide range of non-Muslim Ethiopians—again from diverse perspectives. They all have come by the side of Muslims in the latter’s quest for democracy, secularism, freedom and dignity. It is indeed a spectacular manifestation of the broad-based nature of this movement that it has brought together activists and supporters from all ranges of philosophical, identitarian and political settings.
It is, therefore, both futile and disastrous to require all those who support the Muslim movement to hold fast to a single conception of the political world. It is futile because all sorts of differences are simply a permanent aspect of our polity (which Muslims are a part of). It is disastrous because the more we push forward this agenda of political conformity in relation to the Muslim struggle, the more we entangle this non-political movement with the most divisive political agendas, and thereby, the more we lose the benefit we would gain by supporting it collectively as an unprecedentedly sustainable, formidable and peaceful bulwark against unbridled state autocracy.
It is also important to know that, while people of diverse views in the Diaspora have spoken in favour of this struggle, none can speak on behalf of it. All political analyst Jawar Mohammed (ethno nationalist Muslim)[1], journalist Sadiq Mohammed (Ethiopian nationalist Muslim), and activist Tamagn Beyene (Ethiopian nationalist Christian), for instance, have been highly supportive of the Muslim struggle, but none have dared to claim for themselves any leadership or representative roles. Ironically, Jawar has been the most vocal in this respect. He has time and again emphasized that Diasporas like him can never represent or lead the peaceful struggle back home; only those inside, and those at the battlefront are the actual participants in it. Thus, it is fair neither to any of the Diaspora supporters of the movement nor to the movement itself to associate it with any political, academic or religious figure based just on one’s pro-struggle positions. This is a movement that had been led by its elected leaders for some time, and then, upon their incarceration, by those who got endorsement to lead both by the incarcerated leaders and the Muslim activists at large.
I, therefore, urge all bodies that have been raising immense dust on the question of Jawar to primarily distance their comments from the Muslim movement. It is quite natural and perfectly healthy to discuss Jawar’s politics, and support or destroy it. But it is not healthy to bring that discussion into the Muslim movement and try to derail a magnificently unifying anti-EPRDF force. It is also not fair to expect or require Muslim activists to take sides on political issues in connection with the battle they are waging in Ethiopia. It is, finally, better for all of us, I humbly submit, to temper our inter-group bickering and step up the anti-EPRDF struggle for freedom and justice instead

ተስፋዬ ተካልኝ መከራና የማይሞተው የነፃነት ሕልሙ

July 18, 2013
ዳኛቸው ቢያድግልኝ
ሀዘኑ በተስፋ እንዲተካለት ከልብ የምመኝለት የወያኔ ቅጥረኞች ቁምስቅሉን ያሳዩትን ወጣት ቃለ ምልልስ ኢሳት ላይ እንድመለከት ስጋበዝ ስሜቴን ሰቅዞ የሚይዝ በእጅጉ የሚያስቆጣኝ ጉዳይ እንደነበር አልገመትኩም። ምክንያቱም መከራ ለምደናል፣ ሀዘን ከቤታችን ወጥቶ አያውቅም። ነውጠኞች፣ ባለጌዎች፣ ጎጠኞችና ክብረጠሎች ከእንስሳ ያነሰ ሆዳም ደመነብስ ይዘው ሀገር ማፍረሱን ከያዙ ስለቆዩ ምንም አዲስ ነገር የለም በማለቴ ነበር። ተሳስቻለሁ ተሥፋዬ ከሀዘን ይልቅ ብርታትን፣ ከውድቀትም በላይ መነሳትን ሲናገር ሞትን ፊት ለፊት እየተመለከተ መሆኑ በወጣቱ ትውልድ እጅግ እንድኮራ አድርጎኛል። በዚህ አጋጣሚ የሽንፈት ድባብ በማሸነፍ ተሥፋ እንዲተካልን የምንሻ ሁሉ የዚህን ወጣት ጤና በመታደግ የኛኑ የውስጣችንን የልብ ስብራት ልናክመው ይገባናል። በኢሳት ላይ እንደተጠቀሰው temetoesat@gmail.com ብትጽፉ ወይም በ +447424582713 ሥልክ ብትደውሉና መርዳት ብትችሉ በሰጣችሁት ልክ ከፈጣሪያችሁ ትቀበሉ ዘንድ እምነቴ ነው። ይህንን ቃለ ምልልስ ያልተመለከታችሁ ኢሳትን በዚህ አድራሻ ማግኘት ትችላላችሁHuman Rights abuse in Ethiopia
ተሥፋዬ አርባ ጉጉ ላይ በተነሳው ግጭት አባቱን ያጣና በገዛ አገራቸው ስደተኛ መሆን ተገደው ናዝሬት ውስጥ በጠላ ንግድ በሚተዳደሩ እናት ያደገ ወጣት ነው። የስርዐት ክፋትን ከልጅነቱ እያየ አባትን ያህል ነገር በሞት ተለይተውበት ያደገ ወጣት መሆኑን ከውውይይቱ ለመረዳት ይቻላል። በዚህ አስቸጋሪ ሕይወት ውስጥ ራሱን ማስተማር ችሎ ለሀገሩም ለቤተሰቡም አጋር ለመሆን የበቃ ወጣት ነው ። እንደወጣትነቱና እንደ ኢትዮጵያዊነቱ በነበረው የፖለቲካ አጋጣሚ ከቅንጅት ጎን ቆሞ ነበር። ይህ ግን በጠላትነት አስፈርጆት ቂመኞቹና ዘረኞቹ የትግራይ ተገንጣይ ወንበዴዎች ከመኖርያ ቤቱ ወስደው ለ23 ወራት ገረፉት፣ አሰቃዩት፣ በኤሌክትሪክ ጠበሱት ከሞቀ ውሀ ወደ ቀዝቃዛው እያመላለሱ አካሉን ሰባበሩት። ለኢትዮጵያዊው ወጣት ሀገሩን የገሀንም መናገሻ ከተማ አስመሰሉበት። ይህ ወጣት ዛሬ ሽንቱን አይቆጣጠርም፣ ለነገ ቤተሰብ መስርቶ ልጅ ወልዶ የመኖር ህልም የለውም። ስራው መመለስ አይችልም፣ የነበረው ንብረቱ በሙሉ ጠፍቷል ወይም ተዘርፏል። በቃ ያበቃለት ሰው ነው ብለው ሜዳ ጥለውታል። ቃል ቢተነፍስ እሱ ብቻ አይደለም ዘመዶቹ ሁሉ እንደሚያልቁ ተነግሮታል። ስለዚህ ቆሽሾ ሰው ተጠይፎት ዝንብ ወርሮት ሞቱን እንዲጠብቅ ተፈርዶበታል።
እንዲህ አይነት ግፍ የሚደርስባቸው ሰዎች ብዙ ናቸው ተሥፋዬን ልዩ የሚያደርገው ግን እንቅፋት የመታው እንኳን ያለመምሰሉ ነው። ኢትዮጵያዊነቱን ከስሜቱ ሊያወጡበት አልቻሉም፣ ዓላማውን አልገደሉበትም፣ ፊኛና ኩላሊቱን ቢቀጠቅጡም ወኔውን አላሸኑትም። እጅግ የሚያኮራ ወጣት ነው። እጅግ የሚያበረታታ ሀሳብ ያለውና ከደረሰበት ችግር በላይ ነፃነት ማጣቱ ያመመው ወጣት ነው። ማደርያ የለውም መሸሻም የለውም፣ እኛ ግን መሸሻም ማደርያም አጋርም ወገንም መሆናችንን ልናሳየውና ህልሙ እውን እንዲሆንለት በትግሉም ጠንክረን እሱን ብቻ ሳይሆን ወገኖቻችንን በጠቅላላው ከዚህ ሰቆቃ ነጻ ልናወጣ ይገባል። ተስፋዬ ተካልኝ እንደስሙ ሁሉ የዘረኛነትን ክፋት በኢትዮጵያዊነት ተስፋ ተተክቶ የነፃነት አየር ለመተንፈስ ይበቃ ዘንድ ምኞቴ ነው፡፡

ሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ቀጣይ እቅዱን ይፋ አደረገ

ሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ቀጣይ እቅዱን ይፋ አደረገ

July 18, 2013
የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ዛሬ ሐምሌ 11,2005 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ቀጣይ የህዝባው ንቅናቄ ዕቅዱን አፅድቋል፡፡
በዚሁም መሰረት በሚቀጥሉት የሀገራችን ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባዎችንና ታላላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ጠርቷል፡፡ በየክልሉ ያሉ የአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሮችMillions of voices for freedom - UDJ ለፓርቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ግብረኃይሉ ያቀዳቸው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ከአዲስ አበባ አስቀድሞ በክልል ከተሞች ለማድረግ የተወሰነ ሲሆን የህዝባዊ ንቅናቄው ማጠቃለያ የሚሆነው መስከረም አምስት ቀን 2006ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚደረገው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ይሆናል፡፡ ግብረ ኃይሉ መስከረም 5, 2006 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያቀደው ሰላማዊ ታጋዮቹ አንዱአለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የታሰሩበትን ሁለተኛ አመት ለመዘከር እንደሆነ ታውቋል፡፡
ህዝባዊ ሰብሰባ የሚደረግባቸው ከተሞችና ቀኖቻቸው
========================
ሐምሌ 21 አዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች
ሐምሌ 28 አዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች
ሐምሌ 28 ወላይታ ሶዶ
ሐምሌ 28 መቐለ
ነሀሴ 5 አዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች
ነሀሴ 26 ድሬደዋ
ነሀሴ 26 አዋሳ
ነሀሴ 26 አምቦ
ነሀሴ 26 ደብረማርቆስ
ህዝባዊ ሰልፎች የሚደረጉባቸው ከተሞች
========================
ሐምሌ 28 ባህር ዳር
ሐምሌ 28 ጅንካ
ሐምሌ 28 አርባ ምንጭ
ነሃሴ 12 አዳማ
ነሃሴ 12 ባሌ
ነሃሴ 12 ወሊሶ
ነሃሴ 12 ፍቼ
ነሃሴ 26 ጋምቤላ
ነሃሴ 26 አሶሳ
መስከረም 5 አዲስ አበባ

ESAT Daliy News Amsterdam July 18 2013 Ethiopia

አንድነት ፓርቲ በደሴ ያካሄደው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ – [ቪዲዮ1, ቪዲዮ 2, ቪዲዮ 3] | Zehabesha Amharic

አንድነት ፓርቲ በደሴ ያካሄደው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ – [ቪዲዮ1, ቪዲዮ 2, ቪዲዮ 3] | Zehabesha Amharic