Wednesday, September 24, 2014

በመላ ሃገሪቱ የተነደፈው የተቀናጀ የጐልማሶች ትምህርት ስኬታማ አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ተናገሩ፡፡

በመላ አገሪቱ ከ40 ሚሊዮን በላይ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ወጣት እና ጎልማሶች አሉ ያሉት አቶ ሺፈራው ፤  ይህንን የትምህርት እድል ያለገኙ ወጣቶች እና ጎልማሶች አማራጭ
ትምህርት እንዲያገኙ የተደረገው ሙከራ አፈፃጸሙ ከዜሮ በታች ነው ብለዋል። በኢህአዴግ የእቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ እንደቀረበው በጎልማሶች የትምህርት አቀራረብ  አማራ 0.9፣ ኦሮምያ ፣ 0.71 ፣ደቡብ 0.63 ፣ትግራይ 2.9
በመቶ ፈጽመዋል።
ኢህአዴግ ደርግን ባመሰገነበት የምክር ቤት ውይይት ፤ “ለምን ህዝቡን በዘመቻ አናስተምርም?” ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ ፤ “ኢህአዴግ የተፈጠረው ከዘመቻ ነው፡፡ ወጣቱ ሌላ የትጥቅ ትግል እንዲያደራጅ  መሳሪያ አንሳ ብለን አንልክም”
የሚል መልስ ተሰጥቷል። “በገጠር መሬት አልባ የሆነው ወጣት ፤ በከተማ ስራ አጥ የሆነው የተማረው ሃይል በአንድነት ተገናኝቶ ሊፈጥረው የሚችለው አደጋ ሰፊ ነው፤ ይህ ስጋት ሳይሆን ሃቅ ነው” ሲሉ አቶ በረከት እና አቶ አበይ ፅሃየ
በመደጋገፍ እየተናገሩ ጎልማሶችን በዘመቻ ለማስተማር የቀረበውን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል፡፡ አቶ በረከት እንዲህ አይነቱን አስተያየት የሚያቀርቡት በትጥቅ ትግሉ ወቅት ያልነበሩ አመራሮች ናቸው በሚል አዳዲስ የኢህአዴግን አመራሮች
መወረፋቸው ከኢህአዴግ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

No comments:

Post a Comment