
ሁላችንም እንደምናቀው የኬኒያ፣ የሱዳን፣ የጅቡቲና፣ ሌሎች የጎረቤት ሃገራት በወያኔ በደል ምክንያት ሳይወዱ ተገደው ህይወታቸውን ለማዳን ከሃገራቸው በተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ላይ በተደጋጋሚ አፈና እየፈፀሙ ይገኛሉ። በቅርቡ በኬኒያ መንግስት ታፍኖ ለወያኔ ከተሰጠ በኋላ ህይወቱ እስክታልፍ ድረስ ለአመታት በወያኔ እስር ቤት በተሰቃየው በወንድማችን ወጣት ተስፋሁን ጨመዳ ላይ የተፈፀመውን አሳዛኝ በደልና በኦብነግ አመራር አባላት ላይ የተደረገው አፈና፤ በደቡብ ሱዳን በአቶ ኦኬሎ አኩአይና ሌሎች የጋምቤላ ንቅናቄ አባላት ላይ በተመሳሳይ መልኩ የተደረገው አፈና ያለምንም ተጨባጭ እርምጃ በዝምታ ታልፈዋል። ዛሬ ደግሞ የየመን መንግስት በአሳዛኝ ሁኔታ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በማገት ለወያኔ/ኢህአዴግ ሰውበላ ሥርዓት አሳልፎ ሰጥቶታል። በዜጎቻችን ላይ እየደረሱ ለሚገኙት አሰቃቂ በደሎች በዋነኝነት ተጠያቂው የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ቢሆንም፤ በስደት የሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ ከወያኔ መንግስት ጋር በመተባበር በተደጋጋሚ አፈና እየፈፀሙና አጋልጠው እየሰጡ የሚገኙ የጎረቤት ሃገራት ወደፊት በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ተጠያቂ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለንም። ነገር ግን ይህ አፈና እስከመቼ ይቀጥላል!? ዜጎች ጭቆናን በመቃወማቸው ብቻ በስደት ከሚደርስባቸው ስቃይ በላይ ለምን በየጎረቤት ሃገሩ ይታፈናሉ!? እኛ ኢትዮጵያውያን እስከመቼ እየተናቅን እንኖራለን!?
No comments:
Post a Comment