ዶክቶር ተዎድሮስ ኣድሃኖም በኖርወይ
ዶክቶር ተድሮስ ኣድሓኖም "ኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ" በሚል መርህ በኖርወይ መንግስት ትብብር የኖርወይ ንግድ ምክርቤቶችና ኖርወጂያን ኣፍሪካን ቻምበር ባዘጋጁት ሰሚናር ላይ ከምሳ በፈት ከተሳተፉ በኋላ ከሰዓት በኋላ የስራ ጉብኝቱ በስከታማነት ኣጠናቀዋል፡ ፡ ማምሻዉን ደግሞ በ ግራንድ ሆቴል ኢትዮጵያ በኣሁኑ ጊዜ እያጠደፈች ባለችው የንግድ የኤሌትሪክና የምድር ባቡር ግንባታ ከፍተኛ እዉቀት ያካበቱትና እዉቀታቸውን ለኣገራቸው ጥቅም ለማዋል የሚፈልግ ኢትዮጵያውያንን ጋር ተገናኝተዋል፡ ፡
Publisert: 16.10.2014 20:41
Av Girmay Assemahegn
የኢትዮጵያ ደመኛ ጠላቶች ተላላኪዎች የሆኑ 15 ግለሰቦች ከስብሰባው በኋል በ ፓርላማዉና በግራንድ ሆቴል ኣከባቢ እንቁላል ለመወረወር ሲሞክሩ በስፍራው ለጥበቃ የተሰማራ የፖሊስ ቡድን ለጊዜው በቁጥጥር ስር በማዋል ማንነታቸውን በመመዝገብ ከስፍራው ኣስወግዷል፡ ፡ ማምሻውን የኖርወይ ተለቪሽን 15 መለቀቃቸውን ዘግቧል፡ ፡ የፖሊስ ጥበቃ ቡድን ተወካይ መኮንን በሃገሪቱ ተለቪሽን በመቅረብ " በዚህ ዓይነት መልኩ ራስን ማጋለጡ ኣጸያፊ እንደሆነ ገልጸዋል" ጨዋ ሰላምዊ ትዉልደ ኢትዮጵያዊን የኖርወይ ኗሪዎችን የማይወክሉት እኒዚህ ግለሰቦች ማምሻዉን ኣሳፋሪ ድርጊታቸው ነውር መሆኑን በይፋ ሌላ ጥቁር ነጥብ ኣስመዝገዋል፡ በተለይ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ሂስ የነበራቸው የኖርወይ የኢትይጵያ ጉዳይ ኤክስፐርት ሸቲል ትሮንቮል ለ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ድጋፍ ያቀረቡት ንግግር በእጅጉ ያናደዳቸው መሪዎቻቸው ሙሉ ለወር ያህል ያሰለጠኗቸውን ጥገኝነት ጠያቂዎች ዕለቱን በማሰማረት ለኢሳት ተለቪዥን የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሊያነሱ የፈለጉት የዋሺንግተን ኤምባሲ መሰል የ"ጀብዱ" ክሊፕ ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡ ፡
ቪድዮውን ይመልከቱ
ከ 7፡30 ደቂቃ ጀምሮ ያለውን ይመልከቱ›
På Amharisk
16.10.2014 10:16
ተከታታይ ዘገባ
ኖርወይ ንግድ ምክርቤት ኮንፈደርሽን ጽ/ቤት ኦስሎ
የኖርወይ የንግድ ምክርቤቶች ኮንፈደረሽንና(NHO)የኖርወጂያን ኣፍሪካን የንግድ ቻምበር እንዲሁም የኖርወይ የግል ንግድ ሰክተር ልማት ኣማካሪ ጽ/ቤት(Veiledningskontoret)በጋራ ያዘጋጁት "በኢትዮጵያ ኢንቨስት ኣድርጉ" የተስኘው የዛሬው ኦክቶበር 16 2014 ሰሚናር በኦስሎ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡ ፡ በኢትዮጵያ የኖርወይ ኣምባሳደር ኣንድሪያስ ጎርደር ጨምሮ ኣዘጋጆች የእንኳን ደህና መጣችሁና የመግቢያ ንግግር ኣድርገዋል፡ ፡በፕሮግራሙ መሰረት በ 10:35 የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ተዎድሮስ ኣድሓኖም ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡ ፡ በኖርወይና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሚና ያላቸውና የኖርወይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመወከል የተገኙ 8 ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ብቻ በስብሰባው የመሳተፍ ዕድል ኣግኝተዋል፡ ፡ ሌሎች ተሳታፈዎች ከኖርወይ መንግስትና የንግድ ምክርቤቶች የመጡ ናቸው፡ ፡
እንደተለመደው የኣገሪቷ ልማት የማይዋጥላቸው ጥቂት የ ግንቦት 7 ጀሌዎች ስብሰባዉ ከሚካሄድበት ርቀዉ የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ነው፡ ፡
Les merኖርወይ ንግድ ምክርቤት ኮንፈደርሽን ጽ/ቤት ኦስሎ

12.10.2014 12:42
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተጣለውን ማዕቀብ ኣፈጻጸም የሚከታተለው የኤርትራና የሶማሊያ ተቆጣጣሪ ቡድን(Monitoring Group)ለሶማሊያ መንግስት የተሰጠው የጦር መሳርያ ወደ ኣሸባሪው ቡድን ኣልሸባብ እንደሚደርስ ባቀረበው ሰፊ ሪፖርት ጠቀሰ፡ ፡
ማርች 2013 የጸጥታው ምክርቤት በሶማሊያ ከ 1992 በኋላ ተጥሎ የነበረውን የጦር መሳርያ ሽያጭ ማዕቀብ በከፊል እንዲነሳ ማድረጉ ይታወሳል፡ ፡ በወቅቱ ብዙ ኣገሮች ለ ሶማሊያ ኣዲሱ መንግስት የጦር መሳርያ መሸጥን በተመለከተ ስጋታቸውን ገልጸው የነበሩ ቢሆንም ኣሜሪካ የኢስልምና ኣክራሪ ሽብርተኛ ድርጅቱን ኣልሸባብ ለመታገል የጦር መሳርያ እንደሚያስፈልጋቸው በመከራከር ማዕከቡ በከፊል እንዲነሳ ተደርጓል፡ ፡
በቅርቡ የቁጥጥር ቡድኑ ባወጣው ሪፖርት ከሶማሊያ መንግስት ኣዲስ የጦር ሃይል መሳርያዎች ወደ ሽብርተኛው ቡድን እንደተላለፉ በማስረገጥ በምን ዓይነት መንገድ እንደሚተላለፍ ጭምር ሰንዷል፡ ፡
Les merማርች 2013 የጸጥታው ምክርቤት በሶማሊያ ከ 1992 በኋላ ተጥሎ የነበረውን የጦር መሳርያ ሽያጭ ማዕቀብ በከፊል እንዲነሳ ማድረጉ ይታወሳል፡ ፡ በወቅቱ ብዙ ኣገሮች ለ ሶማሊያ ኣዲሱ መንግስት የጦር መሳርያ መሸጥን በተመለከተ ስጋታቸውን ገልጸው የነበሩ ቢሆንም ኣሜሪካ የኢስልምና ኣክራሪ ሽብርተኛ ድርጅቱን ኣልሸባብ ለመታገል የጦር መሳርያ እንደሚያስፈልጋቸው በመከራከር ማዕከቡ በከፊል እንዲነሳ ተደርጓል፡ ፡
በቅርቡ የቁጥጥር ቡድኑ ባወጣው ሪፖርት ከሶማሊያ መንግስት ኣዲስ የጦር ሃይል መሳርያዎች ወደ ሽብርተኛው ቡድን እንደተላለፉ በማስረገጥ በምን ዓይነት መንገድ እንደሚተላለፍ ጭምር ሰንዷል፡ ፡
11.10.2014 17:50
በኣምባገነንኑ የሻዕብያ መንግስት ፋይናንሳዊ ድጋፍ የሚንቀሳቀስው የግንቦት 7 ኣሸባሪ ቡድን ኣባላት በኖርወይ ጸረ ኢትዮጵያ ያሰለፍዋቸውን ጥቂት ጋጠወጥ ጀሌዎቻቸዉን በማስከተል ሁከት ሲፈጥሩ እንደቆዩ ይታወሳል፡ ፡ በኦክቶበር 16/2014 Invest in Ethiopia በሚል ርእስ በሚደረገው ሴሚናር የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክቶር ተዎድሮስ ኣድሓኖምን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደሚገኙ በመግለጽ ዕለቱን በድረገጾቻቸውና በ ማህበራዊ ገጾቻቸው "ታላቅ የዉርደት " ቀን በሚል ስይመው የሽብር ተግብራቸውን በዕለቱ እንደሚፈጽሙ ሲዝቱና ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል፡ ፡
የሃገራቸውን ሰላምና ልማት የሚመኘውን በኖርወይ የሚገኘው ሰላማዊ ኣብዝሃ ኢትይይጵያውያን ተእግስት እንደ ፍርሃት በመቁጠር የኖርወይ ሕግ ጥሰው ከሻዕብያ በሚደረግላቸው ድጋፍ በኦስሎ ክተማ "የዉርደት ቀን" ብለው የጠሩትን ድራማ ለማሳየት ተዘጋጅተው ነበር፡ ፡
ይህን የሽብር ድርጊትና ሁከት ለመፈጸም ሊጠቀሙበት ያሰቡት የመጀመርያው መንገድ ኣገሪቱ ኢንቨስትመንት የሚያንገበግባቸው ኣገርወዳዶች መስለው በስብሰባው በመገኝት በኢትዮጵያውያን ባለስልጣናት ላይ ጥቃት ለማድረስ ነበር፡ ፡ምሽቱን እራሳቸው በድረገጻቸውና በፈይስ ቡክ ገጻቸው ላይ እንዳወጡት ማስታወቅያ የመጀመርያው ስልታቸው የተነቃበት ስለሆነ ሌላ ዘዴ ተጠቅመዉ በስብሰባው እንዲመዘገቡ ኣዲስ የ ኢ.ሜል ኣድራሻ ሰጥተዋል፡ ፡
No comments:
Post a Comment