***ህወሓት/ኢህአዴግ የፈጠራ ውጤቶች***
ህወሓት/ኢህአዴግ ቡድን የኢትዮጵያን ታሪክ መካድ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ ታሪክን መበረዝ የፈጠራ ታሪክ መፍጠር:: የኢትዮጵያን ህዝብ ባህል ስብእና ዕምነት ኩራት ማንነት ብሄራዊ እሴቱን አንድነቱንና ብሄራዊ መገለጫዎቹን ማጥፋት:: የኢትዮጵያን ታሪክ የወያኔን ታሪክ ብቻ አድርጎ በካድሬዎቹና ለሆዳቸው ባደሩ ተራ ግለሰቦች ገንዘብ ከፍሎ ማፃፍ:: ልክ እንደ ውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ: ማጥላላት: ማናናቅና የመሳሰሉትን አስነዋሪ የቅጥረኝነቱን ተግባር ፈፅሙዋል አሁንም እየፈፅመ ይገኛል::
በ acadamia.org ላይ የመንግስት ሽብርተኝነትን እንደዚህ ጽፎታል፡- State terror refers to the use or threat of violence by the state or its agent or supporters, particularly against civilian individuals and population, as a means of political intimidation and control.
የፖለቲካ የበላይነትን ለመያዝና ጫናን ለመፍጠር በተለይም በሰላማዊ ግለሰቦችና ህዝቦች ላይ ተገቢ ያልሆነን ጥቃትን በራሱ በመንግስት፣ በተወካዮቹና በደጋፊዎቹ ሲፈጸም ይህንን ጥቃት መንግስታዊ ሽብር ብሎታል።
እንግዲህ ህወሓት/ኢህአዴግ ምንም እንካን የመንግስትን ሥልጣን የያዘ ቢሆንም ሌሎች አሸባሪ ድርጅቶች የሚፈጽማቸውን ተግባራት በግልጽና በአደባባይ ይፈጽማል። ከነዚህም ውስጥ ፍንዳታን ይፈጽማል ፣ያፍናል፣ህጋዊ ያልሆኑ እስራትን ይፈጽማል፣በሰብዓዊ ፍጥረት ላይ የማይፈጸሙ ድብደባዎችን፣ በወንዶችም ሆነ በሴቶች የመራቢያ ብልቶች ላይ አደጋን ማድረስ፣አካለ ስንኩል ማድረግ፣ ቤተሰቦች እንዲለያዩ ማድረግ፣ ስውርና የአደባባይ ላይ ግድያዎችንና ሌሎችም ተግባሮችን ይፈጽማል።ከዚህም ድርጊቱ አንጽር ህወሓት/ኢህአዴግ ከአሸባሪነት መገለጫዎች የዘለሉ ተግባሮችን የሚፈጽም ቡድን መሆኑን ያሳያል።
ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን የሽብር ጥቃቶችን ኢትዮጵያውያን በግልጽ የሚያውቁት ጉዳይ መሆኑ ፣የልዩ ልዩ ሃገራት መንግስታትና በኢትዮጵያ የሚኖሩ የልዩ ልዩ ሃገራት አምባሳደሮችም ሳይቅሩ በግልጽ የሚያውቁት መሆኑና ይህንንም የሚያግዙ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ መሆናቸው፤በተለይም የዩ.ኤስ.ኤ አሜሪካንና ሌሎችንም መረጃዎችን በመሰብሰብ እና በማጋለጥ የሚታወቀው ዊኪሊክስ ይፋ ባደረጋቸው መረጃዎች መሰረት እነዚህ እውነታዎች ግልጽ እየሆኑ መምጣታቸውና በተለይም ህወሓት የራሱን የሽብርን ጥቃት ለመፈጸም እንዲያግዘው ኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ጥቃት እንዳለ ለማስመሰል ሲጠቀምባቸው የነበሩትን የማታለያ እንቅስቃሴዎች ማለትም የሽብር መሳሪያዎችን በራሱ ወታደሮችና የደህንነት ሰዎች በልዩ ልዩ ቦታዎች በማስቀመጥ መልሶ በራሱ የደህንነት ሰዎች እንደተገኙ በማስመሰል ያደርገዉ የነበረውን ተግባር አጋልጧል፤ እነዚህም ድርጊቶቹ አስቀድሞም ብዙዎች የነበራቸውን ጥርጣሬም አጠናክሮታል።
እውነታው ይህ ነው።
No comments:
Post a Comment