ተስፋዬ ገብረ አብን ላጋለጠው ጀግናና ለዳኛ ወልደ ሚካኤል ያለን አድናቆታችን እጅግ ታላቅ ነው። ጎልጉል !!
ተስፋዬ ገብረአብ ከኤርትራዊያን ቤተሰቦች ቢሾፍቱ ተወልዶ ያደገ በውብ የስነጽሁፍ ችሎታው ብዙዎች የሚያደንቁት ጋዜጠኛና ደራሲ እንዲሁም የ‹‹ብዙ ማንነቶች›› ባለቤት ነው፡፡ አዎ! ከሁለት ወር በላይ ባልዘለቀ የብሄራዊ ውትድርና ግዳጅ መማረኩ በፈጠረለት ምቹ አጋጣሚ ከከፍተኛ የኢህአዴግ ሹማምንቶች ጋር ለመተዋወቅ ብሎም በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል መጀመሪያ ላይ ሆኖ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት የታጨ፤ በለጋ እድሜው ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ የሆነለት የኢህአዴግ ሹመኛም ነበር፡፡ ያ ግን ትናንትና ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ በማራኪ የስነጽሁፍ ችሎታው በልዩነታችን ውስጥ ስላለው ውበት ሳይሆን በልዩነታችን ልክ እንዴት መጥፋት እንዳለብን የሚሰብክ መሰሪ ባህታዊ ነው የሚሉ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ በዚህ ባህሪው ብዙዎች ግራ ተጋብተዋል፡፡ በተለይ የኤርትራ ገዢዎችን ስውር ዓላማ የሆነውን በኢትዮጵያ ላይ የዘር ጥላቻ የመንዛት ሰይጣናዊ ተልእኮ በየአጋጣሚው በስነ ጽሁፎቹ ላይ የማንጸባረቅ አመሉን የተረዱ ‹‹ተስፋዬ ገብረእባብ›› የሚል ስያሜ እስከመስጠት ደርሰዋል፡፡ እሱም ለኢትዮጵያ ያለውን ‹‹ተቆርቋሪነት›› ያለመታከት ይደሰኩራል፡፡
ዛሬ ግን ይህ ሰው እጅ ሰጥቷል፡፡ ለበርካታ ዘመናት የዘለቀው የተስፋዬ ብልጣብልጥነት በአንድ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ተጋልጧል፡፡ ለሁለት አመት ያህል ተስፋዬን በቤቱ አስጠግቶ ይህንን አስደናቂ የቤት ስራ የሰራው ወጣት አክቲቪስት አለማየሁ መሰለ ይባላል፡፡
ኢ-ፍትሀዊነትን በመቃወም፤ በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚቃጣን አደጋ በመፋለም የሚታወቀውና፤ በእስር ብዛት አገሩን ለቆ እስኪሰደድ ድረስ ከሸዋ ሮቢት እስከ ቃሊቲ ድረስ ለአመታት በኢትዮጵያን እስር ቤቶች ያሳለፈው ይህ ደፋር ወጣት ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር በመሆን የመጀመሪያውን ክፍል መረጃውን ይፋ አድርጓል፡፡ አለማየሁ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጸው ከሆነ ተስፋዬ ከኤርትራው የደህንነት መስርያቤት ጋር በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት የተለዋወጣቸው ምስጢራዊ ሰነዶችና ኦዲዮቪዧል መረጃዎች በአለማየሁ አስደማሚ ጥበብ ኮፒ ተደርገው ተዘጋጅተዋል፡፡ በተለያዩ ክፍሎችም ለህዝብ ይቀርባሉ፡፡ በአለማየሁ መረጃ አቅራቢነት በዳኛ ወልደሚካኤል ተከሽኖ የቀረበው የመጀመሪያው የጽሁፉ ክፍል ከተለያዩ መረጃዎች ጋር ሊንኩን ይክፈቱ
http://
ከአውራምባ ታይምስ ዝግጅት ክፍል የተወሰደ
No comments:
Post a Comment