የኢትዮጲያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግንባር መፍጠር
10 ያህል የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይበልጥ ተባብረው በጋራ ለመታገል ያስችላቸው ዘንድ የጋራ ግንባር መፍጠራቸውን ኣስታወቁ።
እነዚሁ ቀደም ሲል 33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይባል የነበረው ስብስብ አካል የነበሩ 10 ፓርቲዎች የፈጠሩት ጥምረት ትብብር ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ወይንም በአጭሩ ትብብር ተብሎ ይጠራል ተብለዋል።
አዲሱ ትብብር ከምርጫ ቦርድም የምዝገባ ማረጋገጫ ማግኝቱ ታውቀዋል
ሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች እየተባሉ የሚጠሩት ጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ ም በምርጫ ጉዳይ ላይ የአዳማውን ፒቲሺን የፈረሙ ፓርቲዎች ናቸው። ከእነዚሁ መካከል የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት ግን 24 ፓርቲዎች ሲሆኑ ካለፈው ጥቅምት 10 ቀን ወዲህ ደግሞ ወደ ቅንጅት ኣድገው ነበር።
ባለፈው እሁድ በተካሔደው የጋራ ጉባዔ ላይ ደግሞ 10 ፓርቲዎች የመመስረቻ ጽሁፍ የመተዳደሪያ ደንብ እና መለስተኛ የድርጊት ፕሮግራም በመፈረም አቶ አለሳ መንገሻ የጌድኦ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር እና የአዲሱ ትብብር ኣስተባባሪ ኮሚቴ እንዳስረዱት ትብብር ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ወይንም በአጭሩ ትብብር በሚል መጠሪያ መቀናጀታቸውን ኣውጀዋል።
በእርግጥ የመድረክ አባል ድርጅቶች ለመቀናጀት ቴክኒካዊ ችግሮች ስላሉባቸው እንጂ ለመተባበር ዝግጁ መሆናቸውም ተጠቅሰዋል። መድረክ ውስጥ ያለው ቴክኒካዊ ችግር ደግሞ አቶ አለሳ እንደሚሉት መድረክ ግንባር በመሆኑ በመተዳደሪያ ደንባቸው መሰረት ኣንድ የመድረክ አባል ድርጅት ከሌሎች ድርጅቶች ጋር መዋሀድ እንጅ በትብብር ደረጃ መቀናጀት ስለማይችል ነው ተብለዋል። የመድረክ አባል ድርጅቶች የውስጥ ችግራቸውን ከፈቱ በአዲሱ ትብብር በኩል አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም አቶ አለሳ ኣስምረውበታል።
የመድረክ አባል ድርጅቶችን ሳይጨምር በአዲሱ ትብብር ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ውስጥ ካልተካተቱት መካከልም ስማያዊ ፓርቲን ጨምሮ የሲዳማ ህዝብ ዓርነት ንቅናቄ እና የጉራጌ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ይገኙበታል።
ኣሁን ትብብር ፈጥረው እስከ መዋሀድ ልንሄድ እንችላለን የሚሉት ፓርቲዎች ኣንዳንዶቹ ኣገራዊ ፓርቲዎች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ብሔራዊ ፓርቲዎች ናቸው። ይህንኑ ጉዳይ በማንሳት የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በኣንድ ወቅት እሳት እና ውሃ እንዴት አብሮ ለመስራት እንደሚስማሙ ኣይገባኝም ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን አቶ አለሳ ግን በዚህ ኣይስማሙም።
ምንም እንኩዋን የመጫወቻው ሜዳ ችግር እንዳለበት ቢገባንም በህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች ላይ ከኢህኣዲግ ጋር ልዩነት የለንም የሚሉት አቶ አለሳ መንግስት ህገ መንግስቱን እንዲያከብር ተስፋ ሳንቆርጥ እና ሳንታክት ታግለን ህዝባችንን ኣንቀሳቅሰን ለውጥ ለማምጣት እንሰራለን ብለዋል።
No comments:
Post a Comment