Wednesday, October 9, 2013

ወጣቶችን የማደኑ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ወጣት ወይንሸት ስለሺ በትላንትናው እለት ከምሽቱ 1፡00 በፖሊስና ደህንነቶች ተይዛ ፖሊስ ጣቢያ በግድ እንድትሔድ ተደረገ

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መስከረም 19 ቀን 2005 ዓ.ም ባካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ሳቢያ በሰልፉ ላይ የነበሩ ወጣቶችን በተለይም በእለቱ ጎልትው ይታዩ የነበሩ ወጣቶችን ለመያዝ ፖሊስና ደህነት ነን የሚሉ ሲቪል ለባሾች የአደን ስራውን አጠናክረው ቀጥለውበታል በትላንትናው እለት ማለትም በ28/01/2006 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 የአዲስ አበባ ዞን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፀሀፊ የሆነችውን ወጣት ወይንሸት ስለሺን እስታዲዮም አካባቢ ታክስ ለመሳፈር ስትል አንድ የሲቪል ልብስ የለበሰና አንድ የፓሊስ ልብስ የለበሰ ዘገየ የሚል መታወቂያ ካርድ የያዘ ፖሊስ ለምርመራ ትፈለጊያለሽ በማለት ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንድትሔድ ለማስገደድ ቢሞክሩም ‹‹ህጋዊ ዜጋና ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ ያለኝ በመሆኑ የመጥሪያ ወረቀት አለበለዚያ የፍርድ ቤት ማዘዣ ሊደርሰኝ ይገባል እንጂ ማንም እንደፈለገ ተከተይኝ ስላለ እንደበግ ተከትዬህ የምሄድ አይደለሁም መብትና ግዴታዬን የማውቅ ዜጋ ነኝ››አልሄድም በማለቷ ግርግር የተፈጠረ ሲሆን በመጨረሻም በሀይል በማስገደድ ቂርቆስ አካባቢ ወደሚገኝ ፓሊስ ጣቢያ እንደወሰዷትና በወረቀት የተፃፈ ስም ዝርዝር በማውጣት ስሟን እንደገለፁላትና ከሚፈለጉት የአንድነት አባላት መካከል እንዷ እንደሆነች እንዲሁም የሰልፉ እለት ቱታ ለብሰው ከነበሩ ወጣቶች መካከል አንዷ መሆኗንና የወንጀለኛ መቅጫ ህጉን የሚፃረር ድርጊት አንቺና ግብርአበሮችሽ ፈፅማችኋል በዚህም አንለቅሽም የሚሉ ማስፈራሪያና ዛቻዎችን ያደርሱባት እንደነበር የገለፀች ሲሆን ያደረግነው ድርጊት በአደባባይ እንጂ በስውር አይደለምና ወንጀል ሆኖ የሚታይ ከሆነ የፈለጋችሁትን እርምጃ መውሰድ ትችላላችሁ የእኛ መሰረት አሁን በስራ ላይ ያለው ህገመንግስት እንጂ ሌላ መመሪያን ወይም ደንብን መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ነገም ሆነ ከነገ ወዲያ ተመሳሳይ የትግል ስትራቴጂዎችን እንጠቀማለን አይሆንም የምትሉ ከሆነ አሁንም እዚሁ የፈለጋችሁትን ማድረግ ትችላላችሁ ፈርቼ ወደኋላ አልመለስም በማለት አቋሟን እንደገለፀችና በዚህም ምክንያት የተለያዩ የስድብና የማስፈራሪያ ቃላቶችን ይጠቀሙ እንደነበር ከዛም ከምሽቱ 3፡00 ላይ መውጣት እንደምትችል ተገልፆላት ከጣቢያው ብትወጣም ትራንስፖርት ማግኘት ባለመቻሏ በጨለማ በእግር ወደቤቷ ለመሄድ መገደዷን ገልፃለች፡፡ወጣት ወይንሸት በ2005 ዓ.ም ግልፅ ደብዳቤ ለከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በሚል በፃፈችው የጋዜጣ ፅሁፍ ሳቢያ በደህንነቶች ታፍና በመወሰድ የኤሌክትሪክ ሾክና በዱላ እስከመደብደብ የደረሰ ሰብአዊ መብት ጥሰት እንደተፈፀመባት ይታወቃል፡፡

No comments:

Post a Comment