Monday, April 29, 2013



በኖርዌይ የወያኔዋ አምባሳዶር ዳግም በፖሊስ ውሳኔ አዳራሽ ለቀው እንዲወጡ ተገደዱ ።
በአባይ ግድብ ስም ገቢ ለማሰባሰብ በኖርዌይ ሁለት ከተሞች ፕሮግራሞች ነበሩ ። በ አፕሪል 20 ,2013   በስታቫንገር ከተማ የነበረውን ዘገባ እንደ ተከታተላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ። በዚህ ውርደት የተሸማቀቁት የወያኔዋ አምባሰደር  ፌደራል እና አጋዚ ጦር በሌለበት ቦታ ተገኝተው አፕሪል 28 , 2013  በኦስሎ ከተማ ለሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ያለ ተቃውሞ እንዲካሄድ ሞክረው ነበር ። ነገር ግን ፈጽሞ አልተቻለም ። የለመዱትን ቅሌት ከነተከታዮቻቸው ተከናንበዋል ።በፖሊስ ውሳኔ አዳራሽ ለቀው እንዲወጡ ተገደዱ !!!  ለነገሩ ቅሌት ብርቃቼዉ አይደለም !
በዚህ ድራማ ላይ የነበሩትን ምጸቶች ላካፍላችሁ
ምጸት  አንድ – በአባይ ስም ግድብ ገቢ ለማሰባሰብ  ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ዉስጥ አዳራሽ መከራየት ለምን አስፈለገ  ???? ቢሆንም የትም ቢደበቁ ከውርደት አልተረፉም !
ምጸት ሁለት ፦ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጋብዘው ሆድ አደር እና ባንዳዎችን እየመረጡ ማስገባት ተሞከረ ።
ምጸት ሶስት ፦ ለህዝብ ሲያስተዋውቁት የነበረው አድራሻ በ አንድ ሰዐት ዉስጥ ወደ ሌላ አድራሻ መቀየር ።
ምጸት አራት ፦ ተቃዋሚ ወይም ኤርትራዊ ብለው ጥገኝነት ጠይቀው ለወያኔ መጠቀሚያ መሆን ።
ወደ አዳራሹ ለመግባት ብዙ እንቅፋቶች አዘጋጁ ። ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሆቴሉ በር ላይ ተሰባሰበ ፤ ድምጹን ማሰማት ጀመረ ። ፖሊስ ተጨማሪ ሃይል  በሄሊኮብተር ጭምር አመጣ  ፤ ነገሩ ከረረ ። ነገሩ ያላማረው ፖሊስ  ስብሰባው እንዲቋረጥ ወሰነ ። አምባሳደሩዋ በእግሬ አውጭኝ አመለጡ ። ፖሊስ አስራ አንድ የሚሆን ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የኖርዌይ  ዜግነት ያላቸው ጭምር ነገሩን ለማብረድ በቁጥጥር ስር ውለው ነበር  ። የተያዙት የህግ የበላይነት ባለበት ሃገረ ኖርዌይ በመሆኑ ከሶስት ሰአት ቆይታ ቡሗላ በክብር ወደ ኢትዮጵያ ኮሙኒቲ  በመምጣት የደስታ ተካፋይ ሆኑ ።
ከእንግዲ የዉሸት ፋብሪካ የሆነው ኢቲቪ ነጠላ ዜማውን ከሰሞኑ እንሰማለን ። እንደተለመደው  “ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት ሃይሎች ” እያለ በቱልቱላ ጋዜጠኞቹ የህዝብን ጆሮ ሲያደማ እንሰማለን ። ምን ይህ ብቻ የተሰበሰበውንም  ገንዘብ እንደ አስራ አንድ ፐርሰንቱ የልማት ፕሮፖጋንዳ ሊያናፍሱ እንደሚችሉ የሚገመት ነው። ምን ይህ ብቻ “በኖርዌይ የሚኖሩ  አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የአባይን መገደብ ተቃወሙ ” ብሎ እንደሚያቀርብ የሚጠበቅ ነው። ኢቲቪ ምን ይሳነዋል ?
እውነታ ግን የአባይን መገደብ የሚቃወም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የለም ። ነገር ግን አባይ የሚገደበው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀም ከሆነ ፤ ህዝብ ይከበር ነው የምንለው ።   ከአባይ በፊት፦
ዘረኝነት ይገደብ !
ህዝብን ማፈናቀል ይቁም !
ሰብአዊነት  ይቅደም !
በሃገራችን የአፓርታይድ ስርዐት ይወገድ !
የሃይማኖት ነጻነት ይከበር !
አባይን ለርካሽ ፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ ይቁም !
በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች ይፈቱ !
የሙስሊም ድምጽ ይሰማ !
ታሪካዊ ገዳማችን ዋልድባ ይከበር !
በህዝብ የተመረተ መንግስት ይምራን !
የህዝብ ድምጽ ይሰማ !
ነብሰ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ  !  እና ሌሎችን ተያያዥነት ያላቸውን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ነው የተጠየቀው ።
በመጨረሻም  ማለት የምፈልፈው ኖርዌይ የምትኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ዳግም አኮራችሁን !!! ከእናንተ  ሌላው የሚማረው ነገር አለ በተለይ አንድነታችሁን ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
OLYMPUS DIGITAL CAMERA
OLYMPUS DIGITAL CAMERA
Image

No comments:

Post a Comment