Thursday, April 4, 2013

ዕድገትና ለውጥ በኢትዮጵያ ወይስ በፍጥነት ወደ ማዕከለኛው ዘመን ጉዞ! (ፈቃዱ በቀለ)


ዕድገትና ለውጥ በኢትዮጵያ ወይስ በፍጥነት ወደ ማዕከለኛው ዘመን ጉዞ! (ፈቃዱ በቀለ)

ዕድገትና ለውጥ በኢትዮጵያ ወይስ በፍጥነት ወደ ማዕከለኛው ዘመን ጉዞ!

(ፈቃዱ በቀለ)
statistics
April 4, 2013 03:58 am By  Leave a Comment
ሰሞኑን ለአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሸን የገንዘብና የዕድገት ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ የሁለት ዐመት ተኩሉን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ውጤት ሲያብራሩ፣ ከአንዳንድ ሁኔታዎች በስተቀር በአጠቃላይ ሲታይ የኢኮኖሚው ዕድገት አመርቂና ጥሩ ውጤት በማሳየት ላይ እንደሆነ በመዝናናት አብራርተዋል። በሳቸውም አገላለጽ፣ የተተለመው የኢኮኖሚ ዕድገት 11 በመቶ ሲሆን፣ ኢኮኖሚው ያስመዘገበው ዕድገት ግን 8.5 በመቶ ብቻ ነው። ወደ ዝርዝር የመስኮች ዕድገት ሲመጣ በሚኒስትሩ አገላለጽ፣ የኢንዱስትሪው ዘርፍ 17.9 በመቶ ያድጋል ተብሎ ሲጠበቅ፣ ያደገው ግን 13.6 በመቶ 2 ብቻ ነው። በእርሻውም መስክ እንደዚሁ የተጠበቀውን ግብ መምታት እንዳልቻለና፣ 8.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ የተጠበቀው 4.5 በመቶ ብቻ እንዳደገ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ለማብራራት እንደሞከሩት፣ የኢኮኖሚው ዕድገት እንደተጠበቀው ግቡን ባይመታም፣ በአጠቃላይ ሲታይ ኢኮኖሚው በጸና መሰረት ላይ የቆመ መሆኑን ተናግረዋል። ይሁንና ይህ የጸና መሰረት ምን እንደሚመስል በንዑስ-መስክና፣ በየመስኮቹ፣ እንዲሁም ደግሞ በየክፍላተ ሀገራት ያሉትን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችና፣ በኢኮኖሚ መስኩ ቢያንስ ባለፈው ሁለት ዐመት ተኩል ስንት የስራ መስክ እንደተፈጠረ ያቀረቡት ምንም ሀተታ የለም። በደፈናው ኢኮኖሚው በጸና መሰረት ላይ የቆመ ነው ብለው ደምድመዋል። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል

No comments:

Post a Comment