የወያኔ አቀንቃኝ የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ የመለስ ዜናዊ ፎቶዎችና ፖስተሮች ይነሱ! ሲል ጠየቀ
ጋዜጣው በትናንትናው እለት ርዕሰ-አንቀጹ የመለስ ፎቶና ፖስተር ያልተሰቀለበትን የአዲስ አበባ ጎዳና ፈልጎ ማግኘት እንደማይቻልና ፎቷዎቹም በሁሉም ስፍራ እንዳለ በመጥቀስ፦ “አሁን ግን ይብቃ! ፎቶዎቹና ፖስተሮቹ ይነሱ!እንላለን” ሲል ጠይቋል።
ሪፖርተር “በፖስተሮቹና በፎቶግራፎቹ መሰቀል ለመነገድ፣ ለማስመሰልና ለማጭበርበር የሚፈልግ ሰው ካለም በቃህ ሊባል ይገባል፡፡ በመለስ ዜናዊ ስም አትነግድ፣ አታጭበርብር፣ አታታል ሊባል ይገባዋል” ብሏል። አስከትሎም፦ “በተግባር የማይደገፍ የፎቶና የፖስተር መለጣጠፍ መንፈስ ግን ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም። ሒደቱም በጊዜ ወሰን ውስጥ ሊከናወን ይገባል፡፡ በመሆኑም የዚህ ዓይነቱን ጨዋታ ይቁም፡ ፎቶዎች ይነሱ፡ ብሏል። በመጨረሻም ቃላትም ትርጉም ይኑራቸው፡፡ በቃላት ድርደራ ብቻ ‹‹ራዕይ›› እና ‹‹ሌጋሲ›› እያልን እየለፈለፍን በተግባር ግን ራዕዩንና ሌጋሲውን የሚፃረር ሥራ የምንሠራ ከሆነ ያስተዛዝባል፣ ብሉአል።
በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያዊያን የመለስ ዜናዊ ስሙ ሲጠራ እያንገሸገሻቸው መሆኑን በተለያዩ መንገዶች ሲገልጹ እየተስተዋለ ነው። ሰው ፎቶውን ማዬት ሰልችቷል፤ አንገሽግሾታል ወደዚያ አንሱልን” “እኔን የናፈቀኝ ቀጥሎ ደግሞ የማን እንደሚሰቀል ማወቅ ነው” ፣ ስለመለስ ዜናዊ መስማቱና ማየቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንገሽግሾታል እጅ እጅ ብሎታል ሀገር ጥሎ ቢጥፋ ደስ ይለዋል ፎቶዎቹን የሚቀዳድድባቸው ጊዜ እየናፈቀ ነው የሚሉት ከብዙዎቹ የተወስዱ ናቸው።

No comments:
Post a Comment