Sunday, March 17, 2013

በአዲስ አበባ አምስቱም መውጫዎች ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ ነው


በአዲስ አበባ አምስቱም መውጫዎች ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ ነው

በአዲስ አበባ 5ቱም መውጫ በሮች ከፍተኛ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ የከተማዋ ፖሊስ የፍተሻውን ምክንያት ለፍኖተ ነፃነት ለመግለፅ ፍቃደኛ
አልሆነም፡፡ ካለፈው አርብ የካቲት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በአምስቱም የአዲስ አበባ መውጫ በሮች ጥብቅ የፖሊስ ፍተሻ እንዳለ 
ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡ የፍተሻው ጥብቅነት ተጓጆችን ግራ እንዳጋባ የሚናገሩት ምንጮቹ፣ በዚህም ምክንያት 
የተለያዩ ተሸከርካሪዎች በመውጫ በሮቹ ላይ ተደርድረው መታጠታቸውን ገልፀዋል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች በፍተሻው ላይ 
ተሰማርተው ከነበሩ የፖሊስ አባላት መረዳት እንደቻሉት ፍተሻው የተጀመረው ስኳርና ዘይት በህገወጥ መንገድ ከከተማዋ 
እየወጣ ነው በሚል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ፖሊሶቹ ባልተለመደ ሁኔታ ጥብቅ ፍተሻ እንዲደርጉ የተሰጣቸው ትዕዛዝ ምክንያት 
ምን እንደሆነ ለማጣራት የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ስለጉዳዩ መረጃ እንዲሰጡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 
መረጃ ክፍልን ብንጠይቅም በህዝብ ግንኙነት ክፍል ካልታዘዝን እንደዚህ ዓይነት መረጃ አንሰጥም ብለዋል፡፡የከተማ 
መስተዳደሩ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት በተደጋጋሚ ስብሰባ ላይ ነን በማለታቸው አልተሳካም፡፡

No comments:

Post a Comment