Saturday, March 30, 2013


ኢህአዴግን “አድርባይ” አመራሮች አስግተውታል

አባላት “አድርባይነት የመመልመያ መስፈርት ነው” አሉ!!
eprdf 9th meeting
ኢህአዴግ አመራሮቹን “አድርባይነት የተጠናወታቸው” ሲል ፈረጀ። የከፍተኛ አመራሮች የግምገማ ውጤት የሆነውን ፍረጃ የሰሙ “የኢህአዴግ አባል ለመሆን አንዱና ዋናው መስፈርት አድርባይነት ነው” በማለት አድርባይነትን የፈጠረውና ያስፋፋው ራሱ ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት እንደሆነ አመለከቱ።
በባህር ዳሩ የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የነበረ ጋዜጠኛ በምሥጢር የላከው ዜና “አድርባይነት” ኢህአዴግን በሚፈታተን ደረጃ መስፋፋቱ መገለጹ አብዛኞችን የድርጅቱን አባላትን አስገርሟል።
ኢህአዴግን የፈጠረውና ከላይ ሆኖ የሚመራው ህወሃት “ነጻ” አመለካከት የማይወድ፣ የነጻ አስተሳሰብ ባህል የሌለው፣ ራሳቸውን የቻሉ ድርጅቶችን፣ ፓርቲዎችንና ማህበራትን አጥብቆ የሚጠላ፣ ሁሉም ለሱ እያጎበደዱ በሚሰፈርላቸው ቀለብ እንዲኖሩ ሌት ከቀን የሚሰራ መሆኑ እየታወቀ ማንን? ለምንና እንዴት አድርባይ በሚል እንደሚፈርጅ አብዛኞች ግራ መጋባታቸውን የደረሰን ዜና ያመለክታል።
ህወሃት በፈለፈላቸው ድርጅቶችና የአፈና ተቋማቱ አማካኝነት በሂደት የኢትዮጵያን አብዛኛውን ህዝብ “አጎብዳጅ” የማድረግና “አድርባይ” ሆነው የሚኖሩትን ቁጥር ማብዛት ዋናው ስትራቴጂው እንደሆነ እየታወቀ “አድርባይነት” እንዴት ለድርጅቱ በሽታ ሊሆን እንደቻለ ያልገባቸው እንዳሉት “አድርባይነት አስጊ ደረጃ ከደረሰ ህወሃት የለፋበትን ያገኘና በስኬት ጎዳና ላይ ለመሆኑ ማሳያ ነውና ስጋት ሊገባው አይገባም” የሚል የለበጣ አስተያየት መስጠታቸው ተጠቁሟል።
በስብሰባው ላይ በይፋ አስተያየት ከሰጡት መካከል አቶ አባይ ጸሐዬ ይጠቀሳሉ። በህወሃት የመከፋፈል ዘመን ቀደም ሲል ከውህዳኑ ጋር ያበሩ መስለው ሁለት ሳንጃ በመያዝ የተጫወቱት አቶ አባይ አሁን አድርባይ ተብሎ የተፈረጀው የኢህአዴግ አባል በሙሉ ወደ መካከለኛ አመራርነት ከተሸጋገረ አደጋው ከፍተኛ እንደሚሆን ተናግረዋል። ቀደም ሲል አባሉ በተመለመለበት ደረጃ ተግባሩን ሲያከናውን ባግባቡ አለመመዘኑ የአደጋው መነሻ ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል።
ኢህአዴግ አባሎቹ “አድርባይና አጎብዳጅ” እንደሆኑበት የገለጸው ስትራቴጂዎችን የመፈጸም ችግር ስላጋጠመው ነው። በጉባኤው ኢህአዴግን ያስደነገጠው ጉዳይ “አደገ” የተባለው የሰብል ምርት ሪፖርት ጉዳይ በዋናነት የሚጠቀስ ነው። አቶ በረከት በቀጥታ ተጠያቂ ያደረጉት ከፍተኛ ደረጃ ያለውን አመራር ነው። እንደሳቸው አባባል ታላቅ ንቅናቄ ሊፈጥር የሚችል የልማት ሰራዊት ያልተገነባበት ምክንያት ሊገመገም ይገባል።
በአሁኑ ወቅት ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ የተመዘገቡ አባላትን ያቀፈውና የቻይናን ኮሙኒስት ፓርቲ ሞዴል ወርሶ “በመለስ ውርስ ወደፊት” እያለ የሚጓዘው ኢህአዴግ አባላቱ “ፊት እያዩ የሚደፉ” መሆናቸው አደጋ መሆኑ ታምኖ መፍትሄ የተበጀለት ቢሆንም የቁርጠኛነትና በራስ ያለመተማመን ችግሩ ሰፊ ስለሆነ በቀላሉ ሊቀረፍ የሚችል እንዳልሆነ ተመልክቷል።
በተመሳሳይ ጉዳይ ሪፖርተር ባቀረበው ዜና አቶ ስዩም መስፍን “የራሱን የውስጥ ዲሞክራሲያዊ ሕይወት ያላስጠበቀ ካድሬ ወይም አመራር የሕዝቡን መብትና ዲሞክራሲ ሊያስጠብቅ አይችልም። ራሱ ነፃ ያልወጣና እየተሸማቀቀ የሚኖር ካድሬ ወይም አመራር የሕዝብን መብትና ጥቅም አስከብራለሁ ብሎ መንቀሳቀስ አይችልም” በማለት አድርባይነትን የፓርቲው አባላት እንዲታገሉ ማሳሰባቸውን አስነብቧል።
ወ/ሮ አዜብ በኢቲቪ አማካይነት በዚሁ ጉዳይ ሲነገሩ እንደተሰማው ችግሩ የቁርጠኛነት ጉዳይ እንደሆነ ገልጸዋል። “የሚባለው” በማለት የሰሙት መሆኑንን በመግለጽ ወ/ሮ አዜብ እንዳሉት “ለእንጀራና ለምደባ” ሲባል አድርባይነት መንገሱን ገልጸዋል። “ያሉት ክፍተቶች ቀላል አይደሉም” በማለት ማብራሪያቸው የሚያስከትሉት ወ/ሮ አዜብ፣ “ራሳችንን ማጽዳት፣ ግለኝነትን መታገል፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን መዋጋት ያስፈልጋል” ካሉ በኋላ አስገራሚ አስተያየት ሰንዝረዋል።
“ቀናነት” እንደሚያስፈልግ በማሳሰብ “ስትራቴጂው አለ። ሲፈጸምም አይተነዋል” አሉ። በዚህ ንግግራቸው ባለቤታቸውን ያስታወሱት ወ/ሮ አዜብ “መቻቻልና አድርባይነት መጥፋት አለበት” የሚል መፈክር አሰምተዋል። በዚህ አላበቁም “እስከመጨረሻው፣ ከሁሉም ነገር ጽድት ብለን፣ በቁርጠኛነት የሚያደናቅፈንን  መቻቻልና አድርባይነት ከመድረክ ላይ መጥለፍ መቻል አለብን” ብለዋል። “መድረክ” ሲሉ የጠሩትን ግን አላብራሩም።
የኢህአዴግ ጉባኤ ሲጠናቀቅ በተለይም የእህል ምርት በሚገባውና በተቀመጠበት ደረጃ ማደጉ ቀርቶ አፈጻጸሙ ደካማ መሆኑ እንዳሰጋው፤ ምናልባትም የከፋ ድርቅ ሊከሰት የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል የሚለው ስጋት ህዝብን እንዳያነሳሳበት መፍራቱን ምንጮች አመልክተዋል።
የመላው ኢትዮጵያዊ ገቢ መጨመር እንዳለበት አቋም ቢያዝም በተለይም ጡረተኞችን፣ የቤት አበል የሚቀበሉ ቤተሰቦችን፣ እጅግ አነስተኛ በሆነ የደሞዝ ጣሪያ የተቀጠሩትንና በቀን ስራ የተሰማሩትን ስለማካተቱ በግልጽ የተባለ ነገር የለም። በኢትዮጵያ በደርግ ጊዜ ቤት ተወርሶባቸው በ30 እና 40 ብር አበል ላለፉት አርባ ዓመታት ተረስተው የኖሩ ዜጎች ቁጥር ቀልል የሚባል አይደለም። እነዚህ ወገኖች ለአፈር ግብር እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ከሚያገኙት አበል በላይ መሆኑም ይታወቃል። አንዳንድ ቦታ ተከራዮች ከባለቤቶቹ (በውርስ ንብረታቸው ከተወሰደባቸው) በላይ ተከራይቶ በማከራየት ተጠቃሚ ናቸው። ዜናውን የላከልን እንዳለው ያገባናል የሚሉ ሁሉ አስቀድመው በዚህ ጉዳይ ላይ ከህዝብ ጋር በመነጋገር እንዲሰሩ አሳስበዋል። (ፎቶ: Ethiopian Herald)

ወ/ሮ አዜብ ተጨንቀዋል!


ወ/ሮ አዜብ ተጨንቀዋል!

“ከሁሉም ነገር ጽድት ብለን እንታገል”
azebb mesfin
አቶ መለስ ከሞቱ ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች ንግግርና መዕልክት የሚያስተላልፉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን መረጋጋት እንደማይታይባቸው ተገለጠ። አሁንም በባለቤታቸው ስምና መንፈስ ሙግትና ማብራሪያ ከማቅረብ አልተላዘቡም። ይህን የሚያደርጉት ከጭንቀት የተነሳ እንደሆነ ተመልክቷል።
ሰሞኑንን በተጠናቀቀው የኢህአዴግ ጉባኤ አቶ መለስን አስመልክቶ ወ/ሮዋ የተናገሩት ንግግር በጭንቀት ውስጥ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ የተናገሩት አብረዋቸው ባህር ዳር ስብሰባ የተቀመጡ የድርጅታቸው ኢህአዴግ “ባልደረቦቻቸው” ናቸው።
በጉባኤው ወቅት አቶ መለስ ዜናዊን በማወደስ የተዘጋጀው “ዝክረ – መውደስ” ታሪካዊ ሰነድ እንዲሆን ከመጽደቁ በፊት ወ/ሮ አዜብ በሰጡት አስተያየት “በፔሮል የሚከፈለው ብቸኛ መሪ መለስ ብቻ ነው” በማለት ራሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በፔሮል በሚከፈላቸው ገንዘብ ብቻ እንደማይኖሩ የሚያመላክት ንግግር አድርገዋል።
መለስ ደመወዛቸው ስድስት ሺህ ብር እንደሆነ፣ ሁለት ሺህ ብር ሲቆረጥ አራት ሺህ እንደሚቀርና “ይህችኑ ገንዘብ” እየተቀበሉ ላገር ሲሰሩ ያለፉ መሪ መሆናቸውን ያወሱት ባለቤታቸው፣ ለመለስ ዝክረ-መወደስ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ይህ መካተት ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
“መለስ ጭንቅላቱን ይዞ ወደዚህች ዓለም መጣ፣ ለዚህች ዓለም፣ አገር፣ ምድር፣ የምታገለግል ሃሳብ አመነጨ” ያሉት ወ/ሮ አዜብ፣ ባለቤታቸው ግለኝነት ሳይፈታተናቸው፣ ቤተሰቦቻቸውን በመርሳት፣ ላገራቸው የለፉና ድህነትን ሲዋጉ ኖረው ያለፉ መሪ መሆናቸው ሊረሳ እንደማይገባው አመልክተዋል። አያይዘውም ሊተኩ የሚችሉ መሪ እንዳልሆኑ በማሳሰብ ዝክረ-መወድሱ ከአቶ መለስ የሕይወት ጉዞ ብዙ ቁምነገሮችን የዘለለና ያልተሟላ ነው ብለውታል፡፡ እንዲሁም መለስ የኢትዮጵያ መሪም ብቻ ሳይሆኑ የአዲስ ራዕይ መጽሄት አዘጋጅ መሆናቸው አለመጠቆሙ አግባብ እንዳልሆነ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
በጉባኤው ላይ የተገኙ የድርጅት አባላት እርስ በርሳቸው ሲለዋወጡ የነበረውን የተከታተሉና በግልጽ ከስርዓቱ ባህርይ በመነሳት ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ እንዳሉት ወ/ሮ አዜብ የቀድሞው ስብዕናቸው አብሯቸው የለም። እንዲያውም በጭንቀት ውስጥ ያሉ ይመስላሉ ብለዋል።
በድርጅቱ አባላት ከላይ እስከታች የባለቤታቸውን ስልጣን ተገን በማድረግ በጣልቃ ገብነታቸውና ከፍተኛ የሚባል ንብረት በማካበት የሚታሙት ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ስም በመደጋገም የሚያነሱት የሚታሙበትን ጉዳይ ለማስረሳት እንደሆነ እርስ በርስ በእረፍት ሰዓት ይወራ እንደነበር እነዚሁ ክፍሎች ተናግረዋል።
“ሴትየዋ በግልጽ ስለሚነሳባት ጉዳይ ለምን አትናገርም” በማለት የጠየቁ እንዳሉ፣ ከዚህም በላይ በድርጅቱ ውስጥ ነግሷል የሚባለው ሙስና በግልጽ ለምን አጀንዳ ሆኖ እንደማይቀርብ አባሉ ውስጥ ውስጡን ሲያወራ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በትክክለኛው መንግድ ለመታደስና ለመጥራት የሙስና ጉዳይ የድርጅቱ ቀዳሚ አጀንዳ መሆን እንዳለበት አስተያየት የሰጡም አሉ።
ወ/ሮ አዜብ ይህ ገብቷቸው ይሁን አይሁን ስለ ባለቤታቸው ድህነት ሲናገሩ “እንደሚባለው ሳይሆን እኛ እንኮራበታለን” ማለታቸው ከሙስና ጋር በተያያዘ ስጋት ስለገባቸው የአባሉን ልብ ለማራራት እንደሆነ አድርገው የወሰዱትም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። በግልጽ ባያብራሩትም “እንደሚባለው” ብለው በመጥቀስ በይፋ እስከማስተባበል መድረሳቸው በባለቤታቸው ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ራሳቸውም የተረዱት አይመስልም፡፡
አቶ መለስ ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ በሚያገኙት መድረክ ስለ ባለቤታቸው ድህነትና ያለ እረፍት ያለፉ መሪ በማድረግ በስፋት የሚናገሩት ወ/ሮ አዜብ፤ ባለቤታቸውን ዴሞክራት መሪ አድርገው ቢስሉም ሪፖርተር በፖለቲካ አምዱ ያስነበበው እውነተኛ ታሪክ የስጋታቸውና የፍርሃታቸው መነሻ እንደሚሆን ከግምት በላይ የሚናገሩ አሉ። ሪፖርተር ወ/ሮ አዜብን በስም ባይጠቅስም፣ “መሐንዲስ አልባው መተካካት” በሚል ርዕስ በጻፈው “(መለስ) በተለያዩ ጊዜያቶች የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ከፖለቲካ ጨዋታ ውጪ ማድረግ ቢችሉም፣ እስከ 1993 ዓ.ም. ድረስ ሥልጣን የግላቸው አልነበረም፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ላይ ሆነው የፈለጉትን ማድረግ የሚችሉ ሰውም አልነበሩም፡፡ በወቅቱ የሕወሓት መሰንጠቅን ተከትሎ የድርጅቱ ርዕዮተ ዓለም ቁንጮ (አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም) የወታደራዊ ስትራቴጂ ባለቤት (የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ስዬ አብርሃ)፣ የፕሮፓጋንዳ ኃላፊው (የቀድሞ የትግራይ ፕሬዚዳንት አቶ ገብሩ አስራት) እና ሌሎች የድርጅቱ ከ10 በላይ ከፍተኛ አመራሮች መወገድን አስከትሏል፡፡ የእነዚህ የድርጅቱ ወሳኝ ሰዎች መወገድን ተከትሎ በመንግሥትም ሆነ በፓርቲ ሥልጣናቸውን የተደላደለና ምንም የፖለቲካ ተቀናቃኝ የሌላቸው ሰው መሆን የቻሉበት ጊዜ ነበር፡፡ የፈለጉትን ሕግ ማውጣት ያልፈለጉትን የመደቆስ ሥልጣኑም ጉልበቱም ነበራቸው” ሲል ሪፖርተር የጻፈላቸው አቶ መለስን ተገን በማድረግ ወ/ሮ አዜብ በሃብት፣ በጣልቃገብነት፣ በተለያዩ ውሳኔዎች፣ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መቆየታቸው በርካታ ወዳጅ ያፈራላቸው ባለመሆኑ የስጋታቸው መጠን ሰፊና ጥልቅ እንደሆነ በስፋት አስተያየት እየተሰጠበት ነው

Thursday, March 28, 2013

ESAT Daliy News Amsterdam March 28 2013 Ethiopia


“የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም

ትልቁን ድርሻ ኤፈርት ይዟል
hidassie dam
“በራሳችን መሐንዲስ፣ በራሳችን ገንዘብ፣ በራሳችን የተባበረ ክንድ እንገነባዋለን” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና “መዓበላዊ መነቃቃት” ፈጠሩበት የተባለለት የ”ህዳሴው” ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ።
ስማቸው ምስጢር እንዲሆን የጠየቁት ዲፕሎማት እንዳሉት 51 በመቶ ባለድርሻ የሆነችው አገር አውሮፓ የምትገኝ የኢትዮጵያ አጋር አገር ናት። ለጊዜው የባለድርሻዋን አገር ስም መግለጽና የውሉን ዝርዝር ይፋ ማድረግ ያልፈለጉት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የፈለገችውን ውሳኔ በራስዋ ለማስተላለፍ እንደማትችል፤ ያላት ድርሻ 49 በመቶ ብቻ በመሆኑ ድምጽን በድምጽ በሚሽረው በአብላጫ ድምጽ ህግ መሰረት በግድቡ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ 51 በመቶ ባለድርሻ በሆነችው አውሮፓዊቷ አገር መሆኑን አብራርተዋል።
49 በመቶ ተብሎ የተገለጸው የድርሻ መጠን ጅቡቲን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች የተቀራመቱት መሆኑን ያመለከቱት የመረጃው ባለቤት፣ አገር ውስጥ ካሉት የንግድ ተቋማት መካከል ኤፈርት ትልቁን ድርሻ መውሰዱን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።
የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ባለሃብቶች፣ ማህበራት፣ ባንኮችና የተለያዩ ግለሰቦች በትዕዛዝ አክሲዮን መግዛታቸውን ያስታወሱት እኚሁ ዲፕሎማት “በግድቡ ዙሪያ ከሚፈራው የጸጥታ ችግር በላይ አስጊው ጉዳይ የባለድርሻዎች ምስጢር መሆን ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
መንግስት ለግንባታው የሚሆን ከፍተኛ ገንዘብ ከአውሮፓዊቷ አገር ማግኘቱን ያመለከቱት የጎልጉል ምንጭ፣ “ከአገር ውስጥ በአክሲዮን ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ ለአገር ውስጥ በጀት ማሟያና ለመንግስት የስራ ማከናወኛ የሚውል ነው” ብለዋል።
መንግስት በተለያየ መድረክ በተደጋጋሚ ፕሮጀክቱ “በአገር ውስጥ ባለሙያ፣ በአገር ውስጥ ሃብት፣ የሚከናወን የህዳሴ መገለጫ ነው” በሚል ብሄራዊ መነቃቃት የተፈጠረበት የአቶ መለስ ማስታወሻ እንደሆነ ከመግለጽ ውጪ ስለ አክሲዮን ድርሻና አክሲዮን ስለገዙ አገራት እስካሁን የተናገረው የለም።
ግድቡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ መገለጹ ይታወሳል። የአባይ ግድብ ከሱዳን ድንበር 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ቤኒሻንጉል ክልል እንደሚገኝ መንግስት የግድቡን ሥራ ይፋ ሲያደርግ ማስታወቁ አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እያለ ፋና በዛሬው እለት ባሰራጨው ዜና “የወንዙን ተፈጥሯዊ የፍሰት አቅጣጫ የማስቀየሩ ስራ እየተሰራ” መሆኑን የገለጸ ሲሆን፥ “ወንዙ ይሄድበት የነበረውን ቦታ 1780 ሜትር ከፍታ ያለው ግድብ የመካከለኛው ክፍል የሚያርፍበት እንደሚሆንም” የፕሮጀክቱ ሥራአስኪያጅ  ኢንጅነር ስመኘው መናገራቸውን ጠቅሷል። “አቅጣጫውን የማስቀየሩ ስራ ከመጭው ክረምት በፊት” ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን መሃንዲሱ ጠቅሰው፥ በቅርቡም ዕውን ይሆናል ብለዋል። ግድቡ ግንባታው የተጀመረበት 1ኛ ዓመት በዓልም ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ፥ እንዲሁም መጋቢት 24 ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ስፍራ በተለያዩ ስነ ጥበባዊ ዝግጅቶችና  ‘መለስ ቃልህ ይከበራል፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብም በህዝባችን ተሳትፎ እውን ይሆናል’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል” በማለት የዜናው ዘገባ ገልጾዋል

ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?

ethiopia
የኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡
ግራዚያኒ በመርዝ ጋዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፏል፤ ከየካቲት 12 ጀምሮ ለቀናት በዘለቀው የበቀል ጭፍጨፋም በአካፋ ሳይቀር በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በግፍ ጨፍጭፏል፡፡ ግራዚያኒ በወቅቱ በሰጠው ትዕዛዝ የፋሺስት ወታደሮች ህይወት ያለውን ተንቀሳቃሽ ፍጥረትን ሁሉ ገድለዋል፡፡ ይህ እሩቅ በማይባል ጊዜ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለእንዲህ አይነቱ ጨፍጫፊ የተገነባን ሀውልት ለመቃወም በወጡ ዜጎች ላይ የወሰዱት የእስር ተግባር እውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው? አስብሎናል፡፡ ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ በተደጋጋሚ ጥፋት ፈፅሟል፡፡ ሀገራችንን የባህር በር ማሳጣትን ጨምሮ ሀገራዊ ስሜትን አንኳሶ ጠባብ የብሔር ስሜት እንዲንሰራፋ አድርጓል፣ ታሪክን ለስልጣኑ መደላድል ሲል በራሱ መንገድ የሚያዘጋጀው የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያን ጠፍጥፎ እንደሰራት ሁሉ ደርግን ለመጣል ካደረገው ትግል ውጪ ያለውን የአርበኞች ተጋድሎ እውቅና ሲሰጥ አይታይም፡፡
መንግስት ለፋሽስቱ ሩዶልፍ ግራዚያኒ የተገነባውን ሀውልት በመቃወም የወሰደው እርምጃ አለመኖሩ ሳያንስ ግራዚያኒን ለማውገዝ የወጡ ዜጎችን በመደብደብና በማንገላታት ማሰሩ አሳፍሮናል፡፡ ለዜጎቻቸው እና ለሚመሯት ሀገር ክብር የማይሰጡ ይልቁንም የጦር ወንጀለኛና ፋሺስትን ለመቃወም የወጣን ዜጋ ማሰርራቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት ወገንተኝነታቸው ለዜጎቻቸው ነው ወይስ ለፋሺስት? የሚል ዘግናኝ ጥያቄ እንድንሰነዝር ያስገድደናል፡፡
በሰልፉ ላይ የተገኙት ሀገር ወዳድ ዜጎች በማን አለብኝነት ሲታሰሩ ድባደባ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የታሳሪዎቹን የኢሜይልና የማህበራዊ ገፅ የይለፍ ቃል (password) በግዳጅ የሚቀበሉ የደህንነት ሀይሎች ተልከውባቸዋል፡፡ ይህን ቅጥ ያጣ አንባገነናዊ ድርጊት የፈፀመው ወይም እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጠው አካል ማንነት ተጣርቶ የማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡ በየምክንያቱ ዜጎችን ማሰር የለመደው አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ምን ያክል ኢትዮጵያዊነትን እየተዋጋ እንዳለም የሚያሳይ ድርጊት ነው፡፡ መሰረቱ ዜጎች በማንኛውም ጉዳይ ላይ የተቃውሞም ሆነ የድጋፍ ሰልፍ ማድረግ እንደሚችሉ ህገመንግስቱ ደንግጓል፡፡ ይህን መብት ዜጎች እንዳይጠቀሙ ያፈነው መንግስት፣ ኢህአዴግን የሚደግፉ አልያም በራሱ ከተጠሩ ሰልፎች ውጪ ዜጎች እንዳይሳተፉ በአሰራር ከልክሏል፡፡ ይህ የመብት ረገጣ ከመሆኑም በላይ በዜጎች መካከል 1ኛ ደረጃና 2ኛ ደረጃ ዜግነትን ያስቀመጠ ነው፡፡
የኢህአዴግን ባናውቅም፣ እኛ ኢትዮጵያውያን በቅኝ ገዢዎች የተዋረደ ስነልቦና የለንም፡፡ ሆኖም የግል ጥቅማቸውን ለማደላደል ሲሉ ለቅኝ ገዢ ጠላቶቻችን ያደሩ ባንዳዎች እንደነበሩ ታሪክ በጥቁር መዝገቡ ሸክፎታል፡፡ ይህን አሳፋሪ ተግባር በጣሊያን ወረራ ወቅት የፈፀሙ ኢትዮጵያውያን ለልጅ ልጆቻቸው የሚያስተላልፉት አንገት ቀና የሚያደርግ ታሪክ አይኖርም፡፡
በዚህም ዘመን ተመሳሳይ ክህደት የሚፈፅሙ አካላት መኖራቸው አይጠረጠርም፡፡
የኢህአዴግ መንግስት በይፋ ለጦር ወንጀለኛውና ለፋሺሽቱ ሩዶልፍ ግራዚያኒ የተሰራውን ሀውልት በይፋ ካለማውገዝ ባለፈ ለተቃውሞ የወጡትን ኢትዮጵያውያን በግፍ የማሰሩን ምክንያት ስንመረምር አንድ መራራ እውነት እንረዳለን፤ ይኸውም ጣሊያን ለኢህአዴግ መንግስት ዋንኛዋ ለጋሽ ሀገር መሆኗ ነው፡፡ ይህ የኢህአዴግ መንግስት ተግባር በስልጣን ዘመኑ በኢትዮጵያዊነት ላይ ከፈፀማቸው ክህደቶች እኩል በታሪክ ጥቁር መዝገብ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡

ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
bottle
አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር!!
በአፋር የቡሬ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የውሃ ችግር መዳረጋቸውን ውሃ የሚሸጥበትን ላስቲክ በፎቶ በማያያዝ የጎልጉል የአይን ምስክር ከስፍራው አስታውቋል። በክልሉ የጎልጉል ተከታታይ የሆኑ እንደገለጹት በመጠጥ ውሃ ችግር እየደረሰ ያለው ችግር ከፍተኛና ህይወትን የሚፈታተን ነው። አካባቢው የጦር ቀጠና ከመሆኑ አንጻርና የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ እንደሆነ ያስታወቀው የአይን ምስክር “እባካችሁ የሚሰማ ካለ ንገሩልን” ሲል ጥሪ አስተላልፏል።
የውሃ ችግር ጊዜ የሚሰጥ ባለመሆኑ አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር ለመግዛት መገዳዳቸውን፣ በዚህም ቢሆን እንደ ልብ ማግኘት እንደማይቻል አመልክቷል። በስፍራው ያለውን የውሃ ችግር አስመልክቶ ሎጊያ የሚገኝ ጎልጉል የአይን ሪፖርተር አስተያየቱን እንዲሰጠን ጠይቀነው የበኩሉን ማጣራት ካደረገ በኋላ ችግሩ መኖሩን አረጋግጦልናል። ቡሬ አካባቢ ያለው ውሃ ችግር በዋናነት የሚጠቀስ ቢሆንም በተመሳሳይ የሚቸገሩና በድርቅ የተመቱ ቦታዎች እንዳሉ አመልክቷል። አንዳንድ የወታደር ተሽከርካሪዎች ውሃ እንደሚሸጡ መረጃ ማግኘቱንም ገልጿል።

መልካም መሪ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው?!


መልካም መሪ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው?!

በታምሩ ገዳ
በየትኛውም የእድገት  ደረጃ  ይሁን የፖለቲካ  አመለካከት ወይም የሃይማኖት  ስርአት  ውስጥ ለሚገኝ ማህበረሰብ ሁነኛ መሪ ማግኘት ከእድሎች ሁሉ ትልቁ እድል ነው  ቢባል ማጋነንPope Francis breaks with tradition and refuses to move into a palatial apartment  አያስብልም፡፡
ለዚህ ይመስላል የሮማ  ካቶሊክ ቤ\ክርስቲያን   በቀርቡ 266ኛዋን  መሪ (ፓፓ ) ለመምረጥ የሃይማኖቱ አባቶች  በቫቲካን ከተማ  በተሰባሰቡበት  ወቅት በ 150,000ዎች  የሚቆጠሩ ምእመናን ቀጣዩ የሃይማኖታችን አባት  ማን ይሆኑ? በማለት  የምርጫው ውጤቱን ለማወቅ  በታላቁ  የቅዱስ  ጴጥሮስ  አደባባይ ተሰባስበው የነበረው፡፡ በዚህ የምንፈስ  ቅዱስ መሪነት  በተካሄደው  የመጪው  የቤተክርስቲያኒቱ  መንፈሳዊ አባት መረጣ    ላይ  የብዙዎቹ ምርጫ ሆነው  የቀረቡት  ከ120 ሚሊዮን  በላይ የእምነቱ ተከታዮች  ያሏት አገር  ብራዚል  ከሳኦ ፖሎ ከተማ  የመጡት  አርክቢሾፕ ኦዲሎ ሺረር ነበሩ፡፡ ለምን? ቢባል አርክ ቢሾፕ ኦዲሎ  በቫቲካን ውስጥ  በሚገኙ  ታላላቅ መነኮሳት  ዘንድ ቀረቤታ ያላቸው አባት በመሆናቸው ነበር ፡፡ይሁንና የምርጫው ስነስርአት ሲጠናቀቅ  አባ ጆርጁ ቤርጎባሌዮ የ1.2 ቢሊዮን ህዝብ(በአለማችን ላይ ያለው የካቶሊክ አማኞች ቁጥር  መሆኑ ነው) አባት ናቸው  የሚለው  ዜና  ሲሰራጭ በዙዎች  አባ ጆርጁ  ቤርጎባሌዮ ወይም አባ ፍራንሲስ ማናቸው?  የሚለው ጥያቄን መጠየቅ ጀመሩ፡፡ የብጹነታችውን ማንነት ጠንቅቀው የሚያውቁት  በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ አዲስ አባት  አገኘን (we have a Pope!)ሲሉ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ለወትሮው ፓፓው  ለህዝቡ የሚጸልዩት ወይም  ህዝቡን የሚባርኩት እርሳቸው ሲሆኑ በአሁኑ ግን እርሳችው ለተስብሳቢው ህዝብ  !እባካችሁ  ጸልዩልኝ!” ሲሉተማጽነዋል፡፡
ላለፉት ስምንት አመታት  በፓፓነት ማእረጋቸው ሲያገለግሉ ቆይተው በህመም  ምክንያት  በቅርቡ ስልጣናቸውን በፍቃደኝነት  የለቀቁት  አቡነ ቤኔዲክት  16ኛውን በመተካት  ሰልጣኑን የተረከቡት  አቡነ ፍራንሲስ አባታቸው ጣሊያናዊ የባቡር  ላይ ሰራተኛ   ሲሆኑ የፋሺስቱን  አገዛዝ  በመሸሽ በእርጀንቲና  ቦነስ አይረስ  ከተማ  ፍሎረነስ  በተባለች  አንስተኛ አካባቤ  መኖር ጀመሩ ፡፡ ልጃቸው  አቡነ ፍራንሲስ በ1936 እኤአ  እዚያው አርጀንቲና ውስጥ ተወለዱ፡፡  ለደሆች እና ለተፈጥሮ ሃብት ተቆርቋሪ ከነበሩት  ከቅዱስ ፍራንሲስ  (ከሃብታም  ቤተሰብ ተወልደው ስለደሃዎች እና ጭቁኖች መብት መከበር ሲሉ በሮም  ጎስቋላ ስፍርዎች  ከመጻጉዎች እና ከደሃዎች ጋር ይኖሩት ከነበሩት የኦሲሱ  ቅዱስ ፍራንሲስ ናቸው ) መጠሪያ ሰያሜ ያገኙት አዲሱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን  አባት  የሆኑት ብጹነታቸው ለደሃዎች   ደህንነት እና  እኩልነት  የሚሟገቱ ታላቅ  አባት እንደሆኑ ብዙዎች ይመስክሩላቸዋል፡፡አባ ፍራንሲስ  በብዙ መልኩ ከቅንጦት እና ምቾት ካለው  አለማዊ  ኑሮ  ይልቅ ዝቅተኛ የሆነ (ሎው ፕሮፋይል) የሚመርጡ ሲሆኑ እነዚህ ምልካም ተግባሮቻቸው  መካከል  በቅዳሴ ጊዜ  በአለማዊ ሰዎች  ዘንድ  ከተዋረዱት  በእግዚአብሄር  ፊት ግን  እኩል ከሆኑት  በቦይነስ አይረስ  ከተማ  ከሚገኙ የቀድሞ ሴትኛ አዳሪዎች  ጋር አብረው  በመጸለይ የሃይማኖታዊ   አባትነታቸውን  እና አርያነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ከዚያም አልፎ ለስልጣነ ክህነታቸው  ሲባል ለግላቸው የተመደበላቸውን ዘመናዊ ሌሞዚን  መኪና  ከእነ ሹፌሩ  እርግፍ አድርገው በመተው (ሹፌሩን በማሰናበት)  እራሳቸው  በህዝብ የማመላለሻ አውቶቡስ  በመገልገል  የደሃው ህዝብ አካል መሆናቸውን   አስመስክረዋል፡፡
(ወደእኔ ይመጡ ዘንድ ህጻናትን አትከልክሏቸው፡-አባ ፈራንሲዮስ ህጻን  ልጅ ታቅፈው)
በአጠቃላይ አኗኗሯቸው  ቀለል ያለ ኑሮን የሚመርጡት ብጹነታቸው የላቲን አሜሪካ  ካፈራቻቸው  የመጀመሪያው  የሮማ  ካቶሊክ ፓፓ ሲሆኑ እርሳችው መመረጥም  በቤተክርስቲያኒቱ  ውስጥ  ላላፉት 1300 አመታት ከአንድ አካባቢ (ከአውሮፓ ብቻ ) ይመጣ የነበረው የፓፓነት  ስርአትን   በመለወጥ  ፋኖ ወጊ ሆነዋል፡፡ ለዚህ ይመስላል በአሜሪካ:  በአፍሪካ  በደቡብ አሜሪካ እና በእሲያ  የሚገኙ  በቢሊዮኖች  የሚቆጠሩ የካቶሊክ እምነት ተከታዩች   እንዲሁም በርካታ የአገር መሪዎች  የብጹነታቸው ምመረጥን (viva il papa !!) በማለት  እንደ ታላቅ ድል የቆጠሩት ፡፡ብዙዎችም ፓፓው ድህነትን በማስወገድ  ዘመቻ እንዲሳተፉ ተማጽነዋቸዋል፡፡ ምንም እንኳን በጹነታቸው  በግላቸው ለምእመናኑ እና  ለደሃው ህዝብ ቅርብ የሆኑ  መንፈሳዊ አባት  ቢሆኑም  የትውልድ አገራቸው  አረጀንቲና በ1970ዎቹ  እኤአ  በነበረው ወታደራዊ  ጁንታ ሳቢያ  አገዛዙን  በመቃወማቸው ብቻ ህይወታቸውን  ላጡ ከ30,000 በላይ  ሰላማዊ
ዜጎች  ቤተክርስቲያኒቱ ተቃውሞዋን አላሰማችም  የሚል ብርቱ  ወቅሳ ቀርቦባታል፡፡ይህንንም ወቀሳ በተመለከተ አቡነ ፍራንሲስ  በ2010 እኤአ በአርጀንቲና ውስጥ ለሚታተም አንድ ጋዜጣ በሰጡት ሰፊ አስተያየት  አርሳቸው ሰዎች እንዳይታሰሩ  ሙያቸውን  በመቀየር እንዲደበቁ ወይም አገራቸውን ጥለው  እንዲሄዱ በማደረግ የታሰሩትም እንዲፈቱ በመሟገት የበኩላቸውን ጥረት ማድረጋቸውን በመግለጽ ውንጅላውን አስተባብለዋል፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት   በአንዳንዳንድ ምግባረ በልሹ ካህናት  የተነሳ ከሙስና  እንስቶ ጨቅላ ህጻናትን  የመድፈር  እና መሰል  ክሶች የቀረቡባት  የሮማ ካቶሊክ  ቤተክርስቲያን  በቤቷ  ውስጥ የተጋረጡት  ችግሮችን  ለመቅረፍ የአቡነ ፍራንሲስ  ወደ ቤተክርስቲያኒቱ በአባትነት  መምጣት  መልካም አጋጣሚ ቢሆንም  አባጣ ጎባጣ የሆኑ መንገዶችን ለምጥረግ  በርቱ  ፈተናዎች ከፊታቸው  የጠብቋቸውል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የብጹነታቸው  የግል ታሪክ ጸሃፊ የሆኑት  ሴርጆ ሩቤን  ሰለአዲሱ ፓፓ  ባህሪ ሲገልጹ  “በእሁኑ ወቅት  በለውጥ ጎዳና ላይ ያለን ይመስለኛል ፡፡ይህ ሁኔታ  ግን ቀላል  አይደለም፡፡ብጹነታቸው ቤተክርስቲያኔቱ  ወደ አደባባዮች(ጎዳናዎች) መውጣት  ስትችል  ብቻ ነው የህዝቡን ችግር መረዳት የምትችልው ብለው ያምናሉ( poor Church for the poor )፡፡” ሲሉ ተናግርዋል፡፡ በደግነታቸው  እና በእውነተኛ ርህራሄያቸው  በበርካታ የካቶሊክ  ማህበረሰብ ዝንድ  እውቅና ያገኙት አቡነ ፍራንሲስ  የፓፓነቱን ስልጣን ከያዙ  በሁዋላ እንኳን  ያ ደግነት የተላበሰ ባህሪያቸውን ባለመለወጥ ሰሞኑን ከእርሳቸው ጋር ለሚኖሩ  ካህናት  እራሳቸው  ምግብ  አብስለው በማዘጋጀት እራት እንዲቋደሱ አድርገዋል፡፡ አርፈውበት በነበረ አንድ ሆቴል ውስጥም ለተስተናገዱበት ወጪ  ከገዛ ኪሳቸው ገንዘብ በማውጣት  ከዚህ ቀደም የነበረውን የቀይ ምንጣፍ እና ልዩ መስተንግዶ ባህልን  ወደጎን አድርገውታል፡፡
ብጹነታቸው  ባለፈው አርብ ጠዋት ላይ  በቫቲካን ከተማ  ከሚገኙ  የዝቅተኛው  ማህበረሰብ ክፍል ከሆኑት  (ብሉ  ኮላርስ )  እየተባሉ ከሚጠሩት  የቤተመንግስታቸው  አትክልተኞች እና  የጽዳት  ሰራተኞች  ጋር  በጋራ  በመሆን  የህብረት ጸሎት ያደረሱ  ሲሆን በስተመጨረሻም አያንዳንዱን ሰራተኛ  በግል አነጋግረዋል፡፡ለወትሮው  ለጳጳስ  ወደ ተዘጋጀው  የክብር መቀመጫ ከመሄድ  ከምእምናን  በስተሁዋላ  በመቀምጥ  እንደተራው ምእመናን  ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ  የጋራ ጸሎት  አድርገዋል፡፡ ሰሞኑን ምእራባዊያኖች ባከበሩት የ40 ቀናት እና 40 ሌሊት  ጾም(የሁዳዴ ጾም)  ክፍል አንዱ የሆነው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ከሃዋራቱ ጋር የመጨረሻውን እራት(Lord’s Supper) የበላበት እና  የሃዋሪያቶቹን እግር በማጠብ  እነርሱም የእርሱን እርያነት እንዲከተሉ ትህትናውን ዝቅ ብሎ  ያሳየበትን  ምእራፍ በማሰታውስ  ብጹነታቸው ካሳል ዴል ማርሞ (Casal del Marmo) በተባለ የወጣት አጥፊዎች እስር ቤት በመሄድ ከህግ ታራሚዎቹ ጋር  አብረው እንደሚያሳልፉ  ከቫቲካን የወጣው መግለጫ  ያመለክታል፡፡
የቤተመንግስት  ነገር ከተነሳ  ከላይ እንደተገለጸው  ቀላላ ኑሮን ዘወትር የሚመርጡት  ብጹነታቸው አሁንም ወደ ቫቲካን  ተዛውረው  “በቤሊዮን የሚቆጠረው  ምእመናን አባት በመሆኖት ለክብሮት ሲባል የቀድሞው የአቡነ ቤኔዲክት 16ኝውን  ሆነ የቀደምት አባቶች ቤተመንግስትን ይረከቡ” ቢባሉም አሻፈረኝ በማለት  በፓፓው ምርጫ ሰሞን እዚያው ቫቲካን ውስጥ አርፈውበት በነበረው ባለ ሁለት ክፍል ሆቴል ውስጥ  ለጊዜው መቀመጥን  መምረጣቸው ተነግሯል፡፡ይህ ማለት ቤተመንግስቱን ሙሉ በሙሉ አይጠቀሙሙበትም ማለት ሳይሆን  ከመደበኛ ስራዎቻቸው መካከል አንዱ የሆኑት እንግዶችን ለምቀበል ስብስባዎችን ለማካሄድ  ወደ ጽፈት ቤታቸው ጎራ ማለታቸው አልቀረም፡፡  አብዛኞቹ ባለስላጣናት ስልጣን በያዙ ማግስት ዘመድ አዝማዶቻችውን  ለመጥቀም ሲሯሯጡ  ወይም ቀደም ሲል አስቀይመዋቸው የነበሩ ወገኖችን ለማባረር አሌያም ከእነአካቴው ለማጥፋት ላይ ታች በሚሉበት   አሁን ባለንበት በ21ኛው  ክ\ዘመን  በየትኛውም ጎራ ይሁኑ በየትኛውም ስፍራ አንደ አቡን ፍራንሲስ  የመሰለ መንፈሳዊ አባት ማግኘት  ለሃይማኖቱ ተከታዩች ብቻ ሳይሆን እምነት ለሌላቸውም(አለማዊያን) ቢሆን  ጥሩ አርእያ መሆኑ የሚቀር አይመስልም፡፡

Wednesday, March 27, 2013


በአረመኔው የወያኔ አገዛዝ በግፍ እስር ቤት የታጎሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸው ታወቀ

ድምጻችን ይሰማ የሚል መፈክር አንግበው ላለፉት አስራ ሶስት ወራት አፋኙን የወያኔ አገዛዝ መቆሚያና መቀመጫ በማሳጣታቸው በጭካኔ እስር ቤት የተጣሉት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ሪፖርት ገለጸ፣ ፣ እንደዘጋቢያችን ሪፖርት በዘረኛውና አረመኔው የወያኔ አገዛዝ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ታፍሰውና ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ በግፍ ታስረው የሚገኙት ሙስሊም የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ፣ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ ባለማወቃቸው በቀለብ እና በልብስ እጦት እየተቸገሩ ነው ብሏል።
ዘጋቢያችን እንደገለጠው በአቃቂ እስር ቤት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ተማሪዎችና መምህራን እስር ቤቱን አጨናንቀው እንደሚገኙ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፣ ከነኝህ ታሳሪዎች ውስጥ እጂግ በርካቶቹ ቶርቸር ( አሰቃቂ ድብደባ) ተፈጽሞባቸዋል። ይህም አልበቃ ብሎ ተማሪዎቹ በአሁኑ ጊዜ የረባ ምግብ አጥተው በመሰቃየት ላይ እንደሚገኙና ልብሶቻቸው በላያቸው ላይ እያለቁባቸው ለእርዛት እየተዳረጉ እንደሆነም ታውቋል።
አሁንም ጭካኔአዊ አሰራው አለማብቃቱና የተለያዩ ታማሪዎች በየጊዜው እየተያዙ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን በማእከላዊ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ከሚገኙት መካከል የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆኑት ኑርየ ካሲም እና ካሊድ ሙሀመድ፣ የጅማ ዩኒቨርስቲዎቹ ያሲን ፈይሞ፣ ሙሀመድ አሚን ከድር፣ እና ጁነዲን ሁሴን፣ የሚዛን ተፈሪው አብዱላኪም አህመድ፣ የወሎ ዩኒቨርስቲዎቹ ጣሂር ሙሀመድ ፣ ሙሀመድ አብዱራሂም እና ሰኢድ ሙሀዲን፣ የጎንደር ዩኒቨርስቲዎቹ ሰኢድ አብርሀም ፣ኦማር ሙሀመድ፣ እና ሊና ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው አብዱላዚዝ ሰኢድ እንዲሁም የአዋሳ ዩኒቨርስቲዎቹ አብደላ ሙሀመድ ይገኙበታል ብሏል።
የሙስሊም ጉዳይ አምደኛ የነበረው ሶሎሞን ከበደ፣ የከሚሴው ዳኢ ጀማል ከበደ፣ የሻሸመኔው ዳኢ አብዱረዛቅ ሼህ አህመድ፣ የከሚሴው ዳኢ ኢክርሀም አብዱ፣ የሀረርጌው ሁሴን ሮባ፣ የድሬዳዋው ሙሀመድ ሀሰን፣ የከምሴው ሁሴን አሊ እና አደም አህመድ አሊ በማእከላዊ እስር ቤት ከታሰሩትና ከፍተኛ ስቃይ ከደረሰባቸው መካከል ይገኙበታል።
የወያኔ ኢህአዴግ ፈረስ የሆነው ሀይለማርያም ደሳለኝ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እርምጃ እንወስዳለን በማለት ሰሞኑን በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የወያኔ ኢህአዴግ ጉባኤ ላይ መዛቱንም ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ

የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ከቀለደበት  የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ እጅግ በጣም የተሻለ አማራጭ ኃይል እንዳለዉና ይህንን ለኢትዮጵያ አንድት፤ ለህዝቦቿ እኩልነትና ነፃነት በቆራጥነት የቆመዉን አማራጭ ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጥነት እንዲቀላቀልና የትግሉን የመጨረሻ ምዕራፍ እንዲጀምር የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አገራዊ ጥሪ አደረገ። የወያኔ ንቀት፤ጥላቻና ህዝብን ማሸበር ማብቃት አለበት ብለዉ አምርረዉ በተነሱ ወጣቶች፤ምሁራንና ወታደሮች በቅርቡ የተቋቋመዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል በላፈዉ ሳምንት እንዳሳወቀዉ በወያኔ ተራ ካድሬዎች መረገጥና እየተገፋ እስር ቤት መወርወር የሰለቸዉ ኢትዮጵያዊና በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ነጻ ፍላጎት ተመስርቶ ህዝብን በታማኝነት የሚያገለግል ስርአት ለመመስረት ምትፈልጉ ኢትዮጵዉያን ሁሉ ወያኔ እስካለ ድረስ ይህንን ህዝባዊ ስርአት ካለመስዋዕትነት ማምጣት አይቻልምና ለድል ሊያበቃን የሚቸለዉን መስዋዕትነት ለመክፈል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተጠንቀቅ እንዲቆም አገራዊ የአደራ ጥሪዉን አስተላልፏል። የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ይህንን ጥሪ ያደረገዉ የወያኔ ህወሀት ተሸካሚ ፈረስ የሆነዉ ኢህአዴግ ካለፈዉ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን ድረስ ባህርዳር ላይ ጌታዉን ተሸክሞ ያካሄደዉን ትርጉም የለሽ የወሬ ጉባኤ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈዉ መልዕክት ነዉ።
ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ በዘረኝነት ገመድ አስሮ እየረገጠ የሚገዛዉ ወያኔ ለዚህ የበቃዉ በዘረኝነትና በጥላቻ አነሳስቶ ያሰታጠቃቸዉ ገበሬዎች በከፈሉት መስዋዕትነት ነዉ ያለዉ ይሄዉ ህዝባዊ ኃይል ሠላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን ከእነዚህ የቀን ጅቦች ለማላቀቅና አገራችንን የእኩሎች አገር ለማድረግ ማንኛዉንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀት አለበት ብሏል። የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረዉ የፍትህ፤የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል ግቡን እንዲመታ የመጀመሪያዉን እርምጃ የወሰደዉና ትግሉ የሚፈልገዉን የደም መስዋዕትነት ለመክፈል የትግሉ ግንባር የመጀመሪያዉ ደጃፍ ላይ የተሰለፈዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ካሁን በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ የወያኔን ዘረኝነት፤ዝርፍያ፤ጥላቻና ንቀት ለማስቆም መፍትሄዉ ከአገር እየተሰደዱ በየባህሩና በየበረሀዉ መሞት ሳይሆን ለስደታችን፤ ለመዋረዳችንና ለመረገጣችን ቀንደኛ ምክንያት የሆነዉን የወያኔ ስርአት እዝያዉ አገር ቤት ዉስጥ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ብቻ ነዉ ብሏል።
የወያኔ እህአዴግ ዘመን አብቅቷል፤ከአሁን በኋላ ዘመኑ የኛ የኢትዮጵያዉያን ነዉ ያለዉ የግንቦት ሰባት ዝብባዊ ኃይሎች ቃል አቀባይ ይህንን የኛ የሆነዉን ዘመን እዉን የምናደርገዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ከዘረኝነት ነጻ የምናወጣዉ እንደአንድ ሰዉ ቆመን በጋራ ስንታገል ነዉ እንጂ የአገር ማዳኑንና የመስዋዕትነቱን አደራ ለተወሰኑ ወገኖች ብቻ በመተዉ አይደለም ብሏል። በመቀጠልም ወያኔን ፊት ለፊት ተፋልሞ ወንድሞቹንና እህቶቹን ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአባቶቹ በአደራ የተረከባትን ኢትዮጵያን ለልጆቹ ለማስተላለፍ የሚናፍቅ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከዛሬ በኋላ ዬት ሄጄ ወያኔን ልታገል የሚል ስጋት እንዳይሰማዉ አሳስቧል።ባለፈዉ ታህሳስ ወር እራሱን ለህዝብ ይፋ ይደረገዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ አያሌ ኢትዮጵያዉያን በየቀኑ እየተቀላቀሉት ሲሆን ይህንን የህዝብ ተገንና አለኝታ የሆነ ኃይል በመቀላቀል የአዲስቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ለመሆን የምትፈልጉ በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገራት የምትገኙ ኢትዮጵያዉያን ህዝባዊ ኃይሉ በተከታታይ ለሚያወጣቸዉ መግለጫዎችና ህዝባዊ ጥሪዎች ምላሽ በመስጠት እንዲትተባበሩ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ጥሪዉን ያስተላልፋል

“አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች ነበሩ”

የዛሬው እንግዳችን አቶ ታዲዎስ ታንቱ ይባላሉ፡፡ አቶ ታዲዎስ የታሪክ ምሁርና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ነፃ ፕሬስ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን በአሁን ወቅት “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ዋና ሰብሳቢ ናቸው ፡፡ በተለይ ለፋሺስቱ ግራዚያኒ ከተሰራው ሐውልት ጋር በተያያዘ አጭር ቆይታ አድርገናል ተከታተሉን፡፡
በጣሊያን የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ
Interview with Ato Tadiwos Tantu
አቶ ታዲዎስ ታንቱ
ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት
ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ
ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድmወሰንን፡፡
ተቃወቅሞውን ለማቅረብ ያነሳሳችሁ ዋነኛ ምክንያት ምን ነበር?
አቶ ታዲዎስ፡- ብዙውን ጊዜ እኔ በጋዜጦች ስለ አርበኞች ታሪክ ያነበብኩትንና ያወቅሁትን እፅፋለሁ፣ እመረምራለሁ፡፡ የጣሊያኑ ፋሽስት ግራዚያኒ ሀገራችንን በመውረር በአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ አሰቃቂ እንደነበር ስለተረዳሁ፤ ያ ሲቆጨኝ ደግሞ አሁን በጣሊያን ሀገር ለእሱ ሙዚየምና ሐውልት የመሰራቱን ወሬ ከኢንተርኔት ምንጮች ስላየሁ በጣም ተናድጄ እንደውም ተቃውሞ ማሰማት አለብን ብዬ ተነሳሁ፡፡ በኋላ ደግሞ እኛም የአንተ ዓይነት ሐሳብ ነበረን ብለው የባለ ዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር አነጋገሩን፡፡ ከዛ በመቀጠል ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ እንስራ የሚል ጥያቄ አቀረበ፡፡ በዚህ ምክንያት ሶስቱ አካላት በጋራ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት ማድረግ ጀመርን፡፡ ስለዚህ ለኢትዮጵያ ጠላት አይደለም ጣሊያን ሀገር ጨረቃም ላይ ቢሆን ሀውልት እንዲሰራ አንፈቅደም፡፡
በጊዜው ሩዶልፍ ግራዚያኒ ወንጀለኛ በመሆኑ የነበረው ፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተገፎ ከወታደርነቱ ተባሮ በጦር ወንጀል ተከሶ 19 ዓመት ተፈርዶበት ቅጣቱን ሳይጨርስ ከእስር ቢለቀቅም እ.አ.አ. በ1955 ዓ.ም. ሞቷል፡፡ ታዲያ ይህ በጊዜው ወንጀለኛ ለተባለው ሰው ሐውልትም ሆነ የመታሰቢያ ሙዚየም ማሰራት ኢትዮጵየውያንን መናቅና የአባቶቻችንን ክብር የሚነካ በመሆኑ ሊሰራለት አይገባም፤ እንደውም ለፈፀመው እልቂት ጣሊያን በቂ ካሳ ስላልከፈለች ካሳ መክፈልና በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ይገባታል የሚል አቋም ይዘን ነው የወጣነው፡፡ ስለዚህ ግራዚያኒ ከነ አዳፋ ታሪኩ ሌላው እንዳይደግም ሲወሳ መኖር አለበት እንጂ እንደ ጀግና ሐውልት ሊሰራለት፣ሊወደስና ሊመሰገን አይገባም እንላለን፡፡
በወቅቱ የደረስው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ይቻላል?
አቶ ታዲዎስ፡- በወቅቱ ግራዚያኒ በፊርማው በግፍ ኢትዮጵያውያንን ያስጨፈጨፋቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ከነደብዳቤው አለ፤ የዚህ ቅጂ እኔም ጋር አለ ይታወቃል፡፡ በተለይ የካቲት 12-14 ቀን 1929 ዓ.ም. ከ30 ሺህ በላይ ዜጎቻችንን በግፍ አዲስ አበባ ላይ እራሱ ግራዚያኒ አስጨፍጨፏል፡፡ ከ250 በላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ መነኮሳትን አስጨፍጭፏል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በ1938 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው አለም አቀፍ ጉባኤ ያቀረበው ሰነድ እንደሚያስረዳው 760,300 ሺህ ዜጎች ወዲያው ሲገደሉ 525,000 ደግሞ ከነቤት ንብረታቸው እንዲቃጠሉ ተደርጎ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ከሁለት ሺህ በላይ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው መነኮሳት ተገድለዋል፣ በርካታ ቅርሶች ተዘርፈው ተወስደዋል፡፡ በርግጥ ከተዘረፉ ቅርሶቻችን መካከል እስካሁን የተመለሰው የአክሱም ሐውልት ብቻ ነው፤ ሌሎቹ ግን አሁንም እዛው ናቸው፤ ሊመለሱልንም ይገባል፡፡ ከዛ ውጭ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶች በወቅቱ ተዘርፈው ተወስደዋል፤ 7 ሺህ ግመሎችም ተገድለውብናል፡፡ ይህም በሰነድ በተደገፈ ማስረጃ ለዓለም አቀፉ የሰላም ጉባዔ የቀረበ ነው፡፡ በወቅቱ ሰነድ ያልቀረበባቸውና ሰፊ ጥናቶች ሊደረግባቸው የሚገቡ በርካታ ጥፋቶች ተፈፅመዋል፡፡
ይህንን ተቃውሞ በዋነኝነት ማቅረብ የነበረበት መንግስት ነበር የሚሉ ወገኖች አሉ፤ እርስዎስ ምን ይላሉ?
አቶ ታዲዎስ፡- እኔም እስማማለሁ፤ ነገር ግን መንግስት ማዘጋጀት ካልቻለ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማዘጋጀት ይችላል፡፡ እኔ እንደሚገባኝ መንግስት ተቃውሞ ያላቀረበው ከጣሊያን የሚያገኘው ዕርዳታ ይቀርብኛል በሚል ይመስለኛል፡፡ እኔ እስከማውቀው ይሄ መንግስት ዕለታዊና የፖለቲካ ገበያ ጥቅምን መሰረት ያደረገ እንጂ ወደፊት ትውልድ የሚኮራበትን ስራ የመስራት ዓላማ የለውም፡፡ ከዚህ በፊት የቀደሙ አባቶቻችን የሰሩትን በጎ ታሪኮች ሲያንቋሽሽ የኖረ መንግስት ስለሆነ እንዲህ ዓይነት የአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ታሪክና ክብር የሚያስጠብቅ ስራ ይሰራል ብዬ አላስብም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለው፣ ብሔራዊ ስሜትን የጠበቀ ህዝባዊ መንግስት ቢሆን ኖሮ ህዝቡን አስተባብሮ ይሄንን ስራ በቀዳሚነት መስራት የነበረበት እሱ ነበር፡፡ ስለዚህ መንግስት ባያደርግም ዜጎች ይህንን ሰልፍ የማድረግ መብት ስላላቸው እኛም ሰልፉን አድርገናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የሀውልት ግንባታውን አለመቃወሙ ምን ያስረዳናል?
አቶ ታዲዎስ፡- ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በእጅ አዙር ለሀውልት ግንባታው እውቅና እንደሰጠ ይቆጠራል፤ ይህንን እኔም አምናለሁ፡፡ ከዚህም በላይ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች የነበሩ ናቸው፡፡ እንደውም ነፃነታችንን ባወጅንበት ሁለት ዓመት ሳይሞላ በአርበኞች ላይ ጦርነት የከፈቱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለግራዚያኒ የጀግና ሐውልት መሰራቱን ባይቃወሙ አይገርመኝም፤ ምክንያቱም እነሱ የማን ልጆች ናቸው? እስኪ በስልጣን ላይ ካሉት (ከኢህአዴግ) መካከል ለሀገሩ እና ለወገኑ ብሔራዊ ስሜት፣ ነፃነትና ክብር የተዋጋ የአርበኛ ልጅ አንድ ሰው ካለ ንገረኝ? አንድም ሰው የለም፡፡ ስለዚህ የባንዳ ልጅ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ በእጅ አዙርም ሆነ በቀጥታ እውቅና በመስጠት ድጋፍ ቢያደርጉ አያስደንቀኝም፡፡
እናንተ ሰላማዊ ሰልፉን ከማድረጋችሁ አንድ ቀን በፊት መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም ስምንት ሰዎች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ክስተት በሰልፉ ወቅት እስር እንደሚኖር አልጠቆማችሁም?
አቶ ታዲዎስ፡- እሱን አውቀንም ነው ሰልፍ የወጣነው፡፡ አንድ ቀን አስቀድሞ ሌሎች ቢታሰሩም መውጣት አለብን ብለን ነው የወጣነው፤ እኛም ብንታሰር ሌሎችም እንደሚወጡ እናውቃለን፡፡ ችግር ይፈጠራል ብለን አልተውንም ፤መተውም የለብንም፡፡ ምክንያቱም ይሄ የሀገርና የወገን ጉዳይ ነውና፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሰልፉ ላይ የተገኙትን ላመሰግን እወዳለሁ፡፡
የታሰራችሁት ምን ወንጀል ሰርታችኋል ተብላችሁ ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- ፍቃድ አልጠየቃችሁም ፣ አላስፈቀዳችሁም በሚል ነው፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ በነበሩ የአጼ ኃይለስላሴ፣ በደርግ ዘመንም ሆነ አሁንም በወያኔ አገዛዝ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ፈቃድ ይጠየቃል የሚል የተፃፈ ህገመንግስትም ሆነ አዋጅ አልነበረም፤የለምም፡፡ ዋናው ከእኛ የሚጠበቀው ሰላማዊ ሰልፍ እንደምናደርግ ማሳወቅና አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግ ማድረግ እንጂ ፈቃድ መጠየቅ አይደለም፡፡ ይህንንም ለእኛ ጥቅም እንጂ እነሱን ለማስደሰት አይደልም፡፡ እኛ ደግሞ የሀገሪቱን የተፃፈ ህግ ተከትለን ሰልፉን ከማድረጋችን 10 ቀናት አስቀድመን አሳውቀናል፡፡
ኢትዮጵያውያንን በግፍ ለጨፈጨፈው ግራዚያኒ የተሰራለትን ሐውልት በመቃወማችሁ በኢትዮጵያ መንግስት መታሰራችሁ ምን ስሜት ፈጠረባችሁ? ለእኛ የበለጠ የተነሳሽነት ስሜት ሰጥቶናል፡፡ ጉዳዩንም አጠናክረን እንድንሄድ ትልቅ የሞራል ድጋፍ ሆኖናል፡፡
ከእስር ሲለቋችሁ ምን ብለው ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- ምንም ሳይሉን ለሁለት ሰው አንዳንድ ዋስ በማስጠራት ለቀውናል፡፡ ምክንያቱን ግን አልነገሩንም፤አላወቅንም፡፡ ከዛ ስትፈለጉ ትመጣላችሁ ብለው በዋስ ለቀውናል፡፡
በታሰራችሁበት ወቅትስ የገጠማችሁ ችግር አለ?
አቶ ታዲዎስ፡- በርግጥ እኔ ላይ ድብደባ አልፈፀሙም እንጂ ተመትተው ፊታቸው በተለይም አፋቸው አካባቢ የደማ ወጣት አይቻለሁ፡፡ ፊታቸው ያባበጠ ወጣቶችንም አይቻለሁ፡፡ ሌሎችንም ወጣቶች እንደደበደቧቸውም ሰምቻለሁ፡፡ በተለይ ደህንነቶች ማታ መጥተው በግል እያስጠሩ በቢሮ ያናግሩ ነበር፡፡ ስራው ግን የፖሊሶች እንጂ የደህንነቶች አልነበረም፡፡ በታሰርንበት ዕለት ያለምግብና ውሃ ቀን ሙሉ እንድንውል ተደርገናል፡፡ በተለይ እስር ቤቱን ስቃይ አራዳ ፖሊስ መምሪያና ጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ያለውን ስታይ ዕቃ ለማስቀመጥ ሆነ ለሌሎች እንሰሳቶች ለአንዲት ደቂቃ እንኳን እንዲቆዩበት አይመችም፡፡ እስር ቤቱን ስታይ በጣም ያሳዝናል፤ እዛ የገቡ እኮ ጤነኛ ሆነው የመውጣታቸው ዕድል እራሱ አነስተኛ ነው፤ለበሽታ የሚያጋልጡ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ብቻ በጣም ያሳዝናል፡፡ ይሄ ደግሞ የወንበዴ ስራ ነው፤ ይሄንን መንግስት ማረም አለበት፡፡ ሌላው መርማሪ ፖሊሶችና ደህንነቶች ያልተገቡና ከእስሩ ጋር የማይገናኙ የግል ህይወትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፣ የኢ-ሜይል የይለፍ ቃል ይጠይቃሉ፣… ብቻ ብዙ ነው፡፡ በግል እኔን ደግሞ ፊታቸውን በኮፊያ የሸፈኑና ጥቁር መነፅር ያደረጉ ደህንነቶች ዋስ ጠርቼ ከወጣሁ በኋላ አንተ የአርበኞችን ታሪክ እያነሳሳህ ወጣቶችን እያነሳሳህ ስለሆነ ብታርፍ ይሻልሃል፤ በግል ልናናግርህ እንፈልጋለን እያሉ ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡ እኔ ግን በህጋዊ ደብዳቤ ያውም ያመንኩበት ካልሆነ ብትጠሩኝ አልመጣም፤ አላናግርም ብያለሁ፡፡
ከዚህ በኋለስ ይህን ተቃውሞ ለመቀጠልስ እቅዱ አላችሁ?
አቶ ታዲዎስ፡- አዎ አለን፡፡ ይህ ተቃውሞ ምላሽ አግኝቶ ያሰብነው እስኪሳካ እንቀጥላለን፡፡ ነገር ግን ዝርዝር ሁኔታውን በተመለከተ እያጠናን ስለሆነ ወደፊት ሀገር ውስጥ ያለነው ውጭ ካሉ ወገኖቻችን ጋር በመመካከር ምን መልክ መያዝ እንዳለበት ስንወስን ይፋ እናደርጋለን፡፡

Monday, March 25, 2013


የመለስ ዜናዊ ራዕይና መተካካት ያልተንጸባረቀበት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስብሰባ ተጠናቀቀ

News, Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy.የመለስን ራዕይ ከግቡ ሳናደርስ እንቅልፍ አይወስደንም ብለዉ ሲዝቱ የከረሙት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች “መተካካት” የሚለዉን ዋናዉን የመለስ ፖሊሲ ወደ ጎን ትተዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባካሄዷቸው ስብሰባዎች በአብዛኛው ነባር አመራራቸዉን መርጠዉ ድህረ መለስ ጉዟቸዉን መጀመራቸዉን ዘጋቢዎቻችን ከአዲስ አበባ በላኩልን ዜና ገለጹ፡፡ በዚህ ባሳለፍዉ ሳምንት ዉስጥ አዋሳ፤ መቀሌ፤ አዳማና ባህርዳር ላይ በተካሄዱት የየፓርቲዉ ጉባኤዎች ላይ መለስ ዜናዊ መተካካት ብሎ የጀመረዉ ነባር የፓርቲ ሹማምንትን በአዲስ የመተከት ፖሊሰ እምብዛም በተግባር ባይዉልም አራቱም ድርጅቶች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አንዳንድ ነባር አባላቶቻቸዉን ከፓርቲዉ የስራ አስፈጻሚ ከሚቴ አስወግደዋቸዋል፤  በዚህም መሠረት ደአህዴን ተሾመ ቶጋን፤ ህወሀት ስዩም መስፍንን፤ብርሀኔ ገ/ክርስቶስንና አርከበ ዕቁባይን፤ኦህዴድ  አባዱላ ገመዳን፣ ግርማ ብሩንና ኩማ ደመቅሳን ብአዴን ደግሞ ብርሃን ኃይሉን ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት አሰናብተዋቸዋል።
ሟቹ መለስ ዜናዊ በቀየሰዉ ዕቅድ መሰረት መተካካት እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ቀጥሎ ከ2007ቱ ምርጫ በሁዋላ ነባር የአመራር አባላት ሙሉ በሙሉ ይለቃሉ ተብሎ የተገመተ ቢሆንም በሰሞኑ የፓርቲዎች ስብሰባ እንደታየዉ ግን ነባር ታጋዮች ስልጣናቸዉን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ተደርፈጓል። በ2003 ዓ.ም በተደረገዉ የመተካካት ሹምሽር የኃላፊነት ቦታዉን አጥቶ የነበዉ የብአዴኑ አዲሱ ለገሰ ተመልሶ ወደ ስልጣን የመጣ ሲሆን በቅርቡ በወጣት መሪዎች ይተካሉ ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ በረከት ስምኦን፤ ህላዊ ዮሴፍና፣አባይ ወልዱ ጭራሽ ስልጣናቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸዉ ታዉቋል።
በ2003 ዓም በተደረገዉ መተካካት የመንግስትና የፓርቲ ኃላፊነታቸውን የለቀቁት ስዩም መስፍንና ሌሎች ዘጠኝ የህወሃት አባላት ከጤና ጋር በተያያዘ በራሳቸው ፈቃድ  ድርጅቱን ለመልቀቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የተሰናበቱ ሲሆን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ግን የእነዚህን ሰዎች መሰናበት ከመተካካት ጋር አያይዞ ዘግቧል። በአጠቃላይ ብዙ ዉጣዉረድና ድራማ የታየበት የዘንድሮዉ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስብሰባ ሲጀመር የመለስ ዜናዉን ራዕይ ከግቡ እናደርሳለን በሚል መሪ ቃል የተጀመረ ሲሆን ሲፈጸም ግን በመርገጥ “መተካካት” የሚለዉን የድርጅቱን መስራች አላማና ራዕይ በሌላ ነገር በመተካት ተፈጽሟል።
ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ ማቅረባቸው አጋጣሚ ሳይሆን ከመለስ ህልፈት በሓላ በህወሃት ውስጥ ከተፈጠረው ልዩነት ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ምንጫችን ቢጠቅስም ይህን በተመለከተ ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ብዙዎች እንደሚገምቱት ከአርከበ እቁባይ ጋር ጤነኛ ግንኙነት ያልነበራት  አዜብ መስፍን በዚህ ጉባኤ በድል አድራጊነት ወጥታለች።
ከፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የሚካሄደው የኢህአዴግ ጉባዔ ኃይለማርያም ደሳለኝን በሊቀመንበርነት፣ ደመቀ መኮንን በምክትል ሊቀመንበርነት በድጋሚ ይመርጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
የወያኔ ኢህአዴግ ድርጅቶች ያደረጉትን ሹም ሽር በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ የቀድሞ የሀወሀት ነባር ታጋይ ፡ ምርጫውን “ውሀ ቢወቅጡት ነው” ብለውታል። “ከእነዚህ ሰዎች ምንም የሚጠበቅ ነገር የለም፣ ምን አዲስ ነገር እንደማይፈጥሩም ይታወቃል። የአፈና ስርአቱ እንደሚቀጥል ጥሩ ማሳያ ነው” ብለዋል ታጋዩ

Wednesday, March 20, 2013

Ethiopia 'blocks' Al Jazeera websites


03/18/13

Permalink 08:07:56 pm, by nazret.com, 214 words   English (US) latin1
Categories: Press


Ethiopia 'blocks' Al Jazeera websites
Traffic to English and Arabic websites has plummeted since the network aired coverage of protests in August last year.
Al Jazeera’s English and Arabic websites are reported to have been blocked in Ethiopia, raising fresh fears that the government is continuing its efforts to silence the media.
Though the authorities in Addis Ababa have refused to comment on the reported censorship, Google Analytics data accessed by Al Jazeera shows that traffic from Ethiopia to the English website had plummeted from 50,000 hits in July 2012 to just 114 in September.
Traffic data revealed a similar drop for the Arabic website, with visits to the site dropping to 2 in September from 5,371 in July.
A blogger, who cannot be identified for his own safety, said Ethiopian censors had been targeting Al Jazeera since the Qatar-based network began airing coverage of ongoing protests against the way in which spiritual leaders are elected in the Horn of African nation.
The steep decline in web traffic began on August 2 last year, the same day that Al Jazeera Mubasher aired a forum with guests denouncing the government's "interference" with Muslim religious affairs, and three days after Al Jazeera English published an article detailing deadly ethnic clashes between two of the country's southern tribes

የፍትሕ ሁኔታ በትግራይ (ኣብርሃ ከመቐለ)



ኢ.ኤም.ኤፍ – ይህ በስፍራው ከሚገኘው ኣብርሃ ደስታ የተገኘ የትዝብት ዘገባ ነው። እንዲህ ብሎ ይጀምራል።
ኣንድ
ኣቶ ግርማይ ጀርመን ትናንት ማታ በዋስ ተለቀዋል። በኣክሱም ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ያለ ምክንያት (ወይ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት) ታስረው የሚሰቃዩ ንፁህ ዜጎች እንዳሉ ጠቁመዋል። እስረኞቹ የግል ሚድያዎች በኣክሱም ወህኒ ቤት ያለ መጨናነቅ እንዲዘግቡና እንዲያጣሩ ተማፅነዋል።
በትግራይ የፍትሕ ስርዓቱ የተዛባ ከመሆኑ የተነሳ ወንጀል ፈፅመው የታሰሩ (ለምሳሌ ‘ዓዲ ሃገራይ’ ተብሎ በሚጠራ ኣከባቢ ሁለት ልጆች በግፍ የገደሉ ሰዎች) ጥሩ እንክብካቤ ሲደረግላቸው ምክንያቱ በማይታወቅ (ወይ በፖለቲካ) የታሰሩ ግን ብዙ ችግር እንደሚደርስባቸው ተገልፀዋል።
ሁለት
በትግራይ ‘ፈረስ ማይ’ በሚባል ቦታ ዉሃ ከጠፋ ኣራት ወራት ቢያልፍም የሚመለከተው ኣካል መፍትሔ ሊሰጥ ባለመቻሉ ነዋሪዎቹ ለብዙ ዉሃ ወለድ በሽታዎች መዳረጋቸው ለማወቅ ተችለዋል። ኣስተዳዳሪዎች ለፖለቲካዊ ስብሰባዎች ብቻ እንጂ የህዝብ ማህበራዊ ችግሮች ግዜ እንደማይሰጡ ይነገራል።
ሦስት
በደጉዓ ተምቤን ልዩ ስሙ (ቁሸት) ‘ድንግለት’ (ሀገረ ሰላም ኣከባቢ መሆኑ ነው) በሚባል ኣከባቢ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ወደ ቤተክርስትያን (እንዳ ማርያም) እየሄዱ ፖለቲካ ስለሚሰብኩና ዕዳ ያለባቸው ኣባወራዎች ስለሚያስሩ የኣከባቢው ሰዎች ወደ ቤተክርስትያኑ ላለመሄድ በመኃላ ኣድማ እንደመቱና የቤተ ክርስትያኑ ቄሳውስት ሁኔታው በመረዳት ካድሬዎቹ ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ቢመክሩም ሰሚ ስላላገኙ ወረዳ ሄደው መክሰሳቸው ታውቀዋል።
ኣራት
በውቅሮ ኣከባቢ በሚገኝ ኣንድ ትምህርትቤት ተማሪዎች ለህወሓት ድጋፍ ሰልፍ እንዲወጡ ታዘው ፍቃደኛ ስላልሆኑ፣ በፓርቲው ደጋፊዎችና ገለልተኛ ኣቋም ያላቸው መምህራን ኣነስተኛ ግጭት ተፈጥሮ ትምህርትቤቱ ለኣንድ ቀን ተዘግቶ መዋሉ ታውቀዋል።
ኣምስት
(ከወራት በፊት ነው) ኲሓ ኣከባቢ ነው። ኣስተዳዳሪዎቹ የገበሬዎችን መሬት ወደ ከተማ እንዲገባ ተወስነዋል በማለት ለመውሰድ ሲሞክሩ የገበሬዎቹ ተወካዮች “መሬታችን ኣንሰጥም፣ ወደ ከተማ ኣልገባም፣ ከገባ ግን እንዲገባ የተወሰነበት ሕጋዊ የኣስተዳደሩ ወረቀት ወይ ፕላን ኣሳዩን።” በማለት ተቃውማቸው ያሰሙ ሲሆን ተወካዮቹ ያለ በቂ ምክንያት መታሰራቸው ታውቀዋል።
ስድስት
በእንደርታ ወረዳ የሚገኙ ኣርሶ ኣደሮች መሬታቸው በኢንቨስትመንት ስም ተነጥቀው ስርዓቱ ለሚደግፉ ባለሃብቶች እየተሰጠ ሲሆን ገበሬዎቹ ተደራጅተው ጉዳያቸው ለሚመለከተው ኣካል ቢያቀርቡም መፍትሔ እንዳላገኙ ጠቁመዋል። ማስፈራርያም እየደረሰባቸው ነው።
በመጨረሻ
በትግራይ ኣከባቢዎች ባደረግነው ፖለቲካዊ ተሞክሮ መሰረት (ስለ ኣብዛኛው ነዋሪ ቀለል ባለ ግምገማ መሰረት)
1) ለውጥ ፈላጊ: ኣላማጣ፣ ሑመራ፣ ተምቤን፣ ሽረ
2) ጥሩ የፖለቲካ ግንዛቤ ያለው (ለውጥ ለማምጣት ግን ቅስቀሳ የሚያስፈልገው): ውቅሮ፣ ዓዲግራት፣ ኣክሱም፣ ማይጨው
3) በፍርሃት የሚኖር ህዝብ: እንደርታ፣ ሓውዜን፣ ዓድዋ
ባጠቃላይ በትግራይ ሙስና ሕጋዊ ስራ ‘የሆነበት ሁኔታ ነው ያለው’

Tuesday, March 19, 2013


ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን ቀጥለዋል፣ በትናንትናው እለትም ድምጻቸውን አጠንክረው ሲያሰሙ ዋሉ

ለአንድ አመት ከአድን ወር በላይ ህዝብን ባስደነቀ ስርአት መብታችን ይከበር በማለት የመብት ማስከበር ትግል በማካሄድ ላይ የሚገኙት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ይህኑ በጽናት የጀመሩትን ተቃውሞ በመቀጠል በትናንትናው እለት ድምጻቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ሪፖርት ገለጸ። የሙስሊሞቹ የተቃውሞ ድምጽ አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች ጭምር እንደነበርም የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
እንደዘጋቢያችን ሪፖርት የሙስሊም ኢትዮጵያዊያኑ ተቃውሞ በሻሸመኔ፣ አርሲ፣ ደሴ ፣ ስልጤ እና ሌሎችን ከተሞች ያካተተ እንደነበር ታውቋል።
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን አሁንም በማቅረብ ላይ ያሉት ጥያቄ ግልጽና በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ፣ አመራሮች ይፈቱ፣ አገዛዙ ለጥያቄያቸን መልስ ይስጠን የሚሉ እንደነበሩ ታውቋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአገር ቤት የሚደረገውን ተቃውሞ በመደገፍ በትናንትናው እለት በስዊድን የሚገኙ ሙስሊም እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን በጋራ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው ታውቋል።
በትናንትናው እለት በስቶክሆልም ከተማ በኢትዮጵያ ቆንስላ ፊት ለፊት በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ፣ አፋኙ የወያኔ አገዛዝ ለዘመናት ተከባብሮ የኖረውን ሙስሊም እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያንን በማጋጨት አገሪቱን ለማጥፋት የሚያደርገውን ሩጫ በጽኑ አውግዘዋል።
በእለቱ “ሁላችንም አቡበክር ነን፣ ሁላችንም ያሲን ኑሩ ነን፣ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ፣ በጅሀዳዊ ሀረካት ሙስሊም እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ማጋጨት አይቻልም” የሚሉ መፈክሮች መቅረባቸውን ተያይዞ የደረሰን ዘግባ ያመለክታል።


ጀርመናዊዉ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በወያኔ ጫና ስራቸዉን ለመልቀቅ መገደዳቸዉ ተሰማ

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲን ለረጂም ግዜ በፕሬዚዳንትነት የመሩት ጀርመናዊዉ ፕሮፌሰር ዩኪአም ሄርዚግ ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣኖች በስራቸዉ ላይ ጣልቃ እየገቡ ስላስቸገሯቸዉ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ባስገቡ በሦስት ቀን ዉስጥ መቀሌን ለቅቀዉ ወደ አገራቸዉ መጓዛቸዉን መቀሌ ዉስጥ የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን ከሰሞኑ በላኩልን ዜና ገለጹ። ፕሮፌሰሩ ለምክትል ጠ/ሚነስተር ደመቀ መኮንን ባስገቡት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ላይ ስራቸዉን የሚለቅቁት ባጋጠማቸዉ የጤና ችግር ምክንያት እንደሆነ ቢገልጹም ለመቀሌ ዩኒቨርስቲ ቅርበት ያላቸዉ ብዙ ዉስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ ፕሮፌሰር ሄርዚግ ከኃላፊነታቸው የተነሱት በቅርቡ ዩኒቨርሲቲው ዉስጥ በተካሄደ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግምገማ ፕሬዚዳንቱ ሀላፊነታቸዉን አልተወጡም በሚል በተደረገባቸዉ ግፊት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ፕሮፌሰር ዩኪአም ሄርዚግ ከዚህ ቀደም በሁለት የዩኒቨርስቲዉ ምክትል ፕሬዚዳንቶች አሿሿም ላይ ዩኒቨርሲቲውን በበላይነት ከሚመራው ቦርድ ጋር አለመግባባት መፍጠራቸው የሚታወቅ ሲሆን ሁለቱን ተሿሚዎች በተመለከተ ለቦርዱ የጻፉትን ደብዳቤ በአስቸኳይ እንዲቀለብሱ ማስገደዱ ይታወቃል። አንድ ስማቸዉ እንዳይገለጽ የጠየቁ የዩኒቭርሲቲዉ ከፍተኛ ባለስልጣን ቦርዱ ፕሮፌሰር ሄርዚግ ለምክትል ፕሬዚዳንትነት ያጩዋቸውን ግለሰቦች ሳይቀበልና በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ሳይሰጥበት ለሦስት ወራት ያህል ቆይቶ አሁን ግን ሃያ አራት ሰአት በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ለመሾም መቿኮሉ የሚገርመና ግራ የሚያጋባ ነዉ ብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ቴድሮስ ሓጎስ ለዩኒቨርስቲዉ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ሄርዚግ ከኃላፊነታቸው የተነሱት የትራንስፎርሜሽኑን ዕቅድ በሚገባ በስራ አልተገበሩም በሚል እንደሆነ ሲሆን ከእሳቸዉ ሌላ የዩኒቨርሲቲው ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ምክትል ፕሬዚዳንት ወልፍ ቫን ፊርክስንና በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶክተር ዩአኪም ሌንገርትን ቦርዱ ከኃላፊነታቸው ማንሳቱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ሁለቱም ጀርመናውያን ከኃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያትም የአቅም ማነስና የአፈጻጸም ችግር የሚል መሆኑንም የዩኒቨርሲቲው መምህራን ገልጸዋል፡

30 000 ኢትዮጵያውያንን ለጨፈጨፈው ለግራዚያኒ የተሠራውን ኃውልት መቃወም ያስከብራል!

ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ
4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044, USA
መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ/ም
መግለጫMaps
በኢጣልያ፤ ከሮማ ወደ ምሥራቅ ደቡብ በምትገኝ፤ አፊሌ በምትሰኝ ትንሽ ከተማ፤ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” ለተሰኘው፤ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ ነሐሴ 4 ቀን 2004 ዓ/ም የቫቲካን ተወካይRodolfo Graziani Fascist criminal በተገኙበት የተመረቀለትን የክብር መታሰቢያና መናፈሻ በመቃወም፤ እስከ የኢጣልያ ኤምባሲ ድረስ ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ/ም ስድስት ኪሎ የተሰበሰቡትን 43 ሰዎች፤ ዶር. ያዕቆብ ኃይለማርያምን ጭምር፤ ፖሊስ አፍሶ ማሰሩና በማግስቱ፤ መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ/ም መልቀቁ ታውቋል።
አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን፤ ከነዚሁ ውስጥ በሶስት ቀኖች ብቻ፤ በአዲስ አበባ ከተማ 30፣000 ሕዝብ ላስጨፈጨፈው፤ እነአቡነ ጴጥሮስን፤ የደብረ ሊባኖስን መነኮሳትና ሌሎችንም በጭካኔ ለረፈረፈ፤ እንዲሁም 2000 ቤተክርስቲያኖችንንና 525፣000 ቤቶችን ላስወደመው፤ በተጨማሪም በብዙ አይሮፕላኖች ባስነሰነሰው የመርዝ ጋዝ ብዙ ሕዝብ ከመግደሉ በላይ እጅግ የከፋ የአካባቢ ብክለትና 14 ሚሊዮን እንስሶችን ላወደመው የጦር ወንጀለኛ፤ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ የተሠራውን መታሰቢያ መቃወም ለሐገር የሚያኮራና የሚያስመሰግን እንጂ የሚያሳስር አይደለም።
እንደሚታወቀው፤ ለዚህ ዓመት የየካቲት 12 ክብረ-በዓል፤ የፋሺሽቶችን የጦር ወንጀልና የግራዚያኒን መታሰቢያ በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ፤ 30 ከተሞች፤ ማለት፤ ሮማ፤ ኒውዮርክ፤ ዋሺንግተን ዲ.ሲ.፤ አትላንታ፤ ቴል አቪቭ፤ ወዘተ. የሚገኙ የብዙ ሐገሮች ዜጎች፤ ኢጣልያውያን ጭምር፤ ሰላማዊ ሰልፎች፤ ስብሰባዎች፤ ጸሎቶች አከናውነዋል። አዲስ አበባም የከተማው አስተዳደርና የኢትዮጵያ አርበኞች ማሕበር በእለቱ ለክብረ-በዓሉ መታሰቢያ ማከናወናቸው ታውቋል።
ስለዚህ፤ በኢጣልያ ለጦር ወንጀለኛው ለግራዚያኒ መታሰቢያ እስከ መሥራት የደረሰ የፋሺሽት መንሰራራት ሊያሳስበንና ሊያስቆጨን የሚገባው፤ ዋናዎቹ የግፉ ተበዳዮች የሆንነው እኛ ኢትዮጵያውያን በመሆናችን፤ ሐገራችን አሁንም እየጠበቀች ያለችውን ፍትሕ እንድታገኝ በሰላማዊ ሰልፍ ለኢጣልያ መንግሥት ማስገንዘብ የሚደገፍ እንጂ የሚያሳስር መሆን የለበትም።
በመጨረሻም፤ ኢትዮጵያ ለተፈጸመባት እጅግ መራርና ከባድ ግፍ እስካሁን ድረስ ተገቢውን ፍትሕ ስላላገኘች፤ ድርጅታችን ለሚከተሉት ዓላማዎች እየተንቀሳቀሰ ነው፤
(ሀ) የኢጣልያ መንግሥት፤ የጦር ወንጀለኛውን የግራዚያንን መታሰቢያ እንዲያስወግድ፤
(ለ) በቫቲካንና በኢጣልያ መንግሥቶች ይዞታ የሚገኙ የኢትዮጵያ ንብረቶች እንዲመለሱ፤
(ሐ) የኢጣልያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ተገቢውን ካሣ እንዲከፍል፤
(መ) ቫቲካን፤ ከፋሺሽት ኢጣልያ ጋር ተባብራ በተፈጸመው ወንጀል፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤
(ሠ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦር ወንጀሉን እንዲመዘግብ ነው።
ሐገራችን ላይ ለተፈጸመው የጦር ግፍ በሰብአዊ መብት መከበር የሚያምን ሁሉ በሚያከናውነው የተባበረና የጠነከረ ጥረት ተገቢው ፍትሕ ይገኛል።