ዞን ዘጠኝ እየተባሉ የሚጠሩ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ሊከሰሱ መሆኑ ታወቀ
ትናንት ፍርድ ቤት ቀርበው የ10 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ፣ ጸሃፊ ዘላለም ክበረት፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃነና ኤዶም ካሳየ አርቲክል 19 እየተባለ ከሚጠራው የውጭ ድርጅት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የግብጽ፣ የኤርትራ መንግስትንና የግንቦት7 ትን ተልእኮ ለማስፈጸም ይንቀሳቀሱ ነበር የሚል ክስ ሊመሰርትባቸው እንደሚችል ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል።
መንግስት ወጣቶቹ የቀለም አብዮት ለማስነሳት ከተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ገንዘብ እንደተቀበሉ አድርጎ በማቅረብ፣ በሽብረተኝነት ከተፈረጁት ድርጀቶች ጋር ግንኙነት በመመስረት ወንጀል ሊከሳቸው ማሰቡ ታውቋል።
No comments:
Post a Comment