ኢሳትን እንደ ነፃ ሚዲያ አድርጎ በማሰብ ግድ ነው።
አምባገነኖች የሚገዙትን ህዝብ ለመቆጣጠር ከሚወስዷቸው እርምጃዎች ቀዳሚው የመረጃ ፍሰትን
መቆጣጠር ነው። እነሱ ከሚሉት ውጭ እንዳይሰማ ለማድረግ ወደ ህዝብ ጆሮ የሚደርሱትን ነገሮች
ሁሉ የመቆጣጠር ተግባር ይፈጽማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ውሸትን ደጋግሞ በማውራት እውነት
ለማስመሰል ይተጋሉ። ይህ የአምባገነን ሥርዓቶች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው።
የእስካሁኑ የኢሳት የሥራ ጠባይም ይህንኑ የአምባገነን ሥርዓቶች በገሃድ አመላክቷል ። የተለያዩ የፖለቲካ አስተሳሰብ ያላቸውን፤ ካገር ውጭም፤ ካገር ውስጥም ያሉትን አስተናግዷል። የመንግሥት ባለሥልጣናትንም እየጋበዘ ለማነጋገር ሞክሯል። አንዳዶቹ- ለምሳሌ እንደነ አቶ በረከት ሲሞን ያሉት የኢሳት ጋዜጠኛ ሲደውልላቸው በጆሮው ላይ ቢዘጉበትም!
ከመንግስት ቁጥጥር ነጻ የሆነ የመገናኛ ዘዴ፤ ነፃ ሚዲያ/ፕረስ- ለሀገርና ለሕዝብ ልማት በጣም አስፈላጊ ነው። በተለይ ባሁኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘመን ነፃ ሚድያ እያስገኘ ያለው ጥቅም ብዙ ነው። የኢንፎርሜሽ ቴክሎጅን በሰፊው ተፎካካሪ ሀገሮችን ጥለው እንዲገሰግሱ እየረዳቸው ይገኛል። የሰውን ባጠቃላይ ዓለምንም እየለወጠ ነው።
ለምሳሌ፤ ነፃና ጠንካራ የመገናኛ ዘዴ፤ ነፃ ሚዲያ ተቋም፤ነጻ ፕረስ፤ የግል ቴሌቪዝንና ሬድዮ ጣቢያውች መኖር፤ዲሞክራሲ እንዲስፋፋ (እንዲፋፋ) ይረዳል፤ እንዳውም፤ ዲሞክራሲ ያለ ነፃ ሚዳያ ሊኖር አይችልም። ሁለቱን ነጣጥሎ ማየትም አይቻልም!
ንግድ እንዲስፋፋ፤ የገባያ ፉክክር እንዲኖርና እንዲጠናከር ይረዳል። የገባያ ፉክክር ሲኖር ደግሞ ኢኮኖሚው ያድጋል፤ አገርም ትበለፅጋለች።
እውነት የበላይነት እንዲኖራት ይረዳል::
ቅርስንና ታሪክን ዘክሮና ዘግቦ ለውርስ የማስቀመጫ መሣሪያ ይሆናል።
ዜጎች ለችግሮቻቸው መፍትሄ ለመፈለግ እንዲወያዩ፤ እንዲከራከሩ፤ ይፈቅዳል/ይረዳል። በዚህም የተነሳ ዜጎች ብልህና ጠቃሚ ውሳኔዎችን እንዲወስዱም ይረዳል። ዜጎች ለሕብረተሰባቸውና ለሀገራቸው እድገት ሙሉ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል።
ዜጎች በሀገራቸው ላይ የተፈጥሮ አደጋ፤ ተላላፊ በሽታ (ወረርሽኝ) ሲመጣ ባስቸኳይ ለሕብረተሰቡ መረጃዎችን ለማቅረብ፤ ሕብረተሰብም እንዲያውቃቸው ለማድረግ ይረዳል። ዜጎች እንድተባበሩም፤ የዜግነት ግዴታቸውን በፍጥነትና በጋራ እንዲወጡም የመገናኛ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል።
የተጠፋፉ ዜጎችን፤ቤተሰቦችን፤ መተባበር የሚፈልጉ ሙያተኞችን ያገናኛል። በአካል መገናኘት ያልቻሉትን ሁሉ በቀላሉ ያገናኛል።
መንግሥት ሥራውን በትክክል እንዲሠራ ይረዳዋል; መንግሥት ለሕዝብ ተገዢ እንዲሆን ይረዳዋል። ዜጎች የመንግሥትን መጥፎም ሆነ መላካም ተግባሮች እንዲያዩ፤ እንዲገነዘቡና እንዲቆጣጠሩትም ይፈቅድላቸዋል፤ በአንፃሩም፤ አምባገነኖች ሕብረተሰቡን በተራ ውሼትና ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡን ሊያጠምቁና ሊበርዙ ሲፈልጉ መንገዱን ይዘጋባቸዋል። በዚህም የተነሳ ክፍተቶችንም ይሞላል።
ለነፃነት የሚደረገውን ትግል አቀጣጣይ መሳሪያ ሆኖ ያገልግላል። በጭንቅ ጊዜ (በጭንቅ ዘመን) የሕዝቡን አንድነት ሊያስተባብርና ለጋራ ትግሉ የመገናኛ መድረክ ሆኖ ያገለግላል።
ፖለቲካዊና ህበረተሰባዊ ለውጦች እንዲመጡ/እንዲገኙ ይረዳል፤ አምባገነኖችን ከሥልጣን የማስወገጃ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል፤ የሕብረተሰቦችን፤ የዜጎችን ችሎታ ያዳብራል (ኢምፖወር ያደርጋል)።
ነፃ ሚዲያ ኢንፎርሜሽንን ስለሚያቀብል እውቀት እንዲስፋፋ ይረዳል። ባለፉት 21 ዓመታት እንደታየው፤ በርካታ ሀገሮች አዲሱን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ፈጠራ) ተጠቅመው ሕዛባቸው በሥልጣኔና ዕውቀት እንዲገሰግስ አድርጓል። ደቡብ ኮሪያን ልምሳሌ መጠቀስ ይበቃል።
የግል ቴሌቪዝንና ሬድዮ ጣቢያውች መኖር አማራጭን ይሰጣል። ድምፃቸው ለተዘጋቸው ሀሳባቸውን የመግለጫ መንገድ፤ እንደ እንባ ጠባቂ ሆኖም ሆኖ ያገለግላል።
የመረጃ ማዕከሎችን በመፍጠር ትልቅ ሚናን ይጫውታል። መረጃና የመረጃ ተቋም የጋራ ሀብት ነው። መረጃ የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው። መረጃ ኃይል ነው። መረጃ እውቀት ነው። እውቀትም የጋራ ሀብት ነው!
ከላይ የጠቀስኳቸው የነፃ ፕረስ፤ የነፃ ሚዳያና የመረጃ ተቋም መገኛ የሚያስገኛቸው ከፊል ጥቅሞች ናቸው። እነዚህ ጥቅሞች አንድ የጋራ የሆነ ጠባይ አላቸው። ይኸውም፤ ጥቅማቸው በአብዛኛው ለግል ሳይሆን ለጋራና ለሕዝብ ነው።
ወያኔ/ኢሕአደግ እንደ ኢሳት ያሉ ተቋማትን እንደጦር የሚፈራቸውም ያለምክንያት አይደለም፡፡ መላው ዓለም ለኢኮኖሚውና ለኅብረተሰባዊ ዕድገቱ እየተጠቀመበትና የኤኮኖሚ፤ የፖለቲካዊና የሕብረተሰባዊ እድገቱን በፈጠነ መልክ እያስኬደ ባለበት በዚህ የሥልጣኔ ግስጋሴ ዘመን፤ ወያኔ/ኢሕአደግ የሬዲዮ፤ የሳተላይት ቲቪ ስርጭቶችን፤ የኢንተርኔት፤ የእስካፕና ሌላውን ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴ መዝጋቱ፤ ለመዝጋት መጣሩ፤ መበሰሱ፤ ኅብረተሰቡ በጨለማ ውስጥ እንዲጓዝ ማደረጉ፤ የትምህርት ተቋሟት ጥራት መቀነሱ፤ በጣም የሚያስፍር ነው። በሥላጣን ላይ ያሉት ቡድኖችና ግለሰቦች የቱን ያህል፤ወደኋል የቀሩ መሆናችውን ያሳያል። እነዚህን የረከሱ ኋላ ቀሮች እንድንታገላቸው የሚያስችለን እንደ ኢሳት ያሉ ተቋማትን፤ የመረጃ ማዕከላትን በመመሥረትና በቋሚነት በመደገፍ ብቻ ነው።
በኔ አስተያየት ለመጀምሪያ ጊዜ የዲያስፖራው ሕብረተሰብ የሠራው ውጤታማ ሥራ ኢሳትን ማቋቋሙ ነው። ኢሳት በጨለማ ውስጥ እየማቀቀ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነት ችላጭል ሰጥቶታል። ወደፊትም ይህ የመገናኛ ዘዴ የበለጠ እንድንተባበር፤ ለነጻነታችን የምናደርገው ትግላችን እንዲስምር፤ የሕዝባችን አንድነት እንዲጠነክር የሚረዳን፤ እንዳውም ህወሀት በቆፈረልንና እየቆፈረልን ባለው ጉድጓድ እንዳንገባ፤ እንዳንተላለቅ መገናኛና መወያያ፤ የመፍትሄ መፈለጊያ መደርካችን፤ መሳሪያችን ይሆናል ብዬ አጥብቄ አምናለሁ። የመልካም ዜጎች ትልቁ ሚና እና ትልቁ እርዳታ መሆን ያለበት እንደ ኢሳት ያሉ ተቋማትን መፍጠርና ማስቀጠል ነው።
ኢሳት እንዲቀጥል፤ እንዲያድግ፤ ቋሚ ሆኖ እንዲያገለግለን እያንዳንዳችን፤ ሁላችንም – ማንም ሳይነግረን፤ ማንንም ሳንጠብቅ፤ ማንም ሳይለምነን፤ በባለቤትነት፤ በግል ተነሳሽነትና ሀላፊነት በተሞላው መንገድ፤ በቋሚነት ድርሻችንን መወጣት አለብን ብዬ አምናለሁ። እያንዳንዳችን ኢሳትን ለመጠበቅ ዘብ መቆምም አለብን።
ከኢዮብ
No comments:
Post a Comment