Thursday, February 6, 2014

 የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ እንዴት ይረሳል እንዲህ አይነት በደል . . . . .በላ ንገረኝ እንዴት ይለመዳል የዘር ማጥፋት ወንጀል ። . . . . እባክህ ንገረኝ በደል እንዴት ይለመዳል የሰዉ ስጋ እንደ ክትፎ ሲከተፍ በደል እንዴት ይረሳል አኝዋክ በተኛበት በወያኔ እባብ ሲነደፍ። በደል አንዴት ይረሳል የእርሻ መሬት በሰዉ ገላ ሲደለደል . . . . በደል እንዴት ይለመዳል አኝዋክ በቁሙ ሲገደል መሬቱን ተቀምቶ ስጋዉ በአሩር ሲነደል።
እስኪ አስበዉ ወገኔ በደል እንዴት ይረሳል ቤተሰብ ለእልቂት ሲሰለፍ፤ እንዴት ይለመዳል በደል ባል ሚስቱ ፊት ታስሮ ሲገረፍ አባት እናትና ልጅ ለመታረድ ሲሰለፍ። እባክህ ንገረኝ በደል እንዴት ይረሳል አኝዋክ እንደበሬ ሲጠለፍ አጅና እግሩን ታስሮ ሲገረፍ . . . . . እንዴት ይለመዳል በደል ክቡር የሰዉ ገላ እንደቅጠል ሲረግፍ።
አረ ምነዉ . . . .ምነዉ አልደፈፍር አለ ልባችን አልቆርጥ አለ ሀሞታችን . . . . . እኮ ምነዉ አልሰነዝር አለ እጃችን፤ ወያኔ ዘር ለይቶ ሲፈጀን ሽብርተኛ እያለ ሲፈርጀን ተራ በተራ እየለቀመ ሊፈጀን። ምነዉ . . . አረ ምነዉ . . . . . ምንድነን እኛ በሬ ነን ወይስ ጌኛ ሲረግጡን ሲገድሉን ዝም ብለን የምንተኛ። ማነሽ አንቺ . . . ማነህ አንተ አበሻ ነህ ወይስ ፈላሻ ቱለማ ነህ ሜጫ ገፍተዉ ሲጥሉህ የማትንጫጫ እምትወቀጥ እንደሙቀጫ። እስኪ ንገረኛ ማነህ አንተ? አደሬ ነህ ተጉለቴ ጎጃሜ ነህ ይፋቴ እባክህ ነገረኝ በሞቴ። በልኮ ንገረኝ ጉራጌ ነህ ሲዳማ፤ ሃዲያ ነህ ሱማሌ ምንድነህ ንገረኝ ኦሮሞ ነህ ወይስ አማራ እንዳባቶችህ የማታቅራራ ።
ምንም ሁን ምን ሁሉም መልካም ነዉ . . . ማንነትህ ግን አንድ ነዉ . . . . ኢትዮጵያዊነት ነዉ ….አዎ! ማንነት ኢትዮጵያዊነት ነዉ
ኢትዮጵአዊነት ደግሞ ድፍረት ነዉ
አትንኩኝ ባይነት ጀግንነት ነዉ
ኢትዮጵያዊነት . . . .አኝዋክ ሲገደል አላስገድል ማለት ነዉ . . . አማራ ሲፈናቀል ፈንቃዩን መፈንቀል ነዉ
አዎ! ኢትዮጵያዊነት እንደ እስክንድር ጽናት ነዉ . . . እንደ አንዱ አለም እምቢ ማለት ነዉ
ኢትዮጵያዊነት እንደ መይሳዉ ለአገር መሞት ነዉ …. እንደ ዬኔሰዉ መስዋዕት መሆን ነዉ . .
እንደ ዬኔሰዉ . . . . . . እንደ ዬኔሰዉ . . . . . እንደ ዬኔሰዉ መስዋዕት መሆን ነዉ!

No comments:

Post a Comment