Thursday, November 27, 2014


የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ የወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት ታላቅ ሰላማዊሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ ተካሄደ!!!

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ የወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት በዛሬው እለት ሀሙስ (November 27,2014)  በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሩቅም ከቅርብም በአንድነት በመሰባሰብ ከቀኑ 13፡30 እስከ 15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
DSC_0233DSC_0220DSC_0268
የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ  በአንምባ ገነኑ የወያኔ ቡድን በህገ ወጥ መንገድ ታፍነውና ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም ሲሆን በሰልፉ ስፍራ የተገኙ ሰዎች ሁሉ አቶ አንዳርጋቸው ለዲሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት መከበር ከወጣትነት ጀምሮ የታገለ ታላቅ የሰላም ምሳሌ፣ የፍትህ ተምሳሌት፣ የነጻነት በር ከፋች እንዲሁም አገራዊ ስሜት የተላበሰ አርበኛ እንጂ እስር፣ ድብደባና መሰቃየት የሚገባው ሰው አልነበረም በማለት ለእንግሊዝ መንግስት በኢንባሲው አማካኝነት ዜጋዋን ከአረመኔና ጨካኝ መዳፍ እንድትታደግና ፍትህ እንዲያገኝ  በከፍተኛ ድምጽ አሳስበዋል።
ወጣቶች እጃቸውን በሰንሰለት በማሰር እኛም እንደ አርበኛው አንዳርጋቸው ጽጌና በእስር ቤት የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውን የቁም እስረኞች ነን የሚል ጥልቅ መልእክት አስተላልፈዋል። ብዙ መስራትና መጻፍ የሚችሉ እጆች፣ መናገር የሚችል አንደበት፣ የእውቀት ባለቤት የሆነ አእምሮ ታስረዋልና እኛም ወጣቶች እስረኞች ነን በሚል ውስጣዊ ስሜት ለስዓታት የኖርዌ ብርድና ቁር ሳይበግራቸው እጃቸውን በሰንሰለት በማሰር ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል።
DSC_0185DSC_0193DSC_0208DSC_0323

እንዲሁም ሰልፈኞቹ  የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ድምጽና ስሜት ለኢንባሲው  አሰምተዋል።  ከአሰሟቸው  መፈክሮች መካከል ለአብነት “ UK, were is your citizen, Free Andrgachew Tsige, Andargachew is our icon of democracy, where is your action , stop discrimination among citizens, Yes, we are all Andrgachew Tsige, Brtain dont support terrirost regim in Ethiopia” የሚሉት ይገኙበታል::
ሰልፎኞችም የኢንግሊዝ  መንግሥት የነጻነት ታጋዩን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ከወያኔ እጅ እስካላወጡ  ድረስ ተቃውሞው በቀጣይ እስከ መጨረሻው ድረስ ከዚህ በበለጠ ቁጣና እልህ በተሞላበት ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ ተናግረዋል።  በተመሳሳይም ለአንዳርጋቸው ያላችውን ፍቅርና ክብር በአደባባይ አስመሰክረዋል።
በመጨረሻም በድርጅቱ የተዘጋጀውን  ደብዳቤ በድርጅቱ ሊቀመንበር በአቶ ዮሃንስ ዓለሙ  አማካኝነት ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ ጉዳዩ ትኩረት የሚሻና ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን ለማሳሰብ ቢፈለጉም ተወካይ ሊመጣ ባለመቻሉ ደብዳቤው በበር ጠባቂው አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጓል። በተጨማሪም ደብዳቤውን በኢሜይል በድጋሚ እንደሚላክ ለሰልፈኞች አሳውቀዋል። ወደፊት በሚደረገው ተቃዉሞ ላይ ተወካይ መጥቶ እስካልተቀበለንና አቶ አንዳርጋቸው የደረሱበትን እስካላወቅን ድረስ ከኢንባሲው በር የማንቀሳቀስ መሆኑን ሁሉም በከፍተኛ ድምጽ አሰምተው ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ ከቀኑ 15፡00 ተጠናቋል።

ዛሬም ነገም ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ታልቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ ተካሄደ!!!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ የወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት በዛሬው እለት ሀሙስ (November 27,2014) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሩቅም ከቅርብም በአንድነት በመሰባሰብ ከቀኑ 13፡30 እስከ 15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአንምባ ገነኑ የወያኔ ቡድን በህገ ወጥ መንገድ ታፍነውና ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም ሲሆን በሰልፉ ስፍራ የተገኙ ሰዎች ሁሉ አቶ አንዳርጋቸው ለዲሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት መከበር ከወጣትነት ጀምሮ የታገለ ታላቅ የሰላም ምሳሌ፣ የፍትህ ተምሳሌት፣ የነጻነት በር ከፋች እንዲሁም አገራዊ ስሜት የተላበሰ አርበኛ እንጂ እስር፣ ድብደባና መሰቃየት የሚገባው ሰው አልነበረም በማለት ለእንግሊዝ መንግስት በኢንባሲው አማካኝነት ዜጋዋን ከአረመኔና ጨካኝ መዳፍ እንድትታደግና ፍትህ እንዲያገኝ በከፍተኛ ድምጽ አሳስበዋል።
ወጣቶች እጃቸውን በሰንሰለት በማሰር እኛም እንደ አርበኛው አንዳርጋቸው ጽጌና በእስር ቤት የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውን የቁም እስረኞች ነን የሚል ጥልቅ መልእክት አስተላልፈዋል። ብዙ መስራትና መጻፍ የሚችሉ እጆች፣ መናገር የሚችል አንደበት፣ የእውቀት ባለቤት የሆነ አእምሮ ታስረዋልና እኛም ወጣቶች እስረኞች ነን በሚል ውስጣዊ ስሜት ለስዓታት የኖርዌ ብርድና ቁር ሳይበግራቸው እጃቸውን በሰንሰለት በማሰር ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል።
Like· 

Monday, November 17, 2014

ለሃገር መከላከያና ለፖሊስ ሰራዊቱ ፤ እንዲሁም ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አባላት በሙሉ የቀረበ ሃገራዊ ማሳሰቢያ፤
በጥቂት ፈላጭ ቆራጮች የሚመራው የህወሓት/ኢህአዴግ ሥርዓት ሃገርን የማጥፋትና ህዝብን የመነጣጠል እኩይ ዘመቻ፤ ኤርትራን በማስገንጠል ተጀምሮ፤ ዛሬ ውድ ዜጎቻችን ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬአቸው በግፍ ተገፍተውና በየሜዳው ተወርውረው በረሃብ እየማቀቁ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ መሬትና ሃብት ፍፁም ግዴለሽ በሆነ መልኩ፤ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ብቻ በዉለታ ለባዕዳን ሃገራት አየተሰጠና ይህ ነው የማይባል ፋይዳ በሌለው ቤሳበስቲን አየተቸበቸበ ይገኛል። ለዘመናት በደም ተጠብቆና ተከብሮ የኖረው የማንነታችን መገለጫ አርማችን፤ ሰንደቅ አላማችን፤ ክብር ተነፍጎ በየስርቻው ጨርቅ ነው ተብሎ አየተጣለ ይገኛል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚገነዘበው እነኝህ ጥቂት አምባገነኖች ላለፉት 23 አመታት በሃገርና በህዝብ ላይ በማናለብኝነት ያደረሱትን ግፍና መከራ፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስታስፈጽሙና በቸልተኝነት እንደ ባዳ ስትመለከቱት እንደነበራችሁ ይታወቃል። ይሁንና ይህ ሁሉ በደል ሲደርስ አንጀታችሁ እያረረ ልባችሁ በሃዘን እየተሰበረ ምንም ማድረግ ሳትችሉ የቆያችሁበት ምክንያት ሥርዓቱ ያደርስባችሁ በነበረው ከፍተኛ ተፅዕኖና አፈና መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ይረዳል። ነገር ግን ይህን ጠንካራ የህዝብ እምነት የምታረጋግጡት እናንተና እናንተ ብቻ መሆናችሁ የሁሉም ህብረተሰብ እምነት ነው።
ዛሬ ሁላችሁም በጥልቀት መርምራችሁ በማስተዋል መፍትሄዎችን ልታበጁባቸው ግድ የሚሉ ዘርፈብዙ ችግሮች ከፊት ለፊታችሁ ተደቅነዋል። እስከመቼ የጥቂቶች የበላይነት በሃገራችን ነግሶ ይኖራል!? እስከመቼስ በዚህች ታላቅ ሃገርና በክቡር ህዝባችን ላይ የሚደርሰው በደል እንዲቀጥል እንፈቅዳለን!? እስከመቼስ ጥቂቶች በእናንተ ትከሻና ጉልበት ተጠቅመው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብን ሲጨቁኑ ይኖራሉ!? እስከመቼስ ጥቂት የህዝብ ጠላቶችን ስልጣንና ጥቅም ለማስከበር አገልጋይ ሆናችሁ በዝምታ መኖር ይቻላችሁ ይሆን!? እስከመቼስ በጥቂቶች ቀጭን ትዛዝ የምትወዱትን ንፁህ ወገናችሁን ስታሳድዱና ስትገሉ ትኖራላችሁ!? እስከመቼስ በጥቂት ግለሰቦች ጭፍን ትዕዛዝና በናንተ ፈፃሚነት ብዙዎች ሲሰቃዩና ሲጎዱ ይኖራሉ!? የዚህ ሁሉ ችግር ምንጮች ጥቂት አምባገነን ገዚዎቻችን ቢሆኑም፤ መፍትሄው ግን በጃችሁና በጃችሁ ይገኛል።
ውድ የኢትዮጵያ ልጆች! ዛሬ ይህ ለሃገራችሁ የሚጠበቅባችሁን ሃላፊነት በአግባቡ እንዳትወጡ በተለያዩ አፈናዎች ጠፍንጎ መፈናፈኛ በማሳጣት፤ አዋርዶ የምትወዱትን ህዝብና ሃገር ጎድታችሁ የጥቂት አምባገነኖችን ስልጣንና ጥቅም ለማስጠበቅ አገልጋይና ሎሌ ሆናችሁ እንድትቀሩ እያስገደዳችሁ የሚገኘው ጨቋኝ አገዛዝ፤ በህዝብ ትግል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚወገድበት ወቅት መድረሱ እሙን ሆኗል። ይህ ታላቅ ህዝባዊ ድል የተገኘው እንደው ዝም ብሎ በመመኘት ሳይሆን፤ በመላው ኢትዮጵያውያን በዋነኝነት ደግሞ በወጣት ወገኖቻችሁና ልጆቻችሁ የተገነባው ህዝባዊ ንቅናቄ ባካሄደው በሳል ስትራቴጂ፣ ትግልና፣ መስዕዋትነት መሆኑን እንደምትረዱ እናምናለን። ይሁንና ይህ የተቀደሰ የትግል ጅማሮ ፍፃሜው እናንተን ጨምሮ፤ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብን ነፃነት ሊያረጋግጥ የሚችለውና በውጥኑ መሰረት ለሁሉም እኩል የሆነችና ከቂም በቀል የፀዳች ሠላማዊት ሃገርን መገንባት የምንችለው፤ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ቆራጥ ትግልና ርብርብ መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል። ይህ ህዝባዊ ትግል፤ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ፤ እናንተም የህዝባችሁን ህልውናና የሃገራችሁን ዘለቄታዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ከህዝብ ጎን በቁርጠኝነት ተሰልፋችሁ በፅናት በመታገል፤ ነፃነታችሁን የምታረጋግጡበት ወሳኝና መልካም አጋጣሚ ነው። በመሆኑም በቀጣይ በሚደረገው ህዝባዊ የትግል ሂደት ለብዙሃኑ ህዝብ ከለላ በመሆንና ወገንተኝነታችሁን በተግባር በማሳየት፤ ብሎም ህዝብ የጣለባችሁን ከፍተኛ ሃገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት፤ ታሪካችሁን አድሳችሁ በክብር መዝገብ ላይ ታሰፍሩ ዘንድ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚጠብቅ ተገንዝባችሁ፤ የሚጠበቅባችሁን ታሪካዊ ሃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ እንድትሆኑ ስንል ከታላቅ ሃገራዊ አደራ ጋር እናሳስባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Sunday, October 26, 2014

የኖርዌይ ኦስሎ ወጣቶች ስለአገራቸው ውይይት አካሄዱ

የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የወጣቶች ክፍል ቅዳሜ ጥቅምት 10/2007 ዓም(ኦክቶበር 25/2014) “ለአገር እድገትና ለድሞክራሲ ግንባታ የወጣቶች አስትዋጾ” በሚል ሰፊ ውይይት ከ15:00 እስከ 18:00 ስዓት ተካሄደ።
የመግቢያ ንግግሩ በድርጅቱ ህዝብ ግንኙነት በአቶ አቢ አማረ የውይይቱን ዓላማና አስፈላጊነት ለተሳታፊው በመግለጽ ወጣቶች ውይይቱ ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ እንዲካሄድ አጽንኦት ሰጠው ውይይቱ ቀጥሏል።
OLYMPUS DIGITAL CAMERAOLYMPUS DIGITAL CAMERA
በመቀጠልም የአንድ አገር ቀጣይነት ያለው እድገት የሚለካው በአላት ሃብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን ያንን ተረክቦ በአደራ ለትውልድ ማስተላለፍ የሚችል ትውልዳዊ ትስስር መኖርና ይህንንም እንደ ድልድይ ሆኖ ከአንዱ ትውልድ ወደቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንደሆነ፤ በማንኛውም አገር፣ ጊዜና ዘመን እያንዳንዱ ተተኪ ትውልድ የአገሩ ወራሽ፣ ተተኪና ተረካቢ፣ ጠባቂና ለሚቀጥለውም ትውልድ የማውረስ፣ የማስተላልፍና የማስረከብ ኃላፊነትና ግደታ እንዳለበት፤ ወጣት ለአንድ አገር በሦስቱም ዘርፍ ማለትም በማህበራዊ፣ በምጣኔ ሃብታዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማድረግ እንደሚችል ተረድቶ ወጣቱ ትውልድ በዓላማ፣ በቁርጠኝነት፣ በዕቅድና በመደራጀት ለአገር እድገት፣ ነጻነት፣ፍትህና ዲሞክራሲ መታገልና ለውጥ ማምጣት እንዳለበት በክፍሉ ተወካይ በወጣት ይበልጣል ጋሹ ለውይይት እንደ መነሻ ባቀረበው ሃሳብ ላይ ገልጿል። እንዲሁም የወያኔን አስከፊ፣ ዘረኛና አምባገነናዊ ሥርዓት ለማስገወገድ ወጣቱ ትውልድ የበኩሉን ሃላፊነት ወስዶ ይህን ለአገርና ለህዝብ መቆም እንዳለበት በመግለጽ የውይይት ሃሳቦችን አስቀምጦ ስዓቱን ለውይይት ክፍት አድርጓል።
OLYMPUS DIGITAL CAMERAOLYMPUS DIGITAL CAMERA
በውይይቱም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወጣቱ ለክፉም ለመልካምም የራሱ የሆነ ትልቅ አገራዊ ታሪክ እንዳለው በመግለፅ ወጣቱ እንዴት መታገልና ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ገንቢ አስትያየቶች፣ ምክሮችና አቅጣጫ ተሰጠዋል። ከተነሱትት ሃሳቦች መካከልም በበቂ ሁኔታ መደራጀት፣ በእውቀት እራስን ማብቃት፣ አገራዊ ስሜት መላበስ፣ታሪክን ጠንቅቆ ማዎቅ፣ አንድነት መፍጠር፣ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ስልታዊ እቅድ መከተል፣ አቀራረባችንን እና ትኩረታችን መለየት፣ ቀጣይነት ያላቸው የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት እና ክፍሉን ማደራጀት ከተነሱት አበይት ሃሳቦች መካከል ነበሩ። በተጨማሪም ክፍሉ ከሌሎች የወጣት ህብረት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ ወጣቱን ይበልጥ ማንቃትና ፖለቲካዊ አድማሱን ማስፋትና የወያኔን ጨቋን መንግሥት ሊታገል የሚችልበትን አቅጣጫ ማሳየትና መንደፍ ተገቢ መሆኑን አጽንኦት ተሰጦበታል።
በአጠቃላይ ወጣቶች ለአገር እድገት፣ ለነጻነት፣ ለሰባዊ መብት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ ግንባታ የወጣቱ አስትዋጾ ከፍተኛ መሆኑን ተረድቶ በሁለገብ ትግል ወያኔን/ ሕወሓትን ለማስወገድ የበኩሉን ኃላፊነትና ግዴታ መወጣት እንዳለበት በሥፋት ተገልጿል።
በመጨረሻም በአቶ ልዑል ታደሰ ድርጅቱ የድርጅቱ ጉዳይ ሀላፊ የውይይቱ ሂደት ጥሩና የተሳካ መሆኑን ገልጸው ለክፍሉ በማነኛውም መልኩ ድጋፍ ማድረግና ማጠናከር ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅ መሆኑን መልእክት አስተላልፈዋል። ውይይቱም ቀጣይነት እንዲኖረው በተሳታፊዎች አስትያየት ተሰጦ ውይይቱ ተጠናቋል።
ኢትዮጵያለዘላለም ትኑር !!
የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የወጣቶች ክፍል!!

Wednesday, October 22, 2014

አልበርት አነስታይን ኢኒስቲቲውት በኖርዌይ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖችን ለሁለት ስአታት የቆየ የትግል ስልት ስልጠና ስጠ

  • 891
     
    Share
በቅርብ አመታት በነውጥ አልባ የትግል ስልት ጥቃት ሳቢያ ስልጣናችውን ያጡትን በርካታ የስሜን አፍሪካ ጨቋኝ መንግስታትን እጣ ለወያኔ ለማቋደስ ቆርጠው የተነሱት በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጲያውያንን መስረታዊ ትግል ስልቶችን ለማስተማር በማስብ ዴሴሶን ራዲዮ ኦክቶበር18 2014 ያዘጋጀው ስብስባ ውጤታማ ሆኖ ተጠናቋል
የአልበርት አነስታይን ማህከል ዋና ዳይሬክተር የሆነችው ጀሚላ ራኪብን በመጋበዝ የተካሄደው ስብስባ ሰላሳ የሚጠጉ ኢትዮጲያውያን የተገኙበት ሲሆን ፣ የማእከሉ ዋና ዳይሬክተርም ስፊውን ግዜ በመውስድ ሰለ ማእከሉ መስራች ዶር ጂን ሻርፐ ምርምሮችና ስራዎች አብራርታለች።
ላለፉት ሰላሳ አመታትም በጂን ሻርፐ ጥናቶች እገዛ ውጤት ያስመዘገቡ አገሮችን ነባራዊ ሁኔታ በከፊል አብራርታ ህዝባዊ ነውጥ አልባ ትግል እጅግ መታቀድ ያለበት እንደሆነ በመጠቁም ሲሳካም ለምን እንደተሳካ ሲከሽፍም ለምን እንደከሽፈ ማጥናት እንደሚገባ አስረድታለች በተጓዳኝም በርካታ መስረታዊ ጽንስ ሃሳቦችን የተነተነች ሲሆን ከተስብሳቢው በርካታ ጥያቄዋችም ተነስተዋል በነውጥ አልባ ትግልንና ወታደራዊ ትግልን በማጣመር ሁለገብ የሚባለው የትግል ስልት ጥናት እየተደረገበት እንደሆና አመርቂ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችልም ጠቁማለች ።
ውይይቱም 15: 30 ላይ ቢጠናቀቅም በቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ ተመልሳ በመምጣት ስፋ ያለ ስልጠና እንደምትስጥ ለራዲዬ ክፉላችን አስታውቃለች።
rte

Thursday, October 16, 2014

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ወገንተኝነቱን የሚያሳይበት ወቅት አሁን ነው!

ዘረኛውና ፋሽስታዊው የህወሓት አገዛዝ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝነት በመከፋፈል ሹመቱና ጥቅማ ጥቅሙን ለራሱ ወገን፣ ችግሩንና መከራዉን ግን ለሌላው ኢትዮጵያዊ ያደለ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ሳይማሩና ሳይሰለጥኑ የጄኔራልነት ማዕረጎችን በሙሉ ሰብስበው የወሰዱት የህወሓት አባላት መሆናቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው።
በወያኔ መዳፍ ውስጥ እየተሰቃየች ባለችው ኢትዮጵያችን ውስጥ በዘርም ይሁን በፓለቲካ አመለካከት ከህወሓት የተለዩ ኢትዮጵያዊያን ቢማሩም ቢሰለጥኑም ለከፍተኛ አመራርነት እንደማይበቁ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያየነው ነው። አገዛዙ ቅራኔ ውስጥ በገባባቸው ቦታ ሁሉ እየዘመቱ ሕይወታቸውን እየገበሩ ያሉት ግን በመካከለኛና ዝቅተኛ ማዕረጎች ያሉ ኢትዮጵያዊያን መኮንኖችና ብዙሃኑ የሠራዊቱ አባላት የሆኑ ወታደሮችናቸው። ብዙሃኑ የሠራዊት ክፍል አለቆቹን ከመጠበቅ ባለፈ ድምጹን ከፍ አድርጎ ለመናገር እንኳን የማይፈቀድለት ሎሌ ተደርጓል።
ለኢትዮጵያዊ ወታደር ለህወሓት ሎሌ ከመሆን በላይ የሞት ሞት የለም። ብዙሃኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊቱ አባላት በጥቂት የወያኔ ሹማምንት የሚረገጥ መሆኑ የሠራዊቱን አባላት የግል ስብዕና ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሠራዊቱን ክብር ይነካል። የሠራዊታችን የህወሓት አገልጋይ መሆን የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያን ያዋርዳል። ይህ ዉርደት በዚህ ሁኔታ መቀጠል የለበትም።
ከእንግዲህ ጄኔራሎችና ሌሎችም የበላይ አዛዦች ሁሉ የአንድ አካባቢ ተወላጆች በሆኑበት ሠራዊት ውስጥ ተስማምቶ መኖር መቀጠል እያንዳንዱን የመከላከያ ሠራዊት አባል ሊያሰፍር ይገባል። የህወሓት ጄኔራሎች ጮማ በውስኪ ሲያወራርዱ፤ በህንፃዎች ግንባታ፣ በባንኮች ንግድ፣ በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተሰማርተው ቢዝነሳቸውን ሲያጧጥፉ፣ ምስኪኖቹ የሠራዊቱ አባላት በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአማራና በሌሎች የአገሪቱ ግዛቶች እየተወረወሩ ወገኖቻቸውን የሚፈጁበት ሥርዓት ማብቃት አለበት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ብዙሃኑ አባላት ቤተሰቦቻቸው በችጋር እየተቆሉ የአዛዦቻቸው ሀብት ጠባቂ መሆናቸው ማክተም አለበት።
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የጭለማ ዘመን ታሪክ እያበቃ መሆኑን የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ነው። መሣሪያዎቻቸውን እንደያዙ የነፃነት ኃይሎችን የሚቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨረመ መጥቷል። ሠራዊቱ ከሕዝብ ጎን እንደሚቆም ውስጥ ውስጡን የሚላኩ መልዕክቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። ይህ አበረታች ዜና ነው፤ ግን በቂ አይደለም። ወያኔን ከውስጥም ከውጭም የምናጣድፍበት ጊዜው አሁን ነው። የነፃነት ኃይሎችን መቀላቀያ ጊዜ አሁን ነው፤ በሠራዊቱ ውስጥም በህቡዕ መደራጃ ጊዜ አሁን ነው። ይህን ጊዜ መጠቀም ብልህነት ነው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ጥቂት የህወሓት ጥጋበኞች በብዙሃኑ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ላይ የሚያደርሱት በደል ማብቃት አለበት ይላል። ግንቦት 7፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሙስና የደለቡት፣ ትዕቢተኛና ጨካኝ መሪዎቻቸው ፍጹም ኢትዮጵያዊ ባህርይ የሌላቸው ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች እንደሆኑ በመረዳት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ክንዱን እንዲያነሳባቸው ጥሪ ያደርጋል። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሕዝብም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አንድ ወጥ እንዳልሆነ እና በመካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ ያሉ መኮንኖችና አብዛኞዎቹ ወታደሮች የሕዝብ ወገን መሆናቸውን እንዲገነዘብ ያሳስባል። “አብረን ነው ዘረኛውና ፋሽስቱን ወያኔን ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ አውርደን የምንጥለው” ስንል አብዛኛው የመከላከያ ሠራዊታችን ኢትዮጵያዊ ወገናችን እንደሆነ እና በወደፊቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ውስጥም ጉልህ ሚና እንዲጫወት የምንፈልግ መሆኑን ግልጽ ማድረግ እንሻለን። የመከላከያ ሠራዊቱም የሕዝብ ወገንተኝነቱ በተግባር እንዲያሳይ ጥሪ እናደርጋለን። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ አካል ነው፤ የሕዝብ ወገናዊነቱ በተግባር የሚያሳይበት ትክክለኛ ጊዜ ደግሞ አሁን ነው እንላለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
የወያኔ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም ለጥቂ ተሳቱ
ሀፍረትና ይሉኝታ የሚባሉ ነገሮች በአጠገባቸው ያለ የማይመስላቸው ብልግና ጭካኔ ወገንን ካለ ህግ መግደል ማዋረድ የህዝብ ሀብት በጠራራ ፀሐይ መዝረፍ ለሰው የተስጠ ፀጋ አድርገው የሚቆጥሩትን የወያኔ መንግስት በሔደበት ቦታ ሁሉ መዋረድ ማየትና መስማት የተለመደ ሆኖአል።

በዛሬው አለት በኖርዌ Invest in Ethiopia ተብሎ በ Norwegian-African Business Association አዘጋጅነት በተጠራው ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ወደ ኖርዌ የመጣውን የወያኔ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም ላይ Human right before investment አና የተለያዩ መፈክሮች በማሠማትና የእንቁላል ናዳ በማውረድ የሚንስትሩን አንገት በማስደፋት የኖርጂያንን ፖሊስ አጨናንቀውት ውልዋል

የዚህ የወረበላ የወያኔ መንግስት መውደቂያ አሁን ነው በዘር በሐይማኖት መከፋፈል ያክትማል እጅ ለ እጅ ተያይዘን የነፃነት ዜማ አናዜማለን ኢትዮጵያ የብሔር ቢሔረስቦች አገር እንጂ ያአንድ ብሔር አይደለችም በማለት የተቃውሞ ስልፉን በተሳካ ሁሄታ አጠናቋል http://www.nrk.no/nyheter/1.11989821