This Blog is my diary that i express my political, economic, and social views about my beloved country Ethiopia.
Saturday, April 19, 2014
Monday, April 14, 2014
በኖርዌ ያሉ ኢትዮዽያውያን የወያኔን የስለላ መረብ በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

በ11-4-2014 በኖርዌ ያሉ ኢትዮዽያውያን የወያኔን የስለላ መረብና ኖርዌ በስደተኛው ላይ ያላትን ፖሊሲ በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አረጉ። 23 ዓመት እራሱ መራጭ እራሱ ተመራጭ ሆኖ በጠመንጃ አፈሙዝ ህዝቡን እያንቀጠቀጠ የኖረው ወያኔ አንድ ቀን ሕዝብ በቃኝ ብሎ አንቅሮ እንደሚተፋውና ንብ ሆኖ ለነፃነቱ እንደሚነሳ ማወቅ ነበረበት።
ግን አልሆነም ዜጎች እንደዜጋ በሐገራቸው መኖር ቀርቶ በስደትም ሰላማቸውን ማግኘት አልቻሉም።
እስርና እንግልት፣ረሐብና ሰቆቃ፣ስደት የእያንዳንዱ እጣ ፋንታ ሆነ፤በወያኔ ዘመን ሰው ብቻ አይደለም መሬትም መሰደድ ጀምሮ የግል ጥቅሙን ለማስጠበቅ ሲል የኢትዮዽያን ለም መሬት ለሱዳን በመሸጥ ላይ ይገኛል
ኢትዮዽያንና ኢትዽያዊነትን ያሉ ሁሉ አሸባሪ እየተባሉ በየእስርቤቱ ታጉረው እጣ ፈንታቸው እስርና እንግልት ሆነ ሐገራቸውን ጥለው በባሕርና በየብስ አቆራርጠው የሞተው ሞቶ የተረፈው በአለም ዙሪያ ተበትኖ ጥገኝነት በመጠየቅ ይኖራል::
በዚሕም የተሳካላቸው ጥቂቶች ሲሆኑ ባብዛኛው ወያኔ ለውጩ አለማት በሚያሳየው ሁለተኛው ፊቱ ምክንያትና ምእራባውያን ከሐገሪቱ ከሚያገኙት ጥቅም የተነሳ ሐገርህ ዲምክራሲ ነው እየተባለ ፍትሀዊ ያልሆነ መልስ እየተሰጠው በመጉላላት ላይ ይገኛል።
ያም ሆኖ የሐገሩ ጉዳይ በደም ስሩ ሰርጎ የገባው ኢትዮዽያዊ ሁሉ ጠዋት ማታ ኢትዮዽያዬ እያለ ይጮሀል። ይህ የህዝብ ቁጣ ያስፈራው ወያኔ ያለ የሌለ የሐገሪቱን ኢኮኖሚ እየመዘበረ ዜጎችን ይሰልላል ያሰልላል፣አልፎ ተርፎም ዜጎችን ከመሰሎቹ ጎረቤት ሐገሮች ድረስ በመሄድ ጎትተው እስርቤት ያስገባሉ።
ይህንን ለመቃወምና ለማውገዝ ነበር የኢትዮዽያ ስደትኞች ማህበር በኖርዌ ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጅቶ ኢትዮዽያውይኑ ዛሬም ስለ ሐገራቸው ሊጮሁ የወጡት፤ ሰልፈኞቹ ድምፃቸውን እንዲህ በማለት ነበር ድምፃቸውን ያሰሙት እኛ ስደተኞች እንጅ ወንጀለኛ አይደለንም፣ኖርዌ ለማፊያው ወያኔ የምታደርጊውን እርዳታ አቁመሽ ከኢትዮዽያ ሕዝብ ጋር ቁሚ፣ወያኔ የሚያደርገውን ተግባር እናወግዛለን፣ሼም ኦን ዩ ሳውዝ ሱዳን ኦኬሎን አሳልፈሽ የሰጠሽ፣ወያኔ አሸባሪ ነው፣ለውጥ እንፈልጋለን፣ኖርዌ የዩኤንን ህግ ታክብር የሚሉትን የመሳሰሉ ሲሆን
በሰልፉ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች መልክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን የኢትዮዽያ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ተወካይ አቶ ዳንኤል የወያኔን ጀሌዎች የማጋለጡ ስራ በሚገባ እየተሰራበት መሆኑን ሲገልጡ ሰልፈኛው በጭብጨባ የተቀበላቸው ሲሆን የስደተኛ ማህበሩም ተወካይ ኖርዌ ነፃ እንድታወጣን ሳይሆን ለወያኔ የምትሰጠውን እርዳታ አቁማ ድጋፍ እንድትሰጠን ነው፤ በተጨማሪም ኖርዌ አቶ ኦኬሎን ታስለቅቅ በማለት ተጠይቃለች። በሰልፉ ላይ የኖርዌ ሊብራል ፓርቲ ተወካይ ከሰልፈኛው ደብዳቤ ተቀብለው መልክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን የኖዋስ ፣አንቲረሲስት ተወካዮችም እንዲሁ ይዘውት የመጡትን መልክት ለሰልፈኛው አስተላልፈዋል።
ከዚያ በቀጥታ ወደሶፊን በርግ ሎካል አዳራሽ ሰልፈኛው አምርቶ ምሳ ከተበላ በሁዋላ ኮሚቴው ካባላቱ ጋር ሰፊ ዉይይት ያደረገ ሲሆን የ፫ወር የስራ ሪፖርትም አቅርቦአል።
የኢትዮዽያ ስደትኞች ማህበር በኖርዌ
የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እና የዲያስፖራውን ሚና በተመለከተ በኖርዌይ ኦስሎ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ
በዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት አፕሪል ቅዳሜ 12/2014 በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እና የዲያስፖራውን ተሳትፎ በተመለከተ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ተካሄደ:: በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ቁጥራቸው ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ከኦስሎ እና ከተለያየ ከተማ በመምጣት በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል አቶ ቡዙነህ ፅጌ የስብሰባው ተጋባዥ እንግዳ በመሆን ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል::
ሕዝባዊ ስብሠባው በኖሬጅያውያን የሰአተ አቆጣጠር ከቀኑ 15:00 እስከ ምሽቱ 21:00 ሰዓት የተካሄደ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አቢ አማረ በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ አረመናዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ አስር ቤቶች በፖለቲካ ኣስተሳስባችው ምክንያት ያለወንጀላች የሚስቃዩ ውድ ኢትዮጵያዊን ወገኖቻችን በማስብ በዚሁ ዘረኛ ቡድን አስቃቂ የኣካል ጉዳት ለተፈጸባቸው ኢትዮጵያዊን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማስደረግ ስብሰባውን አስጀምረውታል::
በመቀጠለም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዴምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር የመግቢያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ስለ ዲምክራሲያዌ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አመሰራረት እና ስለ ድጋፍ ድርጅቱ አላማ በማብራራት የድጋፍ ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል የወያኔን መንግስት ለመጣል እየታገሉ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶችን እየረዳ እንደሚገኝ እና ከሀገር ውጭ ደግሞ የወያኔን መንግስት በሁለገብ ትግል ለማስወገድ እየሰራ ያለውን የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሴ ንቅናቄ የፖለቲካ ድርጅትን በግንባር ቀደምነት እየረዳ እንዳለ በመግለጽ የወያኔን ዘረኛ ስርአት ለመጣል ሁሉም ሰው አስተዋጿ ማድረግ እንደሚጠበቅበት እና ማንኛውም ኢትዮጵያዌ ዜጋ በሀገራችን የጋራ ጉዳይ ስለሆነው የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ሀሳብ በመለዋወጥ ፣በመካከላችን ያሉትን ማንኛውንም የሃሳብ ልዩነቶች ወደ ኋላ በመጣል ፣ በመቻቻል፣ ሀገር እያፈረሰ እና ሕዝብ እያዋረደ ያለውን የዘረኛውን የወያኔን መንግስት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሁለገብ ትግል ለማስወገድ መረባረብ እንዳለበት አጽኖት ሰተው ንግግር አድርገዋል::
በመቀጠለም ዲምክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ድጋፍ ከሚሰጣቸው ድርጅቶች መካከል አንዱ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል የሆኑት አቶ ቡዙነህ ፅጌ የስብሰባው ተጋባዥ እንግዳ ሰፊውን ጊዜ በመውሰድ ከንጉሱ ስርአት ጀምሮ በደርግ መንግስት ዘመንም በሀገራችን የተደረጉ የፖለቲካ ንቅናቄዎችንና ለውጦችን አንድ በአንድ በመዘርዘር አሁን ካለው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ጋር በማነጻጸር ሰፋ ያለ ትንታኔ ያቀረቡ ሲሆን አሁን ላይ ሀገሪቱን እየመራው ነው የሚለው የወያኔ መንግስት ከዚህ ቀድሞ ኢትዮጵያን ከመሩት ከሁለቱ መንግስታቶች ማለትም ከንጉሱም ከደርግም መንግስት ጋር ሲነጻጸር ፈጽሞ እንደማይገናኝ የወያኔ መንግስት ዘረኛና የዘረኝነት ፖለቲካ እያራመደ ያለ አረመናዊ መንግስት እንደሆነ አብራርተዋል::
የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል አቶ ቡዙነህ ፅጌ አክለውም ከወያኔ በፊት የነበሩ ሁለቱ መንግስታቶች ለውድቀት የዳረጓቸውን ምክንያቶች በመጥቀስ የወያኔን አንባ ገነናዊ መንግስት ለአፋጣኝ ውድቀት ሊዳርጉት ይችላሉ የሚሉትን ግልጽ ምክንያቶች በመዘርዘር አስቀምጠዋል:: አቶ ቡዙነህ በሁለት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በማንሳት እና በማብራራ ከሕዝብ ውይይት እንዲያደርጉበት ለመወያያ ያቀረቡ ሲሆን እነዚህም
1, በሙስሊሙ ማህበረሰብ እና በወያኔ መካከል ያለው ግጭት
2, የህዳሴ ግድብን በማስመልከት ያለው ተቃውሞ
ስለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቃውሞ ሲናገሩ የሙስሊሙ ትግል በሁለት አመታት ውስጥ የተደረገው ሰላማዊ ትግል በጣም የተሳካና ወያኔ በቀላሉ ሊያዳፍነው ያልቻለው ሰላማዊ መብትን የመጠየቅ ትግል እንደሚያደንቁ በመናገር ነገር ይህ በሙስሊም ማህበረሰብ በኩል እየተደረገ ያለው ትግል እስከ አሁን ድረስ ከመንግስት በኩል ምንም አይነት መልስ ሊያገኝ እንዳልቻለ እና ወደፊትም ከወያኔ መንግስት በኩል ምንም አይነት መልስ ያገኛል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል:: ለዚህም ማስረጃው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከጠየቋቸው አራት የመብት ጥያቄዎች አንዱም ካለመመለሱ በተጨማሪ እስካሁን መሪዎቻቸውም በሃሰት ውንጀላ በእስር እየማቀቁ ያለፍርድ እየተንገላቱ መሆናቸው ነው፥፥
ነገር ገን አሁን እየሆነው ባለው ሁኔታ በእንደዚህ አይነት መንገድ እስከመቼ ድረስ የሙስሌሙ ትግል ይቀጥላል በማለት የተናገሩ ሲሆን አሁን እየሄደ ባለው አካሄድ የሙስሊሙ ተቃውሞ የትግል አቅጣጫውን እስካልቀየረ ድረስ ረጅም ርቀትን ትግሉ ሊቀጥል ይችላል የሚል እምነት እንደሌላቸው እና ነግር ግን የሙስሊሙ ጥያቄ ከእምነት መብት ጥያቄ ባሻገር ወደ የዜግነትን መብት ወደ ማስከበር መለወጥና መሸጋገር እናደለበት በመናገር የሙስሊሙ ማእበረሰብ ጥያቄ ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው ትግሉ በዚህ መልኩ ሲቀጥል እንደሆነ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰተዋል:
በሁለተኛም የህዳሴ ግድብ በሚመለከት ያቀረቡት ሀሳብ ወያኔ የራሱን የፖለቲካ ኪሳራና በህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለዉን ግፍ በዕድገት ስም ለመሸፈን ያመጣዉ እንጂ ታቅዶበትና ለህዝቡ በማሰብ እንዳልሆነ በኢትዮጵያና በህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለዉ ግፍ እንደ ማስረጃነት በማቅረብ ያብራሩ ሲሆን እንደ ምሳሌም ወያኔ ሃገራዊ የሆነ አላማ ይዞ ካለመነሳቱ አንፃር የሃገርን ድንበር አሳልፎ እስከመስጠት እየሄደ ያለበትን ሁኔታ ጠቅሰው ይህ አሰራር ደግሞ የዲክታተሮች ባህሪ እንደሆነ አብራርተዋል፥፥
የወያኔ መንግስት በህዳሴ ግድብ ሰበብ ምክንያት በማድረግ በመላው አለም ኢትዮጵያኖች በሚኖሩበት ሀገሮች በመዞር የዲያስፖራውን ቀልብ ለመውሰድ የሚያደርገው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ሩጫ በዲያስፖራ ተቃዋሚዎች አማካኝነት በፍጹም እንዳልተሳካለት ይህንንም የወያኔ በአባይ ቦንድ ሽያጭ ስም ገንዘብ ዘረፋ በመቃወም ወያኔን አሳፍረው ከመለሱት መካከል በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች እንደሆኑ በማስታወስ የዚህ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰበብ የወያኔን መንግስት ወደ መጥፎ ውድቀት ላይ ሊጥለው እንደሚችል በማመን የወያኔ መንግስት በአሁን ሰአት ከግብጽ መንግስት ጋር እየገባ ያለው ሰጣ ገባ ለኢትዮጵያ መጥፎ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ ንግግራቸውን አጠቃለዋል፥፥
በመቀጠልም አቶ ብዙነህ ባነሷቸው ነጥቦችና እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ከስብሰባው ተሳታፊዎች ለቀረበላቸው በርካታ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሰፋ ያለ ውይይትም ተደርጓል፥፥ ከውይይቱም በማስቀጠል የዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዳንሄል አበበ የዲምክራሲያዌ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቋም መግለጫ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ድርጅታቸው ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና በደል ፈጽመው እንደሚያወግዙ እና ዴምክራሲያዌ ለለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሁል ጊዜ ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሴ ንቅናቄ ጎን እንደሚቆም ቃል በመግባት የአቶ ቡዙነህ ፅጌን በኖርዌይ በመገኛት ለህዝቡ ለሰጡት ገለጻ አመስግነዋል፥፥
በዝግጅቱ መጀመሪያና ማጠቃለያ ላይ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል መዝሙር በመዘምራን የተዘመረ ሲሆን በየጣልቃው የተለያዩ የባህል ዘፈኖች በተወዛዋዦች ታጅቦ የቀረበ ሲሆን ጣእም ያለው ባህላዊ ምግብም በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የሴቶች ክፍል ተስተናግዷል፥፥ ስብሰባውን ተጀምሮ እስኪያልቅ አቶ ፍቅሬ አሰፋ መርተውታል::
በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ለዝግጅቱ መሳካት የበኩላችሁን ላበረከታችሁና ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች ረዥም ርቀት በመጓዝ የዝግጅቱ ታዳሚ ለነበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን እና እንዲሁም የድርጅቱ አባላቶች ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን፥፥
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Sunday, April 13, 2014
በኖርዌይ የሚገኙ የወያኔ ሰላዮችን በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኦስሎ ከተማ ተካሄደ
ማርች 11, 2014 በኖርዌ የሚገኘው የኢትዮጵያን የስደተኞች ማህበር ያዘጋጀው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ከተለያዩ የኖርዌ ከተሞች በመጡ ታዳሚዎች እና በኦስሎ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲሁም በተለያዮ መፈክፎች ታጅቦ በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ።
የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዋና አላማ በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው በሚኖሩበት ሐገር እንደሚሰለሉ እና የወያኔ ሰላዮች በኖርዌይ ምድር መኖራቸውን የኖርዌ የደህንነት ፓሊስ ለሀገሪቱ ትልቅ ጋዜጣ መረጃ መስጠታቸውን እና በተመሳሳይ የሂውማን ራይትስ ዋች በቅርቡ ያወጣውን መረጃ መሰረት በማድረግ የኖርዌ መንግስት ለወያኔ ሰላዬዮች የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆም እና አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ለመጠየቅ እና ኖርዌ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ያላትን የአሳይለም ፖሊሲ እንድታስተካክል የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ ነበር።
ፕሮግራሙ ከቀኑ 12፡00 የተጀመረ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ምክትል ሊቀመንበር ሰፋ ያለ የወያኔ ሰላዮችን የተመለከተ ንግግር ያሰሙ ሲሆን የዚሁ ድርጅት የሴቶች ክፍል ተወካይ ወ/ሪት ሔለን ንጉሴ አጠቃላይ በኖርዌ ያሉ ሰላዮችን እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በመስጠት ሴቶች በሁለገብ ትግል ውስጥ ያላቸውን ጉልህ ሚና እንዲሁም ወደፊት ሊኖራቸው የሚገባውን ሚና ጨምረው በማስረዳት ለትግሉ አጋር መሆናቸውን ገልፀዋል። በመቀጠል የስደተኛ ማህበሩ ፀሐፊ ወ/ሪት የሺሃረግ በቀለ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያቀረበች በመሆኑ የሐገሪቱ ዜጎች መልክቱን በደንብ እንዲሰሙ ያደረገች ሲሆን የኖርዌጅያን ተወላጅ የሆኑትና በስደረኞች ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ተወካዮች በተመሳሳይ ስለ ኢትዮጵያ አምባ ገነን መንግስት ከስደተኛው በላይ የሚያውቁትን መረጃ በዝርዝር በየተራ በንግግር አሰምተዋል። ይህንን የሰላማዊ ሰልፍ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ የመሩልን የስደተኛ ማህበሩ የኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ ዮናስ እና አቶ ጌታቸው ናቸው።
በመጨረሻም ከሰላማዊ ሰልፉ በኋላ በወ/ሮ ሰዋሰው እና በባለቤታቸው የተዘጋጀ የምሳ ግብዣ የተከናወነ ሲሆን የስደተኛ ማህበሩም የውይይት ጊዜ አዘጋጅቶ የነበረ በመሆኑ የስደተኛ ማህበሩን የሶስት ወር ሪፖርት ካቀረበ በኋላ በቀጥታ ወደ ውይይት በመግባት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኖርዌ ስለሚገኙ የወያኔ ሰላዮች በሰፊው ምክክር አድርገው ወደፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዴት እነኚህን ሰላዮች በምን መልኩ ማጋለጥ እንዳለባቸው ተወያይተው በመቀጠል አጠቃላይ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ውይይት አድርገው ፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ ከምሽቱ 19፡00 ተጠናቋል።
Sunday, April 6, 2014
ሃያ ሶስት አመታት ለኢትዮጵያ እንደምን ያሉ አመታት ነበሩ?
1.ሃያ ሶስት የወያኔ አመታት ለመጀመሪያ ግዜ በሃገራችን ታሪክ ከአንድ ዘር ብቻ የተሰባሰቡ ጥቂት ግለሰቦች የሃገሪቱን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ስልጣን፤ የሃገሪቱን ሃብት፣ መሬቱንና ማዕድኑ፤ የሃገር ውስጥና የወጭ ሃገር ንግዱን፤ የኮንስትራክሽን፣ የባንክ፣ የኢንሹራንስ፣ የትራንስፖርት፣ የማምረቻና ማከፋፈያ ስራውን የተቆጣጠሩበት፤ እፍረትና ይሉኝት የለሸ ነውረኛና አደገኛ ስራ የተሰራባቸው አመታት ናቸው።
2.ያለፉት 23 አመታት ሃገሪቱ በጥቂት ለዘረፋ ስልጣን በያዙ ዘረኞችና አፋኞች እጅ በመወደቋ ታላቅ የተፈጥሮና የሰው ሃብቷንና እንዲሁም ባለፈው 23 አመታት የተገኘው አንጻራዊ ስላም ተጠቅም ድህነትን ረሃብን ስደትን ሀገራዊ ውርደትን ማስቆም የምትችልበትን እጅግ ታላቅ እድል ያባከነችባቸው አመታት ናቸው።
3.ያለፉት 23 አመታት፣ በየትኛዎቹም ኢትዮጵያ መንግስታዊ ስርአቶች ከቶ ተደርገው የማይታወቁ፤ በሃገራችንና በህዝቧ ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ሃገራዊ ክህደቶች የተፈጸሙባቸው አመታት ናቸው። ኢትዮጵያችን ከዚህች ሃገር ውስጥ በወጡ ልጆቿ ሳይሆን ለሃገሪቱና ለህዝቧ ከፍተኛ ጥላቻ ባላቸው፤ ሃገሪቱንና ህዝቧን መበቀል የግድ የሆነባቸው፤ ቂም አዝለው ስልጣን በያዙ የውጭ ወራሪዎች እጅ የወደቀች እስክትመስል ሃገራዊና ህዝባዊ ክብሯ አጥታ የተዋረደችባቸው አመታት ናቸው።
4.ያለፉት 23 አመታት በየትኛውም ዘመን ስልጣን ላይ የወጡ ገዥዎች አስበውትና አድርገውት በማያውቁት ደረጃ የሃገር ሃብትና ቅርስ ስልጣን ላይ ባሉ ጥቂት የትግራይ ገዥ ጉጅሌ አባላት እየተዘረፈ በባእድ ሃገራት የተከማቸበት አመታት ናቸው። እኝህ አመታት የዘረኛው ገዥ ጉጅሌ አባላት ለዘረፋ እንዲያመቻቸው ያስጠጓቸው የውጭ ሃገራት ዜጎች በሃገራችን ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የህዝቡን ለም መሬት፣ ወርቅ ሌላም ማእድን እንዳሻቸው እየዘረፉና የሃገሪቱን ህዝብ ከባርነት ስርአት ባለተናነሰ የጌታና የሎሌ ግንኙነት እንዳሻቸው እያዋረዱ እንዲያሰሩ ስድ የተለቀቁባቸው አመታት ናቸው።
5.ያለፉት 23 አመታት ዳኝነትና ፍትህ የሚባል ነገር ጭራሽኑ ካገር የጠፋበት፤ ዜጎችና ህዝቦች ተቆጪ በሌላቸው በዘርና በጥቅም በተሳሰሩ የገዢው ጉጅሌ የጦር አዛዦች፣ የደህንነት አባላትና ካድሬዎች እንዳሻቸው የሚረሸኑበት፤ ህዝብ ለሰቆቃና ለእስራት የተዳረገበት፤ ሰው በገዛ ቤቱ ውስጥ ሳይቀር የሚሰማውን መናገር እንዳይችል የስጋትና የፍርሃት ቀንበር ውስጥ የወደቀችባቸው፤ እንዲሁም በዘር ማጥፋትና በሰው ልጆች ላይ እንደተፈጸሙ ተደርገው የሚታዩና በአለምአቀፋዊ ወንጀለኛነት የሚያስጠይቁ ታላላቅ ወንጀሎች በመላው ሃገሪቱ ህዝብ ላይ የተፈጸሙባቸው አመታት ናቸው።
በጥቅሉ ያለፉት 23 የወያኔ የግዛት አመታት የኢትዮጵያን ውርደት፤ የህዝቧን የድህነት፣ የባርነትና የሰቆቃ ህይወት በማየት በሚደሰቱ ጸረ ሃገርና ህዝብ ሃይሎች እጅ ወድቃ አበሳዋን ያየችባቸው አመታት ናቸው። ግንቦት 20 የተባለውን የዛሬውን የወያኔዎች በአል የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስበው፣ በሃዘን በቁጭትና በንዴት ነው። የወያኔ እድሜ እንዲረዝም ሳይሆን እንዲያጥር በመመኘት፣ በመጸለይ፣ በመደራጀትና በመታገል ነው። የግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ስሜትም ከህዝብ ስሜት የተለያ አይደለም። ለዚህም ነው በወያኔ የፈንጠዝያ እለት ውደቀታቸው የማይቀር መሆኑን የምናረዳቸው።
ውድመት ለዘረኛውና ለዘራፊው ጸረ-ሃገርና ጸረ -ህዝብ ጉጅሌ
እርገት ለኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት የእኩልነት የፍትህና የአንድነት ፍላጎት
from GINBOT 7
Saturday, April 5, 2014
አንድነቶች በደሴ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያክል ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ዋሉ!
ነገ መጋቢት ሃያ ስምንት በደሴ “የሚሊዮኖች ድምጽ ለ መሬት ነጻነት” በሚል አንድነቶች ለጠሩት ህዝባዊ ሰልፍ ዛሬ በፓርቲው አመራሮች የተመራ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ውለዋል። ቅስቀሳውን እንደተለመደው በመንግስት “ፖሊስ” እና “ድሀንነት” ናችሁ አይዟችሁ የተባሉ ግለሰቦች ሊያደናቅፉት ሞከረው ነበር። ነገር ግን የደሴ ህዝብ እምቢኝ… አላቸው! እናም ቅስቀሳው ዋናው ሰልፍ እስኪመስል ድረስ ደምቆ ውሏል።
የአዲሳባውን ሰለፍ ለሌላ ቀን አስተላልፉልን የተባሉት አንድነቶች “ለበጎ ነው” በለው ደሴ በመከተም ነገ ጮክ ብለው የህዝቡን ጥያቄዎች ከህዝቡ ጋር ሆነው ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል… እኛም፤ “በሰላም ወጥታችሁ በሰላም እነደትገቡ ይመኝላችኋል መላ ህብረተሰቡ…” እንላቸዋለን!
ከአንድነት ለጆች ፌስ ቡክ ገጽ ያገኝሁትን የቅስቀሳውን መልክ የሚያሳዩ ፎቶዎች በደረ ገጻችን ውስጥ አስቀምጪያለሁ!
Subscribe to:
Posts (Atom)