አንድነቶች በደሴ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያክል ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ዋሉ!
ነገ መጋቢት ሃያ ስምንት በደሴ “የሚሊዮኖች ድምጽ ለ መሬት ነጻነት” በሚል አንድነቶች ለጠሩት ህዝባዊ ሰልፍ ዛሬ በፓርቲው አመራሮች የተመራ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ውለዋል። ቅስቀሳውን እንደተለመደው በመንግስት “ፖሊስ” እና “ድሀንነት” ናችሁ አይዟችሁ የተባሉ ግለሰቦች ሊያደናቅፉት ሞከረው ነበር። ነገር ግን የደሴ ህዝብ እምቢኝ… አላቸው! እናም ቅስቀሳው ዋናው ሰልፍ እስኪመስል ድረስ ደምቆ ውሏል።
የአዲሳባውን ሰለፍ ለሌላ ቀን አስተላልፉልን የተባሉት አንድነቶች “ለበጎ ነው” በለው ደሴ በመከተም ነገ ጮክ ብለው የህዝቡን ጥያቄዎች ከህዝቡ ጋር ሆነው ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል… እኛም፤ “በሰላም ወጥታችሁ በሰላም እነደትገቡ ይመኝላችኋል መላ ህብረተሰቡ…” እንላቸዋለን!
ከአንድነት ለጆች ፌስ ቡክ ገጽ ያገኝሁትን የቅስቀሳውን መልክ የሚያሳዩ ፎቶዎች በደረ ገጻችን ውስጥ አስቀምጪያለሁ!
No comments:
Post a Comment