Thursday, July 10, 2014

Canada Ottawa
Andargachew Tsige is a symbol of freedom Justices and human rights !!! 
Truneh Yirga added 7 new photos — with Netsante Yibeltal and 4 others.

የኦታዋ ከተማ ዓንዳርጋቸው ጽጌ በዓስቸኳይ ይለቀቅ በሚሉ የዓንዳርጋቸው ጽጌን የትግል መንፈስ በተላበሱ ኢትዮጵያውያን ስትናጥ ውላለች፥
በ FREE ANDARGACHEW TSIGE TASKFORCE TORONTO ቡድን ዓሰባሳቢነት ከቶሮንቶና ዓካባቢው ከተማዎች ተጠራርተው በእረጅም የዓውቶቡስ ጉዞ፥ ለአንች ነው አገሬ የሚለውን ቀስቃሽ ዝማሬ እየዘመሩ በመጡ የኢትዮጵያ ልጆች የተመራው ነጻነት ለዓንዳርጋቸው ግብረኃይል እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ከሚጠብቀው የኦታዋና ዓካባቢዋ ነዋሪ ኢዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር በመተባበር፥ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የዘር ድርጅትና ኃይማኖት ሳያግድቻቸው በአንድነት ድምጻቸውን ከፍ ዓድርገው፥
We are Andargachew Tsige!
Free Andargachw Tsige!
Andargachew is our Mandela!
Britain where is your Citizen Andargachew Tsige? እና ሌሎችም ተመሳሳይ መፈክሮችን ዓንግበው፥ የእንግሊዝን ኢምባሲና በኢትዮጵያ ስም የሚጠራውን የወያኔ ኢምባሲ ሲያስጨንቁት ውለዋል፥
በሰልፉ የሚታየው ሁኔታ እጅግ ቁጣ የተቀላቀለበት በየመን መንግሥትና በወያኔው የማፊያ ቡድን ላይ ከፍተኛ የበቀል ስሜትን ያዘሉ የቁጭት መልክቶች የተላለፈበት ትዕይነተ ሕዝብ ነበር፥
የእንግሊዝንም መንግሥት ይህ ሚስጥር ያለበት በሚመስል መልኩ የትውለደ ኢትዮጵያዊ ዜጋዋን መብት የዓለማስከበርና በቸልተኛነት የመያዝ ነገር ዓድልዋዊ እንደሆነ በማሳሳብ በዓጽንኦት ዓውግዘዋል፥
በመጨረሻም ለብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስቴርና በካናዳ ለሚገኘው ዓምባሳደር በግብረ ኃይሉ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በዕጅ ካላስረከብን ሰልፈኛው ከዚህ ዓይሄድም በመባሉ የእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካዩን ልኮ ወደ ሚገባው ቦታ እንደሚያደርሱ ቃል ከገቡልን በኋላ፥
ወደ ኢትዮጵያው የወያኔ ኢምባሲ ፊት ለፊት የየመንና የኢትዮጵያ የውንብድና ስራ ማይድን ጋሻ ጎን ያሰብራል እንደተባለው በከንቱ መወዳጀት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸሙት በደልና ሰንካላ ድፍረት ከባድ ዋጋ በሰዓቱ እንደሚያስከፍላቸው በማሳሰብ፥ TPLF Free our Hero Andargachew! Canada Close Ethiopian Embassy! በሚል ጽኑዕ ቁጣ ሰልፈኛው የየመንን ባንዴራ ከመሬት እየረገጠ ሰልፉ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፥
ታጋይ ይወድቃል ትግል ይቀጥላል፥ የኢትዮጵያ የነጻነት ቀን ቀርቧል፥
ከዚህ በኋላ ወያኔዎች ዓንዳርጋቸውን የሚለቁት ለዕራሳቸው ሲጨንቃቸው እንጂ ለዕኛ ዓዝነው ዓይደለም፥ የዓንዳርጋቸው የዓርበኛነት መንፈስ በሕዝቡ ደምና ዓጥንት የገባ በወያኔ ላይ ካልፈነዳ የማይበርድ እንደ እሳተ ገሞራ ያለ ታላቅ ኃይል ነው፥ ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ተጋድሎ ነጻ ትወጣለች፥

No comments:

Post a Comment