Tuesday, July 15, 2014

በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና ሌሎችም የታሰሩት ኢትዮጵያውያን እንዲፈቱ ጠየቁ

IMG_4245
ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በኖርዌይ የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ የአቶ አንዳርጋቸውን ተላልፎ መሰጠት በእጅጉ አውግዘዋል። ከፍተኛ ቁጣ ባስተናገደው ተቃውሞ እንግሊዝ እየወሰደችው ያለው እርምጃ እንዲብራራላቸው ጠይቀዋል።
በኖርዌይ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ደግሞ በቅርቡ ከደቡብ ሱዳን ተይዘው ለኢህአዴግ የደህንነት አባላት ተላልፈው የተሰጡትን የአቶ ኦኬሎ አኳይን ጉዳይ በማንሳት ኖርዌይ መልስ እንድትሰጣቸው ጠይቀዋል።
የእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ ሰልፈኞቹን ወጥተው ያነጋገሩ ሲሆን፣ እንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸውን ለመጎብኘት ፈቃድ እንዲሰጣት ጥያቄ ማቅረቡዋንና መልስም እየጠበቀች መሆኗን መናገሩዋን የሰልፉ አስተባባሪ ግብረ ሃይል አባል የሆኑት አቶ ደባሱ መሰለ ገልጸዋል። (
ኖርዌይ በበኩሏ የአቶ ኦኬሎን ጉዳይ በቅርብ ተከታትላ አስፈላጊውን መረጃ እንደምትሰጥ መግለጿን አስተባባሪው አቶ ዳንኤል አበበ ተናግረዋል
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአቶ አንዳርጋቸውን በግፍ መታሰር አሁንም የህዝቡ የመነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ ነው። ኢህአዴግን በመረጠው መንገድ እንፋለማለን ያሉ ሰዎች የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶችን እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ ግንቦት7ትን ለመቀላቀል የሚጠይቁ ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው ከፍተኛ መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአቶ አንዳርጋቸው መታሰርን ትህዴን፣ አርበኞች ግንባር፣ አርዱፍና በጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ ማውገዛቸው ይታወቃል። በሰላማዊ ትግል ከሚታገሉ ድርጅቶች መካከል ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ” የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሰብዓዊ አያያዝ እንዳሳሰበውና ” ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ አገዛዝ አያያዛቸውን ግልፅ እንዲያደርግ ሰብዓዊ ክብራቸውም እንዲጠበቅ በጥብቅ” ማሳሰቡ ይታወሳል።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፕሪቶሪያ በሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት ረቡዕ የተቃውሞ ሰልፍ የሚያደርጉ ሲሆን በሎስ አንጀለስ የእንግሊዝ ኮንስላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ደግሞ ማክሰኞ ተቃውሞ ይደረጋል።

Sunday, July 13, 2014

በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አደረጉ

July 13/2014


ቅዳሜ ጁለይ 12/2014 በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አዘጋጅነት ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን በሚል አላማ በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የደንነት ሀይሎች መታፈንና ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ታላልፈው መሰጠታቸውን በተመለከተ ወደ ፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከተለያዩ ከተሞች በመሰባሰብ በኖርዌ ኦስሎ ለአምስት ሰዓታት የፈጀ ውይይት ሲያደርጉ ውለዋል::
ሕዝባዊ ውይይቱ ከቀኑ 15: 00 ሰአት ላይ የተጀመረ ሲሆን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያኖች የአቶ እንዳርጋቸው ምስል ያለበትና ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን የሚል ጹሁፍ የተጻፉበትን ቲሸርት በመልበስ ለስብሰባው ድምቀት የሰጡት ሲሆን ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውንም የትግል አጋርነት አስማስክራዋል እነዚህን ቲሸርቶች የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርንጫፍ በራሳቸው አነሳሽነት የሰሩ ሲሆን የድጋፍ ድርጅታችን ወጪውን በመሸፈን ለተሰብሳቢው በነጻ ኣድሏል።
ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት አላፊ አቶ አቢ አማራ በሃያ ሶስት አመታት በወያኔ ጨካኝ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉትና በግፍ ለሚሰቃይዩ ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማስደረግ አስጀምረውታል በመቀጠልም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር በስብሰባው ላይ የተገኛውን ሕዝብ እንኮን ደህና መጣችሁ በማለትና በማመስገን ፐሮግራሙን በንግግር የከፈቱት ሲሆን አቶ ዮሀንስ በንግግራቸው የወያኔ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ባደረሰው አፈና ግንቦት 7 የክተት አዋጅ ማስተላለፉን ጠቅሰው አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በአሁን ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል እየታገሉ ባሉ ታጋዮች ላይ ሳይቀር እስር እያደረሰባቸው እንዳለ በማመልከት ሰሞንኑን እንኮን የሰመያዊ፣ የአንድነት፣ የአራና የፖለቲካ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ለስር ተዳርገዋል ብለዋል::
ስለሆነም ህዝባችንን ለእስር እያደረገ ያለውን አገዛዝ ለመቃወም ሁሉም በአንድነት መሰባሰብ እንዳለበት አጠንክረው በመናገር በአሁን ሰአት የአቶ አንዳርጋቸው በወያኔ መታፈንና መታሰር መላውን ኢትዮጵያ ዳር እስከ ዳር እያንቀሳቀሰውና ሕዝቡም እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በማለት በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጠቅሰው በአሁን ሰአት ትግሉ የግንቦት 7 ብቻ አይደለም ይህን ትግል በዚሁ አንድ ሆነን መቀጠል እለብን ብለዋል::
በመቀጠል አቶ ደባስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባል የአቶ አንዳርጋቸውን ከወጣት እድሜያቸው ጀምሮ ያለውን የፖለቲካ አካሄድ አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ማን ነው ? በሚል ርእስ የአቶ አንዳርጋቸውን የትግል ጉዞ የሚዳስስ ዘገባ ሰፋ ባለ ትንታኔ በጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በስብሰባው ላይ የኢሀፓ ፣ የአርበኞች ግንባር፣ የሸንጎ ፣የስደተኛው ማህበር ተወካዮች እና ሌሎችም ሰዎች በየተራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የየድርጅቷቹም ተወካዮች የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መታፈንና ለእስር መዳረግን በተመለከተ የድርጅታቸውን አቋም ለተሰብሳቤው ያስረዱ ሲሆን የሁሉም ፖርቲ ተወካይች በአቶ አንዳርጋቸው መታፈንና ለእስር መደረግ ማዘናቸውን ገልጸው ሁሉም በአንድነት በመተባበር በማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ የወያኔንን መንግስት ማስወገድ እንዳለባቸው አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል::
በየፕሮግራሞቹ መሀል ግጥሞችና ሌሏችም ፕሮግራሞች ቀርበው የመጀመሪያው ዞር ተጠናቋል::ከ30 ደቂቃ የእረፍት የሻይ እና የቡና ፕሮግራም በኋላ የሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ፕሮግራም በተያዘለት ጊዜ ተጀምሮ የፕሮግራሙን ተሳታፊዎች ያሰተፈ ፕሮግራም በአቶ አብዱ የሱፍ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ስታቫንገር ቅርንጫፍ ምክትል ሊቀመንበር ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና ተግባሪዊ የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪን ካብራሩ በኋላ ለተሰብሳቢው ለውይይት በማቅረብ በኖርዌ የምንኖር ኢትዮጵያኖች ይህን የትግል ጥሪ ለማስፈጸም ምን እናድርግ በማለት ለውይይት አቅርበው የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በአቶ ዮሀንስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር አወያይ አማካኝነት በስፋት ተወያይተውበታል ::
ተሰብሳቢውም በብዙ ነገሮች ከተወያዩ በኋላ ይሄ ግንቦት 7 ያወጣውን የመጀመሪያ እንከን የትግል ጥሪ ተግባራዊ በየቦታው አለም አቀፍ ታክስ ፎርሶች እየተቋቋሙ እንዳለና በኖርዌይም ይህንኑ ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቷች ያካተተ ታክስ ፎርስ እንዲቋቋም ተወስኖል:: በመቀጠልም በተሰብሰቢዎች በተመረጡ ሰዎች የተጻፋ ባለ ስድስት አሃዝ የተሰብሳቢው የአቋም መግለጫ ለጉባሄው በጹሁፍ ቀረቦል:: ተሰብሳቢው ያወጣው የአቋም መግለጫ
1. ሁላችንም አንዳርጋቸው ወይም አንድ አርጊያቸው ነን ስንል ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሐገራችን ኢትዮጵያ ለማስፈን የሚከፈለውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ማለታችን ነው።
2. የተለያዩ የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት የሚያደርጉትን መጠላለፍ እንዲቀርና በጋራ ወይም አንድ በመሆን እንዲሰሩ ግፊት እናደርጋለን።
3. ለሚቀርብልን ሐገርን የማዳን ጥሪ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።
4. የየመን መንግስት ከአለም አቀፍ ህግ ጋራ የሚፃረር ስራ በመስራት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለወያኔ አሳልፎ በመስጠት የሰራውን ወንጀል ለዓለም አቀፍ ህግ የማቅረብ ስራ በጋራ እንደምንሰራ።
5. የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ መታፈን ትግሉን የበለጠ እንደሚያጠናክረውና ወደ ውጤት እንዲያመራ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናደርጋለን።
6. ወያኔ የተለያየ ምክንያት በመፍጠር ኢትዮጵያውያንን እስርቤት ማስገባቱን እንዲቀርና የታሰሩትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ እንጠይቃለን በማለት የአቋም መግለጫ አውጥተዋል ።
በመጨረሻም አቶ ዳንሄል አበበ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ምክትል ሰብሳቢ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የአቋም መግለጫ ለተሰብሳቢው በጹሁፍ ያሰሙ ሲሆን በንግግራቸውም አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የቋሙ የነጻነት ታጋይ ናቸው እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ የምንል ሁሉ ለሃያ ሶስት አመታት ህዝብን በዘረኝነት የከፋፈለውን ወያኔን በቃ ልንለው ይገባል ካሉ በኋላ በኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ አፈና፣ ግድያው፣ እስራቱ መጨመሩን በመናገር ይኼን ጨቋኝና አፋኝ ስርአት ለማስወገድ እንነሳ በማለት ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን በመጨረሻ እኔ እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ እናንተስ በማለት የፕሮግራሙን ተሳታፊ በመጠየቅ ፕሮግራሙ በተያዘለት ሰዓት ከምሽቱ 20:00 ተጠናቋል ::
እኛ ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ
 

Thursday, July 10, 2014

ኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌይ ፓልቶክ በጀግናው ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሁኔታ ላይ ለመወያየት የተጀመረ ስለሆነ 
ጇላይ 09, 2014 (ከ 22፡00-00፡00) ስለሚኖር እንድትሳተፉ ይጋብዛል
Canada Ottawa
Andargachew Tsige is a symbol of freedom Justices and human rights !!! 
Truneh Yirga added 7 new photos — with Netsante Yibeltal and 4 others.

የኦታዋ ከተማ ዓንዳርጋቸው ጽጌ በዓስቸኳይ ይለቀቅ በሚሉ የዓንዳርጋቸው ጽጌን የትግል መንፈስ በተላበሱ ኢትዮጵያውያን ስትናጥ ውላለች፥
በ FREE ANDARGACHEW TSIGE TASKFORCE TORONTO ቡድን ዓሰባሳቢነት ከቶሮንቶና ዓካባቢው ከተማዎች ተጠራርተው በእረጅም የዓውቶቡስ ጉዞ፥ ለአንች ነው አገሬ የሚለውን ቀስቃሽ ዝማሬ እየዘመሩ በመጡ የኢትዮጵያ ልጆች የተመራው ነጻነት ለዓንዳርጋቸው ግብረኃይል እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ከሚጠብቀው የኦታዋና ዓካባቢዋ ነዋሪ ኢዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር በመተባበር፥ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የዘር ድርጅትና ኃይማኖት ሳያግድቻቸው በአንድነት ድምጻቸውን ከፍ ዓድርገው፥
We are Andargachew Tsige!
Free Andargachw Tsige!
Andargachew is our Mandela!
Britain where is your Citizen Andargachew Tsige? እና ሌሎችም ተመሳሳይ መፈክሮችን ዓንግበው፥ የእንግሊዝን ኢምባሲና በኢትዮጵያ ስም የሚጠራውን የወያኔ ኢምባሲ ሲያስጨንቁት ውለዋል፥
በሰልፉ የሚታየው ሁኔታ እጅግ ቁጣ የተቀላቀለበት በየመን መንግሥትና በወያኔው የማፊያ ቡድን ላይ ከፍተኛ የበቀል ስሜትን ያዘሉ የቁጭት መልክቶች የተላለፈበት ትዕይነተ ሕዝብ ነበር፥
የእንግሊዝንም መንግሥት ይህ ሚስጥር ያለበት በሚመስል መልኩ የትውለደ ኢትዮጵያዊ ዜጋዋን መብት የዓለማስከበርና በቸልተኛነት የመያዝ ነገር ዓድልዋዊ እንደሆነ በማሳሳብ በዓጽንኦት ዓውግዘዋል፥
በመጨረሻም ለብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስቴርና በካናዳ ለሚገኘው ዓምባሳደር በግብረ ኃይሉ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በዕጅ ካላስረከብን ሰልፈኛው ከዚህ ዓይሄድም በመባሉ የእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካዩን ልኮ ወደ ሚገባው ቦታ እንደሚያደርሱ ቃል ከገቡልን በኋላ፥
ወደ ኢትዮጵያው የወያኔ ኢምባሲ ፊት ለፊት የየመንና የኢትዮጵያ የውንብድና ስራ ማይድን ጋሻ ጎን ያሰብራል እንደተባለው በከንቱ መወዳጀት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸሙት በደልና ሰንካላ ድፍረት ከባድ ዋጋ በሰዓቱ እንደሚያስከፍላቸው በማሳሰብ፥ TPLF Free our Hero Andargachew! Canada Close Ethiopian Embassy! በሚል ጽኑዕ ቁጣ ሰልፈኛው የየመንን ባንዴራ ከመሬት እየረገጠ ሰልፉ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፥
ታጋይ ይወድቃል ትግል ይቀጥላል፥ የኢትዮጵያ የነጻነት ቀን ቀርቧል፥
ከዚህ በኋላ ወያኔዎች ዓንዳርጋቸውን የሚለቁት ለዕራሳቸው ሲጨንቃቸው እንጂ ለዕኛ ዓዝነው ዓይደለም፥ የዓንዳርጋቸው የዓርበኛነት መንፈስ በሕዝቡ ደምና ዓጥንት የገባ በወያኔ ላይ ካልፈነዳ የማይበርድ እንደ እሳተ ገሞራ ያለ ታላቅ ኃይል ነው፥ ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ተጋድሎ ነጻ ትወጣለች፥

Monday, July 7, 2014

A tale of two British citizenships

A tale of two British citizenships

July 7, 2014
by Samson B
Being British, by birth or naturalised has a profound meaning for the citizenry in times of adversity, particularly when the incidence happens in foreign lands. The British political system, media and the general public comes to one whenever a citizen is distress abroad whether in adventurous trip or caught by political turmoil and situations like kidnappings and violence. One can sight hundreds of public outrages and diplomatic wrangling on mistreatments of British nationals abroad. You can be a ‘drugs mule’ but the British system would do its best so as you get a dignified treatment and possibly prison swap to the UK after sentencing.A British protection is not a thing to be accorded for every passport holder.
Though the above seems to be a common practice things can be deceiving if taken on face value. A British protection is not a thing to be accorded for every passport holder. There are some ‘British citizens’ who are to be ignored whatever the gravity of their situation is.
Andargachew Tsige, a British national of Ethiopian decent is one of them. In Mid June 2014, Andargachew, secretary general of Ginbot 7 for Freedom and Democracy, a pro democracy opposition party in Ethiopia, has been abducted at a Yemen airport by Yemeni security forces and handed over to Ethiopian secret services illegally. As Adnargachew has previously been sentenced to death in absentia, what members of the Ethiopian community in the UK and worldwide expected was a public outcry of the situation and an assertive diplomatic campaign from the Commonwealth and Foreign Office. No single UK based media outlet covered Andargachew’s case. No single parliamentarian raised the issue at any level. The Foreign Office has chosen to keep quiet regardless of repeated calls from the Ethiopian community and his family members before the two rouge states make a deal on Andargachew’s life.
Who cares for an Afro-British who has been abducted in daylight and then illegally handed over to the tyrannical regime in Ethiopia? None! As Yaya Toure, the famous Manchester City footballer repeatedly asserts Andargachew’s only fault is his origin, Africa. He is an African with a British passport who is not entitled to get a ‘first class’ protection and advocacy in circumstances of adversity. As is the norm in many European countries Africans can carry their passports but it does not worth any better than their driving licence. It does not warranty them a protection and advocacy in situations of distress. Their case would not be a ‘Breaking News’ whether they are butchered abroad or in streets of London.