Sunday, June 8, 2014

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ጁን 8, 2014 በኦስሎ ከተማ የሻማ ማብራት ስነስርአት ተደረገ ።

በምርጫ 97 በወያኔ አጋዚ ጦር በግፍ ለተገደሉ ዜጎቻችንን ለማስታወስ በዛሪዉ እለት ጁን 8, 2014 በኦስሎ ከተማ የሻማ ማብራት ስነስርአት ተደረገ ። የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ይህንን የሻማ ማብራት ያዘጋጀበት ዋናው አላማ በምርጫ 97 የዲሞክራሲ ጥያቄ ባነሱና ንጹሀን ዜጎቻችን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ነው። ዝግጅቱ በግፍ በወያኔ ታጣቂዎች ደረትና ግንባራቸውን ተብለው ለተገደሉ ንፁሃን ወገኖቻችን በማስብ በድርጅቱ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ኀላፊ የህሊና ፀሎት በማሰድረግ የተጀመረ ሲሆን በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ምክትል ሊቀመንበር ምርጫ 97ትን አስመልክቶ ሰፋ ያለ የመግቢያ ንግግር አድርገዋል እደዚሁም የኢትዮጵያ ማህበር በኖርዌ ሊቀመንበርም አጠር ያለ መልክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶችም በምርጫ 97 ወቅት የነበረውን የግፍ ግድያ አስመልክቶ በየተራ መልክቶቻቸውን አስተላልፈዋል። በተጨማሪም በምርጫ 97 በግፍ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን አስመልክቶ አጭር በፊልም የተደገፈ ምስል ቀርቧል። በዝግጅቱ ላይ በርከት ያሉ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን ዝግጅቱ በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 19፡00 ተጀምሮ 20፡30 ተጠናቋል።
የዲሞክራሲያዊ ለውጥበኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
1904209_10152452016217710_6989375044162907904_n10336607_10152452015862710_5814485053426944776_n10297590_10152452016097710_7575685381704132048_n10390432_10152452016762710_8537654287919576772_n

No comments:

Post a Comment