Saturday, August 24, 2013

=====የመለስ ዜናዊ “የሁለት አሐዝ ዕድገት” እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮ====

=====የመለስ ዜናዊ “የሁለት አሐዝ ዕድገት” እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮ====
“ለ7 ዓመታት በተከታታይ 11·6 በመቶ አድጓል” የተባለው የመለስ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፥ የዓለም ባንክ  እና አይኤምኤፍም ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሚገኘው መረጃ ላይ ቢመሠረቱም “የለም፤ ከ6 እስከ 8 በመቶ ነው ያደገው፣ ቢሆንም ቀሽት ነው” ይላሉ።

“ኢኮኖሚው ሲመነደግ” የሕዝቦች ኑሮ ደረጃስ እንዴት ነው?

ኢትዮጵያ በየአረብ አገራቱ የቤት ሠራተኛ አቅራቢነት ከፍተኛ ደረጃ የደረሰችው በመለስ ዘመን ነው። (ለምሳሌ አሁን ኢትዮጵያውያንን አልቀበልም ያለችውን ሳውዲ አረቢያ የቤት ሠራተኛ ፍላጎት 10 በመቶ ኢትዮጵያ ትሸፍን ነበር።) በየአረብ አገራቱ የኢትዮጵያውያን ስም ከሌብነት እና ሴተኛ አዳሪነትጋ የተያያዘ ነው።
ከኢትዮጵያ ውጪ መውጣት ለሁሉም ዜጋ ቢፈቀድ ዐሥር ሚሊዮን ሰው እንኳን ይቀራል ብዬ መገመት ይከብደኛል። ከተሜውም ገጠሬውም ወደቻለው ቦታ ይፈልሳል። የተማረውም፣ ያልተማረውም ኢኮኖሚያዊ ስደትን የመምረጡ እውነት የኢኮኖሚያዊ ዕድገቱን እውነተኝነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተዋል።

የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በተለይ የመንገድ ሥራዎች ሲነቃቁ የግሉ ዘርፍ (ከኢሕአዴግ “የኢንዶውመንት” ቢዝነሶች በቀር) ተዳክሟል። ያሉትም የግል ቢዝነሶች ቢሆኑ በፖለቲካ ጥቅም የሚለመልሙ በመሆናቸው በከተሞች መሐል የሚበቅሉ ብልጭልጭ ሕንፃዎች የሙስና ሲሳይ ናቸው። ከሕንፃዎቹ ጀርባ ያሉት ያው የድሮዎቹ ቆሼ ሰፈሮች ናቸው። እንደ HDI ያሉ የUN የሰብኣዊ ልማት መለኪያዎችም የሚያሳዩን ኢትዮጵያውያን ዛሬም በድህነት እየማቀቁ መሆኑን ነው።

“ስኳር የተወደደው ድሃው ስኳር መብላት ጀምሮ ነው” ያሉት መለስ ስኳሩን የሚልሱት እነማን እንደሆኑ እንኳ ሳይረዱ ያለፉ ይመስለኛል።

አቶ መለስ ምንጩንና መጠኑን ማንም ያልገመተው፣ የባለብዙ ሀብት ባለቤት፣ የትዳር አጋራቸውን ጨምሮ ሌሎች ጥቂት ሀብታሞች ያሉበት የጥቅመኞች ክበብ እየዳጎሰ ብዙኃኑ የሚቀጭጩበትን የቢዝነስ ስርዓት በመፍጠር በቁጥር ጫወታ አድጋችኋል ይሉናል። ድሃ ተኮር ፖሊሲ ቀርጫለሁ፣ ለልማቱ ብዬ ነው ዴሞክራሲን የበደልኩት ብለው ያተረፉልን ነገር ቢኖር አገርክን ጥለህ ብረር፣ ብረር የሚያሰኘው ምስኪን፣ ድሀ ትውልድ ብቻ ነው።

Tuesday, August 20, 2013

ኢትዮጵያ ሃገራችን በታሪኳ በህዝብ የተመረጠ መሪ ሳይኖራት ነገስታትና አምባ ገነኖች ሲፈራረቁባት ኖራለች፡ የ
ኢትዮጵያ ህዝብም ይህንኑ በደነደነ ትከሻው ሲሸከም ኖሯል።

ለፉት 22 አመታት ሃገራችንን የገጠማት አገዛዝ ግን በአለም ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ነው። ራሱን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር ብሎ የሰየመ፤ ለተቀረው ህዝብ ታላቅ ጥላቻና ንቀት ያለው ቡድን ህዝቡን በማሰቃየት ላይ ይገኛል። የመብት ጥያቄ የሚያነሱትን፤ የግፍ አገዛዙን የሚቃወሙትን የተለያየ ስያሜ እየሰጠ ከማሰር፤ ሰቆቃ ከ
መፈጸምም በላይ ዘር እስከ ማጥፋት የሚደርስ ወንጀል በመፈጸም ላይ ይገኛል።

የህዝብ በደል፣ስደት፣እስር፣እንግት፣በአገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠር ይብቃ ካልን
ዛሬ ነገ ሳትሉ በዚህ ታሪካዊ ክስተት የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሀይልን በመደገፍ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ።

“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” 
ተባብረን ወያኔን እናስወግድ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

Sunday, August 4, 2013

የአንድነት ፓርቲ አባላት ከአጉራ-ዘለል የወያኔ ካድሬዎች ጋር ግብግብ ይዘዋል

August 3, 2013
አንድነት ፓርቲ እሁድ ሐምሌ 28፣ 2005 “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ መፈክር ስር በተለያዩ የክልል ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አባላቱ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው። ይሁንና ከወያኔ አጉራ-ዘለል ካድሬዎችና ታጣቂዎች እየደረሰባቸው ያለው ወከባ ተባብሶ ቀጥሏል። ነብዩ ሀይሉ እና ሌሎችም በፌስ-ቡክ ገጾቻቸው ሁኔታውን እንደሚከተለው ይገልጹታል፣
UDJ calling for protest in Bahirdar
በባህርዳር የአድነት ፓርቲ አባላት በቅስቀሳ ላይ። ፎቶ Bisrat Woldemichael
በወላይታ የተሸጠ ጀነሬተር እንዲመለስ ተደረገ
በወላይታ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ አዳራሽ(አዳራሹ ከ200 ሰው በላይ የመያዝ አቅም የለውም) አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሚያከናውነው ስብሰባ ህዝቡን ለመቀስቀስ ሞንታርቦና ጀነሬተር የሚያከራይ ነጋዴ በመጥፋቱ(በከተማው ጀነሬተር በማከራየት ህይወታቸውን የሚገፉ ነጋዴዎች በብዛት የሚገኙ ቢሆንም ካድሬዎች ቀጠን ያለ ትዕዛዝ በማስተላለፋቸው መከራየት አልተቻለም)የጄነሬተር መጥፋት ያሳሰባት ወ/ሮ ጸሀይ ወ/ጊዮርጊስ አነስተኛ ጀነሬተር በ2300ብር ትገዛለች፡፡
ሻጩ ጀነሬተሩን በህጋዊ መንገድ ከሸጠና መኪናው ላይ እንዲጫን ከተደረገ በኋላ ግለሰቡ እንባውን እያዝረከረከ የተከፈለውን ገንዘብ በመያዝ ጀነሬተሬን መልሱልኝ በስህተት ነው የሸጥኩላችሁ››ይላል ፡፡ነጋዴው ለምን እንደዚህ እንደህጻን እያለቀሰ መልሱልኝ ማለቱን የተረዱ የፓርቲው አባሎችም ጀነሬቱን መልሰውለታል፡

ህገ-መንግስታዊ መብታችንን ሳንገል እየሞትን እናስከብራለን! አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

August 4, 2013
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ሰኔ 13 ቀን 2005 ዓ.ም በጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቆ ወደ ንቅናቄው ከገባ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ህዝባዊ ድጋፍና በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃት እና የነፃነት ጥያቄ ድምፅ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በመደመጥ ላይ ይገኛል፡፡
በአንፃሩ ገዥው ፓርቲ የህዝቡን የነፃነት ድምፅ ለማፈን ንቅናቄያአችንን ከጀመርን እለት ጀምሮ በርካታ መሰናክሎችን እየፈፀመ ይገኛል፡፡
በጎንደርና በደሴ ያደረግነውን ሰላማዊ ሰልፍ በተደራጀ መንግስታዊ ሽብር ለማደናቀፍ የተሞከረውን ሙከራ በህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ከሽፎ የህዝቡን የነፃነት ድምፅ ማሰማታችን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ይህንን የነፃነት ድምፅ በሌሎች ከተሞች ተቀጣጥሎ እንዳይዘልቅ ከሼክ ኑር ኢማም አሟሟት ጋር በማያያዝ ገዢው ፓርቲ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ቀን ድረስ በተለያዩ ከተሞች ህዝቡን በማስገደድ አንድነት ፓርቲን እንዲያወግዝ በየቀኑ ሰልፍ በማስወጣት ላይ ይገኛል፡፡Unity for Democracy and Justice (UDJ) party
ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በጂንካ ፣ ወላይታ ፣ ባህርዳር ፣ አርባምንጭ እና መቀሌ ሰላማዊ ሠልፍ እና ህዝባዊ ስብሰባ እናደርጋለን ብሎ አንድነት ካሳወቀ ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው በሚገኙ አባሎቻችን ላይ ማዋከብና ከፍተኛ ጫና ማሳደሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ሐምሌ 27 ቀን 2005 ዓ.ም ወላይታ ለቅስቀሳ የገባው የአዲስ አበባ ልዑክ በአካባቢው ባለስልጣኖች  መንግስታዊ ውንብድና ተፈፅሞበታል፡፡ ታርጋ የሌላቸው ሞተር ሳይክሎች በብዛት በማሰማራት ለቅስቀሳ በተንቀሳቀሱ አባሎቻችን ይዘው የወጡትን በራሪ የቅስቀሳ ወረቀቶችንና የፀረሽብር ህጉን ለማሰረዝ የተሰባሰቡ ፊርማዎችን ከእጃቸው ላይ ነጥቀዋቸዋል፡፡ የፀጥታ ኃይሎችም ዘራፊዎችን ለማስቆም ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ ለቅስቀሳ የተሰማራውንም መኪና አራቱንም ጎማ በማተንፈስና ሹፌሩን በመደብደብ ከተማውን ለቆ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል ፡፡ በድምፅ ማጉያ መሳሪያም  ቅስቀሳ እንዳናደርግ ተከልክለናል፡፡
የአንድነት ፓርቲ የወላይታ የዞን አመራር አባል የሆነችው  ወ/ሮ ሀድያ መሀመድ ከትላንት ሐምሌ 26 ቀን 2005 ዓ.ም እለት ጀምሮ በግፍ ታስራ ትገኛለች፡፡ በእስር ቤትም የማታምንበትን ሰነድ እንድትፈርም መገደድዋን ለማወቅ ችለናል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ህዝበ ሙስሊሙን ለአመፅ እንደሚያነሳሳ አድርገው ያቀረቡትን ሰነድ አልፈርምም ፓርቲዬም ይህንን አልፈፀመም በማለት ፓርቲውን ለመወንጀል በተዘጋጀው የሀሰት ሰነድ ላይ ሳትፈርም ቀርታለች፡፡ በአጠቃላይ የመንግስት የፀጥታ ኃላፊዎች እና የአስተዳድር ኃላፊዎች የህገ-መንግስት ጥሰት በአንድነት ፓርቲ ላይ ፈፅመዋል፡፡ በዚህ አስጨናቂ ሁኔታ ላይ ሆነንም በወላይታ ህዝባዊ ስብሰባውን በነገው ዕለት ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በተያዘለት እቅድ መሰረት በህዝባችን ድጋፍ ይከናወናል፡፡
በጂንካ ፣ በአርባምንጭ እና በባህርዳር  ቅስቀሳው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን  ህዝቡም  ድጋፉን በአደባባይ እየገለፀ ይገኛል፡፡ በተለይም በባህርዳር የባጃጅ ሹፌሮች በግል ተነሳሽነት የቅስቀሳው አካል በመሆናቸው የባህርዳርን ህዝባዊ ሰልፍ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡
በአንፃሩ በመቀሌ ከተማ ከሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ቅስቀሳ ለማድረግ ጥረት ሲያደርግ የሰነበተው ልዑክ ምንም ዓይነት የድምፅ ማጉያ መሣሪያ እንዳይጠቀም ከመታገዱም በላይ ለቅስቀሳ ያዘጋጀውን ሞንታርቮ በአደባባይ በፖሊስ ተቀምቷል፡፡ በቅስቀሳ ላይ የነበሩት የአንድነት ፓርቲ ብ/ም/ቤት አባል አቶ እንግዳ ወ/ፃዲቅ እንዲሁም የትግራይ ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሆኑት አቶ ክብሮም ብርሃነ እና አቶ አርአያ ፀጋይ በቀዳማይ ወያኔ ፖሊስ ጣቢያ በአሁኑ ሰአት በዕስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን በደል በተቀነባበረ መልኩ እየፈፀሙ ያሉት የከተማው አስተዳደር እና የፀጥታ ዘርፍ ክፍሉ በጋራ ሲሆኑ ህገ-መንግስቱን በጉልበት በመናድ በመቀሌ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳናደርግ በኃይል አደናቅፎናል፡፡ ይህንን የህገ-መንግስት ጥሰት አንድነት ፓርቲ በፍፁም በዝምታ አይመለከተውም፡፡ የጀመርነውን ሠላማዊ ትግል አጠናክረን ከሰፊው የትግራይ ህዝብ ጋር በመሆን እንቀጥላለን በቅርብ ቀን በድጋሚ በመቀሌ ከተማ ሠላማዊ ሰልፍ የምንጠራ መሆናችንን እያሳወቅን ገዢው ፓርቲ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በግፍ ያሰራቸውን የፓርቲያችንን አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈታ እንጠይቃለን፡፡ የመቀሌ ነዋሪዎች መንግስት በአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ የፈፀመውን አፈና ፊት ለፊት በመቃወም ያሳዩትን አጋርነት ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ አንድነት ፓርቲ ሳይገድል እየሞተ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ትግሉን አጠንክሮ ዛሬም ወደፊትም ይቀጥላል፡፡
መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ሐምሌ 26 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ESAT BREAKING NEWS

ዛሬ በባህርዳር ከተማ ዝናብ እየዘነበም ቢሆን ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ያለው ምስል በከፊል

August 4, 2013
ፍኖተ ነፃነት
መፈክሮች፣
ያማራው ህዝብ ጨዋ እንጂ ፈሪ አይደለም!
ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠው መሬታችን ይመለስ!
የሙስሊም መፍት ሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ባስቸኩዋይ ይፈቱ!
እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም።!
የመሳሰሉት መፈክሮች ተሰምተል!
Bahir Dar Demonstration against T.P.L.F UDJ
Bahir Dar Demonstration against T.P.L.F
Bahir Dar Demonstration against T.P.L.F
Bahir Dar Demonstration against T.P.L.F
Bahir Dar Demonstration against T.P.L.F

Comments

በኦሮሚያ አርሲ ዞን የሟቾች ቁጥር 11 ደርሰ!

August 4, 2013
Free Our Heroes
አንዲት ሴት እና ህጻን ልጅ ከሟቾቹ ውስጥ ይገኙበታል!
ትናንት ማለዳ ጀምሮ የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ገብተው በሰነዘሩት ጥቃት የሟቾች ቁጥር 11 ደርሰ፡፡ ከሻሸመኔ እስከ ኮፈሌ እና ዶዶላ ድረስ በሚያካልለው በዚህ የመንግስት ወታደሮች ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው እና የታሰሩ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል፡፡ በእለተ ቅዳሜ ምንም አይነት ተቃውሞም ሆነ መሰል እንቅስቃሰሴዎች በማይካሄድበት እና ባልተካሄደበት እለት የመንግስት ወታደሮች እስከገጠር ቀበሌዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት ያለርህራሄ የቀጥታ ጥይት በመጠቀም የአካባቢውን ዜጎች ሲገድሉ ውለዋል፡፡
የመንግስት ቴሌቪዥን በተለመደ መልኩ ‹‹ጂሀድ ሲቀሰቅሱ እርምጃ ተወሰደባቸው›› የሚል ዜና ያሰራጨ ሲሆን የሞቱት ሰዎች ቁጥርም 3 ብቻ መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡ መንግስት ቀድሞ በታሰበበት መልኩ በአካባቢው ከፍተኛ የወታደር ሰፈራ በማድረግና በተጠንቀቅ በማስቆም በፌዴራል ፖሊስ፣ አድማ በታኝ እና በወታደሮች በመታጀብ በአካባቢው ሕዝብ ላይ ከማለዳ ጀምሮ ጥቃት ሰንዝሯል፡፡ አራት ኦራል መኪኖች ላይ የተጫኑ ወታደሮች አካባቢውን በመክበብ መስጂዶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ጭምር ጥይት ሲተኩሱ እንደነበር የታወቀ ሲሆን በዚሁም የአካባበውን ታዋቂ የሃይማኖት መምህር፣ አንዲት ሴት እና ህጻን ልጅን ጨምሮ የሟቾች ቁጥር 10 ደርሷል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ አባላት የራሳቸውን መኪና መስታወት በመሳሪያ ሰደፋቸው በመስበር ‹‹ሕዝቡ ሰበረው›› የሚል ፕሮፖጋንዳ ለመስራት የሚያስችል ጥረት ሲያደርጉም ታይተዋል፡፡
መንግስት ምላሽ መስጠት የተሳነውን ሕገ መንግስታዊ የህዝብ ጥያቄ በጥይት በዚህ መልኩ ምላሽ ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ባለፈው አመት በአርሲ ዞን አሳሳ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽሞ አራት ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በአማራ ክልል ገርባ ከተማና በሐረር ኢማን መስጂድ ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ፈጽሞ በድምሩ ከ13 ሰዎች በላይ ህይወታቸው በመንግስት ታጣቂዎች ጥይት ተቀጥፏል፡፡ መንግስት የገደላቸውን ሰዎች በሙሉ ‹‹ለጂሃድ ሲያነሳሱ ገደልኳቸው›› የሚል ማስተባበያ ሲሰጥ ቢቆይም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ አሁንም ይህ የመንግስት ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ቀጥሏል፡፡
አሁንም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ መንግስት ሊፈጥር እያሰበ ያለውን ተጨማሪ ኹከት በመገንዘብና ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ በማሰብ የመንግስትን ትንኮሳ ቸል እንዲልና በትእግስት እንዲያሳልፍ አስቸኳይ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡ የመንግስት ቀዳሚው ፍላጎት መጀመሪያ እንደታየውም ኹከትና ግጭት በመፍጠርና ጥፋት በማድረስ፣ ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ለመወንጀልና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ለመጠቀም በመሆኑና ይህም በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ በመሆኑ፤ መንግስት ኹከት ሲቀሰቅስ በቸልታና አይቶ በማሳለፍ በመንግስት ወጥመድ ላለመውደቅ ሁሉም ጥረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ ከምንም በላይ ሰላማዊነታችን ዋጋ የምንሰጠው መሆኑን ሁላችንም ከግንዛቤ በመክተት ሰላማችንን ሊነጥቁ የሚመጡ ኃይሎን በሰላም ብቻ እነድንመልሳቸው አደራ እንላለን፡