Wednesday, June 5, 2013

የሰሞኑ የአባይ ግርግር

የሰሞኑ የአባይ ግርግር

እስከ ነጻነት
ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛዎችና የውጭ ዜና አውታሮች ጭምር ስለ አባይ ግድብ ብዙ ሲሉ ይሰማል፡  ለምን? ለምን አሁን? ምን የተለየ ነገር ተገኘ?
በመሰረቱ አባይ መገደብና ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ የመጠቀም መብትም ግዴታም አለባት፡ እዚህ ላይ ማንም ጥያቄ ያለው አይመስለኝም፡ ጥያቄ የሚነሳው ግን በርግጥ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር የሚመራው ብድን አባይን አገድባለሁ የሚለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ነው ወይ? ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መክሮና ተስማምቶ ነው ወይ? ግድቡስ ለግርጌ ተፋሰስ አገሮች ጉዳት ያመጣል ወይ የሚሉት ጥያቆዎች መመለስ አለባቸው።
ስለ አባይ ጉዳይ ዝርዝር ከመግባቴ በፊት ወያኔ ለምን በተለያየ ዘዴ ስለ አባይ እንዲነሳ ፈለገ? ግብጽስ አሁን ሰለጉዳዩ ለምን አጀንዳ አረገችው? ወዴትስ ሊያመራ ይችላል? የሚሉትን ከወያኔ ምግባርና ጸባይ ተነስቼ ያለኝን አስተያየት አጠር አርጌ ላቅርብ፡
ወያኔ ባሁኑ ሰዓት አቅጣጫ ጠፍቶት በትርምስ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፤ የውስጥ ሽኩቻ አለበት፤ ከውጭ ጫና አለበት፤ ህዝብ ጭቆና አንገፍግፎት በቃኝ እያለ ነው፡ ይህን ሁሉ አቅጣጫ ለማስቀየር አንድ ዘዴ መፍጠር አለበት፡ የግብጹ ሙረሲም ከግብጽ ህዝብ ሙሉ ድጋፍ የለውም እና አሱም የግብጻውያንን የልብ ትርታ የሚኮረኩር ነገር ይዞ መቅረብ ይፈልጋል፡ ስለዚህ የጋራ ሴራ አየተሸረበ ሊሆን እንደሚችል አገምታለሁ፤ በዚህ ላይ የውጭ አጅ የለበትም ለማለት አልደፍርም፡ ሁኔታው እየባሰ ከሄደ ወደ ጦርነትም ሊያመሩ ይችላሉ የሚል ግምታ አለኝ፡ በተለይ ኢትዮጵያ ጦር ሃይል ውስጥ የማፈንገጥ አዝማሚያ ያሳያሉ ብለው የሚጠረጥሯቸውን ለማስፈጀት እና እግረ መንገዳቸውንም በመርዝ፤ በጥይት፤ በማፈናቀል አላልቅ ያላቸውን ያማራ ህዝብ ባይሮፕላን ለመደብደብም አይመለሱም የሚል ግምት አለኝ ይህ ደግሞ ለትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር አዲስ ነገር አደለም እንኳን ጠላቴ የሚለውን አማራና ነጻ አወጣሃለሁ የሚለውን ህዝብም ከመጨረስ አለተመለሰም፡
1)  ነጻ አወጣሃለሁ ያሉት ህዝብ ላይ አሲረው የነለገሰ አስፋውንና መንግስቱ ሐ/ማርያምን ደደብነት ተጠቅመው ሃውዜንን በልጆቿ ደም አጨማልቀዋታል፡
2)  ከተሸነፈ ጦር ጋር አብረን አንሰራም ብለው ለልመና የዳረጉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሃገር ፍቅር ስሜቱን ስለሚያውቁና ወደፊት ለሚያቅዱት አገር የማጥፋት ሴራ እንቅፋት ይሆናል ብለው ስለገመቱ ባድሜ የሚል ድራማ ደርሰውና አራግበው በመቶ ሺ የሚቆጠር ወጣት አስጨርሰው፤ ለቤተሰቦቻቸው እንኳ በውል ልጆቻቸው የት እንደወደቁና እና የት እንደሞቱ  አልነገሯቸውም፡
3)  የአሜሪካንን ጦርነትን ለመዋጋት ሶማሊያ ድርስ የተላከው ጦር ሬሳው በመቋዶሾ ጎዳናዎች ላይ ሲጎተት ስንት እንደሞተና ስንት እንደቆሰለ እንኳ አልተነገረም እንደ ርካሽ እቃ ወድቆ ቀርቷል፡
ከዚህ ሁሉ የወያኔ እርኩስ አላማና ዘር አጥፊ ወንጀለኛ ባህሪይ ተነስቼ  በወያኔ ጠባብ ዘረኛ አስተዳደር ላይ ቅሬታ ያላቸውን የጦር ሃይል አባላት ሰብሶቦ ሊማግዳቸው ይችላል የሚል ግምት ባቀርብ የተሳሳትኩ አይመስለኝም፡  ስለዚህ መጠንቀቅ ያለባቸው ጦሩ ውስጥ ያሉና በህውሃት በጥርጣሬ የሚታዩ የሰራዊቱ አባላት ሊጠነቀቁና አይናቸውን ከፍተው በንቃት ሁኔታወችን መከታተል ያለባቸው መሆኑን አስምሬበት አልፋለሁ።
ስለ አባይ ጥቂት መረጃዎች
የአባይ ወንዝ ናይልን ከሚመግቡ ሶስት ወንዞች አንዱና ዋናው ነው፤ የወንዞቹ ተፋሰስ ስፋትና የፍሰት መጠን ከታች ባለው ሰንጠረዥ ይመልከቱ
Ethiopia's Nile river
ያባይ ወንዝ ከፍተኛው የገባር ወንዝ መነሻው 4250 ሜ ከባህር ጠለል በላይ ሲሆን ሱዳን ድንበር ላይ ከባህር ጠለል በላይ ያለው ከፍታ 490 ሜ ነው፡ (የ3760 ሜትር ልዪነት ማለት ነው)
አባይ ተፋስስ ከፍተኛ የሃይል ማመንጨትና የመስኖ ልማት አቅም ያለው መሆኑን በተፋሰሱ ላይ የተደረጉ ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን በነዚህ ጥናቶች መሰረት አባይ ተፋሰስ ውስጥ በመስኖ ሊለማ የሚችል እስከ 700,000 ሄክታር የሚደርስ የመሬት ሰፋትና ከፍተኛ ሃይል ማመንጨት ሊመረትባቸው የሚችሉ አራት የግድብ ቦታዎች የገኛሉ (ካርታውን ይመልከቱ)
Ethiopian proposed hydroelectric dams
ለመስኖ ልማት አመቺ የሆነው መሬት የሚገኘው ከመንዳያ ግድብ ግርጌ ጀምሮ እስከ ሱዳን ጠረፍ ድረስ ነው፡
አባይና ደለል
ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊገነዘበው የሚገባው ነገር፡  አባይ ወንዝ ባማካይ ባመት 320 ሚሊየን ቶን ደለል ከኢትዮጵያ ኮረብታዎች ሸርሽሮና ተሸክሞ አሰዋን ግድበ መዳረሻ ላይ ይዘረግፈዋል፡ ይህም የግድቡን ውሃ የመቋጠር አቅም ይቀንሳል፡ ሊለማ የሚችለው መሬት በደለል ይሸፈናል፤ ደለሉ የውሃ መጥለፊያ ቦዮችን ይደፍናል እናም ሱዳንና ግብጽን በተለይ ሱዳንን ከፍተኛ ወጭ ያስወጣቸዋል፡ ይህ ትልቅ ችግር የሱዳንና የግብጽ የውሃ ባለሙያዎችን እንቅልፍ የነሳ ጉዳይ በመሆኑን በብዙ አለም አቀፍ መድረኮች ሲያቀርቡትና ይህንኑ ለማስቆም ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም አባይ ተፋስስ ውስጥ ከፍተኛ የጎርፍን መሽርሸር መከላከያ ሰራ መሰራት እንዳለበት ይመክራሉ፡ (Ahemed, 2007Betrie  et al., 2010.)  ያቀረቡትን መመልከት ይቻላል፡
የተወራለት የአባይ ግድብ
1) ግድቡ የኢትዮጵያን ህዝብ ሊጠቅም የሚችልና የምግብ ፍላጎት በፍተኛ ደረጃ ሊቀርፍ የሚችለው የመስኖ ልማት አላካተተም
2) ወደ መሃል ሃገር ቀረብ ያሉትንና ለመስኖ ልማት ሊውሉ የሚችሉ ግድቦችን ዘሎ ድንበር ላይ መገደብ ለምን እንደተመረጠና ጠቀሜታውን የሚያረጋግጥ ምንም መረጃ ለህዘብ አልተገለጸም፡ በመስኖ የመጠቀም መብቷንም እስከወዲያኛው የዘጋ ታላቅ ሴራና አገር ክህደት ወንጀል ነው፡
3) ግድቡ የሚያመርተው የመብራት ሃይል ብቻ ነው፡ ከልምድ እንደሚታወቀው ደግሞ የውሃ ሃብት ፐሮጀክቶች ዘርፈ ብዙ እስካልሆኑ ድረስ አትራፊ እንደማይሆኑ ይታወቃል፡ ስለዚህ የአባይ ግድብ በየአመቱ ወደግድቡ የሚገባው 320 ሚሊየን ቶን ደለል ሞልቶት የግደቡ እድሜ አስኪያልቅ ድረስ እንኳን አትራፊ ሊሆን የሚገነባበትን ወጪ ለመመለሱም በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፤ ከህዝብም የተደበቀ የወያኔ ሚስጥር ብቻ ነው፡
4) የተፋሰሱን ጎርፍ ሽርሸራ ለመከላከል ወይም ለመቀነስ የተደረገ የተፋሰስ ልማት ስለመደረጉ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም፡
5) ውሃው የሚተኛበት መሬት እስከመጨረሻው ከጥቅም ውጭ የሚሆን ነው፡ ደለሉ የሚከማችበት ቦታም እንደዚሁ፡ ይህን በተመለከት የምጣኔ ጥናትና አካባቢ ሁኔታ ጥናት(economic analyses, environmental impact assessment) ስለመደረጉና አዋጭ ስለመሆኑ ምንም የሚታወቅ ምንም ነገር የለም፡
6) ግደቡ ከኢትዮጵያ ይልቅ የሚጠቅመው የግርጌ ተፋስስ አገሮችን ነው፤ ወሃው ከደለል ነጻ የሆነና የተመጣጠነ ውሃ ወደ ግርጌ ተፋሰስ አገሮች ስለሚለቀቅላቸው ዋናው አገልገሎቱ ለሱዳንና ለግብጽ ነው
ማጠቃለያ
ከላይ እንደተገለጸው የአባይ ግድብ በዋናነት የሚጠቅመው ሱዳንን እና ግብጽን መሆኑ ግልጽ ነው፤ ምንም ገንዘብ ሳያወጡ በኢትዮጵያውያን ላብ እና ደም የተሰራላቸውን የደለል መቆጣጠሪያ ግድብ እና የመስኖ ልማት የመጠቀም እደሏን እሰከመጨረሻ ያዳፈነ ፐሮጀክት ሊጠሉት የሚችሉበት እና አባይ ግድብን ለማስቆምም ይሁን አደጋ ለማድረስ የሚያስችል ምንም አይነት ነባራዊ ሁኔታዎች የሉም፡ ራሱ ወያኔ ካላፈረሰው በቀር፤ በዚህ ደግሞ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ተመክሮ አለው፡ አዲስ አበባ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ ፈንጂ ቀብረው ንጹሃን ዜጎችን መጨረሳቸውን ሊዘነጋ አይገባም፡
ስለዚህ ግብጽ ስለ አባይ እንዲህ አለች እንደዛ አለች፡ ሱዳን ይህን አለ የሚባለው ወሬ ሁሉ የወያኔና ግብረ አበሮቹ የተለመደ አኪልዳማ፤ ሃረካት ክፍል መሆኑን መረዳትና ለዚህ ወሬ ትኩረት ሳንሰጥ አገራችንን አገራዊ አመራር እንዲኖራት ማድረጉ ላይ ትኩረት መስጠት አለብን። ስለ አባይ ተፋሰስ ልማት ወደፊት ህዝብ የሚመክርበና የሚወስንበት ጉዳይ ነው፡ ምናልባትም አሁን በመሰራት ላይ ያለው ግድብ ቆሞ ከላይ ላሉት ግድቦች ቅድሚያ ሊሰጥ የሚችልበት አጋጣሚም ሊኖር ይችላል።፡ከሁሉ የሚቀድመው ግን ነጻነት ስለሆነ የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባርን ጠባብ ዘረኛ የግዞት ቀንበር መስበር ያስፈልጋል፡ የተጀመረውን ሁለገብ ትግል ማጋጋልና ማጠናከር አለብን አንጂ ስለአባይ ወያኔ የሚያቀብለንን ጉላንጆ በማላመጥ ጊዜም ጉልበትም ማባከን አይገባንም ብዬ ሃሳቤን አጠቃልላለሁ፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊ አመራር ይስጣት
አመሰግናለሁ
እስከ ነጻነት

No comments:

Post a Comment