Thursday, February 28, 2013

መረጃ ቁልፍ ነው። ቁልፉ ደግሞ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን( ኢሳት) ነው።


መረጃ ቁልፍ ነው። ቁልፉ ደግሞ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን( ኢሳት) ነው።

                               NORWAY OSLO ESAT FUNDRAISING FEB.10 2013
የመልካም አስተዳደር እጦት፣ነፃነትና የፍትህ እጦት፣የነፃ ፕሬስ እትመት መታፈን ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች አባልና ደጋፊ በማሰር ፣ጋዜጠኞችን ማሰርና ከአገር እንዲሰደዱ ማድረግ፣የውሸት ምርጫዎች መብዛት የሰብዓዊመብቶች ረገጣ የሥራ አጥነት መበራከት፣ የአግአዚ ጦር ሠራዊት እና “የጆሮጠቢዎች” በወገናችን የሚያደርሱት እልቂትና ስቃይ ሰለባ የሆናችሁና ነጻነትና ፍትህን ናፋቂ የሆንን ፣የአገራችሁ አንድነት የሚያንገበግባችሁ ዜጎች ሁሉአሁን ወቅቱ የሚሻው የትግል ጊዜ ላይ በመሆናችን ለዚህ ሁሉ ደግሞ መረጃ ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለውን የሕዝብ ብሶት የሚያሰማው የሕዝብ ሀብት የሆነውን ኢሳትን መርዳት ከዘመናዊ ባርነት፣ከውሸት ፕሮባጋንዳ ለመዳን፣የሕዝብ ብሶትንና በደልን ለማሳወቅ ትልቁ የመገናኛ መሣሪያ መሆኑን አያጠራጥርም! ኢሳት የማያጠያይቅ ቁልፍ መረጃ ነው።ለዚህ ደግሞ ኢሳትን መርዳትና መደገፍ የዜግነት ግዴታ ውዴታም ነው።የሕዝብን የስቃይ ግዜ ለማሳጠር ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ተደራጅተን መረጃዎችን ለኢሳት በመስጠት ሕዝባችን መታደግ አለብን።

በኖርዌ አገር በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ በጣም የሚያዛዝን ድራማ ተዘጋጅቶም ነበር ። ያም ድራማ የሚያሳየው የውያኔ ሰራዊትና ፌደራል ፖሊስ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በህዝቡ ላይ የሚያደርሱትን ስቃይና እንግልት የሚያሳይ  ተመልካችን በእንባ ያራጨና ወደ ኋላ በትዝታ ወስዶ ለካ እንደዚህም ተደርጓል ብሎ ሕዝቡ ከልብ ያለቀሰበት,፣ ያሳዘበት ግዜም ነበር ! ድራማው ሲተውኑ የነበሩትም ሰዎች በጥሩ ሁናቴ ተጫውተውትም ነበር በተለይ በፌደራል ልብስ ለብሶ ሲተውን የነበረው ዳንኤል በቀለ የተመልካቹን ድባብ በፌደራል ፖሊስ ንግግር ፈገግ አድርጎት አምሽቷል።

 ሀገሩንና ሕዝቡን የሚወድ ደግሞ ኢሳትን ይታደግ!

እውነት እንዲ ነው!! ”…እኔ አርቲስት ነኝ በአርቲስትነት መኖር እችልነበር። መፅሐፉ የሚለው ከፊትህ  እሳት ቀርቦልሃል እጅህንወደወደድከው ጨምር ነው። እኔ እጄን ወደ ውሃ ከትቼ በአርቲስትነቴእየደነስኩ መኖር አያቅተኝም ነበር። ነገር ግን የእውነት ጉዳይስ?የኢትዮጵያ ጉዳይስዝም ብሎ የሚኖር ህሊና አለን?… እድሜዬእንደምታዩኝ ላይሆን ይችላል። ፖለቲካ ያቃጥላል፣ ያናድዳል። ሆኖምግን እስከመጨረሻ ለመፅናት ነው ቃል የገባሁት።አርቲስትናአክትቪስት ታማኝ በየነ
                        ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ጆሮ ነው !
    ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
               ከዘካሪያስ አሳዬ

No comments:

Post a Comment