Saturday, May 24, 2014

በአዲስ አበባ ከሚፈርሱ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እየተከሰተ ነው

May23/2014
ግንቦት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ተጠናክሮ በቀጠለው የቤት ፈረሳ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በድንገት ቤቶቻቸው እየፈረሱባቸው ንብረቶቻቸውን እየተዘረፉ ሜዳ ላይ እየወደቁ ሲሆን፣ ትናንት ሌሊት በድንኳን ተጠልለው ከነበሩት ነዋሪዎች መካከል የ4 ልጆች አባት የሆኑ ግለሰብ በጅብ ተበልተው ዛሬ ከፊል አካላቸው በፖሊሶች መነሳቱን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

ፖሊሶች መረጃው እንዳይወጣ አካባቢውን ተቆጣጥረው ሰዎች እንዳይንቀሳቀሱ ሲያደርጉ የዋሉ ሲሆን፣ ቀሪው አስከሬን ከተነሳ በሁዋላ ደግሞ በማይክራፎን እየዞሩ በላስቲክ ድንኳን የተጠጉትን ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እያዘዙዋቸው ነው። ብዙዎቹ ልጆቻቸውን የት እንደሚያስጠጉዋቸው ጨንቋቸው ለኢሳት በመደውል የድረሱልን ጥሪ አቅርበዋል የሟቹን ግልሰብ ስም ለማግኘት ጥረት ብናደርግም እስካሁን አልተሰካላንም።ፖሊስ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጠን ተደጋጋሚ ሙከራ ብናድርግም አልተሰካላንም።

ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ለኢሳት በጻፉት የጋራ ደብዳቤ ደግሞ ፣ እንደ አዲስ ሰሞኑን የሚፈርሱ ቤቶች በዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተስፋ በተደረገ ፈንድ ለሚገነባው የኦሎምፒክ መንደር ፕሮጀክት ቦታ ለማዘጋጀት ሲባል በመሆኑ ኦሎምፒክ ኮሚቴው የህዝቡን ስቃይ አይቶ፣ ድጋፉን እንዲያዘገይ ጠይቀዋል።

ነዋሪዎቹ በደብዳቤያቸው “የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ 2 ሚሊዩን የኢትዮጵያ ብር እንደሚሰጣቸው” ገልጸዋል።

“በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሦስት ቀናት ውስጥ መኖሪያቸውን ነቅለው ከአካባቢው እንዲወጡ ጥብቅ ትዕዛዝ የተላለፈው ከዚህ ፕሮጅክት ጋር በተያያዘ መሆኑን ነዋሪዎች በደብዳቤያቸው ጠቁመዋል።

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ” የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ከዚህ በፊት ቤታቸውን ነቅለው አካባቢውን እንዲለቁ በተደጋጋሚ እንደ ተገለጸላቸው የሚጠቁም  ቢሆንም ፣  ከዚህ በፊት ቤት ግን አንድም ቀን ነዋሪዎቹ ነቅለው እንዲነሡ እንዳልተነገራቸውና ደብዳቤም ተጽፎላቸው እንደማያውቅ” ጠቅሰዋል፡፡

በሦስት ቀናት ውስጥ ቤቶች እንዲፈርሱ የታዘዘበት ምክንያት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ሁሌም እንደ ሚያደርጉት የኗሪዎችን ቤት ነቅለው በመወሰድ እንጨቶችን፣ ቆርቆሮዎችን፣ በሮችንና መስኮቶችን በወረዳ አሰተዳደር ቅጥር ግቢ እያጫረቱ በመሸጥ ቤት አፍራሾቹና አመራሩ እንዲካፈሉት ለማድረግ መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

“የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ  ከክፈለከተማው አስተዳደር የመጣ ትእዛዝ ነው ምንም ማድረግ አልችልም የሚል መልስ ለአቤቱታ አቅራቢዎች ሲሰጡ፣ የክፍለ ከተማው አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ደግሞ አቤቱታ አቅራቢዎች ከቢሯቸው እንዲባረሩ ማስደረጋቸውን ነዋሪዎች በጽፋቸው አስፍረዋል።

ኗሪዎች በንብረታቸው ላይ ሊካሄድ የታቀደውን ዝርፍያ በመፍራት የቤቶቻቸውን ጣራና በር አንስተው ዘመድ ያለው ከዘመድ የሌላቸው ደግሞ ላስትክ ዘርግተው በተጠለሉበት ቅዳሜና እሁድ ባለማቋረጥ የዘነበውን ዝናብ በላያቸው ማሳለፋቸውን፣ አራስ እናቶች እና አዲስ የተወለዱ ሕጻናት፣  ነፍሰጡር ሴቶች  በበሽታ ላይ መውደቃቸውንም አመልከተዋል።

የኢህአደግ መንግስት በሕይወት እያለን ገድሎን በድኖቻችንን በሜዳ ላይ በትኗል የሚሉት ነዋሪዎቹ፣  በካሬ እስከ ሠላሳ ሺ ብር ድረስ የሚያጫርቱትን የአዲስ አበባ መሬት 18 ብር ብቻ ተቀብለው እንዲለቁ የታዘዙ በዙሪያችን ያሉ የኦሮሚያ አርሶ አደሮች እያለቀሱ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ በደብዳቤያቸው መጨረሻ ” የኦለምፒክ ፌዴሬሽን በዓላማውና ባለው እሴት ሰብዓዊ መብትን ከሚጋፋ ተግባር ጋር የማይተባበር ተቋም ቢሆንም በጭካኔ ከሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግስት መተባባሩን ኮንነዋል።

” በኢትዮጵያውያን ላይ በኦሎምፒክ ኮሚቴ ስም እያረፈ ያለውን ሊረሳ የማይችል ጠባሳ በተመለከተ  በማስገንዘብ በእኛ ላይ ለሚፈጸመው ግፍ ከዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚያገኘውን ፈንድ እንዲቆምላቸው” ጠይቀዋል።

ከአለማቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎችም ጉዳዩን እንዲያደርሱላቸው ተማጽነዋል።
ደብዳቤውን የጻፉትን ሰዎች በስልክ አነጋግረን እንደተረዳነው፣ ደብዳቤያቸውን ከጻፉ 2 ሳምንታት ያለፈው ሲሆን፣ መንግስት የሚወሰድውን እርምጃ በመፍራት እስካሁን ይፋ ለማድረግ ሳይፈልጉ ቀርተዋል።

የአኖሌ ሃውልት ፖለቲከኞችንና ምሁራንን እያወዛገበ ነው

May 24/2014

ታሪኩ አፈ ታሪክ ነው፤ በደንብ ሊጠና ይገባዋል ተብሏል

በአፄ ምኒሊክ ዘመን ተፈጽሟል የሚባለውን ኢ-ሠብአዊ ድርጊት ለማሳየት በኦሮሚያ አርሲ ዞን አኖሌ በተባለ ስፍራ የተገነባው ሃውልት፤ የታሪክ ምሁራንን እና ፖለቲከኞችን እያወዛገበ ሲሆን፤ የታሪኩ እውነተኛነትና የሃውልቱ አስፈላጊነት አከራካሪ ሆኗል፡፡

ተቃራኒ አስተያየቶችን ለአዲስ አድማስ የሰጡ ፖለቲከኞች፤ ታሪኩ እውነተኛ ነው ወይስ አይደለም በሚለው ጥያቄ አልተስማሙም፡፡ በአኖሌ ተፈጽሟል የተባለው ጡት እና እጅ የመቁረጥ ድርጊት በታሪክ ሰነዶች ያልተመዘገበና ያልተረጋገጠ አፈታሪክ ነው የሚሉ ፖለቲከኞች፤ ሃውልቱ ጥላቻና ቂም በቀልን የሚሰብክ ስለሆነ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡ በአኖሌ ኢሰብአዊ ድርጊት መፈፀሙ እውነተኛ ታሪክ መሆኑን የሚያምኑ ፖለቲከኞች በበኩላቸው፤ ሃውልቱ  መገንባቱ ተገቢ የሚሆነው  ድርጊቱ እንዳይደገም መማሪያ ስለሚሆን ነው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህር አቶ አበባው አያሌው፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሴት ልጅ በጦርነት ጊዜ የተለየ ጥበቃ እንደሚደረግላት ጠቅሰው፤ በአኖሌ ጡት ተቆርጧል ለሚለው ማረጋገጫ የሚሆን የታሪክ ሰነድ የለም ብለዋል፡፡ አፈታሪኩ ከብሔርተኝነት ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ነው ያሉት አቶ አበባው፤ አፈታሪክን መነሻ አድርጐ ሃውልት መገንባት አይገባም፤ ከዚህ በተጨማሪ ሃውልቱ ጥላቻና ቂም በቀልን ከማንፀባረቅ የዘለለ ፋይዳ የለውም ብለዋል፡፡

የታሪክ ምሁሩና ፖለቲከኛው ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በበኩላቸው፤ የሃውልቱን መገንባት እንደማይቃወሙ ገልፀው፤ ከአፈ ታሪክ የዘለለ ማረጋገጫ ሰነድ አልተገኘለትም፤ ነገር ግን ከታሪክ የመረጃ ምንጮች መካከል አንዱ አፈ ታሪክ በመሆኑ  በጉዳዩ ላይ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ የሃውልቱ መገንባት ጥላቻና ቂም በቀልን ለቀጣይ ትውልድ ያስተላልፋል የሚለውን አመለካከት እንደማይቀበሉት የገለፁት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ የታሪኩን እርግጠኛነት ከዩኒቨርስቲ መምህራን መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡ ሃውልቱም በትክክል ድርጊቱን ከማንፀባረቅና ለመማሪያ ከመሆን ባለፈ ጥላቻና ቂም በቀልን አያስተላልፍም ባይ ናቸው፤ አቶ ቡልቻ፡፡ የመድረክ አመራር የሆኑት አቶ ገብሩ ገ/ማርያም በበኩላቸው፤ የሃውልቱን መገንባት የሚቃወሙ ሰዎችን አጥብቀው ኮንነዋል፡፡ ጡት እና እጅ የመቁረጥ ድርጊት ተፈጽሟል የሚሉት አቶ ገብሩ፤ ፖለቲከኞች እና ምሁራን ይሄን ታሪክ ለማድበስበስ መሞከራቸው ተቀባይነት የለውም ሲሉ ተችተዋል፡፡ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ሞጋ ፈሪሣ በበኩላቸው፤ ጥንት የተደረገ ታሪክ እየተመዘዘ ለፖለቲካ ፍጆታ መዋሉን ይቃወማሉ፡፡ የአሁኖቹ ባለስልጣናት ሃውልቱን የማስገንባትም ሆነ ታሪኩን የመንገር የሞራል ብቃት የላቸውም የሚሉት ዶ/ር ሞጋ፤ ዛሬም ቢሆን የኦሮሞ ህዝብ በወገኖቹ እየተበደለ ነው ብለዋል፡፡ የፍልስፍና ምሁሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሠፋ፣ የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባው መሃሪ እና የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራር ዶ/ር ሃይሉ አርአያ ሃውልቱን አጥብቀው እንደሚቃወሙ አመልክተው፤ የሃውልቱ መገንባት የፖለቲካ ሴራ ነው ሲሉ ኮንነዋል፡፡ ከሣምንታት በፊት የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከድርን ጨምሮ የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት የመረቁት ይሄ አወዛጋቢ ሃውልት፤ ለግንባታው 20 ሚሊዮን ብር የወጣበት ሲሆን በውስጡ የአካባቢውን ባህል የሚያንፀባርቅ ሙዚየምን ጨምሮ የባህል ማዕከልን እንደማያካትት ታውቋል፡

Thursday, May 22, 2014

Ethiopia: Bloggers of the World, Unite!

May 21, 2014
Zone 9 Bloggers in Ethiopia Jail
Today is the 25th day in jail for Zone 9 Bloggers in Ethiopia. They have not been charged; in fact, the government could not come up with reasonable cause for detaining the 6 bloggers and 3 journalists. It has now come to our attention that two have been tortured. All they did was blog about conditions in their own country. Corruption has gone out of control; in a decade beginning in 2001 $16.5 billions have been illicitly transferred to foreign banks [according to Washington, DC-based Global Financial Integrity]. There are chronic water, power and food shortages. The state security literally eavesdrops on telephone conversations and controls Internet connectivity making Ethiopia the least served in Africa. The ruling party took office through the barrel of the gun and divided the country arbitrarily along ethnic lines [and later orchestrated a sham elections that it won]. This is 22 years ago. It has made it clear that it will not hand over or share power through the ballot box. It refused to abide by results of the 2005 elections when it was dealt a humiliating defeat. A year later, it abolished all opposition on the pretext of terrorism which the US and UK governments wholly endorsed and financed. All grassroots organizations that the ruling party did not like were de-registered. Ethiopia now leads the world in the number of journalists jailed or exiled and in human rights abuses.
If you are a blogger you can be part of a global effort to give voice to those denied and to help free those in jail for demanding their constitutional and unalienable rights. Please send a note to Obama and Cameron Administrations, to European Parliament, etc or simply to friends. We can change conditions both locally and globally if we come together. We refuse to bend to those who seek to divide our humanity in order to remain in power! Freedom! Freedom! Freedom!

Wednesday, May 21, 2014

Democratic change in Ethiopia support organization in Norway proudly announce to all Ethiopians and supports that our radio station soon be on air.

Democratic change in Ethiopia support organization in Norway strongly believe in the existence of free media which is one of the building blocks of democratic system unfortunately the ruling party in Ethiopia crackdown all free media institutions and surpassed freedom of expression for over two decades. 
Our organization relentlessly condemn this inhuman regime ever since our establishment and one of our primary goal is to work with any legitimate organization with the agenda of change the current regime to embark our country to a democratic and peaceful state , on anther hand to help and facilitate the struggle for freedom implying vital instruments , as a result we are proud to announce the establishment of our new radio service via internet in order to reduce the absence of free media in Ethiopia and we aim to intensify our struggles to build democratic system in Ethiopia under which freedom and justice are guaranteed .
10362400_775142339196914_1935924917_n10362400_775142339196914_1935924917_n
Our radio station starts its first broadcast system test on 24th of May 2014 from 1pm till 3pm through our internet radio services dceson.listen2myradio.com/ to all of our esteemed audiences here in Norway and all over the world. 
Our services are accessible everywhere the internet is available. We work alongside with all freedom loving citizens and organizations to get our voice heard as well as to reach out our supporters and members about organizational, local and international activities.
Victory to the people of Ethiopia.
Democratic change in Ethiopia support organization in Norway
-በኦህዴድ -ህወሃት እንደተቀነባበረ በሚነገርለት አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ የሶማሊ ክልል ተወላጅ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ያለመ መሆኑን ለኢሳት ደረሰው መረጃ ያመለክታል።
የመንግስት ካድሬዎች ” የሶማሊ ተማሪዎች ከመንግስት ጎን ቆመው በኦሮሞ ተማሪዎች ዙሪያ መረጃ እየሰጡን ነው” የሚል አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መነዛቱ፣ የሶማሊ ተማሪዎችን ስጋት ላይ የጣላቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ከመንግስት ጎን አለመቆማቸውንና እንዲህ አይነት አሉባልታ እየተነዛ ያለው የሁለቱን ብሄር ህዝቦች ለማጋጨት መሆኑን እየተናገሩ ነው።
የተማሪዎች ወላጆች በሚነዛው ወሬ መደናገጣቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንለት የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አማካሪ የነበረውና የስዊድንን የአንቲገን ሽልማት አሸናፊ የሆነው አብዱላሂ ሁሴን ወሬው እንዲህ አይነቱ አሉባልታ በስፋት የሚሰራጨው የሁለቱን አካባቢዎች ተወላጆችን ለማጋጨት ነው ብሎአል።