Tuesday, March 11, 2014

http://www.abesha.no/P%C3%A5-Amharisk/1586                                 

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኖርወይ
በኖርወይ ኢትዮጵያውያንን የሚወክል ቡድን ኣለ?

ኢትዮጵያውያን በቅኝ ግዛት የተገዛን ህዝቦች ባለመሆናችን እንደ ሌሎቹ ኣፍሪቃውያን ሃገራት በብዛት የምንጎርፍበት የስደት መዳረሻ ኣገር የለንም፡ ፡ ሌሎች ኣፍሪቃውያን በብዛት የሚገኙት በድሮ ቅኝ ገዢያቸው ኣገር ሲሆን እኛ ግን በስደት ብብዛት የምንገኘው በዋንኛነት በጎረቤት ኣገሮች(ሱዳን ኬንያ) በ ኣረብ ኣገሮች ሲሆን በምዕራቡ ዓለም ግን በ ብዛት ኢትዮጵያውያንና ትዉልደ ኢትዮጵያውያንን ያስጠጋች ሃገር ዩ.ኤስ.ኤ መሆንዋ ይታወቃል፡ ፡ ቤተእስራኤላዊያንን በሙሴ ኦፐረሽንና በ80ዎቹ መጀመርያና  በ ሶሎሞን ኦፐረስሽን  በ1991 ዘሮቼ ብላ የወሰደች እስራኤልም በትዉልደ ኢትዮጵያውያን ብዛት ተጠቃሽ ነች፡ ፡በተዛምዶ ከፍተኛ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚገኙባቸው የኣዉሮጳ ሃገራት በቅደምተከተል ጀርመንና ስዊድን ሲሆኑ ኖርወይም በ 2013 መጨረሻ 7000 ያክል ኢትዮጵያውያንና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩባት የኖርወይ የስታትስቲክስ ማእከላይ ቢሮ ዘገባ ያረጋግጣል፡ ፡ ከእነዚህ 2800ዎቹ የኖርወይ ዜግነት ያገኙ ናቸው፡ ፡ 
Publisert: 09.03.2014 12:53
Av Girmay Assemahegn
ከኢትዮጵያ ወደ ኖርወይ በብዛት የፖሊቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ የመጡት የመጀመርያዎቹ ኢትዮጵያውያን እ.ፈ.ኣ. ከ 1974 በኋላ ነበር፡ ፡ ከ 1974-1991 የደርግ መንግስት ተቃዋሚዎች እራሳቸው ኖርወይ እየገቡ ጥገኝነት በመጠየቅና ከኢትዮጵያ ጎረቤት ኣገሮች በተ.መ.ድ. ስደተኞች ኮሚሽን በኩል ኖርወይ ኮታዋን እያነሳች ያመጣቻቸው ኢትዮጵያውያን በኖርወይ እንደ መጀመርያው የትዉልደ ኢትዮጵያውያን ትዉልድ ይቆጠራሉ፡፡

ለጥቆ በኖርወይ በስደተኝነት የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ኢህኣዴግ ለፖሊቲካ ስልጣን ከበቃ በኋላ እ.ፈ.ኣ. ከ 1991 ጀምሮ የገቡት ናቸው፡ ፡  የኢትዮጵያን የንግድ መርከብ በኖርወይ ወደብ ኣሳርፈው እጃቸውን ከሰጡት ሌላ በብዛት በፖሊቲካ ሳቢያ የተሰደዱት ከኢህኣዴግ ጋር የሽግግር መንግስት መስርቶ የነበረው ኦነግ እንደገና የትጥቅ ትግል ካወጀበት ጊዜ በኋላ ነበር፡ ፡ 

እላይ ከተጠቀሱት ኖርወይ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኣያሌ ትዳር መስርተው፡ ቤተሰባቸውን ኣምጥተው ወልደው ከብደው የልጅ ልጅ ያደረሱ በኖርወይ የተሳካ ሂወት መርተው ኖርወይና ትዉልደ ሃገራቸውን በተለያየ ዘርፍ በ እውቀታቸው የሚያገልግሉ ይገኙባቸዋል፡ ፡ በታማኝነትና በሰነምግባር ለሃገሪቱ ኗሪዎች ሳይቀር መልካም ኣርኣያ የሆኑ ይገኙባቸዋል፡ ፡

ከ ምርጫ 97 በኋላም ቢሆን በሃገሪቷ የተፈጠረው ቀላል የማይባል የፖሊቲካ ቀውስ ብዙ ኢትዮጵያውያን የፖሊቲካ ጥገኝነት እንዲጠይቁ ኣድርጓል፡ ፡ ብዙዎች ደግሞ ሃገራቸውን በተለያያ ምክንያት ለመልቀቅ  ፈቅደዋል፡ ፡ ኣገሪቷ ለከፍተኛ ትምህርት ልካቸው ያልተመለሱ፡ የኤኮኖሚ ችግር ኣስገድድዋቸው ቤተሰብ ጥለው የተሻለ ኑሮን ተመኝተው ከኣገርቤት የነጎዱ በዚህኛው ክፍል ይመደባሉ፡ ፡
ፖሊቲካዊ እንቅስቃሴ??

የመጀመርያዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በወቅቱ ጸረ ደርግ ትግል ያካሂዱ የነበሩት ድርጅቶች በተለይም ህወሓትንና ኢህኣፓን በመደገፍ ኣስተዋጸኦ ኣድርገዋል፡ ፡ እ.ፈ.ኣ. ከ 1993 በኋላ የመጡት የኦነግ ታጋዮችና ከድርጅቱ ጋር ንክኪ ያላቸው ስደተኞችም ድርጅቱን እየደገፉ ቢሆንም የድርጅቱ መሰነጣጠቅ የራሱን ጫና እንደፈጠረባቸው ይገመታል፡ ፡ በዚህ ክፍል የሚመደቡት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከሃገር ቤት ጋር ያላቸው ግንኙነት እየጠበቀ መምጣቱን ምንጮች ይጠቁማሉ፡ ፡ በቅርቡ ከኦነግ በበመዉጣት ኦ.ዲ.ግ. የፈጠሩት ኣንጋፋ ታጋይ ሌንጮ ለታ ወደ ኣገርቤት መመለሳቸው ይህን ቁርኝት የበለጠ እንደሚያሰፋው ይገመታል፡ ፡ ከኢትዮጵያ ኣንጋፋ የፖሊትካ ድርጅቶች በ ህወሓት፡ በኢህኣፓ፡ በኦነግና በኦብነግ በኣመራር ደረጃ ሲሳተፉ የነበሩ ወደ ኣገርቤት ብንመለስ ጥቃት ሊደርስብን ይችላል ቢሉ የሰማ የሚያምናቸው ጥቂት ሊህቅ ፖሊቲከኞች በኖርወይም ይገኛሉ፡ ፡
ኦብነግ (ኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ ኣውጭ ግንባር) ኣባላትና ደጋፈዎች በተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች በኖርወይ ህልዉናቸውን ያሳዩ ቢሆንም የድርጅቱ ኣንጃ ከመንግስት ጋር ድርድር ኣድርጎ ኣገርቤት ከገባ በኋላ ብዙ የቀድሞ የድርጅቱ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ መንግስት የልማት እንቅስቃሴና ሰላም ከሚደግፉ ኣካላት በጋራ መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡ ፡ ከምርጫ 97 በፈት የተጀመረና ምርጫው ካስከተለው ቀዉስ ጋር ተያይዞ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን የፖሊቲካ ድርጅት ኣባልነታቸውን እንዲመሰቃቀል ኣድርጎታል፡ ፡

እ.ፈ.ኣ. በ. 2008  በኢትዮጵያ መድረክ ሲመሰረት የመድረክ ኣባላትና ደጋፊዎች ነን እያሉ በይፋ የሚንቀሳቀሱት ጨምሮ  በኢትዮጵያ በኣሸባሪነት የተፈረጀው ግንቦት ሰባትም ለትጥቅ ትግሉ የኖርወይ ክሮነር ትተው ኣስመራ የሚነጉዱለት ኣባላት ባያገኝም 500 ዶላር እየከፈሉ የሚታለቡለት ላሜ ቦራዎች ኣላጣም፡ ፡ ከ 50-70 የሚያክሉ ወጣቶች ቲ ሸርቱን ለብሰው በመሪያቸው በ ዳግማዊ "ባልቻ" ኣንዳርጋቸው ፈት ኣካኪ ዘራፍ ሲሉ በኢሳት መስኮት ታይተዋል፡ ፡ የፊልሙ ቅጅ ቀድመው ለ ስደተኝነት ጉዳይ ይግባኝ ቦርድ የላኩት ከፈሎቹ በኢንቨስትመንት ዓይን ትርፋማ ሊባል በሚችል ሁኔታ በተጻፈላቸው የድጋፍ ደብዳቤ ፍቃድ ኣግኝተውበታል፡ ፡፡
በወቅቱ ኖርወይ በጸረ-መንግስት የተቃዋሚነት  እንቅስቃሴ የላቀ ደረጃ ላይ እንዳለች በተቃዋሚዎች ድረገጽና ማሕበራዊ ሚድያ ገጾች ተጋኖ ሲወራ ይሰማል ይታያል፡ ፡ ኢትዮጵያውያን በቤተክርስትያን ዉስጥ ገብተው ከነቤተሰቦቻቸው ራሃብ ኣድማ መተዋል፡ ፡ ኣገርቤት ከምንገባ እዚሁ ሞታችንን እንመርጣለን ብለው በኖርወይ ፖሊስ እንግልት ሲደርስባቸው ኣይቶ ልቡ ያልተሰበረ ኢትዮጵያዊ ወገን ኣልነበረም፡ ፡ ሰላማዊ ሰልፍ፡ የገንዘብ መዋጮ ላንዳንዶች ወርሃዊ መደበኛ እንቅስቃሴ ሆኗል፡ ፡
ጥያቄው በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ የሚሳተፉት ኢትዮጵያውያን በኣብዝሃ ኖርወይ ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ስንት መቶኛ ናቸው?
በእንቅስቃሴዎቹ ጉልህ ኣስተዋጸኦ ከሚያደርጉትስ ኢትዮጵያውያን ውስጥ ሁሌ 70 በመቶ በላይ ፍቃድ የሌላቸው መሆኑ ምስጢር ይሆን?
ኣንዳንድ ኢትዮጵያውያን የፖሊቲካ እንቅስቃሴያቸው ማሳረገጫ እንዲሆንላቸው የኣንድን ብሔር ኣባላት ለይተው በተለይ በቀጥታ ፊት ለፊት የሚቃወምዋቸውን ግለሰቦች ስም ሰጥተው በኢትዮጵያ መንግስት ስላይነት ከሰዋል፡ ፡  በሰው ያስጻፉትን የኢትዮጵያን መንግስት የሚተች ኣርቲክል የኖርወይ ክሮነር ዉሎ ይግባ ኣንዳንድ የድረገጽ ኣዘጋጆችን ጉቦ በመስጠት ኣስለጥፈው ሲያበቁ፡  ስታቫንገር ድረስ ሄደው መቸውም ድል ነስታ ቆሽታቸውን ያሳረረችውን የብሔር ብሔረሰብ ሰንደቅ ዓላም ሲያወርዱ የተነሱትን ፊልም በኩራት ወደ ዩትዩብ መጫናቸውን  ረስተው ያቀረቡት ክስ ግን እራሳቸውን መልሶ ኣሳፍሯል፡ ፡ ለ ዴሞክራሲ ትግል ተሳታፊነት ማስረጃ ፍለጋ ፎቶግራፎችና ፊልሞች በሳይበር እየለቀቁ የወያኔ ሰላዮች ይከታተሉኛል ማለቱ ለሰሚዎቹ ህግ ኣስከባሪዎች ኣስቂኝ ነበር፡ ፡

ብዙዎች ኢትዮጵያውያን በኖርወይ በ "ሳይለንት ማጆሪቲ" የሚመደቡ እንደሆነ  ዛሬ ኢትዮጵያውያን ስም የሚነግደው ተቃዉሞ ኣስተባብሪው  ሳይቀር ኣምኖበታል፡ ፡
ታድያ! በኖርወይ ኢትዮጵያውያንን የሚወክል ቡድን ኣለን?

Sunday, March 9, 2014

የኢትዮጵያን ለኢትዮጵያ ወይም የወያኔን ለወያኔ

ሚሊዮን ሊማ ከኖርዌይ

በአንድ ወቅትአንድ ዘጋቢ የኢትዮጵያን ባንዲራ  በሚመለከት ተዘዋውሮ ካናገራቸው የመዲናይቱ ነዋሪዎች አንዱ፥ “እኛ አገራችንን የምንወደው ወያኔዎች ስለነገሩን አይደለም።  እሱማ ባንዲራችንን ባጥላሉበት ዘመንም አገራችንን እንወድ ነበር፤ አሁንም እንወዳለን፤ ወደፊትም እንወዳለን። ይህ በደማችን ውስጥ ያለና መቼም ቢሆን ከልባችን ሊወገድ የማይችል ነገር ነው፤” ብለው እንደነበር አስታውሳለው ።
ወያኔ ወደ ሥልጣን የመጣው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያጋየ ነበር። በመጣም በነጋታው ሕገ-መንግሥቴ የሚለውን መጨቆኛ መሣሪያ ለማጽደቁ ኑ ብሎ በጠራቸው የሱ ብጤ ዘረኞች ስብሰባ ላይ ሰንደቅ ዓላማችን፣ ሲዋረድ፣ ሲብጠረጠር እንደነበር ለታሪክ ዩ-ትዩብ በተባለው የዘመኑ የድምጽና የተንቀሳቃሽ ስዕል ማሳያ የድረ ገጽ ማሳያ ላይ ለሕብረተሰቡ ለዕይታ በቅቶ ይገኛል።
ሰንደቅ ዓላማችን እንዳገራችን እራሷ ባለታሪክ ናት። ሰንደቅ ዓላማችን፣ እነሱ እንዳሏት “ጨርቅ” ብቻ ሳትሆን ስንት ደም የፈሰሰባት ወድቃ የተነሳች ልዩ የታሪካችን መዘክርና የማንነታችን ማብሰሪያ ሰንደቅ ናት።
ይችን ያክል ሰለባንዲራችን ካልኩ እስቲ ማለት ወደፈለገኩት ነገር ልሂድ ፦ ለብዙ ግዜ መልስ ያላገኘውለት ጥያቄ ነው ይህ በዚህ ምስል ላይ
የሚታየው. Ebbelsgata1,.0183Oslo.Norway ያለ የወያኔ ትኬት ኦፊስ ነው ።
ባንዲራውንም ጨምሮ  ማለት ነው ። የትኬት ኦፊሱ የቆየ ሲሆን ይህ ደመቅ ብሎ የምትመለከቱት ባንዲራ ግን በቅርብ ግዜ የተቀመጠ ነው፥፣ እስከዛረ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አርማ ብቻ ነበር፥፥ የማን ነው? ማን ነው የሚያስተዳድረው? ባጋጣሚ በዚህ በኩል ባለፍኩ
ቁጥር ያው የሚታየኝ ነገር ቢኖር የእነዚህ ጨካኝ የሰው አውሬ ሆዳሞች ኢትዮጵያን እየመዘበረና እየገዛ ያለ ሌባ ቀማኛና ሰዶማዊ አገዛዝ  ወይንም ደግሞ ዘረኝነት ኧረ ስንቱ ነገር ተነገሮ የማያልቅ መጥፎ ትዝታዎች ብቻ
 ፦ እስቲ መለስ ብለን እናስብ የወያኔ መንግስት ባሳለፍነው23 ዓመት ውስጥ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ምን አይነት ጢባጢቤ
 እየተጫወተበት እንደሆነ መቼም በየቀኑ እያደረገ ባለው ወይም እያየንባለውነገር መቼም ሳንበሳጭ የቀረን ኢትዮጵያዊ ምድሩ 
ይቁጠረን ግን እስከመቼ  ድረስ እስከመቼስ ነው በማናምንበት እና በምንጠላው ነገር ላይ መወሰን የማንችለው
-ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ የግድ የዚህ የወያኔ ትኬት ኦፊስ ብቻ ነው ያለው ?
-ወያኔን መቃወም ካለብንስ በማንኛውምና በምንችለው መንገድ መሆኑን ረስተነዋል ማለት ነው ?
ወይስ የሃገር ኢኮኖሚ ምና ምን  ኧባካችሁ እንዳትሉኝ ወያኔዎች ጢባጢቤ የተጫወቱብን ይበቃናል ለነገሩ  እድገት እኮ 11% lol በመቶ ????በትንሹ ማድረግ ያልቻልነውን እንዴት በትልቁ ማድረግ እንችላለን?
እስከ መቼ ድረስ ነው እነዚህ ሰዎችስ በእንደዚህ ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ እና ባንዲራዋ ላይ በእንዲህ አይነት መልኩ የሚቀልዱት   እስቲ ተመልከቱት ከዚህ በታች ያለውን ፎቶ የማን ነው የቄሳርን ለቄሳር የሕግዚኃብሔርን ለሕግዚኃብሔር አይደል
እንግዲያውንስ የኢትዮጵያን ለኢትዮጵያ ወይም የወያኔን ለወያኔ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ መለያ እስከመሆን የደረሰ ሁላችንም የምንመካበት ተቋም ይሁን እንጂ  ወደ ሃገር ቤት ለመሄድ ትኬት ለመግዛት እዚህ ቢሮ የምንመጣ በኖርዌይ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን እራሳችንን መተየቅ ይገባናል፥፥ በሃገራችን ውስጥ ላለፉት 23 አመታት ግለሰቦች እንጂ ሃገር ወይንም ህዝብ ሲያድግ አልታየም፥፥

ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ እንንቃ!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!




Wednesday, March 5, 2014

The Ethiopian asylum seekers association in Norway met with the Norwegian activist                                      

in a meeting at the anti-racist centre in Oslo on 20-02-2014 at 17o'clock to discuss about the current situations faced by the asylum seekers.
Many topics and questions we're raised concerning the detention and the deportations of Ethiopian asylum seekers.
It is quite obvious that, the world know about the Ethiopian TPLF dictatorship regime, and ethnically brutality.
The TPLF still have an incredible spies anywhere Ethiopians are, to spy on them and send reports, that makes Ethiopians life more risk any where. Like Mubarak an Ethiopian asylum seeker whose life is more at risk now in detention.
During the discussion, the Norwegian activist suggested meeting with the other countries asylum seekers committees, like Iraqis,Iranians, Afghans and others to arrange public seminar in an open place, and to invite famous peoples like politicians, religious leaders, journalist etc, to attends the seminar. We the Ethiopian asylum seekers committee needs public supports and assistance financial,fiscal, transports, journalists, etc, etc,,.
The Ethiopian asylum seekers association would like to thank the Norwegian activist for supporting theEthiopian asylum seekers movement.
"On Tuesday March 04,2014 The Ethiopian Asylum seekers association in Norway committe ,different Norwegian activists , journalists and the artists from Denmark 
(Tone Olaf Nielsen ) was discussing concerning the actual current status of asylum seekers in Norway and how the Norwegian government handles the asyleum Seekers ?. Refering to the dictator regime in Ethiopia and the asylum seekers in Norway there was a lot of questions raised by the comittee and from the Norwegian artists and journalists !!they will have different stages to show up how much the Ethiopian government is dictator ( Solveing and Marius for March 6 2014). FRONTLINE CLUB

Monday, March 3, 2014

በኖርዌይ የሚኖሩትን ኢትዮጵያን ስደተኞችን የአኖኖር ሁኔታ በሚመለከት ህዝባዊ ውይይት እና የኢሳት ምሽት ፕሮግራም በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ተካሄደ 

March 1/2014

በኖርዌይ ከተማ ኦስሎ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች በኖርዌይ የሚኖሩትን ኢትዮጵያን  ስደተኞችን የአኖኖር ሁኔታ በሚመለከት   ሐሙስ የካቲት20,2006 ዓ ም  በአንድ ላይ በመሰብሰብ ውይይት እና ምክክር አድርገዋል :: ስብሰባው በኖርዌይ የስደተተኛ ማህበር የተዘጋጀ ሲሆን በስብሰባው  ላይ ከተለያዩ ከተሞች የመጡ እና በኦስሎ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የተሳተፉ ሲሆን የኢሳት ጋዜጠኛ የሆኑት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ ጋር በመሆን በኖርዌይ ያሉ የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የአኗኗር ሁኔታ እንዲሁም ለስደት ያበቋቸውን ምክንያቶች በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፥፥

   በስብሰባውም ኢትዮጵያኖች በሀገራቸው እንዳይኖሩ የወያኔ መንግስት በሚያደርስባቸው ጫና እና በደል ሀገራቸውን ጥለው ቢሰደዱም ነገር ግን ኖርዌይ ከገቡ በኋላም የኖርዌይ መንግስት የኢትዮጵያኖችን የፓለቲካ ጥገኝነት በሚገባ እንደማያየው እና እንደማይቀበለው በየጊዜው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተለያየ ጫና እንደሚያደርስባቸው በሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን  በስብሰባው ላይ ከነበሩት ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች እና የየእራሳቸውን የህይወት ተሞክሮ እና ኖርዌይ ከገቡ ጀምሮ በሕይወታቸው ያለፈውን እና እየኖሩ ያለው ኑሮ ምን እንደሚመስል እንዲሁም ለስደት ያበቋቸውን ምክንያቶች በተመለከተ ውይይት አድርገዋል  ::

 አንዳንድ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ከሀገር እየወጡ  ኖርዌይ ገብተው የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ ወረቀት ካገኙ በኋላ ወይም ፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂ መስለው ትንሽ ጊዜ በመቆየት ካዛም በገዛ ፍቃዳቸው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ እና  በኢትዮጵያ መንግስትም ምንም አይነት በደል እንዳልደረሰባቸው የኖርዌይ መንግስት እንደሚያውቅ ከዚህም የተነሳ ሌሎች ኢትዮጵያን ስደተኞ ላይ ወደ የፓለቲካ ጥገኝነት እንደማይቀበል ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱም የኖርዌይ መንግስት የተለያየ ጫና እንደሚያደርስባቸው በስብሰባው ከነበሩ ተሳታፊዎች የተገለጸ ሲሆን ነገር ግን  እንደነዚህ አይነት ሰዎች በመጀመሪያ ወደ ኖርዌይ የሚመጡበት ምክንያት እንዳላቸው እና ምክንያታቸውም  በኖርዌይ የሚኖሩትን እውነተኛ የወያኔ ተቃዋሚዎ ችን ለመሰለል እና ለማደን ሲሆን  እንደነዚህ አይነት ሰዎችን እንዳሉ እና እንደሚያውቆቸው ነገር ግን ኢትዮጵያውን እነዚህ የወያኔ ሰላዮች መፍራት እንደሌለባቸው ይህንንም ለኖርዌይ የስደተኞችን ጉዳይ ለሚመለከተው መስሪያ ቤት utlendingsnemnda (UNE) በተለያየ ጊዜ መሳወቃቸውን በስብሰባው ላይ ተገልጾል ::

በስብሰባው ላይ በመገኛት በኖርዌይ ያሉ የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የአኗኗር ሁኔታ ምን እንደሚመስል ጥያቄ ሲጠይቁት የነበሩት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ ኖርዌይ በሚኖሩት ኢትዮጵያኖች በሚያደርጉት ትግል ወይም እንቅስቃሴ በጣም እንደሚደሰቱ እና እንደሚደነቁ በመናገር ማንኛውንም ማድረግ ያለባቸውን እና ማድረግ የሚችሉትን  ነገሮች በማድረግ ከጎናቸው በመቆም አብራቸው እንደሚሰሩ ቃል ገብተውላቸዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት ቅዳሜ የካቲት 22, 2006 ዓም በዛው በኖርዌይ ኦስሎ ኢሳት የእኔ ነው (ESAT IS MINE) በሚል መሪ ቃል የኢሳት ምሽት ፕሮግራም የተደረገ ሲሆን  የኢሳት ጋዜጠኛ የሆኑት ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ እና ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ የዝግጅቱ ተጋባዥ እንግዶች በመሆን በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል ::


 በፕሮግራሙ የተለያየ ዝግጅቶች የተደረጉ ሲሆን በተለያዩ ሰዎች የኢትዮጵያን  የፖለቲካ ሁኔታ የሚዳስስ ጹሁፍ የቀረበ ሲሆን  ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለምንም ፖለቲካዊ ወገንተኝነት መረጃን በማቅረብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አይን እና ጆሮ የሆነውን  ኢሳትን መርዳት እንደሚገባ በኖርዌይ የሚኖሩ የኢትዩጵያን ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ፋሲል እና  የኢሳት ኖርዌይ ዋና ተወካይ ጋዜጠኛ አበበ ደመቀ  እንዲሁም በኖርዌይ የኢሳት ም/ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሙባረክ ንግግር አድርገዋል::በተጨማሪም አቶ እንግዳ ታደሰ የኢሳት በኖርዊይ አመሰራረት እና ስለ ኢሳት ባለቤትነት በህዝብ ዘንድ የሚወራው የተሳሰት ወሬ ትክክል እንዳልሆነ ኢሳት የማንም የፖለቲካ ድርጅት ንብረት እንዳልሆነ እና ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረት እንደሆነ ሕዝቡም ኢሳት የእኔ ነው በሚል ስሜት ኢሳትን እንዲረዳ እና እንዲደግፍ የኢሳትም አባል እንዲሆን ጥሪ በማቅረብ ንግግር አድርገዋል::

በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ አስደሳች ግጥሞች እና መነባንቦች በተለያዩ ሰዎች የቀረበ ሲሆን በጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ ኑ ሀገራችንን እንስራ በሚል ርዕስ ኢትዮጵያኖችን ለስደት የዳረገው ወያኔ በሰዎች ላይ የሚያደርሰው ግፍ እና በደል እንደሆነ እና  ስደት በሰው ሀገር  ምንም ቢመችም ደስታን እንደማይሰጥ የስደትን  ህይወት በሚመለከት አስደሳች እና ልብን የሚነካ ግጥም የቀረበ ሲሆን በጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላም ሁሉም ሰው የሀገሩ ሁኔታ ግድ እንዲለው እና ስለ ሀገር መቆርቆር ፣ሀገርን በሚመለከት ጉዳይ ላይ መሳተፍ  ፖለቲከኛ መሆን እንዳይደለ ሀገራችን ከወያኔ ስርዓት ነጻ እስከምትሆን ሁሉም ሰው በጽናት መታገል እንደሚገባው አጽንኦት ሰጥታ ንግግር ያደረገች ሲሆን በስብሰባው ላይ ዋናው አላማ የነበረው ማንኛውም ሰው ኢሳት የእኔ ነው በሚል ቃል በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የኢሳት የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው ኢሳትን እንዲረዱ ከመሆኑ አኳያ በፕሮግራሙ ላይ ሲተላለፉ የነበሩት ግጥምም ሆነ ንግግር በዋናነት ኢሳት በመርዳት ላይ ያተኮረ ነበር :: በእለቱ የፕሮግራሙ አላማ የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ የጨረታ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በእለቱ ለኢሳት ማጠናከሪያ የሚሆን የተለያዩ ምግቦች ፣መጠጦች፣ ቀለበቶች፣እና ቲሸርቶች ለሽያጭ ቀርበዋል :: በተለያየ ጊዜ ለኢሳት እና ለፖለቲካ ድርጅቶች በሚደረጉ የገንዘብ ገቢ ማሰባሠቢያ ፕሮግራም ላይ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ከየትኛውም ሀገር በበለጠ ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ይታወቃል::