This Blog is my diary that i express my political, economic, and social views about my beloved country Ethiopia.
Tuesday, November 26, 2013
Tuesday, November 12, 2013
ዜጎቹ በአረብ አገር እንደውሻ ሲታደኑ ወያኔ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብሏል ፡፡
ከሳምንት በፊት እዚህ ኖርዌይ አንድ የደቡብ ሱዳን ተወላጅ ነው የሚባል ሰው ፣ የስደተኝነት ጥያቄው አሉታዊ መልስ እንዳሰጠው አውቆ ከከራረመ በኋላ ፣ እንደ ነገ ከመጣበት አግር ወደ እስፔን ሊመለስ በፖሊሶች ዝግጅቱ አልቆ ሳለ መረጃውን ከየት እንዳወቀ ባልታወቀ ምክንያት ፣ ክተጠለለበት ካምፕ ወጥቶ አውቶብስ ይዞ እንደወጣ ፣ ሰይጣን ጆሮው ላይ ምን ሹክ እንዳለው ሳይታወቅ ፣ ከካምፑ ይዞት በወጣው ቢለዋ ፣ አውቶቡሱን አግዶ በአውቶቡስ ውስጥ ያሉትን ሶስት ሰዎች ይገድላል ፡፡
በዚህ አሰቃቂ ድርጊት ሰለባ የሆኑት ፣ የአውቶቡሱን ሾፌር ጨምሮ ፣ አንዲት የ19 አመት ሴት ልጅና አንድ ስዊድናዊ ዜግነት የነበራቸው ሰዎች ነበሩ ፡፡ሁለት ኖርዌጅያኖችና አንድ የጎረቤት አገር ስዊዳናዊ ሰው ፡፡ ይህ ግድያ አንድ መዘዝ ጎትቶ እዚህ ኖርዌይ ያለነውን ኢትዮጵያውያኖችም ሰሞኑን አንገታችንን እንድናጎነብስ እያደረገን ነው ፡፡ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2003 ዓ.ም አንድ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሰው እንዲሁ ፣ በአንድ ካምፕ ውስጥ አብሮት የነበረውን አንድ የኮንጎ ዜጋ ገድሎ ሲያመልጥ ፣ እርሱም እንዲሁ የተሳፈረበትን አውቶቡስ ሾፌር ገድሎ ተይዟላ ፡፡
ከአስር አመት በፊት የተፈጸመው ይህ ክስተት ሰሞኑን ፣ የኖርዌይ ጋዜጦችን አጣቧል ፡፡ ኢትዮጵያዊው ! ኢትዮጵያዊው እየተባለ ፡፡ህዝቡ የሰሞኑ ግድያ አንገፍግፎት ሳለ ! መገናኛ ብዙሃን ደግሞ ከአስር አመት በፊት በኢትዮጵያዊው ገዳይ የተፈጸመውንም በአዲስ መልክ በማራገባቸው ፣ ህዝቡ ለምን አስር አመት ሙሉ እዚህ አገር ተቀመጠ ? ለምን ወደ አገሩ አልተጠረዘም በማለት መንግሥታቸው ላይ በማጉረምረማቸው ፣ ከሶስት ሳምንት በፊት ስልጣን የያዘው አክራሪ የቀኞች አዲስ መንግስት ፣ ጥፋቱ የቀድሞዎቹ የግራ መንግስቶች ችግር ነው ፣ እስከዛሬ ቁጭ አድርገው ሲቀልቡት በማለት ፣ ጦሱን ከስልጣን ለወረደው መንግስት አቀብለውታል ፡፡
ኢትዮጵያዊው ገዳይ ከፍተኛ የአይምሮ መቃወስ ችግር ያለበት ሰው ስለሆነ ፣ ወደ አገሩ ከህመሙ ሳይድን መስደድ አንችልም ፡፡ በዚህ ህመሙ አገሩ ብንሰደው የአገሩን ህዝብ ሊጨርስ ስለሚችል የግድ መዳን አለበት ፣ ወደ አገሩ ከመላኩ በፊት እያሉ የጤና ኃላፊዎቹ ፈርጥመው እየተናገሩ ነው ፡፡ እስቲ እንግዲህ አስቡት ፡፡ የአገራቸውን ዜጎች የገደለባቸው የኖርዌይ መንግስት ሹሞች ፣ ከዚያም አልፈው ኢትዮጵያ ውስጥ ሄዶ ህዝብ ስለሚገድል፣ አክመን አድነን ነው የምንሸኘው ብለው ሲከራከሩ ፣ የአገራችን መንግሥት ደግሞ ፣ ዜጎቹ በአረብ አገር እንደውሻ ሲታደኑ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብሏል ፡፡
ምን አይነት ጊዜ ላይ እንደደረስን አይገባኝም ፡፡ በአጼ ኃይለስላሴ ዘመን እንደዛሬው አረብ አገር ቤንዚን ወጥቶ እንዲህ ሳይቀማጠሉ በፊት ለሃማልነት/ ወይም ኩሊነት እንዲሁም ለግንበኝነት ስራ ተቀጥረው ኢትዮጵያ ውስጥ አረቦችን ያሠረና ያበላ ህዝብ ነው ዛሬ በተራው ተዋርዶ በአረብ አገር የሚገደለው ፡፡ ይህ ታሪክ ለአዲሱ ትውልድ በደንብ መነገር አለበት፡፡ ዛሬ የመንን የሚያስተዳድሩት ሚንስትሮች አብዛኞቹ ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው አረቦችና ፣ መወለዶች ናቸው በልጅነታችን አረብ ሱቅ ሄዳችሁ ቡና ግዙ ስንባል በከረሜላ ምርቃት የሚያፈዙን ኢትዮጵያ በግንበኘነት ቀጥራ ያመጣቻቸው አረቦች ነበሩ ሱቅ ከፍተው አገራችን የከበሩት ፡፡ እስቲ እዚህ ላይ የምታውቁትን ታሪክ አክሉበት ፡፡ አዲሱ ትውልድ የግድ ታሪኩን ማወቅ አለበት ፡፡
Engida Tadesse

Monday, November 11, 2013
አይ ኢትዮጵያነት!
ድህነት ከየቤታቸው ገፍትሮ ወደማያውቁት አገር ያሻገራቸው የአገር ልጆች በየመንገዱ እየተደበደቡ አይሆኑ ሲሆኑ፤ደማቸው እንደቀልድ እየተረጨ መድርሻ አጥተው ሲራወጡ፣ በአገራቸው የመማር፣የመሥራት እና በአግባቡ የመኖር መብታቸውን የሚያከብርላቸው መሪ ባለማግኘታቸው የገዛ አገራቸውን በቅንጦት ለሚኖሩት ገዢዎቻቸው ጥለው የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ሕይወት ለማቆየት ስደትን የመረጡ ኢትዮጵያውያንን ስቃይ እንደማየት እና መስማት የሚከብድ ነገር ይኖር ይኾን? በስቃያቸው ወቅት ከመቆርቆር ይልቅ ስለ አካሄዳቸው ሕጋዊነት እና ሕገወጥነት የሚደሰኩረው ገዢ የዜጎቹን ማንኛውም መብት አክብሮ የማኖር ግዴታውን ቢዘነጋው እንኳን ውርደቱ አያሳፍረው ይኾን? አይ ኢትዮጵያነት!

Thursday, November 7, 2013
የኤሌክትሪክ ችግር በኢትዮጵያ
በኤሌክትሪክ መጥፋት ምክንያት የአገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ሥራ በተደጋጋሚ እንደሚስተጓጓልና በዕለት ተዕለት ኑሮም በኤሌክትሪክ ማብሰያዎች መጠቀም አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን ዶቼቬለ የጠየቃቸው አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል ።
በመላው ኢትዮጵያ ተደጋግሞ የሚደርሰው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በዕለት ተዕለት ኑሮና የሥራ ሂደት ላይ እክል እንደሚያስከትል ህብረተሰቡ አማረረ። አስቀድሞ ሳይነገር በሚደርስ የኤሌክትሪክ መጥፋት ምክንያት የአገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ሥራ በተደጋጋሚ እንደሚስተጓጓልና በዕለት ተዕለት ኑሮም በኤሌክትሪክ ማብሰያዎች መጠቀም አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን ዶቼቬለ የጠየቃቸው አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በበኩሉ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ የደረሰው በተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ችግሮች እንደነበርና አሁን ግን ችግሩ እየተቃለለ መሆኑን አስታውቋል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ አለው።
የስዑዲ ምህረትና የሁለት ኢትዮጵያውያን መገደል
የሳውዲ መንግሥት ለ ሁለተኛ ጊዜ የሰጠው የምህረት አዋጅ ቀነ ገደብ ካበቃበት ካለፈው እሁድ አንስቶ በተካሄደ የፖሊስ ክትትል ሁለት ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን ሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስታወቁ ። እነዚሁ ነዋሪዎች እንዳሉት ባለፉት ሶስት ቀናት ከሞቱት ሌላ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታፍሰዋል ።
በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከሞላ ጎደል ሥራቸውን አቁመዋል። የጅዳው ወኪላችን ነበዩ ሲራክ እንደዘገበው የምህረቱ የመጨረሻ ቀን ካለፈ በኋላ መንግስት በወሰደው እርምጃ ከ 5 ሺህ በላይ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ተይዘዋል። መንግሥት ሕገወጥ የሚላቸው እነዚህ የውጭ ዜጎች የሁለት ዓመት እሥራትና 100 ሺህ የሳውዲ ሪያል ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ከምህረት አዋጁ ማለቅ በኋላ በጂዳ የኢትዮጵያውያን ዓለም ዓቀፍ ትምህርት ቤት ሥራ መስተጓጎሉንም ነብዩ ሲራክ ከጅዳ ዘግቧል ።
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ፣ የቦምብ ፍንዳታ እና ማስጠንቀቂያው
ኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ጥቃቶች ሊደርሱ ይችላሉ በሚል የጸጥታ ኃይሎች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ በታዘዙበት በኣሁኑ ወቅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኣንድ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በፈነዳ ቦምብ አራት ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ።
ከሶስት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ላዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አዲስ ኣበባ ላይ ከናይጄሪያው ቡድን ጋር በሚጫወትበት ዕለት ጥቃት ለማድረስ ሲዘጋጁ ነበር የተባሉ ሁለት የሶማሊያ ኣጥፍቶ ጠፊዎች በራሳቸው ቦምብ መሞታቸው ይታወሳል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግ መንግስት እያሳሰበ ሲሆን የጥንቃቄ ማስጠንቀቂያውን ተከትሎም በተለያዩ አካባቢዎች የጸጥታ ቁጥጥሩ መጠናከሩም ተሰምቷል።
የዛሬ ሶስት ሳምንታት ገደማ መሆኑ ነው የኢትዮጵያ የእግር ኩዋስ ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አዲስ ኣበባ ላይ ከናይጄሪያው ብ/ቡድን ጋር በሚጫወትበት ዕለት ጥቃት ለማድረስ ሲሞክሩ ነበር የተባሉ ሁለት የሶማሊያ ኣጥፍቶ ጠፊዎች የራሳቸው ቦምብ ፈንድቶባቸው ከቤታቸው ሳይወጡ መሞታቸውን የኢትዮጵያ ፖሊስ ኣስታውቆ ነበር። ይኽንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ የደህንነትና ጸጥታ ባለስልጣናት ኣልሸባብ በአዲስ ኣበባ እና በተለያዩ የኣገሪቱ አካባቢዎች ጥቃት ለማድረስ እየተዘጋጀ መሆኑን በመግለጽ የፖሊስ እና ጸጥታ ኃይሎች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ማዘዛቸውን ገልጿል።
ባለፈው ማክሰኞ ደግሞ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰኞ ገበያ በተባለ ስፍራ በህዝብ ማማላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ የፈነዳ ቦምብ አራት ሰዎችን መግደሉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግስት ከኣልሸባብ በተጨማሪም በኤርትራ መንግስት ይደገፋሉ የሚላቸውን ሌሎች በኣገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎችን ከሽብር ጥቃት ጋር ኣያይዞ ሲወነጅል መቆየቱም ኣይዘነጋም።
የፊታችን ህዳር 29 ቀን በጅጅጋ ከተማ ይከበራል ተብሎ ከሚጠበቀው ዓመታዊ የብ/ብ/ ቀን ጋር በተያያዘ ዓማጺው የኦጋዴን ነጻ ኣውጪ ግንባር ጥቃት ሊያደርስ ይችላል በሚል በጅጅጋ ከተማ እና በአካባቢው የጸጥታ ቁጥጥሩ እጅግ መጠናከሩ ሲታወቅ በጅጅጋ ጎዳናዎች ላይ በየ 50 ሜትሩ ሰዎች በፍተሻ እንደሚዋከቡና ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ ደግሞ በጅጅጋ ከተማ የቤት ለቤት ፍተሻም እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል።
በተቀሩት የኣገሪቱ ኣካባቢዎችም ህዝቡ የጸጉረ ልውጥ ሰዎች እንቅስቃሴን እየተከታተለ ለመንግስት እንዲጠቁም እና በተለይ የሆቴሎች አልጋ ኣከራዮችና በየመንደሩ ያሉ ቤት ኣከራዮችም ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ የተለየ ነገር ሲያጋጥም ወዲያውኑ ለመንግስት እንዲያሳውቁ መንግስት ኣሳስቧል።
ስለዚሁ ጉዳይ እንዲያብራሩልን የኢትዮጵያው የኮሞኒኬሺን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲዔታ አቶ ሽመልስ ከማል ዘንድ ስልክ ደውለን ነበር። ፈቃደኛ ግን ኣልነበሩም። የኮሚኒኬሺን ጉዳዮች ሞኒስትሩ አቶ ሪድዋን ሁሴን ግን ለመንግስታዊው የኢትዮጵያ ቴሌቪዢን እንደገለጹት መንግስታቸው የሽብር ጥቃት መታቀዱን መረጃ ማግኘቱን ኣውስተው ህዝቡ ጥንቃቄ በማድረግ እና ለመንግስት ጥቆማ በማቅረብ እንዲተባበራቸው ጥሪ ኣድርጘል።ሆኖም ግን ከጥንቃቄ ያለፈ ህብረተሰቡ ተሸብሮ የዕለት ተለት እንቅስቃሴውን እንዲያቆም የሚያስገድድ ነገር ኣለመኖሩንም አቶ ርድዋን ኣስረድቷል።
በኣልሸባብ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ፍጥጫ መኖሩ ኣይካድም የሚሉት የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ጀዋር መሃመድ የኣሁኑ የኢትዮጵያ መንግስት ማስጠንቀቂያና መግለጫ አዲስ ነገር የለውም ይላሉ። እንደ አቶ ጀዋር ይህ የኢትዮጵያ መንግስት ተቀናቃኞቹን ለማሰር እና የፖለቲካ ትርፍ ለመሸመት የሚጠቀምበት የተለመደ የፕሮፓጋንዳ ስልት ነው።
በዩኤስ አሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የፒኤችዲ ጥናት በማድረግ ላይ የሚገኙት አቲ ጀዋር መሐመድ ከወዲሁ ማስተካከያ ካልተበጀለት የዚህ ኣይነቱ ኣካሄድ አደጋም ኣለው ባይ ናቸው። ምክኒያቱም አቶ ጀዋር እንደሚሉት ተጨባጭ ነገር ሳይኖር ጥቃት ሊፈጸም ነው እየተባለ ህዝቡ የተለመደ የመንግስት ፕሮፓጋንዳ ነው እያለ በተዘናጋበት ኣጋጣሚ እውነተኛው የሽብር ጥቃት በተቃጣ ጊዜ መንግስት ከጎኑ የሚቆምለት ህዝብ ያጣል። አደጋውም የከፋ ይሆናል።
ባሳለፍነው ወር የአልሸባብ ታጣቂዎች በኬኒያ ናይሮቢ በሚገኘው የዌስት ጌት የበያ ማዕከል ላይ በጣሉት ጥቃት 67 ንጹኃን ዜጎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን እ ኣ ዘ ኣ በ 2010 በጎረቤት ኡጋንዳ የዓለም ዋንጫ ጫወታን ለመከታተል በታደሙ ዜጎች ላይ በደረሰ የቢምብ ፍንዳታም እንዲሁ 74 ያህል ሰዎች መሞታቸው ኣይዘነጋም።

The award-winning Ethiopian journalist Eskinder Nega will turn 45 this month in Kaliti prison outside Addis Ababa whilst serving an 18-year sentence as a convicted terrorist. The government in Addis would have the world believe he is a reckless, even racist, agitator bent on violent revolution. Yet, a review of the evidence against him and his writings reveals a thoughtful and principled man whose only crime has been to urge, peacefully and publicly, Ethiopia's rulers to deliver on their long broken promise of peaceful, democratic reform.
"Democracy is so important to Ethiopia, because we need it to moderate the differences between civilization and civilization," Eskinder said in a 2010 interview. "I hope the EPRDF (the ruling party) will be pragmatic enough to realise reform would be the better option, even for itself," he added. "I believe in forgiving… that we shouldn't have any grudge against the EPRDF, despite what it has done. I believe that the best thing for the country is reconciliation. I believe in the South African experience, that model."
In February 2011, inspired by the Egyptian military's tolerance of pro-democracy protesters in Tahrir Square, Eskinder wrote an article urging Ethiopian soldiers to heed their example, should demonstrations break out in Addis Ababa. The column appeared on a US-based Ethiopian news website blocked inside his country. In response, the state security detained Eskinder, accusing him of inciting the public against the government. A senior police official threatened to kill him if he did not stop writing about the Arab Spring.
A few months later, after the government invoked a vague terrorist plot to imprison prominent journalists, lawyers, teachers, academics and other dissidents, Eskinder spoke out again: "None of the recent detainees under the terrorism charges remotely resemble the profile (of a terrorist). Debebe is probably the ultimate antithesis of the fanatic, his pragmatism, his easy nature, defines him," he wrote, referring to prominent actor Debebe Eshetu. "Neither do journalists Woubshet (Taye) and Reeyot (Alemu) and opposition politician Zerihun Gebre-Egzabher fit the profile. The same goes for the calm university professor, Bekele Gerba."
Just five days after writing those words, Eskinder was arrested again, and charged under the same terrorism charges. As evidence, the prosecution submitted a video of a town hall meeting of an opposition party where Eskinder expressed his opinion that if repression continued, the people's patience would run out and there could be Arab Spring protests in Ethiopia. The prosecution claimed that by making such statements he was using his constitutional right to freedom of expression as a cover to overthrow that very constitution.
Eskinder's treatment is emblematic of the conditions facing all Ethiopians and the systematic harassment and incarceration of independent voices. Journalism has its occupational hazards the world over, but in Ethiopia it is impossible to practice the profession honestly and with integrity. The country's anti-terrorism law is sweeping and harsh. It mandates a 20-year sentence for "whoever writes, edits, prints, publishes, publicises, disseminates" statements that the government deems support terrorism. Suspects can be held under these laws for up to four months without charge, let alone a trial – perversely reminiscent of the 90-day (and later 180-day) detention laws of South Africa under apartheid.
In fact, the anti-terrorism law of today's Ethiopia looks very much like the statutes the apartheid government enacted to suppress opposition and maintain a system declared a crime against humanity by the international community. Some of us remember vividly the Suppression of Communism Act of 1950 – later replaced by the Internal Security Amendment Act of 1976, under which even anti-communist writing was banned if it opposed apartheid, and writers were charged and convicted. Ethiopia's anti-terrorist statute is a close cousin of South Africa's Terrorism Act of 1967, which was just as all-encompassing; even the mildest opponents of apartheid became "terrorists" under this Act. Just as in South Africa, Ethiopia's anti-terrorism law has become an instrument of terror itself.
Many people and organisations around the world have spoken on behalf and in defence of Eskinder, but whenever these gross violations of human rights happen in Africa there is either muted protest or utter silence on the part of African writers, intellectuals, artists and media. Why should these violations be Bob Geldof's business and not ours? Surely we also care about human rights because we are directly affected, even more so than those based in the west.
For two decades, Eskinder has been an indomitable free thinker who has refused to give in to anger, resignation or exile despite persistent government intimidation. When his wife, Serkalem Fasil, accepted the PEN Freedom to Write award on his behalf she said that prison had become her husband's "home away from home". Serkalem, herself a fellow journalist and newspaper editor, was imprisoned for exercising her freedom of expression, and their son was born in prison.
Eskinder's continued arrest and the harassment of his family is a travesty that all freedom-loving Africans should protest against relentlessly. It is in this light that the African Commission on Human and Peoples' Rightsshould consider the complaint filed recently by Freedom Now and the Media Legal Defense Initiative on Eskinder's behalf.
What is happening in Ethiopia is a disgrace. An African like me, who is enjoying freedom in South Africa, should have long ago protested this case in the loudest of voices. My silence was complicity. It is important to curb the impunity with which some African governments act against the rights of their citizens. If Ethiopia can get away with it, so will your country next time, and you'll be the victim. It is first and foremost out of human decency that our voices should be heard. But it is also out of self-interest as prospective victims of repression. As the saying goes, if we are silent today, when they come for us there will be no one left to speak
የኢትዮጵያዉያን ስቃይና መከራ በሳዉዲ አረቢያ
የኢትዮጵያዉያን ስቃይና መከራ በሳዉዲ አረቢያ
November 6, 2013
(በሳዲቅ አህመድ)
የመጣኸዉ ባዶህን ነው! ባዶ ሆነህም ትመለሳለህ!…ኢንተ-ጃኢ-ፋዲ ወተርጃእ-ፋዲ…የሳዉዲዎች አመለካከት!
የፈለጋቹበት ዉሰዱን ግን አትደብድቡን…ይላል ኢትዮጵያዊዉ…ለካስ አትደብድቡን ማለቱ የሚያስደበድብ ነበር…
አይደለም የሰዉ ልጅ እንስሳ እንኳ እንደዚህ አይደረግም። የምታዩአቸዉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በሳዉዲ ዜጎች ተይዘዉ ወደ ጀዋዛት (የስደተኛ መምሪያ) ሲወሰዱ ነዉ። እነዚህን ደሃና ከርታታ ኢትዮጵያዉያን በቁጥጥር ስር ያዋለዉ ያገሪቱ ፖሊስ ሳይሆን ያገሪቱ ዜጎች ናቸዉ።”እክስር የዱ!…እጁን ስበረዉ!…” ይላል አንዱ። ከታች ሆኖ የጣር ድምጽን የሚያሰማዉ ኢትዮጵያዊ “ሐላሊ…ሐላሊ… ላቤን ያፈሰኩበት የልፋቴ ዋጋስ? በማለት ሲጠይቅ ዱላዉ ይጠነክርበታል።
ሰዉ የመሆን ማእረግን የተነፈገዉ ሌላኛዉ ኢትዮጵያዊ ደግሞ ዱላዉን እርግጫዉን እየዋጠ ስቃዩን ለመቀነስ “ኻላስ-አነ-ገልጣን…በቃ! በቃ! እኔ-ነኝ-ጥፋተኛ” ይላል። ከሳዉዲ ዜጎች አንደኛዉ ኢትዮጵያዉያኑ በመያዛቸዉ ባይከፋም ዱላዉን እንዲህ እያለ ይቃወማል “ተራ ኤይብ-መጅሙዓ-ተድርቡነ?… ይህ ነዉር ነዉ በህብረት ትደባደባላችሁ?” ግን ማን ሊሰማዉ። የኢትዮጵያዉያኑን የሰራ-አካል ማሰቃየት ብቻ ሳይሆን የሚያራግፉባቸዉም የቃላት ናዳ ስነልቦናን ይሰብራል።
አገር ዉስጥ ካለዉ ስቃይ ለመዳንና የተሻለን ህይወት ለራስም ለቤተስብም ለማምጣት የሚሰደዱት ኢትዮጵያዉን የሚደርስባችዉ መከራና እንግልት ተቆጥሮ አያበቃም። የሳዉዲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ (ኢቃማ) የሌላቸዉ ወይም ከአሰሪያችዉ ጋር የማይሰሩ (ከፊል) በመጡበት የስራ ዓይነት (ሚህና) የማይሰሩት ከአገር እንዲወጡ ወይም የመኖሪያ ፈቃዳቸዉን እንዲያስተካክሉ የሰጠዉ ግዜ ስላበቃ ሰዎችን በዜግነት በሐማኖት ሳይለዩ ማፈሱን ተያዘዉታል። ባንጻሩ እነዚህ ሰደትኞችን ወደ ሳዉዲ በማስገባት ህገወጥ ተግባር የሚፈጽሙን የሳዉዲ ዜጎች መንግስቱ ወጥ የሆነ እርምጃ ሲወስድባቸዉ አይስተዋልም። ስለዚህ የሳዉዲ ዜጎችም ይሁኑ መንግስቱ ተጠያቂ ከመሆን አይድኑም።
ሰዎች ወደ ሳዉዲ እንዴት ይገባሉ የሚለዉን ስንቃኝ…
1) በሐሃጅና በኡምራ(ጸሎት)
ሰዎች ከተለያዩ አገራት ጸሎት እናደርጋለን በማለት ወደ ሳዉዲ ከደረሱ በሗላ እዚያዉ ይቀራሉ። እነዚህን ሰዎች ቀጥሮ በማሰራትም ይሁን ከቦታ ቦታ በድብቅ በማመላለስ ህገወጥ ተግባር ላይ የሚሰማሩት የሳዉዲ ዜጎች ናቸዉ። በነዚህ የሳዉዲ ዜጎች ላይ መንግስቱ በቂ የሆነ እርምጃ አይወስድም፤ የርምጃዉ ሰለባ የሚሆኑት ስደተኞቹ ብቻ በመሆናቸዉ መንግስቱ ተጠያቂ ነዉ።
2) የኮንትራት ስራ (ጠለብ)
በኮንትራት የሚመጡት ሰራተኞች ከዘመናዊ ባርነት ባልተናነሰ መልኩ ከፍተኛ ስቃይ ይደርስባቸዋል። ረጅም ሰዓታትን መስራት ብቻ ሳይሆን ከኮንትራቱ ዉል ዉጪ ለዘመድና ለጎረቤት በተጨማሪ እንዲሰሩ የሚገደዱ አሉ። የጠለብ (የኮንትራት) ሰራተኞች ድብደባ፣ግርፋት፣አስገድዶ መድፈር (rape)ወዘተ ይደርስባቸዋል፤ በዚህም ሳቢያ ከአሰሪያቸዉ በመጥፋት በግል ተቀጥረዉ መስራት ይጀምራሉ።የሳዉዲ መንግስት ዜጎቹ የሰራተኛን መብት እንዲያከብሩ በቂ ግንዛቤን ባለመፍጠሩና ይሕንን መስል ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፍጽሙትን ዜጎች ሕግ ፊት በተገቢዉ መልኩ ባለማቅረቡ ተባባሪ ያስመስለዋልና ተጠያቂ ነዉ።
2) በባህርና ድንበር አቋርጦ መግባት
የሳዉዲ ጎረቤት ከሆነችዉ የመን በኩል ብዙ ስደተኞች ወደ ሳዉዲ ይገባሉ። በተለይም ጀዛን የሚባለዉ የሳውዲ ግዛት ቀድም ሲል የየመን የነበረ ሲሆን ድንበሩን አንድ አይነት ጎሳዎች ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦችም ይጋሩታል፤ በሁለቱም አገራት ያሉ የህግ አስከባሪ አካለት የሚዛመዱበት አጋጣሚ ብዙ ነዉ። በተቀነባበረ የኮንትሮባንድ ስራ ፖሊሶችና ድንበር ጠባቂ ሐይላት ሰዎችን በህገወጥ መንገድ በማስገባት ይተባበራሉ። የሳዉዲ መንግስት በድንበሩ ላይ ባሉ የህግ አስከባሪ ሐይላት ላይ በቂ ቁጥጥር ባለማድረጉ ተጠያቂ ነዉ።
ስደተኞች ወደ ሳዉዲ ሲገቡ የአገሪቱን ግዛቶች አቋርጠዉ ከቦታ ቦታ እንዲዘዋወሩ የኮንትሮባንድን ስራ የሚሰሩት የሳዉዲ ዜጎች ናቸዉ። ለምሳሌ አንድ ስደተኛ ከየመን ድንበር-ጀዛን ወደ ሪያድ ወይም ወደ ጂዳ መግባት ቢፈልግ በጭነት መኪና ከእቃ ጋር ተደብቆ እንዲገባ ይደረጋል፤ካልያም ወንዱ እንደሴት ቀሚስ-ሻሽ-የፊት መሸፈኛ እንዲለብስ ይደረግና የሳዉዲ ዜጎች እንደ ሚስት ወይም ልጆች ጭኖ በኮንትሮባንድ ሰዎችን ከቦታ ቦታ ያመላልሳሉ። በዚህ የኮንትሮባንድ ተግባር ፖሊስ (ሹርጣ) ተባባሪ የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነዉ። ለዚህ ህገ ወጥ ተግባር ከሳዉዲ መንግስት ሌላ ማንም ተጠያቂ ሊሆን አይችልም።
ወደ ሳዉዲ ለምግባት ኢቃማ (የመኖሪያ ፈቃድ) በዉድ ገዝተዉ የሚገቡ ስደተኞች አንዳንዴ የውሸት አሰሪያቸዉ (ከፊል) ጠፍቶባቸዉ የመኖሪያ ፍቃድ ለማዉጣት የሚቸገሩበት አጋጣሚ አለ። አንዳንዴም የመኖሪያ ፍቃዱን ቢያገኙም ፈቃዳቸዉ ሲቃጠል ለማደስ (ተጅዲድ) አሰሪያቸዉ ጠፍቶ ወይም ፍቃደኛ ሳይሆን ይቀርና ሳይወዱ በግድ ህገወጥ ይሆናሉ። ለዚህ ህገወጥና የተዝረከረከ አሰራር ከሳዉዲ መንግስት ሌላ ማን ተጠያቂ ሊሆን ይችላል?
በሳዉዲ ከተሞች ዉስጥ በስፋት ያሉት ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮዎች (መክተበል ሙአቂብ) የመኖሪያ ፍቃድን በተመለከተ የተለያዩ የማጭበርበር ስራዎች (ተዝዊር) በመስራት ይታወቃሉ። እነዚህን ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ ከፍቶ ለመስራት የሳዉዲ ዜጋ መሆኑ ግዴታ ነዉ። በነዚህ ቢሮዎች የዉሸት የመኖሪያ ፍቃድን ከማዘጋጀት ጀምሮ፤ስደተኞች ያለ አሰሪያቸዉ (የዉሸት አሰሪም ቢሆን) ፍቃድ ከአገር ወጥተዉ እንዲመለሱ (ኹርጀል አዉዳ) እስክማድረግ ይሰራል። በነዚህ ቢሮዎች ዉስጥ ሌላዉ ቀርቶ ከስራ ሰዓት ዉጪ ከኢምግሬሽን (ጀዋዛት) በመመላለስ ባዶ ኢቃማ የመኖሪያ ፈቃድ በማምጣት የዉሸት የምኖሪያ ፍቃድ የሚሰጡ የመንግስት ሰራተኞች በርካታ (ነበሩ)ናቸዉ። በዉሸት ከአንድ አሰሪ ወደ ሌላ አሰሪ (ተናዙል-ነቅለል-ከፋላ) በማድረግም የሳዉዲ ህግ አስከባሪ አካላት በመተባበር ህገወጥነትን ያስፋፋሉ። ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ተጠያቂዉ ዛሬ በየመንገዱ እንደ እንስሳ እየታደኑ ኢሰብዓዊ ተግባር የሚፈጽምባቸዉ ስደተኞች ሳይሆኑ የሳዉዲ መንግስት ነዉ። ከሳዉዲ መንግስትም ባሻገር አገሪቷን የተቆጣጠሩት የንጉስ አብድልአዚዝ ቤተሰቦች ያንበሳዉን ደርሻ ይይዛሉ።
በሳዉዲ ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ሲሆኑ በትክክለኛዉ መንገድ ሰርትዉ የከበሩ፤ላገር፣ለቤተሰብ፣ለወገን የተረፉ በርካታ ናቸዉ። ባንጻሩም እንደ ወጡ የቀሩ፤ ጤነኛ ሆነዉ ታመዉ የተመለሱም ይኖራሉ። በህገወጥ መንገድ አረቄና አስካሪ መጠጥን በመጥመቅ ብሎም በዝሙት የሚተዳደሩም ይኖራሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ እዚያዉ-ሳዉዲ የተወለዱ ኢትዮጵያዉያን ህጻናት ሲኖሩ በአገሪቱ ደንብ መሰረት ሁለተኛ ደረጃን ከጨረሱ በሗላ የኮሌጅ ትምርት የማግኘት እድላቸዉ የመነመነ ነዉ (አይቻልም ማለት ይቻላል)። አቅም ያለዉ ልጆቹን ወደ አዉሮፓ እና አሜሪካ ለከፍተኛ ትምርት ሲልክ ዉስን አቅም ያለዉ ልጆቹን ወደ ኢትዮጵያ ልኮ በተለያዩ ኮሌጆች ያስተምራል። ሁለቱንም ማረግ ያልችለ ልጆቹ ያለትምርት የሚባክኑበት አጋጣሚ ሰፊ ነዉ።የባህረ ሰላጤዉን ስደት አስመልክቶ ብዙ ግዜ የሚነገረዉ ለአቅመ አዳምና ሔዋን ለደረሱት ኢትዮጵያዉያን ሲሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የወደፊት እጣ ፈንታቸዉን የማያዉቁ ሕጻናት ስለተዘነጉ ለነርሱም ማሰቡ ታላቅ ሰብዓዊ ግዴታ ነዉ።
በዚህ መከራና ስቃያ ዉስጥ ላሉ ኢትዮጵያዉን ለመታደግ ለዜጎቹ የሚቆረቆር ሁነኛ መንግስት ቢያሻም ሪያድ ያለዉ የሳዉዲ ኤምባሲና ጅዳ ያለዉ የቆንስላ ጽ/ቤት በመጣመር ዜጎችን የሚበድሉ ቢሆኑ እንጂ ለዜጎች ደራሽ ሲሆኑ አይታይም። ከተወሳሰበዉ የሳዉዲ ህግ ለመዳንና የመኖሪያ ፍቃድን ለማደስ ለፓስፖርት እድሳት ኤምባሲ የሚሔዱ ኢትዮጵያዉን ከፍላጎታቸዉ ዉጪ ለአባይ ቦንድ ግዙ ተብለዉ እንደሚቸገሩ ቀደም ሲል የተዘገበ እዉነታ ነዉ።ኤምባሲዉ ኢትዮጵያዉያንን በዘር በብሔር እየመተረ በልማት ስም አፍን ብልጓም ሲዘጋ ኢትዮጵያዉያን በየመንገዱ ላይ ከእንስሳ ባነሰ መልኩ እየተደበደቡ እየተገረፉ ክብራቸዉ ተገፎ ወደ ማጎሪያ ቤት (ተርኺል) እየተወረወሩ ነዉ።
ይህ ኢሰብዓዊ ተግባር አለም አቀፋዊ ትኩረት እንዲያገኝ ለተለያዩ የስብዓዊ መብት ድርጅቶች ማሳወቁ ተገቢ ሲሆን ጉዳዩ ከፍትኛ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ ኢትዮጵያዉያን በያሉበት መንቀሳቀስ አለባቸዉ።የፖለቲካ ድርጅቶችም ኢትዮጵያዉያኑ የሚደርስባቸዉን በደል በማዉገዝ ለጉዳዩ ልዩ አትኩሮትን በመቸር አቅማቸዉ በቻለዉ መጠን ሊንቀሳቀሱ ይገባል። የተለያዩ የሐይማኖትና የሲቪክ ማህበራትም ይሁኑ አክቲቪስቶች በመጣመር የሳዉዲ ኤምባሲዎች በሚገኙበት አገራት ሰላማዊ ሰልፍን ቢያረጉ መግለጫዎችን ቢያወጡ የወገኖቻንን ስቃይና መከራን ማስቆም ባይችሉ እንኳ ሊቀንሱት ይችላሉና-ወገን ለወገን መድረሱ ግድ ይላል።
የመጣኸዉ ባዶህን ነው… ባዶ ሆነህም ትመለሳለህ…(ኢንተ፡ጃኢ፡ፋዲ ወተርጃእ፡ፋዲ) ለሚባሉት ኢትዮጵያዉይን ከኛ ሌላ ደራሽ የላቸዉምንና እንድረስላቸዉ። ልብ ያለዉ ልብ ይበል!
Sunday, November 3, 2013
በቅርቡ ከኢትዮጲያ ኦጋዴን/ሶማሌ ክልል በድብቅ ወጥቶ በስዊዲን ቴሌቪዥን የተላለፈው ዶክመንተሪ ፊልም የዓለም ህብረተሰብን ያስደነገጠና ያስቆጣ በመሆን የወያኔን አረመኔአዊ አገዛዝ በድጋሚ አጋልጧል ።
ይህ ሁኔታ በጉራፈርዳ ፣ በቤንሻንጉል ፣ በአሶሳ ፣ በወልቃይት ፣ በኦሮሞ ፣ በአማራ ህዝብ እንዲሁም በመላ ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ አጉልቶ አሳይቶል ።
በመሆኑም የዓለም አቀፍ ሕግ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የሕግ ጠበቃ Jurist Stellan Gärde ወያኔ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ስለሚቀርብበት አግባቦችና ቅድመ ዝግጅቶች ላይ ለኢትዮጲያዊያን ማብራሪያ በመስጠት ተዛማጅ መረጃዎችንም ለማጠናቀር በስዊድን ስቶክሆልም ከተማ በኖቨምበር 2፥ 2013 , በ HallundaFolketshus ከቀኑ 13.00 ጀምሮ የተካሄደ ሲሆን በስብሰባው ላይ ዶክተር ሙሉዓለም አዳም በኖርዌይ የፖለቲካ አክቲቪስት ፣ መቶ አለቃ አበረ አዳሙ በኢትዮጵያ ፖሊስ በኃላፊነቶች የሠሩና የኢ.ፒ.ፒ.ኤፍ (EPPF) መሥራችና የአመራር አባል የነበሩ፣ ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ የኢሳት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አዘጋጅ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ በቪዲዮ የተደገፈ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ዝግጅቱ የተዘጋጀው በስዊድን በሚገኘው የኢትዮጲያ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ሲሆን በስብሰባው ላይ የኢትዮጲያ ጉዳይ የሚያሳስበው ዜጋና የኢትዮጲያ ወዳጆች ኖርዎይን ጨምሮ ከተለያዩ ቦታዎች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል፥፥
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር !!

በመሆኑም የዓለም አቀፍ ሕግ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የሕግ ጠበቃ Jurist Stellan Gärde ወያኔ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ስለሚቀርብበት አግባቦችና ቅድመ ዝግጅቶች ላይ ለኢትዮጲያዊያን ማብራሪያ በመስጠት ተዛማጅ መረጃዎችንም ለማጠናቀር በስዊድን ስቶክሆልም ከተማ በኖቨምበር 2፥ 2013 , በ HallundaFolketshus ከቀኑ 13.00 ጀምሮ የተካሄደ ሲሆን በስብሰባው ላይ ዶክተር ሙሉዓለም አዳም በኖርዌይ የፖለቲካ አክቲቪስት ፣ መቶ አለቃ አበረ አዳሙ በኢትዮጵያ ፖሊስ በኃላፊነቶች የሠሩና የኢ.ፒ.ፒ.ኤፍ (EPPF) መሥራችና የአመራር አባል የነበሩ፣ ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ የኢሳት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አዘጋጅ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ በቪዲዮ የተደገፈ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ዝግጅቱ የተዘጋጀው በስዊድን በሚገኘው የኢትዮጲያ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ሲሆን በስብሰባው ላይ የኢትዮጲያ ጉዳይ የሚያሳስበው ዜጋና የኢትዮጲያ ወዳጆች ኖርዎይን ጨምሮ ከተለያዩ ቦታዎች የተሰባሰቡኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል፥፥

Subscribe to:
Posts (Atom)