Wednesday, January 7, 2015

የገና ዛፍ ለምን

የገና ዛፍ ለምን ?
በአገራችን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል በምናከብርበት ወቅት ለበዓሉ ድምቀት ሲባል የሚደረጉ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው የገናን ዛፍ መትከል ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በየቤቱ ይህንን ዛፍ ለመትከል ሲል በየከተማው ያለው ዛፍ ይጨፈጨፋል፣ አሁን አሁንማ በከፍተኛ ዋጋ እየተሸጠ ነው፡፡ በአገራችንም ብቻ ሳይሆን በሰለጠኑ አገሮችም የዚህ ዛፍ ጉዳይ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ሆኗል፡፡ እንዲያው ያ ዛፍ በመብራት ተሸቆጥቁጦ በየቤቱና በየቤተክርስቲያን መድረኮች ላይ ካልቆመ በዓሉ በትክክል እንዳልተከበረ ሁሉ ሊታሰብ ይችላል፡፡ ለበዓሉ አከባበር ሲባል የሚቆረጠው ማንኛውም ዛፍ ሳይሆን የሚመረጠው ጥድ ነው፡፡ የገና ዛፍ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ጋር የሚያይዘው ምንድነው፣ ምንስ ትርጉም አለው እንዴትስ በዚህ ታሪካዊ ሁኔታ ውስጥ ሊገባ ቻለ ማለትና መልስ ማግኘት የሚገባ ይመስለኛል፡፡
የገና ዛፍ አጠቃቀም ታሪካዊ አመጣጥ በምንመለከትበት ወቅት ይህ ድርጊት የተጀመረው በጥንታዊቷ ጀርመን በ15ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ ጀርመኖች አሬንጓዴ ዛፎች ወዳሉባቸው ቦታዎች በመሄድ በተለያዩ መብራቶችና የፍራፍሬ ዓይነቶች የስጌጡአቸው ነበር፡፡ የማይደርቁና የማይጠወልጉ አሬንጓዴ ዛፎች ርኩስ መናፍስትን፣ ምትሐትን፣ በሽታንና ድህነትን ያርቃሉ የሚል እምነት ስለነበራቸው ይህንን አጠንክረው ያድርጉታል፡፡ አብዛኛዎቹ የጥንት ሰዎች ፀሐይን አምላክ ብለው ስለሚያመልኩ ክረምት የሚመጣው ያ አምላክ የሆነው ፀሐይ ሲታመም ወይም ሲደክም ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ ከዓመት እስከ ዓመት ሳይጠወልጉና ቅጠላቸው ሳይረግፍ የሚቆዩ እንደ ጥድ ያሉ ለምለም ዛፎች የታመመው ወይም የደከመው ፀሐይ አምላክ እንደገና ኃይል አግኝቶ እንደሚበረታና ክረምቱም አልፎ ፀሐይ እንደሚመጣ የሚያሳስቡ ስለሆነ በጣም ይንካከቡአቸዋል፣በመብራትና በልዩ ልዩ ጌጣጌጦች እያስዋቡአቸው ያመልኩአቸዋል፡፡ አምልኮቱ ግን ለዛፎች ብቻ ሳይሆን ከዛፎች በስተጀርባ ላለው አሬመኔአዊ አምላክ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የጥንት ጀርመናውያን ለምለም ዛፎችን በያሉበት ያስገጡቸው እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ዛፎቹን የተለያዩ ሻማዎችን በማብራት ፣ እንደ ፖም፣ ብርቱካንና፣ ለውዝ ያሉ የአትክልት አይነቶችንና ሌሎች ምግቦችን በቅርንጫፎቻቸው ላይ በማጠልጠልና ልዩ ልዩ ደማቅ ቀለም ያሉአቸውን የጨርቅ ሪባኖችን በላያቸው ላይ ከላይ እስከ ታች ድረስ በመዘርጋት ወዘተ በማስገጥ ያመልኩአቸው ነበር፡፡ በዛፎቹ ላይ ሻማ መብራት የተጀመረው ግን በ18ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡
አሁን ያለን አማኞችም ሆነን ሌሎች የጥድ ቅጠል በየቤታችን ወይም በየበራችን እንደምናደርገው በ15ኛውና በ16ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ ሰዎች ከዓመት እስከ ዓመት ድረስ ሳይረግፉና ሳይጠወለወጉ አሬንጓዴ እንደሆኑ የሚከርሙትን ዛፎች( Evergreen Trees) ባሉበት ማስገጡ ብቻ ሳይሆን ውሎ እያደረ እያንዳንዱ አምላኪ የዛፎቹን ቅርንጫፍ ቆርጦ ወደቤቱ አምጥቶ በበሩና በመስኮቱ እንዲሁም በቤቱ ጣሪያ ላይ ማንጠልጠል ጀመረ፡፡ ይህንን በማድረጋቸው በሽታ ፣ ድህነትና ርኩስ መንፈስ ሁሉ ከበር ይመልስልናል ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡ ከዚያም የተነሳ የአሬንጓዴ ዛፎች ዋጋና ለእነርሱ የሚሰጠው ግምት ምን ጊዜም ከፍተኛ እየሆነ መጣ፡፡ በተለይም ደግሞ ዛፎቹ ከፍተኛ በረዶ በሚወርድቸው የክረምት ወራት ልዩ ትርጉም አላቸው፡፡ በምዕራቡ ዓለም በጋው አልፎ ክረምቱ ማለትም የበረዶ ወቅት በሚመጣበት ጊዜ ዛፎች ሁሉ ቅጠላቸው ይረግፍና የደረቁ እስክመስሉ ድረስ እንጨት ብቻ ይቀራሉ፡፡ ይህ ሲሆን እነዚያ ለምለም (evergreen) የሚባሉ ዓመቱን ሙሉ አሬንጓዴ የሚሆኑ ዛፎች ብቻ ይቀራሉ፡፡ ያኔ ከሰማይ የወረደው በረዶ በየዛፎች ቅርንጫፍ ላይ ቦግ ብሎ መታየት ይጀምራል፡፡ስለዚህም ነው የምዕራባውያን አገሮች የገና በዓል በሚያክሩበት ወቅት በረዶ ወርዶ መሬቱ፣ዛፍ ቅጠሉና የቤት ጣሪያው ሁሉ ነጭ ካልሆነ ደስ የማይላቸው፡፡ ለምሳሌ የዘንድሮ የ2014 ክርስትማስ በሚከበርበት ጊዜ ከምን ጊዜም ይልቅ በአሜሪካን አገር በረዶ በሚያጠቃቸው እንደነ ሚቺጋንና ዊስኮንሲን መሳለሱ ግዛቶች እንኳ በረዶ ስላልወረደ በዓሉ ደማቅ ቢሆንም የብዙዎች ደስታ ቀንሷል፡፡
ጀርመን 15ኛውና 16ኛ ምዕተ ዓመታት የገናን ዛፍ በውጭ ባሉባቸው ቦታዎች ሄደው ማምለክም ሆነ ዛፉን ወደ ቤት በማምጣት የተለየ ትኩረት ሰጥተው በማምለክ ቀዳሚ ትሁን እንጂ በዓለም ዙሪያ ብዙ አገሮች የገናን ዛፍ የማሳመር ሥርዓት ወጋቸው ካደረጉ ቆይተዋል፡፡ በአንዳዶች ዘንድ እንደ ልማድ የሚደረግ ሲሆን አብዛኛዎቹ ግን ቀጥታ የሆነ አምልኮ ያደርጉበታል፡፡ የጥንት ግጻውያንም ኤራ(Ra) የሚባለውን አምላክ ያመለኩት ሲሆን ይህ አምላክ በጭንቅላቱ ላይ ባደረገው ዘውድ ፀሐይን እንደሚያንጸባርቅ ነበልባል የሚለብስ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በጀርመኖች አምላክ እንደነበረው ኤራም ስለሚታመም ከበሽታው እንዲያገግም ግብጻውያኑ ለምለም ዛፎችን ወደ ቤታቸው አምጥተው የሚያስገጡአቸው ሲሆን ይህ ለእነርሱም በሽታንና ሞትን ድል ያደርግልናል ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡ የጥንት ሮማውያንም ሳቱርን ( Saturin) የሚባል የእርሻ አምላክ ነበሩቸው፡፡ ለዚህ አምላክ የሚሰጡት አምልኮ ሳቱሪናሊያ(Saturinalia) መባል የሚታወቅ ሲሆን የአምልኮ ሥርዓቱ የሚከናወነው መኖሪያ ቤቶችንና ቤተ መቅደስን በለምለም ዘፎች ቅርንጫፍ በማጌጥ ነበር፡፡
ጀርመኖች ፀሐይን አምላክ አድርገው በሚያመልኩበት ወቅት የሰማይና የምድር ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ክርስቲያኖች ደግሞ ነበሩ፡፡ የተሃዲሶ እንቅስቃሴ እየተስፋፋ ሲሄድ የፕሮቴስታንት መሪዎች በዓለም ያሉትን ለመማረክ ሲሉ መንፈሳዊ ነገርን በዓለማዊ ልማድ ውስጥ እያስገቡ ሰዎችን በወንጌል የመድረስ ሥራ መሥራት ጀመሩ፡፡ ከእነዚህ ተግባራት አንዱ አሬማውያን የሚያከብሩትን የዛፍ አምልኮ ከኢየሱስ ልደት ጋር ማያያዝ ነበር፡፡ የተሃዲሶ አንጋፈው አቀንቃኝ የነበረው ማርቲን ሉተር የቀድሞዋ ጀርመን ሂዳሴ ወቅት በዛፎች ላይ የሻማ መብራት አስቀምጠዋል ተብሎ በመነገሩ ምክንያት ፕሮቴስታንቶች በክርስቶስ ልደት ጊዜ በአሬንጓዴ ዛፎች ላይ ልዩ ልዩ ጌጦችንና የሻማ ብርሃን በማስቀመጥ ማክበር ጀመሩ፡፡ አሬማውያን አዲስ ዘመን የሚቀበሉት ዛፎች ሁሉ ቅጠላቸው በሚረግፍበት፣ እንደነጥድ ያሉት ደግሞ አሬንጓዴ ሆነው በሚቆዩበትና በረዶ በሚወርድበት የክረምት ወራት በመሆኑ በዓላቸውን የሚያከብሩት የፀሐይ አምላክ ታሞና ደክሞ ከተኛበት እስክነቃ ድረስ እነዚህ ዛፎች ችግርን መከራንና መጥፎ መንፈስን ከበራችን ያርቁልናል ብለው ስለሚያምኑ የዛፎችን ቅርንጫፍ ወደ ቤታቸውም አምጥተው በበራቸውና በመስኮታቸው ሲያኖሩ አማኞች ደግሞ በአንጸሩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ የተወለደበትን በዓል በዚያው ጊዜ ያከብሩ ነበረ፡፡ ስለዚህ እነርሱ በበኩላቸው የክርስቶስ የመወለዱ ዜና የሚያውጁበት አደረጉት፡፡ ይህ ሁኔታ በዚሁ እየቀጠለ መጣና ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች ሁሉ ይዛመት ጀመረ፡፡
በመካከለኛው ዘመን የነበሩ ሰዎች የገና ዛፍን በኤደን ገነት አዳምና ሔዋን የበሉት ዛፍ መታሰቢያ አድርገው ወስደውታል፡፡ እንዲያውም በገና ዛፍ ላይ የምንጠለጠለው የፖም( የአፕል ፍሬ) ሔዋን የበላችው የዛፍ ፍሬን ሲወክል በሥሩ የሚበተነው ብሰኩትና ሳሳ ያሉ ወረቀቶች ለኢየሱስ ሞት መታሰቢያ የሚወሰደውን ቅዱስ ቁርባንን ይወክል ነበር፡፡ ይህም የሚደረገው ዛፎች ባሉበት ቦታ ሲሆን የኋላ ኋላ ግን እነርሱም ሌሎች እንደሚያደርጉት ሁሉ ዛፎችን ቆርጠው ወደ ቤት በማምጣት የማክበሩ ሥርዓት ተለማመዱት፡፡ በአብዛኛው ግን የገና ዛፍ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ወቅት ማክበሩ በተለያዩ አገሮች ሁሉ ልምድ እየሆነ መጣ፡፡ የጀርመኗ ንግሥት ቪክቶሪያ ባለቤት የሆነው ፕርንስ አልቤርት በ1848 በዊንዲሰር ካስተል የገናን ዛፍ ካቆመ በኃላ በክርስቶስ ልደት በዓል ወቅት ዛፍ የማጌጥ ሥርዓት ከጀርመን ጀምሮ፣ በእንግሊዝ፣ በካናዳ፣ በአሜሪካና እንዲሁም በሌሎች አገሮች ሁሉ ተስፋፋ፡፡ ጀርመኖች የገና ዛፍ ለካናዳዎች ያስተዋወቁት በ1700 ላይ ነው፡፡ ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ደግሞ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አማካይነት የገና ዛፍ የክርስቲያኖች ልማድ እየሆነ መጣ፡፡ በተለይም ኤድዋርድ ኤች ጆሐንሶን በ1882 በኒው ዮርክ የመጀመሪያውን ገና ዛፍ ላይ የሚንጠለጠሉ መብራቶችን ከተፈላሰፈና በሥራ ላይ ካዋለ በኋላ የገና ዛፍ ድምቀት እየጨመረ ስለ መጣ ጆሐንሰን the Father of electric Christmas tree light የሚል ግጽል ስም ተሰጠው፡፡ በየዓመቱ በአሜሪካን አገር የገና ዛፍ የሚተከል ሲሆን የሚሸጠውም በውድ ዋጋ ሆነ፡፡ አሜሪካኖች በየዓመቱ ከ33 እስከ 36 ሚሊዮን የተፈጥሮ ገና ዛፎች የሚተክሉ ሲሆን በየቤቱና በአደባባይም የሚቆመውን ሁሉ ጭምሮ ከ1.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገና ዛፍን ለማሳመር ሲባል እንደሚባክን ይገመታል፡፡
ይሁን እንጂ የገና ዛፍ የአሬማውያንን ልማድ ወደ ክርስትና ልማድ ለመቀየር በሚደረገው ጥረትና ተሳትፎ እንዲሁም በኤዴን ገነት የነበረው ዛፍ መታሰቢያ ለማድረግ ሲባል ከተፈጠረው ሰውኛ ልማድ በቀር ሌላ ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የለውም፡፡ አሬማውያን የሚያደርጉትን የጣዖት አምልኮ፣ ዘፈን ፣ እንዲሁም ሌሎች ምልክቶች ተጠቅመን የጌታን ማዳን እናውጅ የሚለው ከመንፈስ ቅዱስ ልዩ አመራር ካላገኙ ሰዎችን ወደ ጌታ ከማምጣት ይልቅ ሊያርቃቸው ሁላ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ መዘምራን ሽብሽባ ለእግዚአብሔር ክብር ሀይማኖታዊ የአምልኮ ሥርዓት ቀይረው በዓለም ያሉትን ለመማረክ ሲባል ከመንፈሳዊ መዝሙር ጋር እስክስታ ምንጃርኛ ፣ ጎጃምኛ፣ ወላይትኛ ፣ ጉራግኛ፣ እንዲሁም ሮምኛ ጭፈራዎችን አክለውበታል፡፡ ይህ ለምን ሆነ ለሚል መልሱ ዓለምን ለመዋጀት ወይም ለእግዚአብሔር ክብር ሲባል ነው ይባላል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ጌታ የሰጠን ዜማና ውዝዋዜ ነው ይሉ ጀምረዋል፡፡ ጌታ ከዘፈን ወስዶ ዜማ፣ ከዓለማዊያን ዳንስ ወስዶ ሽብሸባ የሚሰጠው ምን አልቆበት እንደሆነ ምላሹን ከእነርሱ! ከ2 አሥርት ዓመታት በፊት አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጊቢ ባንደራ ሲተከል ከታየ ያቺ ቤ/ክ በፕሮቴስታንቶች ዘንድ ከፓለቲካው ጋር የተቆራኘት ተደርጋ ትነቀፍ እንደነበር ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ባንዳራ የማይተከልበት የፕሮቴስታንት መድረክ በጣም ጥቂት ነው፡፡ አንዳንዶች ምክንያት ኖሮአቸው ሲያደርጉ ሌሎች ደግሞ ሲደረግ ሲላዩና የመድረኩን ድምቀት ለመጨመር ሲባል ያደርጉታል፡፡ ልምምድ ከአንዱ ትውልድ ወደ ሌላው ሲሸጋገር እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሙጥኝ የሚሉት ዓይነት ስለሆነ ነው፡፡ የገና ዛፍም ጉዳይ ልክ እንደዚህ ነው፡፡ ምንም የቅዱስ ቃሉ መሠረት ባይኖረውም የቀደሙት ስላደረጉት ብቻ የሚደረግና ከጎደለም የጌታን ልደት በአግባቡ ያላከበርከው ተደርጎ ስለሚወሰድ ነው፡፡
ምዕራባውያን በክርስቶስ ልደት በዓል ወቅት የገናን ዛፍ የሚያስጌጡት አንዴም ከአሬማውያን አምልኮ ጋር ስለሚያያይዙትና ሌላም ደግሞ ባህላቸው ስላደረጉት ነው፡፡ በአገራችን ግን ዛፍን በጨርቅ በማስጌጥ፣ በሥሩ ጭስ በማጨስ፣ ቅቤም በመቀባት የሚያመልኩበት መጥፎ ነገር እንጂ ጤናማ ልማድ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል የተወገዘ ሰይጣናዊ አሠራር ነው( ዘጸ፡20፡1-3)፡፡ ሰው እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክና ለእርሱ ብቻ እንዲሰግድ እንጂ ሌላ አምላክ እንዲኖረው አይገባውም፡፡
ምዕራባውያን በተለይም አንደ አሜሪካን ያሉ የሰለጠኑ አገሮች ለገና በዓል ጊዜ የሚሸጡ ዛፎች የሚመረቱበት እርሻና በዚህ የተሰማሩ ገበሬዎች ስላላሉ የእርሻ ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ ሲሆን በአገራችን ግን ማንም በየከተማው የቆመውን ዛፍ በመጨፍጨፍ ወደ ቤቱ መውሰድ ነው፡፡ ድርጊቱን ለሚያይ ሰው የዛሬው በዓል ይድመቅልኝ እንጂ ነገ የሚመጣው ጥፋት አይመለከኝም የሚል ትውልድ እየተፈጠረ ያለ ይመስላል፡፡ የክርስቶስን ልደት ስናከብር እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረ በኋላ ይጠብቃትና ያበጃትም ዘንድ በምድር ላይ ካስቀመጠበት ዓላማ ጋር የሚቃረን የዛፍ ጭፍጨፋ ማካሄድ እግዚአብሔርን ያስከብራል ፣ ለሰውም ጥቅምና ደስታ ይሆናል የሚል የቤተ ክርስቲያንም ትምህርት ሆነ የእግዚአብሔር ህግ የለም(ዘፍ 2፡15)፡፡
ሰለዚህ የጌታችንን የኢየሱሰ ክርስቶስን የልደት በዓል በምናከበርበት ወቅት የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሠራሽ ዛፎችን እቤታችንና በቤክርስቲያንችን መድረኮች ብንተክል አናተርፍም ባንተካላቸውም አይጎድልብንም፡፡ ይልቁንስ ሐዋሪያው ጳውሎስ እንዳለ ጌታችን ኢየሱስ በልባችን ይሳል ዘንድ ይገባዋል፡፡ ክርስቶስ በልባችን መሳሉና መተከሉ የእውነተኞች የእግዚአብሔር ሰዎች ምጥና ጭንቀት ስለሆነ እኛም ስለዚያ ልንጨነቅ ይገባናል(ገላ.4፡19)፡፡ ስለ ዛፍም ከተነሳ መልካምን ፍሬ እንደሚሰጥ በወንዝ ዳር እንደተተከለች ፍሬዋም እንደማይረግፍና ቅጠሉዋም እንደማይጠወልግ ዛፍ ፣ ከክፉዎች ምክርና ከኃጢአተኞች ዱለታ የራቅንና በእግዚአብሔር ሕግ ጥዋትና ማታ የምንደሰት ልንሆን ይገባናል(መዝ 1፡1-6)፡፡ ጌታችን በሰው ሠራሽ መብራት የሚሽቆጠቆጥ ዛፍ ሳይሆን እንደ መልካም የወይን ቅርንጫፍ አብዝቶ የሚያፈራ እውነተኛ የክርስትና ሕይወታችንን ይፈልጋል( ኢሳ 5፡1-5፣ ዮሐ.15፡1-7)፡፡ በመጨረሻው ጊዜ የዚህ ምድር ኑሮ ሁሉ አልፎ እግዚአብሔር ላመኑት ያዘጋጀላቸውን መንግሥት፣ ሞት የሌለበት፣ እምባ የማይታይበት ፣ መርገምም ከቶ የማይሆንበት፣ የእግዚአብሔርና የበጉ ዙፋን ያለባት፣ እኛ ባሪያዎችም በግምባራችን ላይ ስሙ ተጽፎ ፊቱን እያየን የምናመልክባት፣ የፀሐይ ብርሃን በማያስፈልግባትና በጉ ኢየሱስ ብርሃን ሰለሆነ ሌሊትና ጨለማ የሌለባት አገር ልንወርስ ተጠርተናል፡፡ በዚህች አገር ቅጠሏ ለሕዝብ ሁሉ መፈወሻ የሚሆን በየወሩ 12 ፍሬ የምትሰጥ የሕይወት ዛፍ አለች( ራዕይ 22፡1-5)፡፡ ይህቺ ዛፍ ያለችበትን ውብ አገር ሊያስወርሰንና መንገድ ሊሆነን ጌታችን ኢየሱስ በመጨረሻው ዘመን ከሕግ በታች ከሴት የተወለደበትን እያሰብን በእውነትና በመንፈስ እናምልከው እንጂ በልማድና በወግ ብቻ አይሁን(ገላትያ 4፡4፣ዮሐ 4፡24)፡፡ የኢየሱስ መወለድም የመጨረሻውን ዘመን የሚያሳይ ስለሆነ የክርስቶስ ዳግም ምጽዓት በደጅ እንደሆነ እናስተውል፡፡ የዘንድሮው የልደት በዓል ብዙዎች የክርስቶስን አዳኝነት አውቀው ሕይወታቸውን ለጌታ እንዲሰጡ አንደበታችን የሚመሰክርበት የተባረከ በዓል ይሁን፡፡ አሜን፡፡

15 comments:

  1. newcrack.co/xlstat-crack
     with over 200 diverse statistical instruments and characteristics for simple investigation and re-formation your data along with ms-excel; it's but one on advance five apps.
    new crack

    ReplyDelete
  2. https://ethiozare.blogspot.com/2015/01/blog-post.html?showComment=1539568319281#c8294946538925102624

    ReplyDelete
  3. This design is wicked! You most certainly know how to keep a reader amused.
    Between your wit and your videos, I was almost moved to start my own blog (well, almost…HaHa!) Great job.
    I really loved what you had to say, and more than that, how you presented it.
    Too cool!
    mount and blade serial key for free
    pinnacle studio torrent
    plagiarism checker x torrent
    avast internet security crack
    pdq deploy torrent
    Crack Like

    ReplyDelete
  4. Sincerely, I'm glad that I stumbled into your website when searching on Google.
    I'm still here for another reason, and I'd want to express my appreciation for an excellent essay.
    It's an excellent site in every way (and I really enjoy the theme/design).
    outbyte pc repair crack
    outbyte pc repair crack key
    sublime text rack

    ReplyDelete
  5. I am very thankful for the effort put on by you, to help us, Thank you so much for the post it is very helpful, keep posting such type of Article.
    KC Softwares PhotoToFilm Crack
    Project IGI 3 PC Game
    TeamViewer Crack

    ReplyDelete
  6. Your writing abilities as well as the cleverness with which you've organized your blog as a whole have really impressed me.
    https://hdlicense.net/retail-man-pos-crack-download/

    ReplyDelete
  7. Nice information, valuable and excellent design, as share good stuff with good ideas and concepts, l
    armello crack
    ancient cities crack
    Strange Brigade Crack

    ReplyDelete
  8. Dom To Ethiopias: የገና ዛፍ ለምን >>>>> Download Now

    >>>>> Download Full

    Dom To Ethiopias: የገና ዛፍ ለምን >>>>> Download LINK

    >>>>> Download Now

    Dom To Ethiopias: የገና ዛፍ ለምን >>>>> Download Full

    >>>>> Download LINK Ff

    ReplyDelete
  9. Dom To Ethiopias: የገና ዛፍ ለምን >>>>> Download Now

    >>>>> Download Full

    Dom To Ethiopias: የገና ዛፍ ለምን >>>>> Download LINK

    >>>>> Download Now

    Dom To Ethiopias: የገና ዛፍ ለምን >>>>> Download Full

    >>>>> Download LINK WW

    ReplyDelete